June 24, 2010

የብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

(ደጀ ሰላም፣ ጁን 23/2010)፦ የከምባታ፣ ሐድያ፣ ጉራጌና ስልጢ አህጉረ ስብከተ ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የነበሩት ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሥርዓተ ቀብራቸው ሰኔ 15 ቀን 2002 ዓ.ም (ጁን 22/2010) ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናት አባቶችና ምእመናን በተገኙበት በምሁር ኢየሱስ ገዳም ተፈጸመ፡፡ ስለ ብፁዕነታቸው የማ/ቅዱሳን ድረ ገጽ የሚከተለውን ምጥን ጽሑፍ አትሟል።

ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ያስተዳድሩት በነበረው ሀገረ ስብከት ውስጥ በሚገኘው እዣና ወለኔ ወረዳ /ምሁር ኢየሱስ ገዳም አካባቢ/ ከአባታቸው ከመምሬ ክንፈ ሚካኤልና ከእናታቸው ከወ/ሮ አስካለ ማርያም በ1951 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ የምሁር ኢየሱስ ገዳም ቄሰ ገበዝ የነበሩት አባታችው በዚያው ፊደልና የቁጥር ትምህርት አስተማሯቸው፡፡

በመቀጠል ወደ ተለያዩ አካባቢዎች በመሔድ ቅኔ፣ መዝገብ ቅዳሴና ሌሎች ትምህርቶችን ተምረዋል፡፡ ከተማሩባቸው ቦታዎች መካከል አንዱ የዝዋይ ሐመረ ብርሃን ቅዱስ ገብርኤል ገዳምና የካህናት ማሠልጠኛ ተቋም በዋናነት ይጠቀሳል፡፡ በዚሁ ማሠልጠኛ በመምህርነትና በአስተዳዳሪነትም አገልግለዋል፡፡

የሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ከነበሩት በብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልአይ እጅ መንኩሰው ቅስና የተሾሙ ሲሆን፤ በ1987 ዓ.ም በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ የኤጲስ ቆጶስነት መዓርግ ከተሰጣቸው የቤተ ክርስቲያን አባቶች መካከል አንዱ ነበሩ፡፡

ኤጲስ ቆጶስነት ከተሾሙበት ጊዜ ጀምሮ ዐረፍተ ሞት እስከገታቸው ድረስ የከምባታ፣ ሐድያ፣ ጉራጌና ስልጤ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በመሆን አገልግለዋል፡፡ የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከትም በተጨማሪነት በሊቀ ጳጳስነት ማስተዳደራቸው የሚታወስ ነው፡፡ እንደዚሁም ከ1997 ዓ.ም እስከ 1999 ዓ.ም ድረስ የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ በመሆን ማገልገላቸው ይታወቃል፡፡

8 comments:

Anonymous said...

ጁላይ 15,2009 የወጣው የደጀ ሰላም ዘገባ ይህ ነበረ።
“”(ሰበር ዜና፣ Breaking News) ብፁዓን አባቶች ላይ አደጋ ተጣለ”
ከዚያን ግዚ ጀምሮ በርካታ አባቶች ችግር አየደረሰባችው ነው። ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ በከባዱ ታመው ሀኪም ፍለጋ ውጭ ህደው ታከሙ። የጉራጌ፣ ሀድያና ስልጢ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ የሆኑት ብፁዕነታቸው አባታችንም አቡነ ጳውሎስን ከሚቃወሙ ወገኖች መካከል አንዱ ነበሩ።ወዲያው በጉበትና ካንሰር በሽታ ታመሙ ተባለ።አዲስ አበባ ውሰጥ ውሰጡን የሚወራው አባታችን የሞቱት በደባ መሆኑን ነው።ከምግብ ጋር በተሰጠ መድሀኒት መታመምና መሞታቸው ይናፈሳል።ደጀ ሰላሞች ባካቸሁ ጦማራችሁሚስጥር ልታገኝ ስለምትችል investigative journalism ብታካሂዱ።
ሚስጥር አዋቂ

የፍቅር አባት said...

እግዚአብሔር ሰጠ
እግዚአበሔር ነሳ አለ
ብሎ ተናገረ
የእግዚአብሔር ወዳጅ
ኢዮብ የተባለ
ተሰጥቶን ነበረ ለኛ በአባትነት
በጎቹ እንድንሆን እርሱም በረኛነት
ሲያሰማራን ነበር ከውሃው ከለምለሙ
አምላኩ እንዳዘዘው በብዙ ድካሙ
እኛስ መስሎን ነበር የማይለየን
እንዲህ በቀላሉ የማይወስድብን
የማይወቅሱትና የማይከሱት ጌታ
በገዛ ንብረቱ ምን እንካ ሰላምታ
ወዳጁን ያውቀዋል የርሱ የሆነውን
ቶሎ ይወስደዋል ያዘጋጅለታል
ክቡር ማረፊያውን
የሰጠን አስቦ ለጊዜው ነው ነበረ
ቀሪው ሕይወታችን እንዲሆን የከበረ
እግዚአብሔር ቢሰጥ እግዚአብሔር ቢነሳ
ሁለቱም አንድ ነው የለበት ወቀሳ
ስራ ሰርቶብናል በአገልጋዩ አድሮ
ምስክርነቱን በልባችን ጭሮ
ወቀሳው ለኛ ነው የክሱ መዓት
ፍሬ ባናፈራ ሆነን በመገኘት
ለምለሟን መሬት
እንግዲህ አባታችን አፈሩ ይቅለለው
ከቅዱሳኖቹ ዘንድ ነፍሱን ያሳርፈው

ከለንደን

selamawi said...

በስመ ስላሴ አሃዱ አምላክ አሜን

የአባታችንን ነፍስ ከአገልጋዮቹ ከቅዱሳን ጋራ ይደምርልን

በተረፈ ከላይ ,,,,,,,

ወዲያው በጉበትና ካንሰር በሽታ ታመሙ ተባለ።አዲስ አበባ ውሰጥ ውሰጡን የሚወራው አባታችን የሞቱት በደባ መሆኑን ነው።ከምግብ ጋር በተሰጠ መድሀኒት መታመምና መሞታቸው ይናፈሳል።ደጀ ሰላሞች ባካቸሁ ጦማራችሁሚስጥር ልታገኝ ስለምትችል investigative journalism ብታካሂዱ።
ሚስጥር አዋቂ,,,,,,,,ተብሎ ለተሰጠው አስተያየት የተሰማኝን ለመጠቆም ነው ምን መሰላችሁ ወገኖቼ የምንገምተው ነገር ሁሉ እውነት ሊሆን ይችላል ነገር ግን ያለእግዚአብሔር ፈቃድ የሚሆን ነገር የለም አባታችን እንደተባለው መርዝ ተመግበው ነው ብንል እንኳ እርሱ ወዶ ፈቅዶ በዚያች እለት ባይጠራቸው ኖሮ መርዙም ኃይል ሊኖረው አይችልም ስለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ ወደ ኤፌሶን ሰዎች 4፥29 ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ። ,, እንዳለው እዚህ መድረክ ላይ ሰዎችን የሚያንጽ መልእክት ለማስተላለፍ ብንሞክር መልካም ነው እላለሁ

Anonymous said...

Egziabher hoy yeytopiya mekera ena fetenachin beza! Mirt Mirt abatochachin aleku. Amlak hot bekachu belen?

Ye abatachinin nebs ante mar.

Dan said...

selamawi said...

"ለተሰጠው አስተያየት የተሰማኝን ለመጠቆም ነው ምን መሰላችሁ ወገኖቼ የምንገምተው ነገር ሁሉ እውነት ሊሆን ይችላል ነገር ግን ያለእግዚአብሔር ፈቃድ የሚሆን ነገር የለም አባታችን እንደተባለው መርዝ ተመግበው ነው ብንል እንኳ እርሱ ወዶ ፈቅዶ በዚያች እለት ባይጠራቸው ኖሮ መርዙም ኃይል ሊኖረው አይችልም"

ይህ አስተያየት ትምህርት የጎድለው ይመስላል:: ክፋት መጥፎ ተግባርና የበደል ሥራዎችን እግዚአብሔር አይፈቅድም::
አንድ ወንበዴ ስው ቢገድል ያሰው የሞተው እግዚአብሔር ስለፈቀደ ነው ማለት ትክክል አይደለም::
እንዲህ ያሉ የልማድ አነጋግር ከክርስቲያን አይጠበቅም::

Anonymous said...

selamawi said...

ለተሰጠው አስተያየት የተሰማኝን ለመጠቆም ነው ምን መሰላችሁ ወገኖቼ የምንገምተው ነገር ሁሉ እውነት ሊሆን ይችላል ነገር ግን ያለእግዚአብሔር ፈቃድ የሚሆን ነገር የለም አባታችን እንደተባለው መርዝ ተመግበው ነው ብንል እንኳ እርሱ ወዶ ፈቅዶ በዚያች እለት ባይጠራቸው ኖሮ መርዙም ኃይል ሊኖረው አይችልም ......እላለሁ"

selamawi ሆይ, ይህ አስተያየት ትምህርት የጎድለው ይመስላል::

ክፋት ምጥፎ ተግባርና የበደል ሥራዎችን እግዚአብሔር አ ይፈቅድም::

አንድ ወንበዴ ስው ቢገድል ያሰው የሞተው እግዚአብሔር ስለፈቀደ ነው ማለት ትክክል አይደለም::

እንዲህ ያሉ የልማድ አነጋግር ከክርስቲያን አይጠበቅም::

Anonymous said...

It is naive to think that weyane will let the EOC free of his political security interest,therefore it must have short list of whom will replace in case Abba Paulos dies. This leads to intellectual guess of eliminating charismatic individuals who might not fit weyane's interest.Abune Melketsedek's death circles in this raduis.But God is watching...He will redem His church.Dear father R.I.P.

selamawi said...

በስመ ስላሴ አሃዱ አምላክ አሜን

ሰላም ለኩልክሙ አበውየ ወእምየ አኃውየ ወአኃትየ

ሰላም ሰላም ሰላም አሁንም ሰላም ለሁላችን ይሁን መቸም ይች ደጀ ሰላም የምትባል ቦታ ድሮ ጮማና ጠጁን እንዳልቆረጥንባት ዛሬ መቆራረጫ ወደ መሆን እየተቀየረች ነው ምን ይደረግ ጸጋችን ተገፈፈ እለት እለት በደል ማከማቸት እንጅ ማቃለል የለ አምላክ ሆይ ከደ ጀሰላምህ አታርቀኝ ነው የሚባለው

እስቲ ወደ አስተያየቴ ልምጣ ሰሞኑን መቸም እንደምታውቁት ቤተክርስቲያን የተመሰረተችበት በዓል በመላዋ የተዋህዶ ቤ/ክ እንደሚከበር ይታወቃል ታዲያ ይህችን እንደእናት ጡት አጥብታ ያሳደገችንን ቤተክርስቲያን በድንግል ደጅ ሆኖ ለማክበር እድሉ ገጠመኝና ለጥቂት ቀናት ያክል ወደ ደጁካ ብቅ ሳልል ብቀር -- -- መጣብኝ አይገርምም ?

በተረፈ በመጀመሪያ ዳን የተባልክ ወንድሜ እንዴት አለህልኝ መቸም ለስሙም አያምርም ደጀሰላም ተጣሉ ቢባል አይደል ? ምን ይታወቃል የዛሬን አያድርገውና ምናልባት አማናዊቷ ደጀሰላም ተገናኝተን አንድ ማእድ ተቋድሰን ይሆናል ማን ያውቃል? ለማንኛውም ጥሩ አድርገህ መሃይምነቴን ስለነገርከኝ አመሰግንኃለሁ ይህንን ቃል ታውቀዋለህ?

ዘፍ 49፥17 ዳን በጐዳና ላይ እንደ እባብ ይሆናል፥ በመንገድም እንደ ቀንዳም እባብ ፈረሱን ከሰኮናው ይነክሳል፥ ፈረሰኛም ወደ ኋላው ይወድቃል። እግዚአብሔርም ያድነው ዘንድ ይጠብቃል፤

ደስ የሚለኝ ቃል ነው አንተም ስሙን መያዝ ብቻ ሳይሆን ተጠቀምበት እንጅ?

ኮሎ ዘፈቀደ ገብረ እግዚአብሔር በሰማይኒ ወበምድርኒ በባህርኒ ወበኩሉ ቀላያት እያልን መኖራችንን >> እውቀት የጎደለው >> የልማድ አነጋገር ነው ካልክማ ? ሰዓሊ ለነ ቅድስትም ልማድ ነች ማለት ሊመጣ ነው አንተ ታውቃለህ

ለማኝኛውም መክብብ 10፥8 ላይ ጕድጓድን የሚምስ ይወድቅበታል፥ ቅጥርንም የሚያፈርስን እባብ ትነድፈዋለች።

እንደተባለው በእግዚአብሔር ሰዎች ላይ ማንም ተነስቶ መርዝ አበላለሁ ቢል ተዋጊ አምላክ ስለሆn ያላቸው እርሱ መርዙን መድኃኒት ማድረግ ይችላል ለማለት ፈልጌ ነው ከተረዳኸኝ

ኢሳ 65፥25 ተኵላና ጠቦት በአንድነት ይሰማራሉ፥ አንበሳም እንደ በሬ ገለባ ይበላል፥ የእባብም መብል ትቢያ ይሆናል። በተቀደሰው ተራራዬ ሁሉ አይጐዱም፥ አያጠፉምም፥ ይላል እግዚአብሔር፦ ታዲያ ይህ በማን ፈቃድ ነው የሚሆነው

ቅዱስ ጳውሎስ ሮሜ 3፥13 ላይ ,,ጕሮሮአቸው እንደ ተከፈተ መቃብር ነው፥ በመላሳቸውም ሸንግለዋል፤ የእባብ መርዝ ከከንፈሮቻቸው በታች አለ፤ ,, እንዳለው ዛሬ የተዋህዶ ልጆች ከአንደበታችን በሚወጣ መጥፎ ንግግር ከእናት ቤተክርስቲያናቸው እየኮበለሉ የተኩላ መጫወቻ እየሆኑ ነው ስለዚህ ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን እንደተባለው እግዚአብሔር የማያውቀው አንዳች ነገር የለምና ሁሉም በሱ ፈቃድ ነው የሆነው በሚለው አቋሜ እንደጸናሁ ነኝ ነገር ግን ቅዱስ ዮሐንስ በመልእክቱ 1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3፥15 ወንድሙን የሚጠላ ሁሉ ነፍሰ ገዳይ ነው፥ ነፍሰ ገዳይም የሆነ ሁሉ የዘላለም ሕይወት በእርሱ እንዳይኖር ታውቃላችሁ። እንዳለው ስለምክርህ አመሰግናለሁ እንጅ ቅሬታ የለኝም ቸር ይግጠመን

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)