May 18, 2010

የዳላስ ቅ/ሚካኤል ጉዳይ በቴሌቪዥን ቀረበ

An internal affairs complaint has been filed against the Garland Police Department by a woman who says she was roughed up while being removed from a church service by police. FOX 4's Shaun Rabb has the story you'll see only on FOX 4.


ለምን ይህ ሆነ?
(ሙና፣ Moona)
የማናውቀው ያለመድነው ነገር በቤተ ክርስቲያንናችን ላይ ለምን ተከሰተ? ለምንድን ነው እየተከሰተ ያለው? በቤተ ክርስቲያንያናችን የሚነሱ አለመግባባቶች እንዴት ነበር የሚፈቱት? በካህናትና በካህናት፣ በዲያቆናትና በዲያቆናት፣ በካህናትና በዲያቆናት፣ በምዕመናንና በምዕመናን... ወዘተ የሚነሱ/ ሊነሱ የሚችሉ ችግሮችን የምንፈታበት ሥርዓት፣ ሕግ፣ ትውፊት የለንም ወይ? የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ምን ይላል? ልናስተውል ይገባናል:: ልንነጋገር ይገባል!! ልናውቅና ልንነቃ ይገባል!!

ኧረ ለመሆኑ! የቤተ ክርስቲያን ያአስተዳደር ሥርዓት፣: ችግሮች ቢነሱ የሚፈቱበትን ሕግ፣ ትውፊት ማነው የሰጠን ?- ዛሬ የሰጠን ወያኔ ነው? አቡነ ጳውሎስ ናቸው ?! ማህበረ ቅዱሳን ነው?! እነ ወዘተ ናቸው?! ልባችን ከፈቀደው ጋር እያገናኘን እንትን እንደነካው እንጨት የምንንቀውን፣ ገሸሽ የምናደርገውን የአስተዳደር ሥርዓት ካልተጠቀምንበት መና ሆነን እንቀራታለን:: ይህንን ጥያቄ ልንመልስ ይገባል:: ማፈርም ካለብን ማፈር ያለብን ይህን የዘመናችንን ትልቁን ጥያቄ ባለመመለሳችን ነው እንጂ ችግራችንን የምንፈታበትን ሥርዓት፣ ትውፊት ንቀን፣ ትተን የደረሰበን መዋረድ በድረ-ገጽ ላይ ስለታየ አይደለም:: የተዋረድ ነው የቤተ ክርስቲያንን ፈተና አብረን እየጸለይን መጋፈጥ አቅቶን ለየራሳችን ማኩረፍያ ጎጆ የቀልስን ጊዜ ነው:: በቦርድ የሚመራ ቤተ-እምነት:: አገር ቤት "እንዲህ አደረጉ" ብለው ከሚያሟቸው ሰዎች የማይሻሉ:: እዛ አገር ቤት "አያደርጉትም" ብለው እንደሚያሟቸው ሰዎች ጥያቄ መጠየቅ የማይወዱ አምባገነኖች::በምን ይለያሉ:: ወያኔ ጥያቄ ጠየቃችሁ ብሎ ተቃወማችሁ ብሎ በፖሊስ ያስግዛል እድሜ ልክ ይፈርዳል - ይገድላል:: እነዚህም ዝም! ለማሰኘት በፖሊስ ያስግዛሉ - አገሩ አይመችም እንጂ ያስግድላሉ፣ :: እንዴ! “main line protestant” ነን የሚሉት እንኳ ቤተ-እምነታቸውን የሚያስተዳድሩበት ወጥ አሰራር አላቸው:: የእኛ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ የአስተዳደር አሰራር ብቻ አይደለም ያላት:: ሃይማኖታዊ የአስተዳደር ሥርዓት ነው ያላት:: ሰሜን አሜሪካንን ከረግጥኩ ጅምሮ እንደ ተቃጠልኩ አለሁ:: እንንቃ!!!!


37 comments:

Anonymous said...

Is there anything we all Ethiopians can learn from this tragic incident?. It doesn't matter if we are MK, CLERGY,BOARD,SUNDAYSCHOOL members. We all have failed and brought disgrace to our nation and church.We should all be ashamed and rushed to repentance.

Anonymous said...

This is so Embarrassing and full of Shame!!! Diros Feriha EgziAbhier yelelebet Board Betekiristianin siyastedadir....Abatochin siyakel ena ende tera serategna siketiri ena siyabarir.....Betekiristian ahunim bihon mechiem bihon be Board atimeram!!!.....SHAME ON ALL OF US!!!

EgziAbhier yitareken....lela min yibalal???

Ewnetu said...

We do learn a lot from this incident. It helps us to figure out who is killing our church.

Unknown said...

Be it Mahebere Kidusan, Sinod, Papas, Kes, Board, etc...what is the one thing they are fighting for? POWER...They all want to take power and take it for good. They come up with all kinds of justifications that why they are better than the others. Better yet, they tell you, their way is the right way and others are dead wrong. Ask or talk to one of them, you will never hear them say, they leave power for the good of the church or Orthodox Tewahedo. They always claim Orthodox Tewahedo is about to be extinct unless they stay in power and their opponets disappear. So what we see at Dallas Michael is only a very small part what will come in the near future. I have been to Dallas Michael what a great Church that was! It had such great leaders, a very nice church and a service you could never get enough of. Unfortunately all that is gone. All we have is a bunch of self righteous tuggs balming each other for the destruction of once great Church.
Lord have merch on all of you.

Anonymous said...

No one in this incident is clean. From the Zerihun sisters to the clergy, and the police, they are all sinners. They will go to hell. What is happening to the Ethiopian Diaspora is sad and disgraceful. It is a community utterly divided, and lacks respect for one another or the Church.

selamawi said...

በስመ ስላሴ አሃዱ አምላክ አሜን

ያልጠፋነው ከእግዚአብሔር ምህረት የተነሳ ነው ሰቆ, ኤ 3፥22

በመጀመሪያ በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስቲያን አጥቢያ ለምትገኙ ምእመናን ጌታ በኃይሉና በችሎቱ ያበርታችሁ እላለሁ

በተረፈ ለተዋህዶ ልጆች እንዲህ አይነቱ ፈተና አዲስ ነገር አይደለም ቅዱስ መጽሐፍ ወዘኢትለምዱሰ ይበጽኃክሙ ( የማትለምዱት መከራ ይመጣባችኋል ) ነው የተባለው በወጀብና በአውሎ ነፋስ መካከል ለተተከለች ድንኳን መከራ አዲስ አይደለም እኔን ግን ግርም የሚለኝ ነገር የቦርድ አባላት የተባሉት ሲመረጡ ክርስቲያን መሆናቸው መረጋገጥ አልነበረበትም ? ነው ወይንስ አብዛኛው መራጭ ህዝብ ክርስትና ማለት ምን ማለት እንደሆነ አያውቅም ፣ ይህን እንድል ያስገደደኝ የቦርዱ ኃላፊዎች ልክ ጌታን አይሁድ ሊይዙት ሲመጡ ይሁዳ እየመራ ይዟቸው እንደመጣ እነሱም እግዚአብሔር በሚከብርበት በቅዳሴ ሰዓት የአህዛብ ወታደር ከነጫማው እየመሩ የእግዚአብሔርን ልጆች ለማሳሰር ይዘው መምጣታቸው በጣም ብዙ ጥያቄ ያስነሳል ከምንም በላይ ደግሞ ካህናት ተብየዎች በአይናቸው እያዩ ክርስቲያኖች ከቤተመቅደስ እየታነቁ እንደወንጀለኛ ሲባረሩ ዝም ብለው ማየታቸው ሰይጣን ዲያቢሎስ ምን ያህል እንዳሸነፈን ማረጋገጥ ይቻላል በኃገራችን እንኳን ሊያስቀድስ የመጣ ክርስቲያን ይቅርና ነፍስ በስህተት ያጠፋ ሰው እንኳን ቤተክርስቲያን ከገባ አይነካም ነበር ሁሉም ነገር በነበር እየቀረ ነው ለማንኛውም ክርስቲያኖች ከላይ ለመጥቀስ እንደሞከርኩት ስለቤተክርስቲያናችን ጥፋት ሁላችንም ተጠያቂዎች ነን ያንን ማመን አለብን በዘር በጎሳ አንዲቱን ቤተክርስቲያን እየከፋፈልን ለመናፍቃን መሳለቂያ አደረግናት እስቲ ከዚህ እንማር ማንም እንዳላትርፈ ያውቀዋል ድጋሚ ወደ ኪሳራ መሄዱን እንተውና ወደ ራሳችን እንመለስ ምናልባት እኔን መሰል የቤተክርስቲያን ልጆች በዚህ ላንደነቅ እንችላለን ምክንያቱም ከዚህ በላይ ብዙ ሲደረግ አይተናል የሚያንጽ ስላልሆነ አልዘረዝረውም ኢይጻእ አቢይ ነገር እምአፉክሙ (የሚያንጽ ካልሆነ በቀር ካፋችሁ ክፉ ቃል አይውጣ ) ስለሚል የእግዚአብሔር ቃል ብዙ የሚሰናከሉ ሰዎች እንደሚኖሩ ግን ይገመታል ለሁላችንም ማስተዋሉን ይስጠን //
ወስብሃት ለእግዚአብሔር

Anonymous said...

This is America,where the action of the law enforcement officials is put in balance.

ME said...

YES VIOLENT CHURCH ARREST!!!!! Greatest thanks goes for the reporter and the news channel for brining up such Public violent activity in church and inocent folks so that law of the church should come up in control ...so taking out the shoes will not be the primary mistake of the police men rather it was supposed to be the job of the "shameful board member who have been leading the police officers to the church ......He should been doughted for being orthodox christan not even in sunday clothes(of the church) ..despite of this police officers should now for all times to take off the shoes ...Rather than that Let you be aware that who ever bringing up the police officers for simple questions asked by church memebers are those board members who are trying to courrupt the church money to thier pocket. And let church higher Synod in Ethipia see the case except the violent activity. Thanks all for standing up for ONE CHURCH!!!!

Anonymous said...

YES VIOLENT CHURCH ARREST!!!!! Greatest thanks goes for the reporter and the news channel for brining up such Public violent activity in church and inocent folks so that law of the church should come up in control ...so taking out the shoes will not be the primary mistake of the police men rather it was supposed to be the job of the "shameful board member who have been leading the police officers to the church ......He should been doughted for being orthodox christan not even in sunday clothes(of the church) ..despite of this police officers should now for all times to take off the shoes ...Rather than that Let you be aware that who ever bringing up the police officers for simple questions asked by church memebers are those board members who are trying to courrupt the church money to thier pocket. And let church higher Synod in Ethipia see the case except the violent activity. Thanks all for standing up for ONE CHURCH

Moona said...

ቁጭ ብለን ልንነጋገር ይገባል::
ለምን ይህ ሆነ ?
የማናውቀው ያለመድነው ነገር በቤ/ክናችን ላይ ለምን ተከሰተ ?
ለምንድን ነው እየተከሰተ ያለው ? በቤ/ክያናችን የሚነሱ አለመግባባቶች እንዴት ነበር የሚፈቱት ?
በካህናትና በካህናት : በዲያቆናትን በዲያቆናት: በካህናትና በዲያቆናት :በምዕመናንና በምዕመናን...ወዘተ የሚነሱ/ሊነሱ የሚቸሉ ችግሮችን የምንፈታበት ሥረዓት :ሕግ: ትውፊት የለንም ወይ ?
የቤ/ክ ሥረዓት ምን ይላል ?
ልናስተውል ይግባል::ልንነጋገር ይገባል !! ልናውቅና ልንነቃ ይግባል !!
እረ ለመሆኑ ! የቤ/ክ ያአስተዳደር ሥረዓት : ችግሮች ቢነሱ ይሚፈቱበትን ሕግ: ትውፊት ማነው የሰጠን ?- ወያኔ ነው ? አቡነ ጳውሎስ ናቸው ?! ማ.ቅ ነው ?!እነ ወዘተ ናቸው ?!- ዛሬ የሰጡን::ልባችን ከፍቀደው ጋር እያግናኘን እንትን እንደነካው እንጨት የምንንቀውን ; ገሸሽ የምናደርገውን የአስተዳደር ሥረዓት ካልተጠቀምንበት መና ሆነን እንቀራታለን::ይህንን ጥያቄ ልንመልስ ይገባል::ሕገ ቤተክርስቲያን ! ማፈርም ካለበን ማፈር ያለብን ይህን የዘመናችንን ትልቁን ጥያቄ ባለመመለሳችን ነው እንጂ ችግራችንን የምንፈታበትን ሥረዓት :ትውፊት ንቀን ትተን የደረሰበን መዋረድ በድረ-ገጽ ላይ ስለታየ አይደልም::የተዋረድ ነው የቤ/ክ ፈተና አብረን እየጸለይን መጋፈጥ አቅቶን ለየራሳችን ማኩረፍያ ጎጆ የቅልስን ጊዜ ነው::በቦርድ የሚመራ ቤተ-እምነት(እኔ ስልችት ስላልኝ ቤ/ክ አልለውም)::
ጨካኝ ! አገር ቤት እንዲህ አድረጉ ብለው ከሚያሟቸው ሰዎች የማይሻሉ::እዛ አገር ቤት አያድርጉትም ብለው እንደሚያሟቸው ስዎች ጥያቄ መጠየቅ የማይወዹ አምባገነኖች::
ምን ይለያሉ:: ወያኔ ጥያቄ ጠየቃችሁ ብሎ :ተቃወማችሁ ብሎ በፖሊስ ያስግዛል እድሜ ልክ ይፈርዳል -ይግድላል::እነዚህም በፖሊስ ያስግዛሉ-አገሩ አይምችም እንጂ ያስግድላሉ: ዝም! ለማሰኘት::
እንዼ! main line protestant ነን የሚሉት እንኳ ቤተ-እምንታቸውን የሚያስተዳድሩበት ወጥ አሰራር አላቸው::የእኛ ቤ/ክ ደግሞ የአስትዳደር አሰራር ብቻ አይደለም ያላት ::ሃይማኖታዊ የአስተዳደር ሥረዓት ነው ያላት ::ሃይማኖታዊ!!
ሰሜን አሜሪካንን ክረግጥኩ ጅምሮ እንደ ተቃጠልኩ አለሁ ::
እንንቃ!!!!

Anonymous said...

በመላ አሜሪካ ያላችሁ፡ ክርስቲያኖች፡ እባካችሁ ቤተክርስቲያንዋን ከቦርድ አስተዳደር ነጫ አድርጉት፡ በተለይ በዲሲ አካባቢ ያላችሁ ስባኬያን፣ ካህናት ፣መዘምራን ፣በተለያይ ጥቅም ተደልላችው ይህንን በደል ባትቃውሙ እውነት በኢሳይያስ ላይ ይውጣች ለምጭ በራሳችሁ ትውርድ።

Anonymous said...

በመላ አሜሪካ ያላችሁ፡ ክርስቲያኖች፡ እባካችሁ ቤተክርስቲያንዋን ከቦርድ አስተዳደር ነጫ አድርጉት፡ በተለይ በዲሲ አካባቢ ያላችሁ ስባኬያን፣ ካህናት ፣መዘምራን ፣በተለያይ ጥቅም ተደልላችው ይህንን በደል ባትቃውሙ እውነት በኢሳይያስ ላይ ይውጣች ለምጭ በራሳችሁ ትውርድ።

adam9 said...

Guys wht ar u expecting, I am really getting angry when those people start shouting and claiming as if the police is committing a sin or violating our church law.The mistake is with those bunch of people named Christian; who goes in the first place in this type of church who don't follow our church's canon
to conclude u deserve it u ediotes and please stop complaining

Tazabiw said...

This is just shameful. We know the so called 'Board' members don't even care about the Church. I don't think they are even Christians. They are just politicians.It is the greed for power and control. The real members should throw them out and take back their Church. That is the only solution.
very sad!

Gudu said...

ከበለስ ወይን ከኩርንችት ፍሬ የሚለቅም ማን ነው?
በለስ በለስነትን ካልለቀቀ በቀር ወይንን ሊያስገኝ እንደማይችል ኩርንችትም ኩርንችትነቱ ቀርቶ ፍሬ ሰጭ ተክል ካልሆነ በቀር ፍሬ እንዲሰጥ እንደማይጠበቅ አስረጅ ነው ከላይ በርእሱ የሰፈረው።ይህን ኃይለ ሐሳብ እንዳነሳ ያነሳሳኝ በዳላስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በተነሳው ሁከት ቅዳሴ ሊያስቀድሱ ቃለ እግዚአብሔር ሊሰሙ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ሊቀበሉ የሄዱ ምእመናን ወንጀል ሲሰሩ እጅ ከፍንጅ እንደ ተያዘ ወንጀለኛ ሲጎተቱ የሚያሳይ ፊልም በቴሌቪዥን ሲቀርብ በማየቴ ነው።እጅግ አሳዛኝ ነው።አሳዛኝነቱ ክርስቲያን ለሆነ እንጅ እምነቱ ፓለቲካ ለሆነ ለዚያውም በኢኅአፓ ርእዮተ ዓለም ለተጠመቀ እና ለቆረበ አይደለም።ክርስቲያን ለቤተ ክርስቲያን፣ ለእግዚአብሔር ቤት ቀናኢ ነው፣ክርስቲያን ቅዱሱን ቦታ በአሕዛብ አያስደፍርም።ክርስቲያን ቤተ ክርስቲያን የምታዝዘውንና አድርግ የምትለውን ያደርጋል።በፊልሙ ስመለከት የገረመኝ ነገር ቢኖር ምእመናን ወንዶችም ሆኑ ሴቶች በቤተ ክርስቲያናቸው ሥርዓትና ትውፊት መሠረት ነጠላቸውን አመሳቅለው ሥርዓተ ጸሎቱን ሲከታተሉ የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳዳሪዎች የሚባሉት ቦርዶች በኮት ታጅለው በክራቫት ታንቀው ሕዝበ ክርስቲያኑን ያተራምሳሉ።የቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓትና ትውፊት እነሱን አይመለከት ይሆን? ዓውደ ምሕረቱ ላይ እንዲያ ተራቁተው ሲቆመበት ተናግረን እናውቅ ይሆን? ነጠላ ማመሳቀል ለተራ ሰው እንጅ ቦርድነት የሚባል ደረጃ ለደረሰ ሰው ግን ውርደት ነው ብለው ይሆናላ! ታዲያ ከእነዚህ ሰዎች ምን ጠብቀን ይሆን የምንጮኸው? እነዚህ ሰዎች እኮ በመጀመሪያ ቤተ ክርስቲያንን እንደ አንድ የሥራ ቦታ እንጅ እንደ እግዚአብሔር ቤት አያይዋትም።የእግዚአብሔርን ህልውና በሚክድ ኢኅአፓኛ የደነዘዘን አእምሮ ስለ ቅዱስ ቦታ ግድ ይኖረዋል ብሎ መጠበቅ ሞኝነት ነው።ዞሮ ዞሮ እጃችንን አንስተን ቤተ ክርስቲያንን ምሩ፤ ሥሩ፤ ቅጡ ብለን በሰጠን በሁላችን በአማኞች ላይ እንዲሁም ያለማዳላት፣ ያለ አንዳች ፍርሃት በድፍረት የእግዚአብሔርን ወንጌል እንድንሰብክ የተሰጠንን ክህነት ከእንዲህ አይነት ግለሰቦች ጋር ለጊዜያዊ ጥቅም ብለን የምንሸቅጥ ካህናት፣ ዲያቆናት. መምህራን ተጠያቂዎች ነን።
ቀደም ባሉ ዓመታት ቤተ ክርስቲያንን ሲሳለቁባት አብረን ስናጨበጭብ ኖረን ዛሬ ከድርጊታችሁ ተቆጠቡ ብንላቸው እምቢ አሉ በቅድስናዋ የምናምንባትን ፈጣሪን የምናመልክባትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን በፖሊስ አስረገጡ ልባቸው ደንድኗላ!ያደሩ ባቄላዎች ስለሆኑ አልቆረጠምም ብለዋላ! ከዚህ በኋላ እንደ እነዚህ አይነት ሰዎች በወንጀል ላይ ወንጀል በድፍረት ላይ ድፍረት ቢጨምሩ እንጅ አይመለሱም።የማያልቅ የወንጀል ሰንሰለት ውስጥ ናቸውና። መግደልን እንደ መፍትሔ የሚያይ መሪ ሁልጊዜ የችግር መፍቻው ያው መግደል ነው።ቦርዶች እንዲህ ዓይነቱን ወንጀል ከፈጸሙ በኋላም አላረፉም።እንደ አበደ ውሻ ያገኙትን ሁሉ ይለካክፋሉ። �ሰንበቴ� በሚባል የጡመራ መድረካቸው ቀደም ሲል እዚያው ሚካኤል በአገልጋይነት ሲሰሩ የነበሩ በኋላ ግን አምላክ ልሁንባችሁ አምልኩኝ ላላቸው ቦርድ አንገዛም አናመልክም ብለው እምቢኝ ብለው ወጥተው አብያተ ክርስቲያናትን ከፍተው በሚያገለግሉ ካህናትና መምህራን ላይ ዘለፋና በሬ ወለደ ውዥንብርም ሲነፉ አስተዋልሁ።በዚሁ �ሰንበቴ� በተባለው የጡመራ መድረካቸው ከእነሱ አፈንግጠው የወጡትን ካህናትና መምህራን ከአባ ጳውሎስ ጋር ቴሌኮንፈረንስ አደረጉ ብለው የሐሰት አባቷ ከሆነው ከግብር አባታቸው ከዲያብሎስ በወጣው ሐሰት ወንጅለዋል።የገረመኝ ነገር ቴሌኮንፈረንሱን አብረው እንደተከታተሉ አድርገው ነው ሪፖርት ያቀረቡት።እንዴት አድርገው ሰሙት? ስልክ ጠልፈው ይሆን? ለነገሩ ለቦርድ ምን ይሳነዋል አማልክት ስለሆኑ አይደል የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት የሚጠቀጥቁት? ምሉዓን በኩለሄ-በሁሉ ቦታ ሙሉ አይደሉ እዚህ ሆነው እዚያ ሰምተው ይሆናላ! እንዲያም ከሆነ ደግ የቴሌኮንፈረንሱን ሙሉ ውይይት ለማስረጃነት ያቅርቡልን ሁላችንም እንስማው እና የሚሉት እውነት ከሆነ እናረጋግጥ።
ወደ ቀደመ ነገሬ ልመለስና የተወደዳችሁ የቤተ ክርስቲያን ልጆች ያለፈውን ይቅር የሚል የሚመጣውን እኛ በማናውቀው እሱ በሚያውቀው መንገድ የሚመልስ አምላካችን የታመነ ነው።የቤተ ክርስቲያን ትምህርትና ትውፊት ያልገራቸው ልበ ደንዳኖችን እየተከተልን ደግነትን ከጠበቅን ከበለስ ወይንን ከኩርንችትም ፍሬን ለማግኘት የምንሞክር ሞኞች አንሁን።ከትንሹ ስላላረቅናቸው አሁን ከመሰበር በቀር አይቃኑም።ለዚህ ሐሳብ ማወራረጃ አንድ አባባል ጣል አድርጌ ላብቃ።ሌብነትን ግብሩ አድርጎ ያደገ ሰው ሌብነቱን ባገኘው አጋጣሚ ሁሉ ያከናውናል።ብዙ ጊዜ ሲሰርቅ ግን ሳይነቃበት የኖረ ሌባ ነው አሉ፤ከእለታት አንድ ቀን በሬ ሲሰርቅ ይያዛል፤በሀገራች ሌባ ሲያዝ ዱላ ገደብ የለውም፤ �ሌባ ተይዞ ዱላ አይጠየቅም� ይባላልና።በደንብ ያገኘው ሁሉ ከነረተው በኋላ ወደ ዳኛ ይወሰድና ዳኛው ይጠይቀዋል እንዲህ ሲል �በሬ ስትሰርቅ ይዘነዋል ብለው ከሰውሃል፤ሰርቀሃል?� ሌቦም አልካደም እንዲህ ሲል መለሰ �አዎ ጌታዬ ሰርቄአለሁ� ዳኛውም መለሰና �ስለዚህ ተጠያቂ ነህ� ሲለው ሌቦ መለሰ እንዲ ሲል �እኔ ተጠያቂ ልሆን አልችልም፤ለዚህ ጉዳይ ተጠያቂዋ እናቴ ናት� ሲል ዳኛው ገረመውና �እንዴት ሆኖ? በምን መንገድ?� ሌቦ ገለጣውን ቀጠለ �በቤቷ ሳድግ ያልሰረቅሁት ነገር አልነበረም በሌለችበት መሶብ ከመክፈት ጀምሮ ሳንቲም፣ እንቁላል ስሰርቅ እያወቀች አልቀጣችኝም ከዚያም ዶሮ ከፍ አልሁና በግ ፍየል ስሰርቅ እያወቀች አልተናገረችም፤ ለዳኛም አላመለከተችም� አለ ይባላል።የቦርድም ነገር እንዲሁ ነው።
ጸልዩ በእንተ ሰላመ ቤተ ክርስቲያን
ጉዱ ነኝ ከዳላስ

Unknown said...

ምን አይነት ድፍረት ነው በቦርድ የሚመራ ቤተክርስቲያን ቤተክርስቲያን አይመስለኝም የሚያስብል?
በየአካባቢያችን የአምላካችን የእግዚአብሔር ሥጋና ደም የሚፈተትባቸው፣ ሥርዓተ ቅዳሴው በትክክለኛው እና በተሟላ ሁኔታ የሚቀደስባቸው፣ የእመቤታችን ተአምር የሚነበብባቸው፣ የክርስቶስ ወንጌል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ሥርዓትና ሕግ መሠረት የሚሰበክባቸው የእግዚአብሔር፣ የአገሩም ሆነ የሰው ህግ በትክክል የሚተገበርባቸው ብዙ በጣም ብዙ ቤተክርስቲያኖች አሉ። ነገር ግን ገና ለገና ቦርድ ተመሩ ተብሎ እንዲህ አይነት የድፍረት እና ስድብ ቃል ሊሰነዘርባቸው አይገባም።
በዘፈቀደ የተስሩ ቤተክርስቲያን እንዳሉ ሁሉ የብዙውን ጉልበት ገንዘብ እና ጊዜ ፈጅተው የተሰሩም እንዳሉ መዘንጋት የለብንም።
ዝም ብሎ ዛሬ መጥቶ ይሄ ልክ ነው ይሄ ልክ አይደለም ማለቱ ደፋርነትን እና አላዋቂነትን እንጂ ሌላ ምንም አያሳይም።
የእግዚአብሔር ትምህር ፍቅርና ይቅርታ እንጂ ጥላቻ፣ ፈራጅነት እና ከፋፋይነት አይደለም ያ ፈሪሳዊነት ነው እንደሱ አይነት ፀባይ ባሁኑ ጊዜ በብዙዎች ላይ ይታያል። ልበ ደንዳናነት፣ አውቃለሁ ባይነት፣ ደፋርነት በብዙዎች በጣም እየተስተዋለ ያለበት ጊዜ ነው ያለንበት።
ሁሉም ነገር እኛ ባልነው ሳይሆን በእግዚአበሔር ጊዜና ሰአት ይከናወናል። እስከዛው ድረስ ፅናት ከሁሉ ይበልጣልና በፅናት በያለንበት ቤተክርስቲያን በምዕመንነትም ሆነ በገልጋይነት እንቆይ። እምነት በጓደኝነት፣ በዝምድና ፣በቲፎዞነት፣ በስማ በለው ወይም በማህበር አባልነት ሳይሆን ጥርት ባለው በቤተክርስቲያን መንገድ እየሄዱ ፍቅርና ይቅርታን እስጡና እየተቀበሉ የወደቁትን እያነሱ መሄድ ነው።
የይቅርታ እና የፍቅር አምላክ አግዚአብሄር በምህረቱ ይመልከተን!

desa said...

GEN LEMEN GETA HOY???

desa said...

GEN LEMEN GETA HOY???

Anonymous said...

Wey guuuuuuuuuuuuuud.

Anonymous said...

I have a question to the father and son priests at St. Michael: are u feeling good to what has happened? Why is it "new" servants of the church always pushed out and U the bullet proofs remain "saints"? Please pray for the next priest to be like u. Yes like u, who will conspire with the enemey of the church to disperse the sheep. Good luck!

Godolias said...

ABETU BEMHIRETIH ASBEN.
Wegenoche yetegnan kalen yemininekabet,gra yegeban kalen yeminastewulibet,be atekalay sigawi astesasebn titen ye EGZIABHERN fikad yeminifestimbet wekt newu.Ye EMNET sewu be EMNET ende AMLAK fikad yinoral enji gena legena be EMINET tila yepoletica timatun yemiweta mehon yelebetim.Minewu wede huala hedet bilen ye BETEKRSTIANIN tarik binimeremir?B/K bizu fetenan eko asalifalech.Be yetignawum gize gin be bord weyim belela melik altegenetatelechim.Bizu gize poletikegnoch be ABATOCHACHIN wenber tekemtewu neber.Gin be abatochachin andinet,stelot,lekiso hulum be andit B/K sirat ena denb bemestnat askebrewatal.Tadia yezarewochu bord,geleltegna,sidetegna tebyewochu minewu ye TSELOTIN hail zenegut.tihtnan resut.fikrin talut.BEKIDSINAWU sifra endih ayinet asafari drgit yawum tedefra bematawuk BETEMEKDES festemu? wegenoch" BEMENFES BTINORU ERASACHIHUN MERMRU" endetebalin eminetin ena poletican leyiten bekedemechitu siratachin lay mekom yishalenal.BETEMEKDES yeselam sifra enji ye huketina yeshibr sifra ayidelechim.AMILAKE KIDUSAN EGZIABHER ASTEWAY LIBONAN YADLEN.

hayalu said...

We all should be ashamed of what has happened.We should ask our selves what the motive we have in doing this stupid thing.It is not just shouting. All those in the drama have something to accomplish.This is just being idiot.Count the number of groups fighting, but the sad thing is the innocents are suffering a lot.

Anonymous said...

I saw the news and it made me cry when i see it again and again. It is really sad. Specially the guy who was leading the police officers he better get something to say infront of God. If you don't love a person that you can see how can you say, you love God that you can't see?I can't even imagen what a cruel heart these kahenat had when their people been taken and dragged on the floor by police and they(kahenat) are in prayer. Who are they praying to? to God? I don't think so. If it was they would respect his maderiya(church). It make me cry all the time when i think about it. Please don't give up you, children of God. He is with you all the time. ///the board members what do you have to say now? did you do this because of Abune Paulos's bad adminstration. Atafrum eko.Enante eko telalachu. Shame on you.

Anonymous said...

Absolutely disgraceful! As if the disruption they have created within the church, "ye EgziAbiher bet", was not enough, they have went on to make a news on a national television and put the entire community to shame. How in God's name a man chooses to call law enforcement because a member of a church demanded answer for her question? Isn't the church the house of God where questions are answered in the most open and clearest manner? We don't have the level of intellect and civility to discuss issues peacefully, we don't respect each other, evidently we don't even respect the church itself and especially the community. Min yakl endenekezin ayachihu sewoch? Thank God i have stopped going to church long time ago. Midre Leba, Amba genen, power hungry, Kemagna and phony christian hula! I believe that today the church is more corrupted than our political institutes in Ethiopia.

Stop blaming the police officers who were simply performing their duty! They have done nothing wrong.

Anonymous said...

Well all of you guys put my feeling. I would say this is happened to 75% of north Amercan churhs. Here in Austin even not 200 members face the same problem. This is not a problem caused by Mehabere kedusan members as the so called board brodcast, instead this is the question raised by registered members of the church. Instead, that's the reason Mehabere kedusan preached about"serte betekerstin, kenona betekrstian and history of the church". we were not hunted be the polticains if we deeply understand our church history and structure. Serate betekrstian has nothing to do with Abune Paulos. And when we cast our fingers on him, look what is happening to churches so called "gelelteegna". geletegna from what? serate betekrstian. How many church fathers expel from dallas kedus mecheal and where are they now. Who church father came to bless that church after Abun Yeshke passed away. what we learn is chain is broken and manem endfelegne yecheferebet. Yabatoche berket ena selot sekuarete, the church is controled by evils. Then more worse than abune paulso christians kicked from church by police and snifer dogs, sad, sad, sad......what else is next for geletegnoche" I advice all come to churchs which is led by fathers related to the hgere sebkets of Enate betekrstian. I hate the so called sedetegna sinodos, they are also well orgainsed poleticians who love lemozins. Don't forget there are lots churchs who lack candle and you guys enjoy Lemos.
ayeeeeeeee yeken godolo...........

yonas said...

አረየቅዱሳንያለ !!!!!!!!!!!!!!
ወዴት አቤት እንበል ? መቼይሆን ፍርዱን የምናያው
እኔ በበኩሌ የምሰጠዉ አስተያየት .ለነ አይሁድ ካህናትነው.
ለሆዳችሁ ያደራችሁ ሆዳሞች፣ድሮውንስ ቢሆን ፣አገር ያስካዳችሁ
ለነገሩማ ሆዳችሁ አይደል? እንግዳማ ሐይማኖት እንዳይደል፣እናንተምአይጠፋችሁ? እኛም እናውቃለን.ደሞ የሚገርመው፣ያ ደደብ ዲያቆን ተብየውስርአት እንዳይጓደል ያሰበ ይመስል በሰላም ግቡ ይላል.እንኳን መዳኒታችንኢየሱስ ክርስቶስ፣እንኳን በዚህዘመን አልተሰቀለ!
እባካችሁ ፣መስቀላችንን፣ ተዋሕዶ ሐይማኖታችንን፣ተዉልንና
ውጡልን፣የናንተ ስ ፍራ……….መቼም አይጠፋችሁመቺም
ሰይጣን እንኳን በዕድሚ እንጂ በተንኲል አይበልጣችሁአይደል? ባለፈውዝምተበለው የታለፉትስ፤ እነ ቀስ.ታደሰ ባለፈው Virginia ኪዳነምህረት የተሰራውስራ
የሚረሳ አይደለም ለማንኛውም “የአለሚቱን ጠባሳ ያየ በሳትአይጫወትም”እንጠንቀቅ፣ ቤተክርስቲያናችንን ፣በንቃት እንድንጠብቅ፣ እግዚዐብሔር ይርዳን
አሚን

Anonymous said...

Unfortunately I was there when all these things happened. The mastermind of all these violence is one of the board member called Girma Wolderufael. He claimed to be a doctor (may be an animal doctor as he thinks like animal) but he is a cab driver and very unpopular among his colleagues as he was instrumental in dismantling their unity.
I don't know who recruited him into the board since this guy never even attend the divine liturgy (KIDASE) like the other board members.
The good news is all the board members have been criminally charged and once this fake doctor goes to prison, he would know the power of God and will never mess with the church again.
May God save our Tewahedo church from Menfiqan board members. Amen

Goba, from Dallas

Unknown said...

Slam for our church in evry where. why this is happin in our church? this is really sad very sad! where is Lord Christ, in our heart do we really think about him the sacrifice Jesus mad for us. Christ died for us with un accountable pine but we still ignore that for our personal need that make us do so wrong things.Because no one that who has love of Christ do such thing. If our problem is financial God is great he can give us more than all we can ask or imagine. Lead him befor us and afeter we would be blessed instead of cursed.we are just like Cain if we hate one anther. We must know who hate a brother or sister are a murderers.We should know Jesus laid down his life for us that is a true Love no one can't give us so we ought to lay down our lives for one another please lettuce prey for our church and our self brothers and sisters let ask God to open our heart and to come to us and remind us he realy truly lovs us.Thats whay the joy may be with us. Unless otherwise we goin to be a blind unttil we made at the agony that it will be our final destination no matter who we are a priest or his son.By the way priest remine at the church at moment or his son i belive they don't have enough knowledge about the Holly Bible that is obvious if so when something traged happens all this time to the church they act just like nothing is happen but every sonday show up to be at the church and screaming even to disturbed the Holly prey that is not get us any where screaming with no control that is not fith. God did't count that. Befor we try in to do any thing we must love one another then every thing is become so great. That what our Lord Jesus teach us this is siple and any human being has a posetive thinking mind know. Brothers if we bite eche other and kick out that from chuerch those can be able to teach us the Holly Bible do you think that is fith? let me ask you this? if i did't have enough to know the Holly Bible so how can I receive the Holly Communion? Just like you by experience but not by knowlege. Brothers please forgiveme to say this.This is not personal.I don't think that will be enough for the priest just flow in what the been told by whom order them they need to know God is a head of our curch. Every church we had that by blood of Jesus Christ no one but hem ! so we all of us has to come as one be together worship him our Father Lord and show him the fruit we bears.If not God will removes us. Because we are the branch bears no fruit.I believe all of us that bear much fruit to complete our joy and glorified GOD. Its befor too late even those who call them self us a priest. To our GOD be glory in the church and in CHRIST GESUS to all generations, forever and ever. Amen.

Anonymous said...

ከሐሰ ተኞች ነቤያት ተጠበቁ በሰው ደም ከሰከሩ ቤተክርስቲያንን በጫማ ከሚጠቀጥቁ ካህናትንና ምዕመናን ከሚያሳድዱ በከንቱ የሰውን ስም ከሚያጠፉ ጳጳስ አያስፈልግም ሲኖዶስን አንቀበልም ገለልተኛ ነን ከሚሉ አሳፋሪ ከሆኑ ከነፍሰ ገዳዮች
ከኢሃፓ ከኢድዩ ከቀይ ከጥቁር ቨብር የኢትዮጵያውያንን ንጹሕ ደም ካፈሰሱ ክርስቲያን መስለው መልካቸውን ቀይረው በቤተክርስቲያን ውስጥ ከተደበቁ እስላማውያን እመቤት ዮሴፍና አበራ ፊጣ ጵሮቴስታንት ዶክትር ግረማ ተብየው ሰሎሜ አበበ ጤፎ ወዘተ ከመሳሰሉት ፀረ ቤተክርስቲያን ያንን የመሰለ ደብር የፕሮቴስታትና የካቶሊክ የተሐዲሶ መነሃረያ አደረጉት በዚህ ቤተክርስቲያን ይህ ሁሉ ጉድ ሲፈ’ፀም ቁመው ከሚያዩ ሁሉ ቀሳውስት ነን ዲያቆናት ነን ከሚሉ ሆዳሞች ዘመን ከወለዳቸው መናፍቃን ህመምተኞች ጠበቁ

Anonymous said...

FOR THE SAKE OF OUR BELOVED ORTHODOX CHURCH, NATION AND NEXT GENERATION OF CHRISTIANS, PLEASE STOP TRYING TO CHANGE THE CHURCH AND INSTEAD BE READY FOR THE CHURCH TO CHANGE YOU! THIS WILL BENEFIT US ALL AND THE CHURCH IN THE LONG TERM.

Ene Le Enante Boardoch said...

This is rediculus. I can't believe my eyes that this is happening in the orthodox tewahedo church. Shame on you, who led the officers to get in to our church with their shoes. You will pay for it. Are you going to say you did this for "legeta kebir"? Very Embarrassing. Are you going to say you did this because of Abune Paulos's bad adminstration. Believe me you are going to pay for it. You will see if you have children or you will not have one. All of you who disgrace and disrespect God's place will pay for it. I am done.

Anonymous said...

"Anonymous said...

በመላ አሜሪካ ያላችሁ፡ ክርስቲያኖች፡ እባካችሁ ቤተክርስቲያንዋን አድርጉት፡ በተለይ በዲሲ አካባቢ ያላችሁ ስባኬያን፣ ካህናት ፣መዘምራን ፣በተለያይ ጥቅም ተደልላችው ይህንን በደል ባትቃውሙ እውነት በኢሳይያስ ላይ ይውጣች ለምጭ በራሳችሁ ትውርድ.።

Read the bible and learn.
ስባኬያን፣ ካህናት ጳጳስ ከአስተዳደር ነጫ ለጸሎትና ቃሉን ለማገልገል ይትጉ

የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 6
1 በዚህም ወራት ደቀ መዛሙርት እየበዙ ሲሄዱ ከግሪክ አገር መጥተው የነበሩት አይሁድ በይሁዳ ኖረው በነበሩት አይሁድ አንጐራጐሩባቸው፥ በየቀኑ በተሠራው አገልግሎት መበለቶቻቸውን ችላ ይሉባቸው ነበርና።
2 አሥራ ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሁሉን ጠርተው እንዲህ አሉአቸው። የእግዚአብሔር ቃል ትተን ማዕድን እናገለግል ዘንድ የሚገባ ነገር አይደለም።

2 አሥራ ሁለቱም ደቀ መዛሙርት ሁሉን ጠርተው እንዲህ አሉአቸው። የእግዚአብሔር ቃል ትተን ማዕድን እናገለግል ዘንድ የሚገባ ነገር አይደለም።

3 ወንድሞች ሆይ፥ በመልካም የተመሰከረላቸውን መንፈስ ቅዱስና ጥበብም የሞላባቸውን ሰባት ሰዎች ከእናንተ ምረጡ፥ ለዚህም ጉዳይ እንሾማቸዋለን፤

4 እኛ ግን ለጸሎትና ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን።

እኛ ግን ለጸሎትና ቃሉን ለማገልገል እንተጋለን።

5 ይህም ቃል ሕዝብን ሁሉ ደስ አሰኛቸው፤ እምነትና መንፈስ ቅዱስም የሞላበትን ሰው እስጢፋኖስን ፊልጶስንም ጵሮኮሮስንም ኒቃሮናንም ጢሞናንም ጳርሜናንም ወደ ይሁዲነት ገብቶ የነበረውን የአንጾኪያውን ኒቆላዎስንም መረጡ።

6 በሐዋርያትም ፊት አቆሙአቸው፥ ከጸለዩም በኋላ እጃቸውን ጫኑባቸው።

7 የእግዚአብሔርም ቃል እየሰፋ ሄደ፥ በኢየሩሳሌምም የደቀ መዛሙርት ቍጥር እጅግ እየበዛ ሄደ፤ ከካህናትም ብዙ ሰዎች ለሃይማኖት የታዘዙ ሆኑ።

Unknown said...

የጌታ ያልሆነው ሁሉ ተቆርጦ ሊጣል ግድ ነው።

Anonymous said...

be seme selassie!

Le Ethiopian orthodox tewahdo betekristian lejoch bemulu sile hatiyatachin, silebedelachin, sile alemetazezachin yemetaben newena maninim baniwekese, baniferede b/c hulum yerasun yeteyekebetalena.

Esti ande tiyake lansalechu lemehonu ye ethiopian orthodox tewahdo church ke meche wedeh new be board yemitetedaderew? be yetegnawese zemen new be board tedadera yemitawekew? Papasat erasua sateshom enkuan ke Egypt aleneber yeshomelat yeneberew? Board maletes mindenew? Kenona ena degema yelelat yimesele? Tadiya Abun Paulos siletelan be board metedader aleben? lemen be ethiopia orthodox tewahdo semen enachebereberalen? be board yeminetedader kehon lela seme enefeleg enji ye wahun christian be ethiopian orthodox tewahdo semen banatalelew. christian wondimoch ena ehetoch degemo ye betekerstian sereatuan ena denbuan benaneb ena benawek ke acheberebariwoch mebenikek enchilal kalehon gin ahun yetefeterew heneta hulem mekestu ayikerem.
selam egziabher ke hulachim gar yehun

zemenu wajut tebelual ena hulachinim be ande libe honen enitseley

red said...

ወዳጅ መስለው፣ በጎ አስመስለው ክፉን ሐሳብ በቤተክርስቲያኒቱ አሰራር ላይ የሚናገሩ የሽንገላ ከንፈሮች ዲዳ ይሁኑ!

ehete micheal said...

abettt yante yalh minew yhenen kemay moch bhone noro uuuuuuuuuuuuu

Anonymous said...

What a disgrace to our church, country and humanity. When are we going to learn to talk to one another in respect? Those who defy God's will just for the mere wish of power has departed the church and its people from God for so long. It is time to say no to self aggrandizing clergy and bigot board members and mahbers. Remember we will not achieve God's kingdom by mahber but rather our individual deeds. Isn't it sad that people from such poor country has the money to pay fat lawyers and argue in earthly court rather than be submissive and pray? What a TRAGIC REMINDER. We the people, we followers of EOTC need to rescue and save our faith from selfish and power mongering clergy and mahberats and boards. How sad must Aba Teklehaimanot, Aba Gebremenfes kidus and all those Ethiopian saints who gave their life to save the Dogma and doctrine of EOTH to us while current Clergy and mahberat destroy it and the church for their selfish needs.

Egziabher yasiben, Let the destruction and bigotry stop and lets start praying.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)