May 2, 2010

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ


ዲስ አበባ, ሚያዝያ 23 ቀን 2002 (ኢዜአ) - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተለያዩ የሀገሪቱን ልማትና ብልጽግና የሚያስገኙ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያኗ አገልግሎቶችን የሚያበረክቱ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ፡፡
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ጽሕፈት ቤት ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው ከሚያዚያ 19 ቀን 2002 ዓ.ም ጀምሮ ባካሄደው ምልዓተ ጉባኤ ከጥቅምት ጀምሮ ለስድስት ወር የተወሰኑትን የሥራ ክንዋኔዎችን ገምግሞ ከበፊቱ የበለጠ የቤተክሰታኗን የልማት እንቅሰቃሴ በማጎልበት አንዲንቀሳቀስ ወስኗል፡፡

የአለም አብያተ ክርስትያን ፕሬዚዳንትና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም ፕሬዚዳንት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትሪያርክ ዘኢትዮጵያ ጉባኤው ሲጠናቀቅ እንደገለፁት የሀገራችን ሰላምና አንድነት እዲጠበቅ ሁሉም ህብረተሰብ ከጥንት ጀምሮ ሲያደርገው የነበረውን ተጋግዞ የመራትና ችግርን የመፍታት ባህል አጠናክሮ እንዲቀጥል መክረዋል፡፡

ቤተክርስተያኗ ለሶስት ተከታታይ ዓመታት ተመርጠው ይሰሩ የነበሩትን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የቅዱስ ሲኖዶስ ፀሐፊ በመቀየር በምትካቸው መርጧል፡፡

ከኢትዮጵያ ውጭ ባሉ አህጉረ ስብከቶች በተበታተነ መልኩ የሚታዩትን አንዳንድ አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት በቤተ ክርስቲያኗ ስር በተሰራው መዋቅር በመሰባሰብ ለሀገር ልማትና እድገት በአንድነት እንዲሰሩ ጉባኤው መመሪያ ሰጥቷል፡፡

ሀገራችን መካከለኛ ገቢ ካላቸው አህጉር እንድትቀላቀል ለተዘረጋው የልማት እቅድ አፈፃፀም ወጣቱ ትውልድ የሥነ አእምሮ ብቃቱን አሳድጎ ሥራ የመፍጠር ክህሎቱን እንዲያዳብር ቅዱስ ሲኖዶስ ጥሪውን አሰተላልፏል፡፡

ቤተ ክርስቲያኗ ኤችአይቪ/ኤድስ ለመከላከል የሚታደረግውን እንቅሰቃሴ በማጠናከር ህበረተሰቡን የማስተማር ተግባር አጠናክራ እንደሚትቀጥል ተጠቅሷል፡፡

የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ከጥቅምት ጉባኤው ጀምሮ የፈፀመውን የሥራ ክንዋኔ ሪፖርት በማዳመጥ አስፈላጊውን መመሪያ የሰጠ ሲሆን በመንፈሳዊና ማህበራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይቶ በመወሰን ዓመታዊ መደበኛ ስብሰባውን አጠናቋል፡፡


1 comment:

Addis said...

በርቱ....ስለሁሉም ነገር

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)