May 11, 2010

ቅ/ሲኖዶስ ሰባክያንንና ዘማርያንን የተመለከተ ያወጣውን ሕግ ለሚመለከታቸው አካላት አስተላለፈ


(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 10/2010)፦ ቅ/ሲኖዶስ ባለፈው ዓመት ያወጣውን ስለ ሰባክያንና ዘማርያን የተመለከተውን መመሪያ በማጠናከር ፈቃድ ሳይኖራቸው ስለሚሰብኩ እንዲሁም በሊቃውንት ጉባዔ እና በሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን አካላት ሳይታዩ ስለታተሙ ሕትመቶች ጉዳይ ለመንግሥት አቤቱታ አቀረበ።
ከሁለት ሳምንት በፊት በተደረገው የቅ/ሲኖዶስ ጉባዔ በአዲስ ሊቀ ጳጳስ በተተኩት በብፁዕ አቡነ ይስሐቅ ፊርማ ወጪ የተደረገውና ለበጎ አድራጎትና ማኅበራት ኤጀንሲ የተላከው ደብዳቤ “ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ሰባክያነ ወንጌል እና ዘማርያን ነን የሚሉ ጥቂት ግለሰቦች ያለ ቤተ ክርስቲያኒቱ ፈቃድ በግል ፈቃዳቸው እየተነሡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ስርዓትና ደንብ ተጠብቆየታተመ በሚል መጻሕፍት፣ የስብከት እና የመዝሙር ካሴት፣ ሲዲ፣ በቪሲዲ በማሳተም ለሕዝበ ክርስቲያኑ እያሰራጩ ከመሆኑም በላይ በየአብያተ ክርስቲያናቱ አካባቢና በልዩ ልዩ ጎዳናዎች ላይ ትልልቅ ድምፅ ማጉያዎችን በመኪና በመትከል ድምፅ በመበከል በቤተ ክርስቲያናችን ስም እየነገዱ ሕዝቡን ግራ በማጋባት ላይ” እንደሚገኙ ገልጿል።

ከዚህ በኋላ በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም እነዚህን ሕትመቶች ሊያሰራጭ የሚችል ማንኛውም ግለሰብ ከሊቃውንት ጉባዔ ፈቃድ ማግኘት እንደሚገባው የሚያትተው የብፁዕነታቸው ደብዳቤ ይህንን መመሪያ ሳይከተሉ የቤተ ክርስቲያኒቱን ስም ተጠቅመው የሕትመት ውጤቶችን ለሚያሰራጩ በሙሉ ግን ኤጀንሲው ጥብቅ መመሪያ እንዲሰጥ ይጠይቃል።

የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ጥያቄ ሥራ ላይ የሚውል ከሆነ፦
1.      ማንኛውም ሰው ከጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት እና ከየአህጉረ ስብከቱ ሊቃነ ጳጳሳት የስብከተ ወንጌል ፈቃድ ከሌለው መስበክ አይችልም፣
2.     በቤተ ክርስቲያኒቱ ስም መጻሕፍትም ሆነ የኦዲዮ/ቪዲዮ ሥራዎችን ማሰራጨት በሕግ ያስጠይቃል ማለት ነው።

ቅ/ሲኖዶስ ይህንን መመሪያ ባለፈው ዓመት የካቲት 2001 ዓ.ም ባደረገው ጉባዔ ያስተላለፈው መሆኑን ማስረጃዎች ቢያመለክቱም እስካሁን ድረስ ተፈጻሚ ሳይሆን ቆይቷል። ጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ከዚህ በፊትም በተለያዩ ዓመታት ሰባክያንን የተመለከቱ መመሪያዎችን የማውጣትና የማስተላለፍ ልምድ ቢኖረውም ራሱ ቅ/ሲኖዶሱ የሚያወጣውን ሕግ በተዋረድ ያሉ አህጉረ ስብከትና የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አስተዳደሮች ስለሚጥሱት መመሪያዎቹ የወረቀት ላይ ነብር ከመሆን አልፈው አያውቁም ነበር። ይህ አዲሱ መመሪያ ከወረቀት ነብርነት አልፎ ትርጉም ያለው ሥራ ይሠራ እንደሆነ በጊዜ የሚታይ ይሆናል።

12 comments:

ኃ/ሚ said...

ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚበጅ በመሆን እጅግ የሚያስደስት ውሳኔ ነው። ትልቁ ነገር ደንቡ መጽደቁ ሳይሆን ተግባራዊ ማድረጉ ነው። ለዚህ መሳካት ከእኛ ምን ይጠበቃል ለሚለው ጥያቄ መልስ ልንሰጥ ይገባል። የሚታዩኝ
. ከጠቅላይ ቤተ ክህነት እስከ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ያሉ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደር አካላት ደንቡን አስመልክተው ምእመናንን የማሳወቅ(Conceptualization)ሥራ ቢሰራ፤
. የተለያዩ የቤተ ክርስቲያን ማኅበራት (ሰንበት ት/ቤቶች፣ የጽዋ፣ የአገልግሎት ማኅበራት)አስፈላጊውን ድጋፍ ቢያደርጉ የሚል ሀሳብ አለኝ

GKidan said...

It is one step forward. Now we will have a share for the enforcement.
GKidan

selamawi said...

በስመ ስላሴ አሃዱ አምላክ አሜን

መመሪያ ማውጣቱ አይከፋም ነገር ግን መመሪያ አውጭው ክፍል በራሱ ችግር ያለበት ስለሆነ ተፈጻሚነት አይኖረውም በመሰረቱ ቤተክርስቲያኗ የራሷ ቃለ አዋዲ ያላት ስለሆነ አድስ መመሪያ ማውጣት አያስፈልግም ነበረ የነበረውን ህግ ማስከበር ነው የሚያስፈልገው በቤተክርስቲያኒቱ ውስጥ የተፈጠረው ስርዓተ አልበኝነት በቤተክህነቱ ውስጥ ስለሆነ አሁንም የወጣው መመሪያ ለቤተክርስቲያኒቱ እንዲጠቅም ተብሎ ሳይሆን በቤ,ተክህነት አካባቢ ያሉ ኃላፊዎች እንደፈለጉ እንዲጽፉ እንዲዘምሩ ወ ።ዘ ። ተ ምናም ን ነው አምላክ ይታረቀን

ወልደ መድህን

Unknown said...

Unless it is so late, it is appropriate!!.
A good progress in the administration and management of the the mother church 'Ethiopian Orthodox Tewahido Church'!!!

Long live our Fathers!!!

Moona said...

ይህ ህግ በአግባቡ ከተጠቀምንበት ቤ/ክንን የሚያስከበር ህግ ነው ::ለዚህ ዓይነቱ ወሳኝ ህግ ደግሞ ከላይ እስክታች ያለን የቤተ ክርስቲያን ልጆች ለተግባራዊነቱ ወሳኝ ትሳትፎ ልናደርግ ይገባል::
1.አርቅቀው አጽድቀው የሰጡን አባቶቻችን ተግባራዊ መሆኑን ሊከታተሉ ይገባል::በየሃገረ ስብከታቸው ሥር ያሉትን የአስትዳደር አካላት ሊያስግነዝቡ ይገባል::ከጠቅላይ ቤተክህነት እስክ ወረዳ ቤተከህነት : ከወረዳ ቤተክህነት እስክ አጥቢያ ቤ/ክ ተናቦ የሚሰራበትን መመሪያ መስጠት አለበት::ልማዳዊ አሰራርን ማስወገድ ወይም መቛቛም::
2.የቅ. ቤተክርስቲያን ልጆች በየአጥቢያ ቤተ ክርስቲያናችን ውሳኔውን ልናግዝ ይገባል::ልማዳዊ ከሆነ አስተሳሰብ ወጥተን ቤ/ክ የመሰከረች ለትን መምህር ልንቀብል ይገባናል::ቤ/ክ ተቋማዊ በሆን መልኩ የኔ ነው ያለቺውን ካሴት;ሲዲ: መጽሐፍ ....ወዘተ ብቻ ልንቀበል ይገባል::
3.የሊቃውንት ጉባኤ ውይም ሌላ የቤ/ክኗ አካል ይህ የቤተክርስቲያናችን ትምህርት ነው ብሎ ሊነግረን ይገባል::ይህ ይመለይት ሥራ የሚጠቅመው ለኛ ለአማኒያን ብች ሳይሆን ቤ/ክ የምትናገረውን ለማውቅ ለሚፈልግ ኢ-አማኒም ጭምር ነው::

alganan said...

ደንቡ የሚያስደስታቸው የቤተክርስቲያን ልጆችን ነው ሰው የሚያመልኩትን ያስከፋል ድሮም ቢሆን ቤ/ክን ያስቸገራት ሰው አምከላኪ እንጅ ክርስቲያኑ ድሮም አለ አሁንም መመሪያ አያስፈልገውም!

dani said...

yhe hge ktserabte behwenet bmeskene mehmene eybeltsegu yalutene yemelye selhone letgebarawentu hulme yebekulene yenqsaqse.

kassaye said...

We expect more information about who is who and what is what continousely.
kassaye.Assefa

Anonymous said...

ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚበጅ በመሆን እጅግ የሚያስደስት ውሳኔ ነው። ትልቁ ነገር ደንቡ መጽደቁ ሳይሆን ተግባራዊ ማድረጉ ነው። ለዚህ መሳካት ከእኛ ምን ይጠበቃል ለሚለው ጥያቄ መልስ ልንሰጥ ይገባል።in

ehete micheal said...

Good job God bless you even if we are late this is really great job .
TEBARKULGN

Anonymous said...

since it is not based on honesty and organized research it is just nothing.

kaleb the ethiopia said...

ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን የሚበጅ በመሆን እጅግ የሚያስደስት ውሳኔ ነው። ትልቁ ነገር ደንቡ መጽደቁ ሳይሆን ተግባራዊ ማድረጉ ነው። ለዚህ መሳካት ከእኛ ምን ይጠበቃል ለሚለው ጥያቄ መልስ ልንሰጥ ይገባል።

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)