June 14, 2010

አቡነ ቄርሎስ ሕክምናቸውን ጨረሱ፣ በመልካም ጤንነት ላይ ናቸው

(ደጀ ሰላም፤ ጁን 14/2010)፦ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ በጀርመን አገር ፍራንክፈርት ከተማ ሲከታተሉ የነበረውን ሕክምናቸውን ጨረሱ፣ በመልካም ጤንነት ላይ ናቸው።


አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ በጀርባቸውና በእግራቸው ላይ የሚሰማቸውን ሕመም መፍትሔ ለማግኘት ኤፕሪል ወር መጀመሪያ ላይ በመጀመሪያ ወደ ግሪክ ያቀኑ ሲሆን ቀጥሎም ለተሻለ ሕክምና ወደ ጀርመን ተጉዘው ነበር። በሰው ድጋፍ ይንቀሳቀሱ የነበሩት ብፁዕነታቸው በአሁኑ ወቅት በተሻለ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል። 


ብፁዕነታቸው የጀርባ እና የእግር ሕመም የነበረባቸው ሲሆን በጀርመን ባገኙት የፊዚዮቴራፒ ሕክምና ከሕመማቸው ስላገገሙ በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ ይመለሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)