June 25, 2010

ለብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሥርዓተ ጸሎተ ፍትሐት በአሜሪካ ተካሄደ

(ደጀ ሰላም፣ ጁን 25/2010)፦ የሚከተለውን ዜና በ"ፌስቡክ" ሣጥናችን ያደረሱን "መሐሪ ሙሉጌታ ማራናታ" የተባሉ እና "የብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ማስታወሻ ገጽ" በሚል በፌስቡክ መታሰቢያቸውን የሚዘክሩ ደጀ ሰላማዊ ናቸው። ስለ ሪፖርታቸው ከልብ እናመሰግናለን። እኛም የእርሳቸውን ዓይን "ዓይናቸን" አድርገን፣ በቦታው እንደተገኘን አስበን ዘገባውን እናስነብባለን።
ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን
++++
"እንኳንስ ተለያይተን፤ አንድ ሆነንም አንችለውም። ዘመኑ እኩይ ነው ዘመኑ ክፉ ነው ወገኖቼ ..." ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሊቀ ጳጳስ
(ዋሺንግተን ዲሲ)፦ ትላንት ሐሙስ ሰኔ ፲፯ ቀን ፳፻፪ ዓ/ም የብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሊቀ ጳጳስ ሥርዓተ ጸሎተ ፍትሃት በዚህ በሰሜን አሜሪካ ዋና ክፍለ ከተማ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው በደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ አብርሃም የዋሽንግተን ዲሲና የአካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የሲዳማ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ ከተለያዩ አድባራት የመጡ የደብር አስተዳዳሪዎች፣ ቆሞሳት፣ ቀሳውስትና ዲያቆናት እንዲሁም ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ዘማርያን፣ ሰባኬ ወንጌላውያንና የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን በተገኙበት ከተደረገ በኋላ ብፁዕነታቸው በሕይወት በነበሩባቸው ጥቂት ዘመናት የሰሯቸው አያሌ ቁምነገሮች መካከል ጥቂቶቹ በምስልና በድምፅ የተዘጋጁት መረጃዎች ታይተዋል።
እንዲሁም በተወለዱበትና በአደጉበት ብዙ ሥራዎችንም በሰሩበት በምሁር ኢየሱስ ገዳም የተፈጸመውም ሥርዓተ ቀብራቸው በዚያ የተገኙ ምዕመናን በቪዲዮ የማየቱን ዕድል አግኝተዋል። ከዚያም በኋላ የሕይወት ታሪካቸው የደ/ም/ቅ/ሚካኤል ቤ/ክ አስተዳዳሪ በሆኑት በቆሞስ አባ እስጢፋኖስ ባህሩ ተነቦ በመጨረሻም ብፁዕ አቡነ አብርሃም ቃለ ምዕዳን ከሰጡ በኋላ የሥርዓቱ ፍጻሜ ሆኗል። የብፁዕ አባታችንን ነፍስ አምላካችን ከደጋጎቹ ወገን ያኑርልን። ለቤተሰቦቻቸውም ፍጹም መጽናናት ያድልልን። አሜን።

4 comments:

Tade... said...

Sign of unity!!! I love such type of news.

Thank you DejeSelam.

Anonymous said...

"እንኳንስ ተለያይተን፤ አንድ ሆነንም አንችለውም። ዘመኑ እቡይ ነው ዘመኑ ክፉ ነው ወገኖቼ ..." ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሊቀ ጳጳስ የሚለው….. “ዘመኑ እኩይ ነው”…..በሚለው ቢስተካከል???

Anonymous said...

ቅዱስ አባታችን እግዚአብሔር ነብሶትን በገነት ያኑርልን ለቤተክርስቲያን የነበሮትን ፍቅር ምን ያህል እንደነበር የምናውቀው ነው ፡፡ እርሶ አረፉ እኛ ግን በሚያሳዝን ድምጽ አንጀት በሚበላ ቃል ስለ እግዚአብሔር ፣ ስለ እመቤታችን እና ስለ ቅዱሳን የሚነገረን አባት አጣን
እንግዲህ መቃብር ጠንክረህ ተማር
ድጓ ተሸክሞ መጣልህ መምህር

Anonymous said...

It's a sad news that I'm just hearing. Aba was my spiritual father who ordained me as a deakon and I always reminds him im my prayers for he inpired me a lot for spiritual services. I believe he will continue praying 4 us all in Heaven. Oh! aba I remember what U said for us while ordaining us as deakons " serve the church without criticism of sin..." May your prayer help me to....

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)