June 29, 2010

ማስታወቂያ፦በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ዙሪያ የሚያጠነጥን አዲስ ብሎግ እና የጡመራ መድረክ

 http://www.onetewahedo.blogspot.com፦ "በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው ስላለችው ቤተ ክርስቲያን አንድነት የምንወያይበት የጡመራ መድርክ።" ውድ የደጀ ሰላም አዘጋጆች እንደምን ከረማችሁ? በደጀ ሰላም በተለያዩ የመወያያ ርዕሰ ሀሳቦች ላይ “አቤል ቀዳማዊ ወይም አቤል ወለቴ” በሚለው ስም የራሴን ሀሳብ ስገልጽ ቆይቻለሁ። ዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው  ውስጥ እጅግ በርካታ ኢትዮጵያውያን እንደሚኖሩ የተለያዩ የሕዝብ መገኛኛ ብዙሃን ይናገራሉ። በዚሁ አካባቢ የተዋሕዶ እምነት ተከታዮች  ምንም እንኳ ትክክለኛ ቁጥር መናገር ቢያዳግትም በርካታ ናቸው። በአካባቢያችን ቤተ ክርስቲያናችንም በተለያየ መልኩ ተከፋፍላ ትርምስ ውስጥ ትገኛለች። ስለዚህ በዋሽንግተን ዲሲና አካባቢው  ያሉት አጥቢያ አቢያተ ክርስቲያናት ልዩነቶቻቸውን አጥብበው እንዴት ወደ አንድነት ሊመጡ ይችላሉ? በሚሉትና በሌሎችም ርዕሰ ሀሳቦች ላይ የምንወያይበት የጡመራ መድረክ ጀምሬያለሁ።

June 26, 2010

የአባቶች ሽምግልና እና እርቅ ከየት ይነሣ፣ የት ይድረስ?


(ደጀ ሰላም፣ ጁን 26/2010)፦ በግንቦቱ የቅ/ሲኖዶስ ጉባዔ ላይ እንደተገለፀው ከአምስተኛው ፓትርያርክ ከብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሲመት ማግስት ጀምሮ በቤተ ክርስቲያኒቱ የተነሣውን መከፋፈል ለማቆምና በአባቶች መካከልም የተፈጠረውን እስከ መወጋገዝ የሚያደርስ ልዩነት በእርቅ ለመጨረስ እንቅስቃሴ ተጀምሯል። ይኸው ከአበው ካህናት፣ ከምእመናንና ከታዋቂ ግለሰቦች በአባልነት የተውጣጡ ሰዎች የሚሳተፉበት ነው የተባለው አንቀሳቃሽ ቡድን በግንቦት ወር ወደ ጠቅላይ ቤተ ክህነት (አዲስ አበባ) እንዲሁም ወደ ኒውዮርክ ልዑካንን በመላክ እርቁ እንዲጀመር አግባብቷል።

June 25, 2010

ለብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሥርዓተ ጸሎተ ፍትሐት በአሜሪካ ተካሄደ

(ደጀ ሰላም፣ ጁን 25/2010)፦ የሚከተለውን ዜና በ"ፌስቡክ" ሣጥናችን ያደረሱን "መሐሪ ሙሉጌታ ማራናታ" የተባሉ እና "የብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ማስታወሻ ገጽ" በሚል በፌስቡክ መታሰቢያቸውን የሚዘክሩ ደጀ ሰላማዊ ናቸው። ስለ ሪፖርታቸው ከልብ እናመሰግናለን። እኛም የእርሳቸውን ዓይን "ዓይናቸን" አድርገን፣ በቦታው እንደተገኘን አስበን ዘገባውን እናስነብባለን።
ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን
++++
"እንኳንስ ተለያይተን፤ አንድ ሆነንም አንችለውም። ዘመኑ እኩይ ነው ዘመኑ ክፉ ነው ወገኖቼ ..." ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሊቀ ጳጳስ
(ዋሺንግተን ዲሲ)፦ ትላንት ሐሙስ ሰኔ ፲፯ ቀን ፳፻፪ ዓ/ም የብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሊቀ ጳጳስ ሥርዓተ ጸሎተ ፍትሃት በዚህ በሰሜን አሜሪካ ዋና ክፍለ ከተማ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው በደብረ ምሕረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ብፁዕ አቡነ አብርሃም የዋሽንግተን ዲሲና የአካባቢው ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል የሲዳማ ሃገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እንዲሁም የቅዱስ ሲኖዶስ አባል፣ ከተለያዩ አድባራት የመጡ የደብር አስተዳዳሪዎች፣ ቆሞሳት፣ ቀሳውስትና ዲያቆናት እንዲሁም ሊቃውንተ ቤተክርስቲያን፣ ዘማርያን፣ ሰባኬ ወንጌላውያንና የሰንበት ትምህርት ቤት መዘምራን በተገኙበት ከተደረገ በኋላ ብፁዕነታቸው በሕይወት በነበሩባቸው ጥቂት ዘመናት የሰሯቸው አያሌ ቁምነገሮች መካከል ጥቂቶቹ በምስልና በድምፅ የተዘጋጁት መረጃዎች ታይተዋል።

June 24, 2010

London to host EOTC’s Europe Spiritual Conference

By Tamiru Geda
(NewsDire):- Debre Genet Holy Trinity Church ,London based, is said a bit busy to organize the thirteenth Spiritual Conference of The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in Europe that would be held between 16-18 July 2010. It reported that several hundreds worshipers showed their interest to pilgrim to London.

According to the organizers, preparation for the conference is undertaken and lot of Londoners are regrouping themselves and waiting for the arrivals of their gusts from Ethiopia, America, Europe and other places. On this spiritual conference different activities: spiritual Gospel preachings, Spiritual songs, Spiritual Drama and the like would be preformed . The organizers said that to minimize logistical problems and to get better facilities, gusts who come from out side United kingdom are advised to contact organizers in advance .Last weekend , organizers updated their followers that more than three hundreds worshipers have already registered to attend the London’s conference.

የብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሥርዓተ ቀብር ተፈጸመ

(ደጀ ሰላም፣ ጁን 23/2010)፦ የከምባታ፣ ሐድያ፣ ጉራጌና ስልጢ አህጉረ ስብከተ ሊቀ ጳጳስ እና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል የነበሩት ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሥርዓተ ቀብራቸው ሰኔ 15 ቀን 2002 ዓ.ም (ጁን 22/2010) ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናት አባቶችና ምእመናን በተገኙበት በምሁር ኢየሱስ ገዳም ተፈጸመ፡፡ ስለ ብፁዕነታቸው የማ/ቅዱሳን ድረ ገጽ የሚከተለውን ምጥን ጽሑፍ አትሟል።

ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ያስተዳድሩት በነበረው ሀገረ ስብከት ውስጥ በሚገኘው እዣና ወለኔ ወረዳ /ምሁር ኢየሱስ ገዳም አካባቢ/ ከአባታቸው ከመምሬ ክንፈ ሚካኤልና ከእናታቸው ከወ/ሮ አስካለ ማርያም በ1951 ዓ.ም ተወለዱ፡፡ ዕድሜያቸው ለትምህርት እንደደረሰ የምሁር ኢየሱስ ገዳም ቄሰ ገበዝ የነበሩት አባታችው በዚያው ፊደልና የቁጥር ትምህርት አስተማሯቸው፡፡

June 21, 2010

(ሰበር ዜና) ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ አረፉ፣

(ደጀ ሰላም፣ ጁን 21/2010)፦ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ከዚህ ዓለም ድካም ዛሬ ጁን 21/2010 በሞት ተለዩ።

የጉራጌ፣ ሀድያና ስልጢ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ የሆኑት ብፁዕነታቸው በጉበት ካንሰር በሽታ ሲታከሙ ቆይተው ዛሬ ሌሊት አርፈዋል። አስከሬናቸውም ዛሬ ወደ ታላቁ የምሑር ገዳም የተሸኘ ሲሆን ሥርዓተ ቀብራቸውም ነገ ማክሰኞ ይፈጸማል።

June 19, 2010

“ሁለቱን ሲኖዶሶች” ለማስታረቅ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኘው ስብስብ ጉባዔውን አካሄደ


(ደጀ ሰላም፤ ጁን 19/2010)፦ ሁለቱን “ሲኖዶሶች” ለማስታረቅ ጥረት በማድረግ ላይ የሚገኘው ስብስብ ጉባዔውን አካሄደ። ከሁለቱም “ሲኖዶሶች” በጎ ምላሽ ማግኘቱ ታወቀ።

ከአምስተኛው ፓትርያርክ ማግስት ሹመት እና ከአራተኛው ፓትርያርክ ስደት ማግስት ጀምሮ በተነሣው ክፍፍል እስከ መወጋገዝ የደረሱትን አባቶች ለማስታረቅ በመሞከር ላይ የሚገኘውና ራሱን “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን የሰላምና አንድነት ጉባኤ” እያለ የሚጠራው ስብስብ በዋሺንግተን ዲሲ ያካኼደው ይኸው ጉባዔ ወደ አዲስ አበባ እና ኒውዮርክ የላካቸውን ልዑካን ሪፖርት ከማድመጡም ባሻገር ከሁለቱም “ሲኖዶሶች” የሚመጡ ተወካዮች ሊያደርጉት ስለሚችሉት የመጀመሪያ ስብሰባ እንዲሁም ይህ የዕርቅ ሒደት ሊገጥሙት ስለሚችላቸው ችግሮች መክሯል።

June 16, 2010

ፍርድ ቤት የዳላስ ቅ/ሚካኤል ቦርድ ላይ ዕግድ ጣለ፣ ከዚህ በሁዋላ ሰዎችን በፖሊስ መከልከል አይችልም

 የዳላስ ክፍለ ከተማ (County) ፍርድ ቤት ዳኛ ማርቲን ሎዊ የቅ/ሚካኤል ቦርድ ላይ ዕግድ ጣሉ፣ ከዚህ በሁዋላ በፖሊስ መከልከል እንዳይችልም ፈረዱ።  በአቶ ተኮላ መኮንን እና በአቶ ፀሐየ ጽድቅ ቤተ ማርያም ከሳሽነት በሜይ 18/2010 በመዝገብ ቁጥር 10-05578-ኢ በቦርዱ አባላት በሆኑት በዮሴፍ ረታ፣ ሙሉጌታ ፋንታሁን፣ አበበ እውነቱ፣ ኢዩኤል ነጋ፣ አበራ ፊጣ፣ ወ/ሮ ተዋበች ታደሰ፣ አቶ ብዙአየሁ ጌታቸው እና በወ/ሮ ሰሎሜ መኮንን ላይ የተከፈተው ክስ ብይን አግኝቶ በዳኛው ፊርማ የፀደቀ ሲሆን በብይኑ መሠረት ከዚህ በሁዋላ ተከሳሾቹ ማንንም ከቤተ ክርስቲያን መከልከልም ሆነ ማስወጣት አይችሉም።

አክሱምላይት፡ ፕሮግራሚንግ በአማርኛ፤ በግዕዝ ፊደላት

(መሸሻ ክብረት፣ ሶፍትዌር ኢንጂነር፣ አሜሪካ)
በዓለም ላይ ያሉ የቴክኖሎጂ ዕድገትን ካፋጠኑ ግኝቶች አንዱ የኮምፒዩተር ፕሮግራም ነው። በአሁኑ ወቅት የኮምፒዩተር ፕሮግራምን የማይጠቀም ተቋም የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም።

በሃገራችን የኮምፒዩተር ቴክኖሎጂ ከገባ ዓመታት ቢቆጠሩም፤ በዘርፉ የሚፈለገውን ያህል ርቀት ተጉዘናል ማለት ግን አያስደፍርም። ለዚሀም የተለያዩ ምክንያቶች ቢኖሩም ቅሉ፣ በራሳችን ቋንቋ ሶፍትዌር ያለመሰራቱ አንዱ ችግር  ነው። የኮምፒዩተር ኦፕሬቲንግ ሲስተም እና መሰል መተግበሪያ ሶፍትዌር በሙሉ የተገነቡት በተለየ ቋንቋ ሰለሆነ ለሃገራችን ተጠቃሚዎች አስቸጋሪ ሆኖ ቆይቷል።

June 14, 2010

አቡነ ቄርሎስ ሕክምናቸውን ጨረሱ፣ በመልካም ጤንነት ላይ ናቸው

(ደጀ ሰላም፤ ጁን 14/2010)፦ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ በጀርመን አገር ፍራንክፈርት ከተማ ሲከታተሉ የነበረውን ሕክምናቸውን ጨረሱ፣ በመልካም ጤንነት ላይ ናቸው።


አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ በጀርባቸውና በእግራቸው ላይ የሚሰማቸውን ሕመም መፍትሔ ለማግኘት ኤፕሪል ወር መጀመሪያ ላይ በመጀመሪያ ወደ ግሪክ ያቀኑ ሲሆን ቀጥሎም ለተሻለ ሕክምና ወደ ጀርመን ተጉዘው ነበር። በሰው ድጋፍ ይንቀሳቀሱ የነበሩት ብፁዕነታቸው በአሁኑ ወቅት በተሻለ ሁኔታ ላይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል። 

June 11, 2010

ያለ ኤጲስ ቆጶስ ፈቃድ ቀሳውስት ተሰባስበው የቃል ኪዳኑን ታቦት በመንበሩ መሰየም ይችላሉን?


(ወለተ አቤል፤ ከአሜሪካ)፦ እዚህ በዲያስጶራው በተለይም በሰሜን አሜሪካ በኛ ዘመን ለታቦት የሚገባውን ክብር እንዳንሰጠው አንዳንድ ካህናት ሲያቃልሉት እያየን ነው። ሰሞኑን እኔ በምኖርበት በዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው “ቨርጂኒያ፣ ዉድ ብሪጅ” በሚባል ቦታ ከሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ከብፁዕ አቡነ አብርሃም ዕውቅና ውጪ ራሳቸውን "በአስተዳደር ገለልተኛ  ነን" የሚሉ በአካባቢው የሚገኙ ካህናት ተሰባስበው ሥልጣኑ ሳይኖራቸው ቤተ ክርስቲያን “ከፍተናል”፣  “ባርከናል” ብለዋል። ታዲያ ታቦቱን ማን በመንበሩ ሰየመላቸው? ታቦቱንስ ከየት አመጡት? ይህንን ቤተ ክርስቲያን “ባርኮ የከፈተውስ ማን ነው? እነማን ናቸው? በዕለቱ በቦታው የተገኙት ካህናትስ እነማን ናቸው?” መልሱን ለራሳቸው መተው ቢገባም ምእመናን ደግሞ መጠየቅ ይገባቸዋል።

Russians to celebrate Christianization of Rus Day: Bravo Russia!!!!!


(The Moscow Times)Russia will celebrate a new holiday next month under a decision backed by the Kremlin and Russian Orthodox Church that is stirring up decidedly unholy feelings among non-Orthodox Russians.
Christianization of Rus Day on July 28 won't be counted as a day off work, but it will be recognized on calendars as the country's ninth so-called "memorial holiday," which also includes Cosmonauts Day on April 12 and Constitution Day on Dec. 12.
The new holiday commemorates the baptism in 988 of Vladimir the Great, who accepted Christianity together with his family and the people of his state, Kievan Rus, the predecessor to the Russian Empire and whose capital was Kiev.

June 10, 2010

‹‹ትላንትና ያየሁት ሕይወት የት ሄደ?››

 (ደጀ ሰላም፣ ጁን 9/2010)፦ ከዚህ በታች ያለው ቀልድ አዘል ቁምነገር የተገኘው ከ "  ፌስቡክ "  ላይ ሲሆን ፀሐፊዋ "  ብሌን ተስፋዬ "  ናት። እናንተ ደጀ ሰላማውያንም ብታነብቡት እየሳቃችሁ ትማሩበታላችሁ ብለን ስላሰብን ልናካፍላችሁ ወደድን።
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ሟችነፍሱ ሰማይ ቤት እንደደረሰ የሰማይ ቤት ዳኞች ገሃነም ወይም ገነት ለመግባት ሁለቱንም ስፍራዎች ጎብኝቶ መምረጥ እንዳለበት ይነግሩታል፡፡ በመርሐ-ግብሩ መሰረትም በመጀመሪያ ገሃነምን እንዲጎበኝ ይጋበዝና ገና ከበሩ ላይ በመልካም አለባበስ የተሸቆጠቆጠው ሳጥናኤል በሞቀ ሰላምታ ተቀብሎት ወደ ውስጥ ይዞት ይገባል፡፡

ዋሺንግተን ዲሲዎች እናመሰግናለን!!!

(ደጀ ሰላም፣ ጁን 9/2010)፦ በቅርቡ በዚህቹ የጡመራ መድረካችን በ"ደጀ ሰላም" ላይ የወጣውን "ቤተ ክርስቲያን የሚባርከው (“የሚከፍተው”) ማን ነው? ሥልጣኑስ የማን ነው?" የሚለውን መጣጥፍ በዲሲ እና በአካባቢው የሚገኙ ደጀ ሰላማውያን በማባዛት ለምእምናን ማድረሳቸውን በመስማታችን በደጀ ሰላም ስም "እናመሰግናለን" ለማለት ወደድን። ደጀ ሰላማውያን እንደጻፉልን ከሆነ ይኸው ጽሑፍ በአሜሪካዋ ዋና ከተማ በዋሺንግተን ዲሲ እና በአካካቢዋ በሚገኙት ታላላቅ አብያተ ክርስቲያናት በዕለተ ሰንበት ለማስቀደስ ለመጣው ሕዝበ ክርስቲያን እንዲደርስ ተደርጓል። ይሁን እንጂ ይህ ተግባር ያሳዘናቸው ሰዎች በበኩላቸው በጻፉልን የኢ-ሜይል መልእክት "እንዲህ ዓይነቱን አስነዋሪ ተግባር" እንድናቆም አስጠንቅቀውናል።

June 9, 2010

Holy Synod of the Coptic Church Rejects Egyptian Court Rule

(Deje Selam, June 9/2010):- The Coptic Orthodox Holy Synod rejected the unchristian decision passed by the Egyptian Islamic court. An Egyptian court issued a controversial ruling on Saturday, May 29, which deprived the head of the Egyptian Coptic Orthodox Church of the control over matters of divorce and marriage, giving the civil courts the authority to oversee affairs which the Church considers are in its core religious competencies.

አብያተ ክርስቲያናቱ የሚዲያ የጋራ መድረክ ለማቋቋም ተስማሙ

(ሪፖርተር ጋዜጣ፣ ጁን 9/2010):- በክርስቲያን ሚዲያ (መገናኛ ብዙኀን) ውስጥ የሚታየውን አሳሳቢ ገጽታ ለመለወጥ በኦርቶዶክስ፣ በካቶሊክና በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ስር ያሉ የሚዲያ ተቋማት የጋራ መድረክ ለማቋቋም ተስማሙ፡፡

የኢትዮጵያ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር (ኢመቅማ) ግንቦት 27 እና 28 ቀን 2002 ዓ.ም. የክርስቲያናዊ ሚዲያ አገልግሎትን አስመልክቶ በአብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ለሚገኙ በሚዲያ ሥራ ለተሰማሩ ባለሙያዎች ባዘጋጀው ዐውደ ጥናት ላይ የጋራ መድረክ ለመመሥረት የተስማሙት ሦስቱም አብያተ ክርስቲያናት ናቸው፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)