June 21, 2010

(ሰበር ዜና) ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ አረፉ፣

(ደጀ ሰላም፣ ጁን 21/2010)፦ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ከዚህ ዓለም ድካም ዛሬ ጁን 21/2010 በሞት ተለዩ።

የጉራጌ፣ ሀድያና ስልጢ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ የሆኑት ብፁዕነታቸው በጉበት ካንሰር በሽታ ሲታከሙ ቆይተው ዛሬ ሌሊት አርፈዋል። አስከሬናቸውም ዛሬ ወደ ታላቁ የምሑር ገዳም የተሸኘ ሲሆን ሥርዓተ ቀብራቸውም ነገ ማክሰኞ ይፈጸማል።
ብፁዕነታቸው በታታሪነታቸው ከሚመሰገኑ አበው መካከል አንዱ ሲሆኑ ባለፈው ዓመት በቤተ ክህነቱ በተነሣው የሕገ-ቤተ ክርስቲያን ይከበር ጥያቄ ሐምሌ 8 ቀን 2001 ዓ.ም መኖሪያቸው ከተደበደበውና አደጋ ከተጣለባቸው ብፁዓን አባቶች መካከል አንደኛው መሆናቸው ይታወሳል።
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)