June 10, 2010

ዋሺንግተን ዲሲዎች እናመሰግናለን!!!

(ደጀ ሰላም፣ ጁን 9/2010)፦ በቅርቡ በዚህቹ የጡመራ መድረካችን በ"ደጀ ሰላም" ላይ የወጣውን "ቤተ ክርስቲያን የሚባርከው (“የሚከፍተው”) ማን ነው? ሥልጣኑስ የማን ነው?" የሚለውን መጣጥፍ በዲሲ እና በአካባቢው የሚገኙ ደጀ ሰላማውያን በማባዛት ለምእምናን ማድረሳቸውን በመስማታችን በደጀ ሰላም ስም "እናመሰግናለን" ለማለት ወደድን። ደጀ ሰላማውያን እንደጻፉልን ከሆነ ይኸው ጽሑፍ በአሜሪካዋ ዋና ከተማ በዋሺንግተን ዲሲ እና በአካካቢዋ በሚገኙት ታላላቅ አብያተ ክርስቲያናት በዕለተ ሰንበት ለማስቀደስ ለመጣው ሕዝበ ክርስቲያን እንዲደርስ ተደርጓል። ይሁን እንጂ ይህ ተግባር ያሳዘናቸው ሰዎች በበኩላቸው በጻፉልን የኢ-ሜይል መልእክት "እንዲህ ዓይነቱን አስነዋሪ ተግባር" እንድናቆም አስጠንቅቀውናል።
በእርግጥ "ቤተ ክርስቲያን የሚባርከው ማን ነው?" ብሎ መጠየቅ እና ለዚያም ቤተ ክርስቲያኒቱ የምታስተምረውን ትምህርት ማሳወቅ "አስነዋሪ" የሚሆንባቸው ይህ ትምህርት ከአማኙ ጆሮ እንዲደርስ የማይፈልጉ ብቻ ናቸው። ጉዳ  ይልቁንም የበለጠ እንድናስብበት እና የበለጠም እንድንጽፍበት ይገፋፋናል። በተለይም በሰሜን አሜሪካ ያለው የቤተ ክርስቲያን ችግር መነሻ እና መድረሻ ስለሆነ ደጀ ሰላም አበክራ ማሳሰቧን ትቀጥልበታለች። እስከዚያው ግን ይህ ጉዳይ ለሕዝበ ክርስቲያኑ እንዲደረረስ ያደረጉትን በሙሉ በቤተ ክርስቲያን ስም ከልብ እናመሰግናቸዋለን፤ በረከተ አበው ያድርባቸውም ዘንድ እንመኝላቸዋለን።
ቸር ወሬ ያሰማና፣
አሜን

7 comments:

የጻፍኩትን_ጻፍኩ said...

መጽሐፉ ጥሩ አድርጐ አሰቀምጦታል የእኒህን ሰዎች ባሕርይ ሲገልጥ..." ምክር ያጡ ሕዝብ ናቸው፥ ማስተዋልም የላቸውም። አእምሮ ቢኖራቸው፥ ይህንን ያስተውሉ ነበር፥ ፍጻሜያቸውንም ያስቡ ነበር።" ዘዳግም 32:28 "እንዲህ ዓይነቱን አስነዋሪ ተግባር" እንድናቆም አስጠንቅቀውናል። አይደል የተባለው ... ትክክለኛው ነገር ሲነገር አየሩም እውነት እውነትን ሲያውድ የእነሱ በሐሰት ላይ የተመሰረተ "እውነት" ቦታ ስለማይኖረው ነው እውነተኛውን ነገር በእነሱ አባባል "አስነዋሪ ተግባር" ብለው ጥላሸት መቀባታቸውን የተያያዙት። አስነዋሪው ተግባር ግን የትኛው እንደሆነ ልቦናቸው ያውቀዋል። እውነቱን መቅበር ደግሞ እንደማያዛልቃቸው ማን በነገራቸው? ... "እነዚህ ግን የማያውቁትን ሁሉ ይሳደባሉ፥ አእምሮም እንደሌላቸው እንስሶች በፍጥረታቸው በሚያውቁት ሁሉ በእርሱ ይጠፋሉ። ወዮላቸው፥ በቃየል መንገድ ሄደዋልና ስለ ደመወዝም ለበለዓም ስሕተት ራሳቸውን አሳልፈው ሰጥተዋል በቆሬም መቃወም ጠፍተዋል።" ይሁዳ 1:10 ተብለው በመጽሐፍ የተቀመጡት..... ልብ ይስጣቸው ከማለት በቀር ምን እንላለን ?

Anonymous said...

selam tx

Anonymous said...

betam teru

Anonymous said...

I am so Proud of my Brothers and Sisters!!!

desa said...

good job degeselamawyan!!! yketil.

Anonymous said...

nequ behaimanot qumu golmesu tenkeru benante zend hulu befeker yehun
rome 16;13-14
hulachen endemnawekew yetfeterw neger yasazenal neger gene ewnetawn maregaget yegebal yeteliaye asteiayet eyteset new yalew ebakachiew kemimelaketaw akale melsun asawekun yesew sem eytakesu mesadeb yemigeba yehaimanot akahed aymeslagem
hulu lemanets yehun

Anonymous said...

Engme Betame Yegeremegn Sele Feker Eyesebekulen Enresu Rasachew Feker Yelelachew Sewach Nachew....Teleku Sehetet Degemo Atefiwene Leyto Endemewekes Beteserew Tefat Yelilubeten Sewach Seme Eytekesu Mesadebachew Newe...Gene Lebitekerestian Ekorkoralehu Kemile sewe Endezihe Ayenet neger Tegebi Newe????...Ewenete Lebeitekerstian Tekorkuri Kehone Kerbo Menegager Ayeshaleme Neber???...Wnedemune Yemayewede..Agelegaye Endite...Seleb/Kn....tekorekquri Lihone Yechlale???...Betechluse Huluneme Befeker Lemaderge Mokeru...Fekre Yhege hulu Fetsamia Newena.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)