May 3, 2010

ዳላስ ቅ/ሚካኤል በብጥብጥ እየታመሰ ነው


  • ሁለት ካህናቱ ተባረዋል፣ ምእመናን በፖሊስ ከቤተ ክርስቲያን ተይዘው ወጥተዋል፤
(ደጀ ሰላም፣ ሜይ 3/2010)፦ በዳላስ ቴክሳስ የሚገኘው የደ/ምሕረት ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አዲስ የተመረጠው ቦርድ ሁለት አገልጋይ ካህናቱን ካባረረ በኋላ እሑድ ሜይ 2/2010 ዕለት ደግሞ ድርጊቱን የተቃወሙ ምእመናንን በፖሊስ እያስያዘ ሲያስወጣ መዋሉ ተሰምቷል። 
የዳላስ ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለረዥም ጊዜ በተለያዩ ቡድኖች መካከል በተነሣ ውዝግብ የፍርድ ሒደት ላይ የሚገኝ ሲሆን አዲስ የተመረጠው ቦርድ ካህናቱን በማባረር በቤተ ክርስቲያኑ ያለውን ውጥረት ከፍ አድርጎታል ተብሏል። አሁን በሥልጣን ላይ ያለውም ሆነ ከዚህ በፊት የነበረው ቦርድ “ገለልተኛ” የሚባለውን የዚህን ቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ያባክናሉ እየተባሉ ከመወንጀላቸውም በላይ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ያልሆኑ ፕሮቴስታንቶች ሳይቀሩ በቦርድ አባልነት ያሉበት እንደሆነ ምእመናን ይናገራሉ። (ፎቶ፦ ከግራ ወደ ቀኝ ቀሲስ መስፍን እና መ/ሣ አወቀ)


የዳላስ ቅ/ሚኣኬል ቤተ ክርስቲያን በሰሞኑ ውሳኔው በሕዝብ ዘንድ ተወዳጅነት እንዳላቸው የሚነገርላቸውን ቀሳውስት መላከ ሣሕል አወቀ ሲደልልን እና ቀሲስ መስፍን ደምሴን  ካባረረ በኋላ ተቃውሞው ጠንክሮ ቀጥሏል። በአሜሪካን ሀገር ውስጥ በተለይም ገለልተኛ ነን በሚሉት አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ቅጥ ያጣ የሰላም ማጣትና መካሰስ የበረከተ ሲሆን ሌላው ቀርቶ በእምነት በኩል መታየት የሚገባቸው ሃይማኖታዊ ጉዳዮች ሳይቀሩ ሊመለከታቸው የሚችል የሃይማኖቱ የበላይ አካል ባለመኖሩ (ሁሉም ነገር እዚያው ሞላ፣ እዚያው ፈላ እየሆነ) ኦርቶዶክሳዊ እምነት የሌላቸው ሰዎች “ቦርዶችን በመቆጣጠር” እምነቱን ወደሚፈልጉት ለመምራት በመሞከር ላይ ናቸው የሚል ስሞታ እየተሰማ ነው።

በዚህ ዓይነት የፍርድ ቤት ክስ ከሚገኙት መካከል የዲሲው ቅ/ሚካኤል እና የዳላሱ ቅ/ሚካኤል አብያተ ክርስቲያናት ተጠቃሾች ናቸው። የዲሲው ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ አቡነ ፋኑኤል (አባ መላኩ) የተመሠረተ ሲሆን እርሳቸው ማዕረገ ጵጵስና ተቀብለው ወደ ሀገር ቤት ከገቡ ወዲህ በቦርዱና ቦርዱን በሚቃወም ቡድን መካከል የቆየ ትግል በመደረግ ላይ ይገኛል። 
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

9 comments:

Anonymous said...

የተዛባ መረጃ አታስተላልፉ፡፡ ከሥራ የተሰናበቱት መልአከ ሣህል አወቀ ናቸው፡፡ ቄስ መስፍን ግን ይህንን ድርጊት በመቃወም በሚያስተምሩት ትምህርት ጣልቃ ከባድ የሆነ የስንብት ንግግር አድርገው ፤ ሥራቸውንም በፈቃዳቸው መልቀቃቸውን ለሕዝብ በይፋ ኣሰውቀው ነውና የወጡት በዚህ እንዲታረም አሳስባለሁ፡፡
እሸተ ማርያም ከዳላስ

Anonymous said...

በስመ ስላሴ አሃዱ አምላክ አሚን

ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች እናንተ ግን የወንበዴዎች ዋሻ አደረጋችኋት ማቴ 21፥13

ውድ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ምእመናን በዚህ አትሸበሩ ይህ ይሆን ዘንድ ግድ ነው ማስተዋል ካልተነሳን በስተቀር ቤተክርስቲያን ከፈተና ነጻ የሆነችበት ዘመን አልነበረም ነገር ግን በቅዱስ ወንጌል እንደተነገረው ማሰናከያን ለሚያመጣ ለዚያ ሰው ወዮለት እንደተባለ ክርስቲያን መስለው ነገር ግን ክርስቶስን የማያውቁ ብዙ ሰዎች ቤተክርስቲያንን እንመራለን በማለት ስርዓት ሲያፋልሱ ይታያሉ ለነሱ ወዮላቸው በመሰረቱ ቤተክርስቲያንን የሚመራት ክርስቶስ ሆኖ ሳለ በጥላቻና በዘረኝነት የተሞሉ የሰውን እንጅ ፍጹም የእግዚአብሄርን ቸርነት የማያውቁ ሰዎች ቤተክርስቲያንን በመምራት ላይ ይገኛሉ ለዚህ ሁሉ ተጠያቂው ከላይ ጀምሮ ቤተክርስቲያኗን የሚመሩት የሃይማኖት መሪዎች ይመስሉኛል ምክንያቱም እርስበእርሳቸው ፍቅር ሆነው በአንድነት ህዝቡን መምራት ቢችሉ ኖሮ ለፖለቲከኞች መግቢያ ቀዳዳ ባልተፈጠረም ነበር አሁንም አምላክ ፈቃዱ ሆኖ ቤተክርስቲያንን በቅንነት የሚመሩ አባቶችን እንዲሰጠን እንጸልይ ደግ መሪ የሚሰጠው ለመልካም ህዝብ ነውና በመካከላችን ያለውን የዘረኝነት የስጋ ጥቅም አስወግደን ወደአምላካችን በንስሃ ከተመለስን አባቶቻችንን መልካም መሪ ያደርግልናል ስለ ሁሉም የሱ ፈቃድ ይሁን የእናቱ የንጽህት የቅድስት ድንግል ማርያም ምልጃና በረከት ከሁላችን ጋራ ይሁን


ወስብሃት ለእግዚአብሄር

Anonymous said...

የፍቅር ባለቤት የሰላም ንጉስ ሰላማዊ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላሙን ፍቅሩን ይስጠን

ኤልሮኢ ዘ ገቺ said...

በውጭም በሀገር ውስጥም ላላችሁ በሙሉ መቼም በእኛ ኃጢያትና አለመታዘዝ ይህንን ሁሉ መከራና ስቃይን እንቀበላለን እስቲ መለስ ብለን እንመልከት ዙርያችንን እንቃኝ የተሳለ የዓለም ሰይፍ በሙሉ በኛ ላይ ተስሎ ነው ያለው ለምን ካለፈው ተምረን እግዚአብሔርን አንከተልም፡፡ሰዎች እንደፈለጉ የሚያሽከረክሩን የዕመነት ጽናት ማጣትና የእግዚአብሔርን ቃል ካለማስተዋል ነው የሚመስለኝ እባካችሁ በተለይም በውጭ ዐለም ያላችሁ እኛ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለነው ምዕመናን ከእናንተ በላይ ፈተና እናዳለብን የምታጡት አይመስለኝም እኛ ከእናንተ ብዙ ነገርን ስንጠብቅ እናንተ ግን በትንሹም በትልቁም ተባላላችሁ እባካችሁ እስቲ ቆም ብላችሁ አስተውሉ ለምን ግን እርስ በእርሳችን መስማማት አቃተን የመናፍቃን የግለሰቦች ጥቅም አስከባሪዎችስ ለምን እንሆናለን ግን ለምን እሰቲ አስቡበት፡፡

በመጨረሻም በምቾት ዕንቅልፍ ያንቀላፋን መልካም የሰራን መስሎን በአባቶች መካከል ወሬ የሚያማሙቁ ስውር ተልዕኮ ያላችሁ ሰው ባያይ እግዚአብሔር ያያልና ከጥፋታችሁ ብትታቀቡ፡፡ እግዚአብሔር ልብ ይስጣችሁ፡፡

ምዕመናንም በዚህ በታናሽነቴ የጻፍኩላችሁን በንፁህ ህሊና ልብ ብተሉት መልካም ነው፡፡
ውሻ በቀደደው ጅብ እንዳይገባ ምንቸገረኝ ይቅር፡፡

እልሮኢ
ዘ ገቺ

alganan said...

ለምን ግነ?

Rodas said...

the reason for all this is that the Hirarchy of the church ends with the board. What happen to the church that raised us! remember! the church where the Arch Bishopes.
Listen! Dallas! your kids deserve a lot better than this. there are two churches in Dallas that are truely part of the Ethiiopian orthodox church, and this sort of nonsence is Garrantied not to ever happen.

1. Genete Tsege Giorgis
2. Debre Tsehay Tekle Haymanot.

Anonymous said...

This is inappropriate as a Christian to do in its Church if it is claiming it own. As we see from the clip on you tube, the Priest is on a service proceeding and the MOB are distracting. Who ever is part of this and taking this picture than pray is shameful? Living in the USA and especially in the Church, there are plenty tools to defuse any disagreement and resolving dispute. If you cannot a good follower, you cannot be a good leader. This kind of behavior may apply in lawless state. If you learn this from where you come you are completely wrong on this time of age in a great nation of ours. It is clear that you punch of peace hater were armed with video record and disturb the peace of other to pray. As an Ethiopian origin and as an American I ask when are you guys learning being civil for one to the other. If you are, only a member of that specific Church there should be a rule to follow, if you said you are in the same faith, hope there is other Church to join or open. Grow up and think big and do better for your community, get out of such box you become your own prison as you used to grow you moron!

Selam from Dallas

Anonymous said...

Shame on Deje Selam for posting the clip as if it would benefits the image of EOTC. The victim is the Church herself in this case. Who is the agressor here? There is a Church adminstration board that is give the responsibility of running the affairs of the church and there are those who would loose much because of actions this board has decided to take.

I am not in support of the actions taken by the board. In fact, I oppose the involvement of the Police to settle disputes in our church. Although this is not the first time this type of action has taken place in an Ethiopian church, it still does not make it right for any board to exercise their right to call the Cops on its members.

However, many disputes in our church have resulted in involving cops. This is simply because we, Ethiopians, consistently fail to sit and hold discussions to resolve our differences in a manner that is civilized. We live in a country that wwas founded on compromises, yet we cannot see the value of compromising on issues and protect the integrity of the church.

The agressors at Dallas Michael are those who fail to see the interest of the entire congregation and only focus on the interest of their mahiber.

What I want to know from the bloggers on this site is why they decided to share this news with us ... Why not the background of the story .... what has been going on at the Dallas church? Can you shade light on the court cases? ... how about the attempts to settle issues by shimagile?
" ...

selamawi said...

የመላእክት አለቃ ሚካኤል እንኳ ስለ ሙሴ ስጋ ሰይጣን በተከራከረው ጊዚ የስድብ ቃል አልተናገረም እግዚአብሔር ይጣልህ አለው እንጅ ይሁዳ 1፥9
የምህረት መልዓክ ቅዱስ ሚካኤል በምህረት ይጎብኛቸው

አሜን

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)