May 6, 2010

ማኅበረ ቅዱሳን ዲያቆን በጋሻውን ከሰሰ


(አዲስ አድማስ ጋዜጣ; May 02, 2010 )፦ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የአገሪቷ ክልል ከተሞች እየተዟዟረ የሚሰብከው ዲያቆን በጋሻው ከስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ፈቃድ ውጪ በድሬዳዋ ከተማ በቅዱስ ገብርተ ክርስቲያን ባደረገው ሰበካ “ማኅበረ ቅዱሳኖች የተለያዩ ወንድሞችን ደም የሚመጡ፣ ደማቸውንም በጽዋ ተቀብለው የሚጠጡ ናቸው» በማለት ሕጋዊ ፈቃድ ተሰጥቶት የሚንቀሳቀስን ተቋም ስም አጥፍቷል በሚል ማኅበሩ ክስ መስርቷል።  በማኅበረ ቅዱሳን የድሬዳዋ ማዕከል፣ ሰባኪው በማኅበሩ ላይ ያደረጉት ሕገ ወጥ ስም ማጥፋት በሕግ አግባብ ታይቶ ሊቀጡ ይገባል የሚል አቋም ስላለው በድሬዳዋ ከተማ ቤተ ክርስቲያኑ በሚገኝበት አካባቢ ባለው ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ክስ መመስረቱን አስታውቋል።
“እኛ ስማችንንርቶ እንዲያመሰግነን አንፈልግም። ይህንንም አንጠብቅም። ነገር ግን የእግዚአብ በሚሰበክበትተ ክርስቲያን ስማችንን ያለ አግባብ ሊያነሳ አይገባም የሚል አቋም ስላለን ወደ ክስ አምርተናል” ብሏል- ማኅበሩ።
ስብከቱ ከመደረጉ አስቀድሞም ሆነ በኋ በድሬዳዋ ሀገረ ስብከት በሚገኘው በቅዱስ ገብር ክርስቲያን እና በአካባቢው ባሉት አብያተ ክርስቲያናት ፍቃድ ላቸውና ሕጋዊ ያልሆኑ ሰባክያነ ወንጌልን በመጥራት ሕዝበ ክርስቲያን በማወክ ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችሎአል። እንዲሁም ቅዱስኖዶስ የወሰነውን ውሳለሀገረ ስብከቱ ሥራ አስኪያጅ መልአከ ምሕረት አባ ኃሐማርያም ወልደ ሳሙኤል በእጅ መሰጠቱ የሚታወቅ ሆኖ እያለ በማን አለብነት ክርስቲያኗን መዋቅር ባልበቀ መልክ ከመሠራቱም በላይ የህዝብን ሰላም ማወክ እንዲሁም በዐውደ ምሕረት ላይ ለብጥብጥ ማነሳሳት ተገቢ ተግባር አይደለም። ይህ ድርጊት በአስቸኳይ እንዲቆም በጥብቅ እያስታወቅን ከአሁን በኋ ያለ ስብከተ ወንጌልናዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ፈቃድ ፍቃድ የሌላቸው ሰባክያነ ወንጒልና ዘማርያን መድረክ ላይ እንዳይቆሙ በጥብቅ እናስታውቃለን” የሚል ደብዳቤ ደርሶት እያለ ስብከቱ እንደተደረገ ማኅበሩ ገልፆ የመንበረ ­ፓትርያርክቅላይ ቤተ ክህነት ትዕዛዝ ተጥሶ በተደረገ ስብሰባ የማኅበሩ ስም አላግባብ መነሳቱን ማኅበሩ ገልጿል።

የድሬዳዋ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን የሕዝብ ግንኙነት አገልግሎት ማሻሻያ ዋና ክፍል ኃላፊ አቶ ቢኒያም ወርቁ ስለ ጉዳዩ ተጠይቀውማኅበረ ቅዱሳን ክስ መስርቷል። የቀረበውን መረጃ መሠረት በማድረግ የማጣራት እየተሰራ ነውብለዋል።

ደጀ ሰላም፦ ዲ/ን በጋሻው ከዚህ በፊትም በዲላ ከተማ ባደረገው ዝግጅት ላይ ማ/ቅዱሳንን በመዝለፍ ሲናገር የተደመጠ ሲሆን ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የተቀሰቀሰበትን መጠን ሰፊ ተቃውሞ ከማኅበሩ ጋር ያያይዘዋል ተብሏል። ይህንን በተመለከተ ወደፊት ሰፊ ሐተታ እናስነብባለን።
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)