June 9, 2010

አብያተ ክርስቲያናቱ የሚዲያ የጋራ መድረክ ለማቋቋም ተስማሙ

(ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ጁን 9/2010):- በክርስቲያን ሚዲያ (መገናኛ ብዙኀን) ውስጥ የሚታየውን አሳሳቢ ገጽታ ለመለወጥ በኦርቶዶክስ፣ በካቶሊክና በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ስር ያሉ የሚዲያ ተቋማት የጋራ መድረክ ለማቋቋም ተስማሙ፡፡

የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር (ኢመቅማ) ግንቦት 27 እና 28 ቀን 2002 ዓ.ም. የክርስቲያናዊ ሚዲያ አገልግሎትን አስመልክቶ በአብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ለሚገኙ በሚዲያ ሥራ ለተሰማሩ ባለሙያዎች ባዘጋጀው ዐውደ ጥናት ላይ የጋራ መድረክ ለመመሥረት የተስማሙት ሦስቱም አብያተ ክርስቲያናት ናቸው፡፡

የኢመቅማ ጠቅላይ ጸሐፊ አቶ ይልማ ጌታሁን በዐውደ ጥናቱ ላይ እንደተናገሩት፣ ክርስቲያናዊ ሚዲያ ሃይማኖቶች ተከባብረው የሚኖሩበትን ገንቢ ሚና መጫወት አለባቸው፡፡ መንፈሳዊ የሕትመት ውጤቶች ከማቀራረብ ይልቅ የማራራቅና የመጠላላት መንፈስን ሲዘሩ አንዳንድ አፍራሽ ተግባራትንም ሲያከናውኑ መቆየታቸው አግባብ ባለመሆኑ ከእንግዲህ ተቀራርበው የመሥራቱን ልምድ ማዳበር እንደሚገባቸው አመልክተዋል፡፡

ማኅበሩ እንዳለው፣ አብያተ ክርስቲያናቱ ልዩነታቸው እንደተጠበቀ ሆኖ ተደማምጠው የሚሠሩበት ሁኔታ ለመፍጠር ዐውደ ጥናቱን ማዘጋጀቱ አስፈላጊ ሆኗል፡፡

በኅትመት ሚዲያ ውስጥ ስለሚታዩት አሳሳቢ አቀራረቦች "የክርስቲያን ሚዲያ ሜዳ" በሚል ርእስ ዳሰሳ ያቀረቡት አቶ ንጉሤ ቡልቻ እንደተናገሩት፣ ከሦስቱም አብያተ ክርስቲያናት አማኞች ብዙ በጎ ነገር እየተጻፈ ቢሆንም፣ ባሁን ጊዜ የሚጻፉትን አንዳንድ ጽሑፎች አጠቃላይ መልክ ሲጤኑ በምእመናን መካከል ጠብ የሚጭሩ፣ የራስን እምነት በትህትና ከማስረዳት ይልቅ በሌሎች አስተምህሮና ሥርዓት ላይ ስላቅና ትችት የሚያበዙ፣ የስሜት ትኩሳት በእጅጉ የሚያይልባቸው፣ ለኅብረተሰቡ የዘለቄታ ጥቅም ከማሰብ ይልቅ የዛሬ ማታ "ድል" የሚያጓጓቸው፣ ከመጽሐፍ ቅዱስና ከሕሊና እውነት በላይ የቡድን ታማኝነት የሚያሸንፋቸው፣ ከብርሃን ይልቅ ሙቀት የሚጨምሩ ጽሑፎች ሆነው እናገኛቸዋለን፡፡

አቶ ንጉሤ ለቅርርብ ያለውን ሜዳ ያጠባል ብለው ያነሷቸው በመጽሔቶችና በጋዜጦች፣ በመጻሕፍትም ውስጥ አንዱ ሌላውን ለመጥራት የሚጠቀምባቸው ልዩ ልዩ ስሞችን ነው፡፡ "ለምሳሌ መናፍቅ፣ አሕዛብ፣ ጴንጤ ወይም ይህን የሚመስሉ የተባለው ወገን ራሱን ያልሰየመበት በመሆኑ፣ የስድብ አጠራር እንደሆነ በመቁጠር ለቅርርብ ያለንን ሜዳ ያጠብብናል ብዬ እሰጋለሁ፤" ብለዋል፡፡

በዐውደ ጥናቱ ላይ "አሁን ምን እናድርግ? ዝምታ ወይስ ቱማታ?" ብለው የጠየቁት አቶ ንጉሤ፣ በክርስቲያን ሚዲያ ያሉት ሁሉ በሥነ ምግባር የተገራ ጨዋ ተግባቦት ይኑረን፤ በትሕትናና በአክብሮት፣ በዕውቀትና በግልጽነት፣ በእውነትና በርኅራኄ፣ በመደማመጥም ከዚህ ሁሉ ጋር ደግሞ በሚዛናዊነት እንነጋገር ብለዋል፡፡

ከኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን አቶ ሀብታሙ አብርደው "የክርስቲያን ሚዲያ ሚና ለሰላምና ለልማት" በሚል ርእስ ባቀረቡት ጥናት እንደጠቆሙት፣ የክርስቲያን ሚዲያ ከሌላው ሚዲያ የሚለየው ተልዕኮ አለው፡፡ ሌላው ሚዲያ ገበያ መር ሊሆን የሚችልበት ሰፊ አጋጣሚ ሲኖር፣ የእነርሱ ግን ሰብዓዊ ክብር ግድ የሚላቸው ተልዕኮ መር ናቸው፡፡ በዋናነት በሰዎች መካከል በጎ ሥነ ምግባር እንዲዳብር መርዳት ተግባራቸው ነው፡፡ ሚዲያው በሃይማኖቶች መካከል ያለው መቀራረብ የበለጠ እንዲጠናከርና በጋራ የሚያከናውኗቸውን ተግባራት በመዳሰስ ጅምሩን ያበረታታል፡፡ ከሰው ሕይወት ክቡርነት በተጻራሪ የሚነሡ እንደ ውርጃ፣ ሕገ ወጥ የሰው ዝውውር፣ የሕፃናትና የጾታ ጥቃት፣ የጉልበት ብዝበዛ፣ ኢፍትሐዊነት ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችና የመሳሰሉ አስከፊ ተግባራትን ይቃወማል፡፡

የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ከዚህ ቀደም ለልማትና ፍትሕ፣ ለሰላም በጋራ የመሥራት ሰፊ ተሞክሮ ያላቸው በመሆኑ፣ ዛሬም ሚዲያውን በማስተባበር በኢትዮጵያ የበለጠ ልማት እንዲረጋገጥና ዘላቂ ሰላም ማስፈን ይቻላል የሚሉት አቶ ሀብታሙ፣ የዑጋንዳን ተሞክሮ ያሳያሉ፡፡ በፖለቲካ ግጭትና በማኅበራዊ እሴቶች ችግር የታወቀ ታሪክ ያላት ዑጋንዳ፣ የአገሪቱ ሚዲያዎችም በሚቀጣጠለው እሳት ላይ ቤንዚን በመጨመር ሲያባብሱ ቢስተዋሉም፣ ለዚሁም መፍትሔ ይሆን ዘንድ "ዩጋንዳ ሚዲያ ዴቬሎፕመንት ፋውንዴሽን" የተባለ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት በአገሪቱ የሚሠሩ የሚዲያ ተቋማትን እና የክርስቲያን ሚዲያዎችን በማስተባበር የፍትሕና ሰላም ግንባታ ሥራ ለመሥራት ተችሏል ብለዋል፡፡

የቤተ ክርስቲያንና የሌሎች ሚዲያ ባለሙያዎች በጋራ መሰልጠናቸውና የዕውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ማድረጋቸው፣ ግጭት ነክ ዜናዎችን እንዴት ማስተላለፍ እንዳለባቸው በጋራ ስምምነት ላይ የደረሱበትን መመርያ ለማውጣትና በዚያም ለመመራት መቻላቸውንም አመልክተዋል፡፡  

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ መምህር ዳንኤል ሰይፈ ሚካኤል በበኩላቸው ባቀረቡት ጥናት፣ በክርስቲያኖች ጋዜጣ የሚታየው ገጽታ አሳሳቢ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
"የእኛ የክርስቲያኖች ጋዜጣ በዓለማውያን ብዙም የማይታየውን፣ ከማያምኑ ሰዎች እንኳ የማይጠበቅን ሥራ በማስተናገድ የስድብና የድብድብ፣ የጠብና የጥላቻ፣ የስጋትና የትርምስ፣ የሐሰትና ኃላፊነት የጎደለው የቡድነኛነት መገለጫ መሆናቸው የቤተ ክርስቲያንን ዓላማ ሊገልጽ ይቅርና አንድ በሰለጠነ ዓለም የሚኖር የሃያኛው ክፍለ ዘመን አዋቂ ሰውን ገጽታ የሚያስገምቱ ሆነው ይገኛሉ፤" ያሉት መምህሩ፣ "ከዚህም የተነሣ ዓለሙን ለመዳኘት የበጎነት ትክክለኛ ሚዛን እንድንሆን ብንጠራም፣ በመንፈሳዊ ፍጹም ሚዛንም ሆነ በዓለም ሚዛንም የጎደልን ሆነን ተገኝተናል፤ እንግዲህ ዋናው ጉዳይ የሚዛኑ መሰበር ከሆነ ተመዛኙ እንዴት ሊበቃ ይችላል?" በማለት ጠይቀዋል፡፡

መምህር ዳንኤል፣ "ለእያንዳንዱ እንዴት እንድትመልሱ ታውቁ ዘንድ ንግግራችሁ ሁልጊዜ በጨው እንደተቀመመ በጸጋ ይሁን፤" በማለት መፍትሔ ይሆናል ብለው የዘረዘሩት፣ በክርስቲያን ሚዲያ መካከል የጋራ መድረክ መፍጠር፣ በክርስቲያን ሚዲያ ሰፊ ተሳትፎ የሚያደርጉ የሥርጭት ዘርፎች በመከባበርና በመቻቻል፣ በመተዋወቅና የመረጃ ልውውጦችን በማድረግ፣ በዓለማዊው ሥርዓት ሙያተኞች የሙያቸውን ክብር ለማስጠበቅ የሚመሩበትን መተዳደርያ አዘጋጅተው በመተግበር፣ ሰላማዊ የእድገትና የማኅበራዊ ብልጽግናን ማምጣት እንደቻሉ ሁሉ፣ እኛም የሙያ ሥነ ምግባር መመርያ ማዘጋጀት፣ በክርስቲያን ሚዲያ መስክ ውስጥ ያሉ አዘጋጆችን፣ ዘጋቢዎችን፣ ባለቤቶችን እና ተያያዥ ሥራን የሚሠሩ ወገኖች የግንዛቤ መድረክ መፍጠርና የተጠያቂነት መንፈስ እንዲያድርባቸው ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡

በአሁኑ ጊዜ በሀገሪቱ ባሉ መንፈሳውያን ሚዲያዎች ስለሚታዩ የሕግ ጥሰቶች ያወሱት ደግሞ አቶ ጥበቡ ጋሹ ናቸው፡፡ እንደርሳቸው አገላለጽ፣ በተለያዩ መንፈሳዊ ሚዲያ የሰዎች ግላዊ ሕይወት በአደባባይ ሲወጣ፣ ያለፈቃዳቸው ምስላቸው የመጽሔት ሽፋን ሲሆን፣ ወይም በተለያዩ ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለሕዝብ ሲቀርብ ይታያል፡፡

የተለያዩ የሃይማኖት መሪዎችና አገልጋዮች እንዲሁም አባሎች ለዚህ የከፋ ድርጊት ያለምንም ርህራሄ የአደባባይ መነጋገሪያ ሆነዋል፡፡ ሃይማኖታዊ (መንፈሳዊ) ፕሬሶች ወይም በእምነት ስር የሚሰጡ መግለጫዎች ብዙ ትኩረት የማይሰጣቸው፣ ነገር ግን ከፍተኛ የሕግ ጥሰት የሚካሄድባቸው ቦታዎች ሆነው እናገኛቸዋለን ያሉት አቶ ጥበቡ፣ ቤተ እምነቶቹም ሆኑ የተለያዩ ሚዲያ የግለሰቦችን ሰላም ከመድፈር አልፈው የማይመለስ ወይም በገንዘብ እንኳ ሊተመን የማይችል መልካም ስማቸውንና ዝናቸውን ሲያብጠለጥሉ እናያለን፤ ይህም ከፍትሐ ብሔር ጉዳይነት አልፎ በወንጀልም የሚያስጠይቅ ነውም ብለዋል፡፡

አቶ ጥበቡ እንዳሉት፣ በአሁኑ ጊዜ ያለውን ሁነታ ስንመለከት በመንፈሳዊ ሚዲያ አንዱን እምነት ከሌላው ጋር በሚያጋጭ ሁኔታ የሚጻፉ ወይም በተለያዩ የኤሌክትሮኒክ ሚዲያ የሚተላለፉ ሐሰተኛ ወሬዎች በየጊዜው የሚያጋጥሙን ናቸው፡፡ እዚህ ወሬዎች ሕዝብን ከሕዝብ የሚያጋጩ እና ለፀብ የሚያነሳሱ ናቸው፡፡

በሕግ የተሰጠውን ገደቦች የሚጥሱ ሚዲያዎች በፍትሐ ብሔርም ሆነ በወንጀል ሕግ ኃላፊነት የሚቀጡ ቢሆንም፣ ከዚህ ቅጣትም ባለፈ የመንፈሳዊ ሚዲያ ዋነኛ እሴት ክርስትያናዊ ሰላም መሆኑ መዘንጋት የለበትም፡፡ በመሆኑም በመንፈሳዊ ሚዲያ የሚዘግቡት ማንኛውም ነገር ሕዝብን የሚያፋቅር፣ የሚያስማማ፣ መለያየትን የሚኮንን ግጭቶችን የሚያበርድ ሊሆን ይገባል፡፡

የሦስቱም አብያተ ክርስቲያናት ተወካዮችና የሚዲያ ባለሙያዎች በተገኙበት ዐውደ ጥናት ላይ የበላይ አባቶች ተገኝተውበታል፡፡

ብፁዕ አቡነ ገብርኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ የበላይ ኃላፊ ጉባኤው አስፈላጊ መሆኑን በማመልከት፣ "ደዌያችን መለያየት ነው፤ መንቀፍ፣ ማቃለል ከክርስትና ውጭ የኾነ ነገር ነው፤ መስመሩን ጠብቀን መሄድ አለብን፡፡ በፍቅር በመከባበር ሳይሆን በመነቃቀፍና ጥላቻ ያለበት ነገር ብዙ አልፏልና ተፋቀሩ፣ ተዋደዱ፤ እንላለን፤" ብለዋል፡፡

"በውስጠ ደንብ ብንለያይም ኅብረት እጅግ አስፈላጊ ነው" ያሉት አቡነ ገብርኤል፣ "ልብ ገዝተን፣ ንሥሐ ገብተን፣ የእኔ እምነት ወርቅ ነው፤ ማለት ትተን እምነቱን ባንጋራ ሁሉም በየራሱ ይዞ መቀራረብ ያስፈልጋል፤" በማለት አጽንዖት ሰጥተውበታል፡፡

የአዲስ አበባ ካቶሊካዊት ሰበካ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ልሳነ ክርስቶስ ማቴዎስ፣ እያንዳንዱ ሚዲያ የሌላውን እምነት ሳይነካ የራሱን ማስተላለፍ እንዳለበት አሳስበው፣ የያንዳንዱ ሰው ሕይወት ይለወጥ ዘንድ ቸርነትን፣ ደግነትንና ፍቅርን ማስታወስ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

"በሚዲያ በተሰራጩት ሁኔታዎች ውድቀትም ትንሣኤም ታይቷል፤" ያሉት የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ኅብረት ዋና ጸሐፊ ቀሲስ ዓለሙ ሺጣ ናቸው፡፡

በቀሲስ ዓለሙ አገላለጽ፣ መልክተኛ መሆን መታደል ነው፡፡ መልእክት ወደ ተቀባዮች ከመድረሱ በፊት ብስለትና ብቃት፣ ክህሎትንም መያዝ አለበት፡፡

የሚዲያ ሰዎችም የሰላም መልእክተኛ መሆናቸውን ላፍታም መዘንጋት እንደሌለባቸውና ከዐውደ ጥናቱም የተገኘው ውጤትም አድማሳቸውን እንደሚያሰፋ እምነታቸው መሆኑን ዋና ጸሐፊው ገልጸዋል፡፡

11 comments:

samueldag said...

በስመአብ፡ ወወልድ፡ወመንፈስ ቅዱስ፡ አሀዱ፡ አምላክ፡ አሜን።
ደጀሰላምን፡በአምላክ፡ ስም፡ አመሰግናልሁ። ይህ፡አሁን፡የምናነበው፡
እውን ፡ለቅድስት፡ቤተክርስትያን፡ቀዳሚ፡ጉዳይ፡ነው?ወይስ፡ሌላ፡
ምስጢር ፡ይኖረው፡ይሆን? ብጹእ፡አባታችን፡እንዳሉት፡ግን፡ውስጠ
ደንብ፡ብቻ፡ያለያየን፡ሳንሆን፡ሀይማኖት፡እንጅ፤አዎ፡አባታችን፡የኛ፡ሀይማኖት
የእውንት፡ ወርቅ፡ነው።ክርስቶስ፡በወርቀ፡ደሙ፡የመሰረታት፡ናትና፡፡
መች፡ተለመደና፡ከተኩላ፡ዝምድና፣፣፣፣፣፣ለምን ፡ለመመሳሰል፡ተፈለገ
ተኩላ፡ተኩላነቱን፡ላይተው_ - - ፖለቲካ፡ከሆነ፡ለፖለቲከኞቹ፡ተዉላቸው
ዛሬ፡ቤተ-ክርስቲያን፡የራስዋን፡ቤተሰብ፡አንድ፡ማድረግ፡ቀዳሚ፡ተግባርዋ፡
ሊሆን፡ሲገባ፡የማይስፈልግ፡ግንኙነት፡በግልጽ፡በጎችዋን፡እየነጠቁ፡ዘመቻ፡
ካወጁባት፡ጋር፡ጊዜን፡ከማባከን፡ለቤተ-ክርስቲያን፡አንድነት፡ብትጸልዩና፡ብትሰሩ
ይበጃል፡እላለው፡፡
በጎደለ፡እመቤቴ፡ትሙላው፡፡የበላየሰብ፡እመቤት፡ተዋህዶ፡ሀይማኖታችንን፡በቃል-ኪዳንዋ
ትጠብቅልን፡፡የእግዚአብሄር፡ቸርነት፡አይለየን፡፡አሜን፡፡፡፡፡፡፡
ሀይለገብርኤል-

Anonymous said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን፡፡ ይህ የሚዲያ አንድነት የተባለዉ ሀሳቡ በሃሳብነት ደረጃ ጥሩ ነዉ ልንል እንችላለን ዳሩ ግን ሥጋ በል እፅዋት ለመሆን የተጠነሰሰች ሚስጢር ናት፡፡ አሁን እኮ ከእንግዲህ በሆላ እኮ አንድ ሆነናል አብረን እኮ እየሰራን ነዉ እና መሰል የማስመሰያ የሥጋበልእፅዋትነታችንን የመደበቂያ ስልቶች በመጠቀም ድብቁን ፍላጎታችንን ለማስፈጸም መንገድ እየፈለግን እንገኛለን፡፡

kenaw said...

No No No No No No way nebr yabablal abablo libla ayhonm ayhonm ayhonm.ante hizb nika abatoch eysmamuh nwna kahzab temesatrew lishetuh yihe yehuletu sewoch yewst deba new alkemes silalk liababluh sishu yihenn ametu. nika nika nika

Anonymous said...

All Samueldag's Idea is also mine.
Endet hibret ke Menafkan gar?
Betekiristian yerasuan media lemazegajet Atansim.
Egziabher Betekiristianachinin yitebikilin.

Anonymous said...

ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው? ክርስቶስስ ከቤልሆር ጋር ምን መስማማት አለው? ወይስ የሚያምን ከማያምን ጋር ምን ክፍል አለው? ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም አለው? እኛ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነንና እንዲሁም እግዚአብሔር ተናገረ እንዲህ ሲል። በእነርሱ እኖራለሁ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፥ አምላካቸውም እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ። ስለዚህም ጌታ። ከመካከላቸው ውጡና የተለያችሁ ሁኑ ርኵስንም አትንኩ ይላል፤ ሁሉንም የሚገዛ ጌታ። እኔም እቀበላችኋለሁ፥ ለእናንተም አባት እሆናለሁ እናንተም ለእኔ ወንድ ልጆችና ሴት ልጆች ትሆናላችሁ ይላል።

Anonymous said...

I donot know the reason why our Fathers like to Cooporate with TEKULAS. Have we any relation with them? No, we have on the opposite way. It is the choice of death and salivation.We have alot of assignments for our church. Then, why do we kill our time by cooporating with those that are in opposite way with us.

Anonymous said...

ይድረስ ለብጹዕ አቡነ ገብርኤል

ቡራኬዎ ይድረሰኝ ብፁዕ አባታችን!

እንደው አንድ ግልጽ ሊያደርጉልኝ የምፈልገው ነገር አለ ይኸውም ልብስዎን ስመለከት የበግ ልብስ ይመስላል ድምጽዎትን ስሰማ ግን የተኩላ ድምጽ መሰለኝ እንደው ግራ ገባኝ፡፡ ከየትኛው ነዎት?

AY

Anonymous said...

ጴንጤ ካላልናቸው ምን ሊባሉ ይፈልጋሉ?

Anonymous said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሀዱ አምላክ አሜን!
ለምን እንደዚህ ይሆናል ? አባቶቼ ምን ነካችሁ ? በምዕመኑ ላይ ጋዝ ማርከፍከፍ አይደለም እንዴ ?እደዚሁም ህዝቡ በግሎባላይዜሽን፤ በመናፍቃን ደባ ኀይማኖትን መከተል እንደ ኃላ ቀር /በግዴለሽነት በሚያይበት ወቅት ለምን እንዲህ አይነት ነገር ይሰራል ? በሀይማኖታችን ታሪክ በጭራሽ ታየቶ የማይታወቅ ነገር! እንዲያውም የተለየ ሀሳብ ያለውን አካል እንከን አብረው ሊሰሩ ቀርቶ አዉገዘው ይለዩት አልነበረም እንዴ? እውነት እና ሀሰት እነዴት አብረው ይሄዳሉ? ብንጠነቀቅ አይሻልም ? የማንወጣው አዘቅት ውስጥ ለምን እንገባለን!
አቤቱ አማላክ ሆይ የዋሁን ህዝብህን ጠብቅ!
ደረሰ ዘባህርዳር

ኤልሮኢ ዘ ገቺ said...

እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥:(ማቴ24-15)

ምነው አባቶቼ መቼም ለእንንተ ማስተማር ይከበዳል ያልተማረውን ምዕመን ያህል እንኳን ማሰብ ያቃታችሁ ብቻ ብዙ ነገር ልጽፍ ፈልጌ ቢቀርስን መረጥኩኝ ላምን ቢባል ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ አሉ፡፡ በተናጠል በህብረት ስንጠቃ አሁን ደግሞ መሃላችን ገብቶ ብትንትናችንን ለማውጣት የሚስማማ ተስማማሁ ቢል ምዕመኑ ግን ምርጫውን ያውቀዋል::

ለአባቶች ግን ይህንን ተውትና ከቻላችሁ ራሳችሁን ለማስተካከል ሞክሩ በእናንተ ጦስ ስንቱ የዋህ ምዕመን ወዳልፈለገው አመራ፡፡
ልብ ይስጣችሁ፡፡ አንድ ነገር ትዝ አለኝ "ጋሪው ፈረሱን ይጎትታል" ካጠፋሁ ፈጣሪ ይቅር ይበለኝ የተባለው ነገር ግን ለኛ ምንን አይጠቅመንም፡፡

እንግዲህ በነቢዩ በዳንኤል የተባለውን የጥፋትን ርኩሰት በተቀደሰችው ስፍራ ቆሞ ስታዩ፥ አንባቢው ያስተውል፥:(ማቴ24-15)

GULILAT said...

I afraid where our final chance will be and till when our orthodox tewahido church will be governed by irresponsible clerks.
dear our clerks(papasat),do you have any care for you church? I do not think so. you are living only for your necessities rather than doing for your church.
may our GOD will give us a true religious leader instead of you,who are intending to mix the sheep with foxes.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)