June 26, 2010

የአባቶች ሽምግልና እና እርቅ ከየት ይነሣ፣ የት ይድረስ?


(ደጀ ሰላም፣ ጁን 26/2010)፦ በግንቦቱ የቅ/ሲኖዶስ ጉባዔ ላይ እንደተገለፀው ከአምስተኛው ፓትርያርክ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሲመት ማግስት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያኒቱ የተነሣውን መከፋፈል ለማቆምና በአባቶች መካከልም የተፈጠረውን እስከ መወጋገዝ የሚያደርስ ልዩነት በእርቅ ለመጨረስ እንቅስቃሴ ተጀምሯል። ይኸው ከአበው ካህናት፣ ከምእመናንና ከታዋቂ ግለሰቦች በአባልነት የተውጣጡ ሰዎች የሚሳተፉበት ነው የተባለው አንቀሳቃሽ ቡድን በግንቦት ወር ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት (አዲስ አበባ) እንዲሁም ወደ ኒውዮርክ ልዑካንን በመላክ እርቁ እንዲጀመር አግባብቷል።
በዚህም ከሁለቱም በኩል ቀና ምላሽ አግኝቷል። ቀጣዩ ሁለቱንም ወገኖች ፊት-ለፊት፣ መሳ-ለመሳ ማገናኘትና ማወያየት ይሆናል። ሁሉ ነገር ምሥጢር፣ ሁሉ ነገር ከመጋረጃ ጀርባ ተጀምሮ ከመጋረጃ ጀርባ በሚያልቅበት “የምሥጢር ማኅበረሰብ” መካከል ስለምንኖር ልናውቀው የሚገባንን ሳናውቅ፣ የበኩላችንን ድርሻ ልንወጣበት የሚገባው ነገር ላይ ምንም ሳናከናውን ጊዜው እንዳያልፍ ግን አስግቶናል። ከመጋረጃ ጀርባ የሚደረጉ ቲያትሮች ታዲያ ጦሳቸው ጥንቡሳታቸው ዘግይቶ ይደርሰንና “ለምን የመጣ ለምን ይተርፋል” ይሆናል። በፖለቲካችንም፣ በቤተ ክህነታችንም፣ በሃይማኖታችንም ሁሉ ከጀርባ እያለቀ የሚመጣው ነገር አገሪቱንም፣ ቤተ ክርስቲያኒቱንም ሲያምሳት እነሆ የአንድ ሰው ዕድሜ በላይ ሆኖናል። ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስና “የእርቁ ነገር” ላይ ለመወያየት እንሞክር።

ጥንተ ታሪክ

ኢሕአዴግ ስልጣን በያዘ ማግስት “ከደርግ ጋር አብረዋል” ያላቸውን አራተኛውን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን “እንደማንኛውም ደርግ/ ደርጌ” በመቁጠር አብሯቸው ሊሠራ እንደማይችል በወቅቱ አዛዥ ናዛዥ በነበሩት በጠቅላይ ሚኒስትር ታምራት ላይኔ በኩል ግልጽ አደረገ። እርሳቸውን ከስልጣን ለማውረድ ከቤተ ክህነቱም ከቤተ መንግሥቱም ስምምነት ላይ ተደረሰ። እርሳቸው ፓትርያርኩም አልተቃወሙም። ጥያቄው ከወረዱ በኋላ ስለሚኖሩት የኑሮ ዓይነት ነበር። በምትካቸውም አፈር ይቅለላቸውና በቅርቡ ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ አቃቤ መንበር (መንበር/ ወንበር/ ዙፋን ጠባቂ) ሆነው ተሾሙ። ከዚያም ጊዜውን ጠብቆ አዲስ ፓትርያርክ እንዲመረጥ ተወሰነ። ለእጩነት የቀረቡት ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ ተመረጡ እና አምስተኛው ፓትርያርክ ሆኑ። በወቅቱ “ብፌ እንኳን ለማንሳት ዕውቀት ያልነበራቸው አባቶች አልፈው እንግሊዝኛ ተናጋሪ፣ ዶክተር፣ ዓለምን ጠንቅቆ ያወቀ አባት ተገኘ” ተባለና ሁሉም አባት ደስ አለው። “ይደልዎ”!!! እያለ በቪዲዮ ተቀረፀ። ትንሽ ቆይቶ ደግሞ በኬንያም፣ በባሌም፣ በቦሌም ወደ አሜሪካ መጡ እና “ሕጋዊ ቅዱስ ሲኖዶስ” ተመሠረተ ተባለ። አራተኛውም ፓትርያርክ ተቀላቀሏቸው”። ከዚያም “ስደተኞቹ አባቶች” የዚህኛው ቡድን ፖለቲካ አቀንቃኝ፣ አምስተኛው ፓትርያርክ ደግሞ አዲስ አበባ ተቀምጠው የሚኒሊክ ቤተ መንግሥትን የተቆጣጠረው ቡድን አቀንቃኝ ሆነው በሬዲዮም፣ በጋዜጣም፣ በእንቁላልም ሲደባበደቡ 20 ዓመት ሊሞላ አንድ ፈሪ (ማለትም 19 ዓመት) ሆነው።

ዛሬ አሜሪካ የተሰበሰቡት ስዱዳን አባቶች ቅ/ሲኖዶሱን ጥለው ከወጡ ጀምሮ ከአሜሪካ ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሰሞን አንገታቸውን ደፍተው በትህትና ሲመላለሱ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ጳውሎስ አንገታቸው ቀና አደረጉና ሌሎችን አንገት አስደፉ። ስደተኞቹ ከአሜሪካ እንቁላላቸውን በወረወሩ መጠን አቡነ ጳውሎስም ከመንገዳቸው ወደ ኋላ ከመመለስ ይልቅ የበለጠ ገፉበት። ከዚያም በውጪ ያሉት አባቶች “ጳጳሳት ሾምን” ብለው የበለጠ ልዩነቱን አስፍተው ቀኖና እስከመጣስ ድረስ ሄዱ። ከዚያም ውግዘት ተከተለ እና አራተኛው ፓትርያርክ እና አብረዋቸው ያሉት አባቶች በሙሉ በየስማቸው ተወገዙ። እነርሱም በፈንታቸው ሌላውን አወገዙ። እንዲህ እንዲህ ቆይቶ አሁን የእርቅ ዜና ተሰማ። ተመስገን። ነገር ግን እርቁ በየትኛው ላይ ይሆን? ውይይቱና ሽምግልናውስ እስከምን ድረስ?

ለእርቅና ለሽምግልና የሚያስፈልጉ አራት ነጥቦች
ይህንን የመሰሉ አገራዊ አጀንዳዎችን ይዞ የሚነሣ አካል ሊያውቃቸው የሚገባ አራት ነጥቦች አሉ። የመጀመሪያው አብረውት የሚሠሩ የቴክኒክ እና የምክር ኮሚቴዎች ሊኖሩት እንደሚገባ ነው። አንድ ሰው ተሰሚነት ያለው ሰው በመሆኑ ብቻ ሽማግሌ ይሆናል፣ ለማስታረቅ የሚያስችሉ ዲፕሎማሲያዊ፣ ታሪካዊ እና ንግግራዊ ክህሎቶች አሉት ማለት አይደለም። የሁለቱን ወገኖች ታሪካዊ ሽግግር፣ የልዩነት ምክንያቶች፣ የሌሎች አገሮች ተሞክሮ (ልምድ)፣ ከዚህ በፊት የነበሩ የእርቅ-ድርድሮች ሊከሽፉ/ሊሳኩ የቻሉበት ምክንያት፣ የታራቂዎቹ ጠባይ ወዘተ የሚለውን የሚያጠና፣ ስልት የሚጠቁም እና ሙያዊ እገዛ የሚያደርግ አካል ያስፈልጋል። አንዳንድ ጊዜ ታራቂዎቹ የሃይማኖት ሰዎች ሆነው አስታራቂዎቹ ግን የሃይማኖቱን ቀኖና እና መሠረተ ሐሳብ ያልተረዱ አልያም ታራቂዎቹ ፖለቲከኞች ሆነው አስታራቂዎቹ የፖለቲካን አካሄድ ጭራሽ ያልተረዱ ከሆኑ እርቁ በደፈናው “አንተም ተው፣ አንተም ተው” ዓይነት ይሆናል። በዚህ ጊዜ አካሄዶችን አጥንተው መንገድ የሚያሳዩ ባለሙያዎች ያስፈልጋሉ።

ሁለተኛው ነጥብ ደግሞ የሕዝብ ይሁንታ ነው። አገራዊ የሆኑ እርቆች ሲደረጉ ሕዝቡ ስለጉዳዩ ሐሳብ እየሰጠ፣ አቅጣጫ እየጠቆመ. ከመነሻው ይሁንታውን እየሰጠ መሆን አለበት። የሕዝብ ጉዳይ ለሕዝብ ዱብ ዕዳ መሆን የለበትም። እንዲህ ዓይነቱ ዱብ ዕዳ ሲከሰት ሕዝቡ ስለ እርቁ የራሱን ምክንያት እና አንድምታ ይሰጥና ከእርቁ መንፈስ ይወጣል። የሰዎቹን እርቅ ቅቡልነት (ተቀባይ መሆን) ጥርጣሬ ላይ ይጥለዋል። በርግጥ በእርቁ ሒደት ምስጢራዊ ሊሆኑ የሚገባቸው አንዳንድ ነገሮች ይኖራሉ። ይህ ማለት ግን ሁሉም ነገር ምስጢራዊ ይሆናል ማለት አይደለም። ልዑል እግዚአብሔር እንኳን ከሰዎች ልጆች ጋር እርቅን ሲመሰርት መንገዱን፣ አመጣጡን፣ አሠራሩን ከመጀመሪያው ጀምሮ ሱባዔ አስቆጥሮ እና በኦሪት እና በነቢያት አናግሮ ነው። መቼ ከዚ ምስጢር (ከምስጢረ ሥጋዌ) የበለጠ ምንም ምስጢር የለም።

ሦስተኛው ነጥብ ደግሞ የሽማግሌዎቹ ለእርቁ ተገቢ መሆን እና በሰዎች ዘንድ ያላቸው ተቀባይነት ነው። ሽምግልናው ተቀባይነት የሚኖረው ሕዝቡ ሲቀበለው፣ ሽምግልናው ውጤት ሲያመጣ እና ለሌሎችም ምሳሌ መሆን ሲችል ነውና ይህንን ለማድረግ አደራዳሪዎቹ ራሳቸው በሌላው ዘንድ ተቀባይነት ያላቸው፣ ወገንተኝነት ያላጠቃቸው መሆን አለባቸው። አሁን በተጀመረው ሽምግልና ማን ሽማግሌ እንደሆነ፣ ሽማግሌዎቹ በምን መመዘኛ እንደተመረጡ፣ ዓላማቸው ምን እንደሆነ በትክክል ለሕዝብ አልተገለጸም። ይህ ደግሞ ውሎ አድሮ ጥያቄ ማስነሣቱ አይቀርም። ነገሩ የሃይማኖት መሆኑን ስናውቅ ደግሞ ይበልጥ አሳሳቢ ያደርገዋል።

የተሸምጋዮቹ ሽምግልናውን እና የእርቅ ጥያቄውን መቀበላቸው ብቻ ጅምሩን የተሳካ አያደርገውም። ለምሳሌ የቀድሞ የቅንጅት አመራሮችን የተፈቱበትን ሒደት እንመልከት። በሽማግሌዎቹ አማካይነት የታሠሩት ተፈቱ ተባለ። ይህ መልካም ነው። የሽምግልናው ሒደት ግን ምስጢራዊነቱ እጅግ የበዛ እና ሽማግሌዎቹ እንዴት ሊሸመግሉ እንደበቁ ባለመገለጡ ውጤቱ እስካሁን በሕዝቡ ዘንድ ጥያቄ እንዳስነሣ ነው። እንኳን ሕዝቡ ራሳቸው ተሸምጋዮቹ ጥያቄ የሚያነሡበት ሒደት ሆኗል።

አራተኛው ነጥብ የሽምግልናው ግብ በግልጽ መቀመጥ መቻሉ ነው። ሽማግሌዎቹ ዓላማቸው ምንድርነው? የሚጠብቁት ውጤትስ ምንድርነው? ሽምግልናው ተሳካ/አልተሳካም የሚሉት የት ጋር ሲደርሱ ነው? እነዚህ እና እነዚህን መሰል ጥያቄዎች በግልጽ ተነሥተው በግልጽ መልስ ማግኘት አለባቸው። “አለባብሰው ቢያርሱ ባረም ይመለሱ” እንደሚባለው እንዳይሆን።

ከዚህ አንጻር አሁን የተጀመረው መልካም የእርቅ እና የሽምግልና ሒደት ግቡን እንዲመታ የሽማግሌዎቹ ቡድን እነዚህን ጉዳዮች ለመፈተሽ ሃይማኖታዊም፣ ባህላዊም፣ ሞራላዊው ግዴታ አለበትና በዝርዝር ሊመለስበት፣ ጋዜጣዊ መግለጫ በመስጠትም ሆነ ሕዝቡን ይወክላሉ የሚባሉ አካላትን በማማከር ገለልተኛነቱን እና ብቃቱን ማሳየት አለበት እንላለን። አለበለዚያ ግን እንደ አልጀርሱ የኢትዮ-ኤርትራ ሽምግልና “ተፈፀመ፣ ታረቁ” የሚለው ፊርማ ሳይደርቅ “አልታረቅንም” የሚል መግለጫ እንደማይወጣ ማስተማመኛ አይኖረንም።

በመጨረሻ
ይህንን ሁሉ ማለት የፈለግነው እንዲያው በደፈናው “ጨለምተኞች” (ፔሲሚስት) ስለሆንን፣ ወይም ይህ እርቅ እንዳይሳካ ስለምንፈልግ፣ ወይም እንዲያው ነገር ለማዳመቅ ከመሻት አለመሆኑን ማንም አስተዋይ ልቡና ያለው ሁሉ ይረዳዋል ብለን እንገምታለን። ሽማግሌዎች እና ተደራዳሪዎቹም ጭምር።

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

13 comments:

Anonymous said...

Dear Dejeselam,

The article is well written and it came at the right time. I hope most of the church leader read this article. If possible I reccomned to send to the 'Shimgles' and main church leader the hard copy by post and soft copy email. Who knows they may change their direction. If you allow me at current setution of Ethiopia Prof Issac should leave this shimglan work. Totally he desnot deserve it. He is an 'enemy' for Ethiopia politics.

UkMan

Anonymous said...

"ጸልዩ በእንተ ሰላም ፍጽምት ወፍቅር ተዓምሁ በበናይቲክሙ በአምሃ ቅድሳት።"

Anonymous said...

enem bezih hasab ismamalehu. gelelitegna yebetekristian amakari yashal. amlak cher yaseman, betun yitadeg, amen

Anonymous said...

ALL OUR HOLY FATHERS ARE AGING.IF THEY KEEP ON REFUSING TO BRING PEACE AND UNITY IN THE CHURCH WHILE THEY ARE ALIVE ...DON'T WORRY...GOD WILL GET RID OF THEM...EITHER ABUNE MERKORIOS OR ABUNE PAULOS!.PLEASE MAKE HISTORY AND DIE AFTERWARDS.IF U PASS AWAY WITH OUT CONTRIBUTING TO THE PEACE AND UNITY OF ORTHODOX CHURCH ,LEAVING ALL OF US IN CHAOS THEN I WOULD SAY "SHAME ON ABUNE PAULOS OF ETHIOPIA AND ABUNE MELKETSEDEK OF USA".U GUYS SHOULD HAVE TO CONSENSUS WHEN U'RE ALIVE WITH OUT THIRD PARTY INVOLVEMENT.I WILL CONTINUE MY DAILY PRAYER AND I KNOW GOD WILL GIVE ME A RELIEF SOON.

Anonymous said...

why did you erase my comments? sounds like you are only posting who is on your side? Egziabhere aywerdewem!

Anonymous said...

Hi is any body can tell me how can I wright in Amharic font on this blog.

Thanks in advance!!!

Anonymous said...

DEAR ABATOCHE,
JESUS CHRIST DIED ONCE FOR US.HE SHOWED US HOW TO LOVE EACH OTHER BY SACRIFICING HIMSELF.ABUNEPAULOS AND ABUNE MELKETSEDEK OF USA ARE SITTING ON THE DRIVER'S SEAT .SO MANY ACCIDENTS HAPPENED TO YOUR NAIVE PASSENGERS.PLEASE STOP DRIVING US WITH RED LIGHT.SO MANY INDEPENDENT DRIVERS ARE FLOURISHING AND GIVING A FREE RIDES TO YOUR PASSENGERS.LOOK,LISTEN AND FEEL YOUR PASSENGERS OTHERWISE YOUR PASSENGERS WILL SAY NO EVEN TO FREE RIDE IN THE NEAR FUTURE.

Anonymous said...

ውድ ደጀ ሰላም
ስለ ሃይማኖታችን ዜና በተመለከተ ለማንበብ ስፈልግ ምርጫየ እናንተ መሆናችሁ ስገልጽ በደስታ ነው.ግን በዚህ የሽምግልና ጉዳይ በተመለከተ የምትጽፉት ጽሁፍ ግን ትንሽ አይስማማኝም. አንድ ጽሁፉ የበሰለ ሆኖ አይታየኝም ሁለተኛ ነገሮችን አገናዝቦ የሚጽፍ አይመስለኝም. እነዚህ ሽማግለዎች ሰው እንዲሰማላቸው ወይም እንድያይላቸው ሳይሆን የቤተክርስትያኒቱን አንድነቱዋን ናፍቆዋቸው መለያየቱዋን ደግሞ አሳዝኖዋቸው አባቶችን አንድ የማድረግ ሃላፊነት ተሰምተዋቸው ነው. ከዚህ በፊትም አሁንም የምትጠቅሱዋቸው ሁለት ነጥቦች አሉ: ምስጢርና ቀጣዩ ሁኔታ የሚሉ. ሚስጥር የምትሉትን ነገር አልገባኝም ምክንያቱ ምስጢር የሆነው በቭኦኤ ወይም ኢቲቭ ወይም ሌሎች የመሳሰሉ አውታሮች በዜና መልክ ስላልተላለፉት ነው? ወይስ ህዝቡን ስላላማከሩት? ነገሩኮ አቡነ ዜና ማርቆስ ባማለፋቸው በተነሱ ነጥቦች ስሜት የተቀሰቀሱ ይመስለኛል. ነገሩ ገና ጅምር ነው. የሁለቱም አካላት ይሁንታ ከተገኘ በሁዋላ ነገሮች ቀስበቀስ ወደ ህዝቡ መድረስ ይችላሉ.እናንተ ምስጢር ምስጢር እያላሁ ነገሮች ከማስተካከል ይልቅ ነገሮች እንዳታባላሹ ጠንቀቅ ማለት ይበጃል. የሸምጋዮቹ ብቃትና ችሎታ ሳይሆን ሊያሳስባቹሁ የሚገባ አባቶች ይህንን ነገር ጀመሩ እኛስ በበኩላችን ምን እናድርግ ብላችሁ ህዝቡን የሚያወያዩ ነገሮች አምጡ. ለትችት ግዜው አልደረሰምና. ህዝቡ ብያውቀውና ቢወያይበት ጥሩ ነው ግን እንደምናየው እነዛ በህዝቡ መሃከል ተሽግሽገው የቤተክርስትያኒቱ አንድነት የማይፈልጉ ገብተው ሊዘባርቁ ስለሚችሉ ውጤት ያለው ፍሬ እስኪገኝ ድረስ በሽማግሌዎቹ እጅ ቢቆይ ጥሩ ይመስለኛል. የህዝቡ ተቀባይነት ይኑራቸው አይኑራቸው ቢታወቅ ላላችሁ ደግሞ: በህዝቡ ታዋቂነት ያላቸው ምን ስያደርጉ አየንና? በህዝቡ ዘንድ ብዙም የማይታወቁ ግን ለቤተክርስትያኒቱ ቀናኢ የሆኑ ብዙዎች አሉ ስለዚህ ይህንን ነገር ግቡ ላይ ካደረሱት በህዝቡዘንድ ታዋቂነት ሊኖራቸው ይችላ. ተቀባይነት ኖራቸው አልኖራቸው ሳይሆን ነገሩ ግቡ መምታቱና አለመምታቱ ነው.
ሌላው ከዕርቁ በሁዋላ የሚል ነው. ቤተክርስትያኒቱ አንድ ከሆነች አባ ጳውሎስም ሆኑ አባ መርቆርዮዎስ ነገ ማለፋቸውን አይቀርም ከዛበሁዋላ የሁለቱም ሲኖዶስ ጥምር የሆነ ጉባኤ የመረጣቸው አባት ቤተክርስትያኒቱን አንድ የማድረግ ሃልፊነት አላቸው. መጥፎ የምሆነው ግን እነዚህ ሁለት አባቶች ሳይታረቆ ያለፉ እንደሆነ ነው.
ስለዚህ ትልቁ ነጥቤ ደጀ ሰላም የአባቶች ብቃትና ተቀባይነት ግምገማ/ሂስ ከምታካሂዱ ይልቅ እናንተም ህዝቡ ህሳቡን የሚገልጽበት ነጻ መድረክ አዘጋጁ ነገር ግን እንደዚህ ያለ አሻሚ የሆና መዋያያ ነጥብ መሆን የለበትም. ምክንያቱም እንደዚህ ያለ ነጥብ ከጥቅሙ ይልቅ ጉዳቱ ሊበዛ ይችላልና.
ይህንን ሃሳብ ስሰነዝር ግን ለደጀ ሰላም ያለኝን አክብሮት ከመግለጽ ጋራ ነው.

Anonymous said...

LET'S BE PRACTICAL.THE MAIN DIFFERENCE BETWEEN THE 2 MAIN GROUP BECOMES BEYOND ADMINISTRATION.THE USA GROUP LED BY ABUNE MELKETSEDEK(SORRY ABUNE MERKORIOS HAS NO ADMINISTRATIVE POWER)ARE SHOWING US WORSHIP WITH PIANO/ORGAN,AMERICANIZED MASS AND LIVING WORLDLY.THE ABUNE PAULOS GROUP IS MORE OF ETHNOCENTERIC,POLITICALY AFFILIATED WITH FULL OF INJUSTICE AND CORRUPTION.I DON'T WANNA SAY MORE BUT GOD HAS TIME TO PUNISH THOSE WHO ARE PLAYING THE ACTIVE DRAMA.IF U ARE TRUE CHRISTIAN KEEP ON PRAYING.GOD HAS A POWER AND CAN'T WAIT TO SEE WHAT HAPPEN SOON.

abe said...

ደጀ ሰላማውያን ያቀረባችሁትን ለእርቁ ሊጠቅም ይችላል ብላችሁ ያሰባችሁትን ግሩም የሆነ አስተያየት መሳይ ግን ጥሩ የሆነ አቅጣጫ ሊያሳይ የሚችል ጽሁፍ ወድጀዋለሁ። ሌላውም የቤተ ክርስቲያኒቱ ያለችበት ችግር የሚገደው አንባቢ የሆነ አገልጋይም ሆነ ምእመን ገንቢ የሆነ አስተያየት በመስጠት ይበልጥ ለውይይት እንዲቀርብ ጥረት ቢደረግ መልካም ይመስለኛል። ነገር ግን ከአንዳንድ አስተያየት ሰጭዎች ጽሁፍ እንደማነበው፡ እርቁ እንዲኖር ከማይፈልጉና ይህ ያሉበት ሁኔታ በተለያየ መልኩ በቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ስም ጠቅሞዓቸው የሚገኙ ካህናትም ሆነ ምእመናን ስለ ቤተ ክርስቲያን ስርዓት፣ ቀኖናም ሆነ አንድነት ጥበቃ ስራ ለመስራት የሚነሳን አካል ሁሉ "እነዚህ ከአንድነታችን ሊለያዩን፡ ሊከፋፍሉን ነው የመጡ" ሌላም በማለት የሚሰብኩ፣ አስተያየት የሚሰጡና በተከታዮቻቸውም ዓእምሮ ውስጥ ለማስረጽ የሚሰሩ ሰዎች ስላሉ ቢቻላችሁ እነዚህ ሰዎች ወደ ህሊናቸው እንዲመለሱ የሚያደርግ ስራ እንዲሰራ ሁሉም የቤተ ክርስቲያን ተቆርቋሪ ሁሉ ቢጥር መልካም ነው። ይህ ግን አንድነትስ የሚሉት አጥቢያቸ ውን፣ ገለልተኛነታቸውን ወይስ ስደተኝነታቸውን?
አገር ውስጥም ሆነ ከሀገር ውጭ ያለ የቤተ ክርስቲያኒቱ ተከታይ፡ እንደተባለው ለእርቁ በጎ የሆነ ተጽዕኖ በአባቶቻችን ላይ ማምጣት እንዲችል ተመሳሳይ የሆነ ግንዛቤ እንዲኖረውና ሊከሰት ይችላል ተብሎ ከሚፈራው ያለመተማመን ችግር እንዲድን በዓግባቡ እንደሚስጥር መያዝ የማይገባቸው ሂደቶች እና ጉዳዮች ግልጽ የመደረግ ድፍረቱ ቢታይ፡ ቢለመድ መልካም ይሆናል ብዮ አምናለሁ።
መልካሙን ዘመን ያምጣ።

Anonymous said...

What makes unity difficult within EOTC is the fact that the external and internal Synods have entrenched themselves along political lines: one in support of the Woyane and the other one opposed to it.

The solution is that Mi'imenan should rise in unity against political engagements of the above genre and focus on only religious perspectives

አግናጢዋስ ዘጋስጫ said...

መግቢያ ባጣ ነበር

በሰሜን በደቡብ በምዕራብ በምስራቅ
ከአድማስ እስከ አድማስ ከቅርብ እስከ ሩቅ
ሰው በሚኖ ርባት በዚች ዓለማችን
አልሰ ማሁም ከቶ አንድም ቀን ሰላምን
በመላዋ ምድር በሁሉም አቅጣጫ
ሁሌም ንትርክ ሁሌ ም ፍጥጫ
የምድር መናወጥ ጦርነት ፍንዳታው
የዉሃ መጥለቅለ ቅ የ እሳት አደ ጋው
ሳይሰማ ዉሎ አንድም ቀን አያዉቅም
ሰላም አይሰ ማም ነገሩን አላዉቅም
ምድር ከጥላቻ ከበደል ርቃ
ርኃብ ጦርነት አደጋውን ናፍቃ
ሁሉም የአዳም ዘር መሆኑን ተረድቶ
በሰላም በፍቅር ቢኖ ር ተስማምቶ
መግቢያ ያጣ ነበር ጥንተ ጠላታችን
የሰው ልጆች ጸር ሰይጣን ፈታኛችን::

Anonymous said...

Please browse: www.eotcipc.org

Let Mi'imenan unite!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)