May 17, 2010

የሃይማኖት መሪዎች ለተፎካካሪ ፓርቲዎች መልዕክት አስተላለፉ

(ሪፖርተር)፦ በመጪው ሳምንት የሚካሄደው አራተኛው አገራዊ ምርጫ ሰላማዊ እንዲሆን የሃይማኖት መሪዎቹ ለ63ቱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሰላም መልዕክት አስተላለፉ፡፡የኦርቶዶክስ፣ የእስልምና፣ የካቶሊክና የፕሮቴስታንት የሃይማኖት መሪዎች ግንቦት 5 ቀን 2002 ዓ.ም. በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ የሃይማኖት መሪዎቹ ላለፉት ስድስት ወራት የሰላም ምኞትን ዕውን ለማድረግ በሠፊው ሲንቀሳቀሱ እንደነበር አስታውቀዋል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎችም በምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት በመገኘት የጥሪ መልዕክቱን ተከታትለዋል፡፡

በወቅቱ የተገኙት የሃይማኖት መሪዎች፣ የኦርቶዶክስ ፓትሪያርክ አቡነ ጳውሎስ፣ የኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳይ ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ሼሕ አህመዲን ሼህ አብዱላሒ፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካውያን ጳጳሳት ጉባኤ ፕሬዚዳንት አቡነ ብርሃነ ኢየሱስ ሊቀ ጳጳሳት ዘካቶሊካውያን፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት መካነ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ጠቅላይ ጸሐፊ ዶ/ር ቄስ ብርሃኑ ኦፍገአ ናቸው፡፡

በአቡነ ጳውሎስ በተጀመረው መልዕክት ሁሉም የሃይማኖት መሪዎች ምርጫው ፍትሐዊና ሰላማዊ እንዲሆን ጥልቅ ፍላጐት እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡

የሃይማኖት መሪዎቹ ምርጫው ፍትሐዊና ሰላማዊ እንዲሆን ፀሎት እንደሚያደርጉ የገለጹ ሲሆን፣ ሁሉም የፖለቲካ ፓርቲዎች በወንድማማችነት መንፈስና በመፈቃቀር አብረው እንዲሠሩ የሰላም ጥሪ አስተላልፈዋል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲዎቹ በአመለካከት ቢለያዩም የአንድ አገር ዜጐች በመሆናቸው፣ ልዩነታቸውን በፀጋ በመቀበል ለአገሪቱ እድገት፣ ብልጽግናና ከድኅነት መላቀቅ በአንድነት መሥራት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡ አክለውም ..የፖለቲካን ሸክም ለመሸከም የሚወዳደሩ ግለሰቦችን በአክብሮት እንመለከታቸዋለን.. ብለዋል፡፡

ምርጫው ሰላማዊና የተዋጣለት እንዲሆንና በሰላም ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ "የፓርቲ መሪዎች፣ የዕጩ ተወዳዳሪዎች ታሪካዊ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ አደራችን የጠበቀ ነው" ብለዋል፡፡ ፓርቲዎቹ ልዩነቶችን በውይይት እንዲፈቱ፣ ያለፈውን ስህተት እንዳይደግሙና ለትውልድ መልካም ትምህርት ጥለው እንዲያልፉ በመናገር በፀሎትና በቡራኬ አጠናቀዋል፡፡

ከስብሰባው በኋላ ያነጋገርናቸው አንዳንድ የተቃዋሚ ፓርቲዎች መሪዎችና የገዢው ፓርቲ አመራሮች የተላለፈው መልዕክት መልካም እንደሆነ ተናግረዋል፡፡ አንዳንዶቹም ሃይማኖት ጣልቃ መግባት የለበትም የሚል አስተያየት ሰንዝረዋል፡፡

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መርጋ በቃና በበኩላቸው፤ የሃይማኖት መሪዎች በራሳቸው ተነሳሽነት በመምጣት ለተወዳዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሰላም መልዕክት በመግለጻቸው ምስጋና አቅርበዋል፡፡ አክለውም፣ "ቦርዱም ከክቡራን የኢትዮጵያ ሃይማኖት መሪዎች ጋር በጋራ ለመሥራት ያለውን ቁርጠኝነት በዚሁ አጋጣሚ ለመግለጽ እወዳለሁ" ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ፕሮፌሰር መርጋ የፖለቲካ ፓርቲዎች በሥነ ሥርዓቱ ላይ መገኘታቸውን አመስግነው፣ የሃይማኖት መሪዎቹ ያስተላለፉትን የሰላም መልዕክት በአክብሮት እንደሚቀበሉና ተግባራዊ እንደሚያደርጉት ተስፋ እንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
(በሰብለወንጌል ሀብታሙ)

4 comments:

Anonymous said...

I know Deje selam people , you don't post my words

Anonymous said...

Let it be. They might made it just to renew their past mistake. But as some opposition parties indicated, they should also play their mediation role on political prisoners.

Unknown said...

God bless Ethiopian

ግርማ ሀብታሙ said...

"እግዚአብሔር ትሁት ና አስተዋይ ልቦናን ያድለን" እላለሁኝ።
ህዝበ ክርስትያን እናስተዉል፦
ኧረ ምነው በከንቱ ባንኮነን፤
ለምን ብባል ብዙዎቻችን ስለ ማህበረ ቅዱሳን ምንም ግንዛቤ ሳይኖረን ቃላቶቹን እያማረጥን የስድብ መኣታችንን እናዘንባለን።
እንግዲህ ማህበረ ቅዱሳን ማለት የማህበሩ አባላት ቅዱሳን ናቸው ማለት አይደለም፤ነገር ግን የቅዱሳን ስም የምዘከርበት ማህበር ማለት ነው እንጂ።
ለምሣሌ፣የእመቤታችን ማህበር ስንል የማህበሩ አባላት በሙሉ ቅ/ዲ/ማሪያም ናቸው ማለት እንዳል ሆነ ሁሉ።ክር ያሰረ ሁሉ ክርስትያን ልባል አይገባም።አዎ፦እመቤታችንን የማያመሰግን ትውልድ ዛሬም ነገም ክርስትያን ልባል አይገባም። ሉቃ፩:፵፰-፵፱ "እነሆ ከዛሬ ጀምሮ ትውልድ ሁሉ ብፅዕት ይሉኛል" ብላ ራሷ ዲንግል ማሪያም ተናግሪለችና።ዲ/ን በጋሻው ማለት
ማን እንደ ሆነ እናውቀዋለን ወይስ ዝም ብለን ተከተልነው?
እንግዲህ ሰው ሰውን ትቶ እግዚአብሔርን ብከተል ምናለበት
እስኪ የቀደሙ አባቶችን እንጠይቃቸው እነ ኣባ ሕርያቆስን እመቤታችንን እንዴት እንዳመሰገኗት የነአርዮስንም ከሰይጣን ያገኙትን ጥበብ እንመልከት።
አርዮሳውያንን አንከተል።
በቀደምት አባቶቻችን እንመራ።
(wolde26girma@yahoo.com)or
(ghbefree7@gmail.com)
Contact me!!!
"ክርስቶስ አስተዋይ ልቦናን ለሁላችን ያድለን!"
=>ከግርማ ሀብታሙ ከአዳማ ዩኒቨርሲቲ

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)