May 3, 2010

አባቶችን የማስታረቅ ሌላ ጥረት ተጀምሯል

(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 2/2010)፦ በስደት ከኢትዮጵያ ወጥተው በአሜሪካ እና በሌሎች አገሮች የሚገኙትን አባቶች እና ቅዱስ ፓትርያርኩን ለማስታረቅ ሙከራ እየተደረገ መሆኑ ታወቀ።


በመንግሥት ለውጥ እና በአምስተኛው ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሲመት ማግስት በተፈጠረው መከፋፈል ከቅዱስ ሲኖዶስ ተለይተው በተለምዶ “ስደተኛ ሲኖዶስ” በሚል ስብስብ የሚታወቁትን አባቶች በማስታረቅ ወደ ቀደመ አገልግሎታቸው እንዲመለሱ የማድረግ ዓላማን ያነገበ  ስብስብ መልእክተኞቹን ወደ አዲስ አበባ እና ወደ አሜሪካ ማሠማራቱ ታውቋል።

ከብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ አረፍተ-ሞት በኋላ የአንድነቱ ስሜት በመንቀሳቀሱ የተለያዩ ውይይቶች ሲደረጉ እንደነበረ የደጀ ሰላም ሪፖርተሮች ያረጋገጡ ሲሆን ስብስቡ በተለምዶ “ገለልተኛ” የሚባለውን እንዲሁም ከዚያ ውጪ ያሉትንና “ስደተኛ” በሚባሉ አብያተ ክርስቲያናት ሥር የሚያገለግሉ ካህናትንም ያቀፈ መሆኑ ታውቋል። ይኸው ስብስብ ለግንቦቱ የርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ እንዲያስረዱ ልዑካኑን የላከ ሲሆን ባለፈው ሐሙስ ጉዳዩን ለአባቶች ማቅረባቸው ተሰምቷል።
ከአሜሪካ ወደ አዲስ አበባ የሄደው ልዑክ አባላት ሊቀ ካህናት ኃ/ሥላሴ ዓለማየሁ (ከዴንቨር)፣ መላከ መንክራት ቀሲስ አንዱዓለም ይርዳው (ከፖርትላንድ) እና ዲ/ን አንዱዓለም ዳግማዊ (ከካናዳ) እንዲሁም ፕ/ር ኤፍሬም ይስሐቅ (ከአሜሪካ) ሲሆኑ ከኢትዮጵያ ደግሞ አትሌት ኃይሌ ገ/ሥላሴ እንዳሉበት ለማወቅ ተችሏል።
በተመሳሳይ መልኩም ሌላ የልዑካን ቡድን ወደ አሜሪካ በተለምዶ “ስደተኛ ሲኖዶስ” ወደሚባለው ክፍል እንደተላከ ታውቋል።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)