June 16, 2010

ፍርድ ቤት የዳላስ ቅ/ሚካኤል ቦርድ ላይ ዕግድ ጣለ፣ ከዚህ በሁዋላ ሰዎችን በፖሊስ መከልከል አይችልም

 የዳላስ ክፍለ ከተማ (County) ፍርድ ቤት ዳኛ ማርቲን ሎዊ የቅ/ሚካኤል ቦርድ ላይ ዕግድ ጣሉ፣ ከዚህ በሁዋላ በፖሊስ መከልከል እንዳይችልም ፈረዱ።  በአቶ ተኮላ መኮንን እና በአቶ ፀሐየ ጽድቅ ቤተ ማርያም ከሳሽነት በሜይ 18/2010 በመዝገብ ቁጥር 10-05578-ኢ በቦርዱ አባላት በሆኑት በዮሴፍ ረታ፣ ሙሉጌታ ፋንታሁን፣ አበበ እውነቱ፣ ኢዩኤል ነጋ፣ አበራ ፊጣ፣ ወ/ሮ ተዋበች ታደሰ፣ አቶ ብዙአየሁ ጌታቸው እና በወ/ሮ ሰሎሜ መኮንን ላይ የተከፈተው ክስ ብይን አግኝቶ በዳኛው ፊርማ የፀደቀ ሲሆን በብይኑ መሠረት ከዚህ በሁዋላ ተከሳሾቹ ማንንም ከቤተ ክርስቲያን መከልከልም ሆነ ማስወጣት አይችሉም።
ከዚህም በተጨማሪ ማንኛውንም ቤተ ክርስቲያኑን የተመለከተ ነገር "መደበቅ፣ ማጥፋት ወይም መረጃዎችን ማውደም፣ የሒሳብ ማስረጃዎችን ማሸሽ እና መደበቅ ወይም ማጥፋት፣ ቪዲዮዎችን፣ ፎቶዎችን ከቤተ ክርስቲያኑ ሴኪውሪቲ ሲስተም ውስጥ ለይተው ማጥፋት" እናዳይችሉ ተበይኖባቸዋል። ይህ ጊዜያዊ ዕገዳ ጉዳዩ እንዲታይ እስከተወሰነበት እስከ ኦክቶበር 6/2010 ድረስ የፀና እንደሚሆንምተገልጿል።
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)