May 27, 2010

ቤተ ክርስቲያን የሚባርከው (“የሚከፍተው”) ማን ነው? ሥልጣኑስ የማን ነው?

(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 27/2010)፦ ከዚህ መግቢያ ቀጥሎ የምናስነብባችሁ ይህ ጽሑፍ የአንዱ ደጀ ሰላማዊ የገብር ሔር ዘመ/መንግሥት ሲሆን በአስፈላጊው ጊዜ ስለደረሰን አምላካችንን እያመሰገንን ልናስነብባችሁ ወደድን። ጽሑፉ በተለይም በዳያስጶራ ያለችውን ቤተ ክርስቲያን ሁኔታ ይመለከታል። በዳያስጶራው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን እየተስፋፋች ቢሆንም የመስፋፋቷ ምክንያት ሥርዓትና ሕጓን በጠበቀ መልኩ ሳይሆን አንዳንዴም ፈር በለቀቀና ኢ-ኦርቶዶክሳዊ በሆነ መንገድ መሆኑን ያጠይቃል። ይህ ችግር ካለፉት ጥቂት ዓመታት ወዲህ በመጠኑ ጋብ ያለ፣ ቤተ ክርስቲያን በተለይም በአገረ አሜሪካ 3 ሊቃነ ጳጳሳትን ከሾመች ወዲህ መስመር እየያዘ የመጣ ቢመስልም ነገሩ አሁንም እንዳያገረሽ የሚያሰጋ እንደሆነ ፍንጮች እየታዩ ነው። ያለ ጳጳስ ፈቃድ “ራሳቸውን ጳጳስ ያደረጉ” ሰዎች አብያተ ክርስቲያናትን “ባረክን፣ ከፈትን” ሲሉ፣ ሕዝቡንም ስተው ሲያስቱ እያየን እየሰማን ነው። እኛም በበኩላችን "ኧረ እንዴት ነው ነገሩ?" ለማለት ወደድን። የአዲስ ነገር ጋዜጣ ብዕረኛ መስፍን ነጋሽ “ልብ አይሰደድም፣ ሕልም አይነጠቅም” እንዳለው ሳይሆን ከአገራችን ስንሰደድ ጊዜ “ልባችንም፣ ሃይማኖታችንም፣ ሥርዓታችንም፣ ጨዋነታችንም እኛን ጥሎ ተሰደደ” እንዴ? በሌላ ጽሑፍ በሰፊው ልንመለስበት ቀጠሮ ይዘን ወደዚህ ጽሑፍ እንግባ። መልካም ንባብ።
ቸር ወሬ ያሰማን፤ አሜን።

"አለን በእግዚአብሔር ሁሉን አልፈን" (ግሩም መዝሙር)

Ethiopian Orthodox Hymn (Alen Be Egziabher Hulun Alfen/ አለን በእግዚአብሔር ሁሉን አልፈን)

St. TekleHaymanot (2010) Feast in USA

May 25, 2010

EU observers say Ethiopia election "falls short of certain international commitments"


(BBC):- EU observers have criticized Ethiopia's election, as Prime Minister Meles Zenawi holds a victory rally attended by tens of thousands of people.
There was an "uneven playing field", said chief EU observer Thijs Berman. Mr Meles is heading for a landslide victory, election officials say but the opposition has complained of vote-rigging. Violent protests over alleged fraud in the last poll in 2005 left about 200 people dead.
"This electoral process falls short of certain international commitments," Mr Berman said, pointing to the use of state resources to campaign for the governing Ethiopian People's Revolutionary Democratic Front (EPRDF).

May 18, 2010

የዳላስ ቅ/ሚካኤል ጉዳይ በቴሌቪዥን ቀረበ

An internal affairs complaint has been filed against the Garland Police Department by a woman who says she was roughed up while being removed from a church service by police. FOX 4's Shaun Rabb has the story you'll see only on FOX 4.


ለምን ይህ ሆነ?
(ሙና፣ Moona)
የማናውቀው ያለመድነው ነገር በቤተ ክርስቲያንናችን ላይ ለምን ተከሰተ? ለምንድን ነው እየተከሰተ ያለው? በቤተ ክርስቲያንያናችን የሚነሱ አለመግባባቶች እንዴት ነበር የሚፈቱት? በካህናትና በካህናት፣ በዲያቆናትና በዲያቆናት፣ በካህናትና በዲያቆናት፣ በምዕመናንና በምዕመናን... ወዘተ የሚነሱ/ ሊነሱ የሚችሉ ችግሮችን የምንፈታበት ሥርዓት፣ ሕግ፣ ትውፊት የለንም ወይ? የቤተ ክርስቲያን ሥርዓት ምን ይላል? ልናስተውል ይገባናል:: ልንነጋገር ይገባል!! ልናውቅና ልንነቃ ይገባል!!

May 17, 2010

የዳላስ ቅ/ሚካኤል ጉዳይ ዛሬ ሰኞ በቴሌቪዥን ሊቀርብ ነው

(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 17/2010)፦ሚያዚያ 24 2002 ( May 2 2010 ) በዳላስ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የአስተዳደር ቦርድ በጠራቸው ቁጥራቸው ከ20 በላይ በሚሆኑ (ወንጀለኛን በውሻ በሚፈልጉና ቦንብ ፈታሽ በሆኑ) ፖሊሶችና በምእመናን መካከል በቤተ መቅደስ ውስጥ የተፈጸመውን ግርግር በተመለከተ በዩቱብ ለዓለም የተሠራጨው የቪዲዮ ፊልም የሜዲያን ትኩረትን ስለሳበ ዛሬ ሰኞ May 17 2010 ከምሽቱ 9.00pm ላይ በቻናል 4 (FOX 4) ላይ በቴሌቪዥን እንደሚተላለፍ ታወቀ፡፡

የሃይማኖት መሪዎች ለተፎካካሪ ፓርቲዎች መልዕክት አስተላለፉ

(ሪፖርተር)፦ በመጪው ሳምንት የሚካሄደው አራተኛው አገራዊ ምርጫ ሰላማዊ እንዲሆን የሃይማኖት መሪዎቹ ለ63ቱ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የሰላም መልዕክት አስተላለፉ፡፡የኦርቶዶክስ፣ የእስልምና፣ የካቶሊክና የፕሮቴስታንት የሃይማኖት መሪዎች ግንቦት 5 ቀን 2002 ዓ.ም. በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡ የሃይማኖት መሪዎቹ ላለፉት ስድስት ወራት የሰላም ምኞትን ዕውን ለማድረግ በሠፊው ሲንቀሳቀሱ እንደነበር አስታውቀዋል፡፡ የፖለቲካ ፓርቲዎችም በምርጫ ቦርድ ጽ/ቤት በመገኘት የጥሪ መልዕክቱን ተከታትለዋል፡፡

May 12, 2010

የሃይማኖት መሪዎች ምርጫውን በማስመልከት ፓርቲዎችን ሊያነጋግሩ ነው

- ፓርቲዎቹ የተለያዩ አስተያየቶች ሰጥተዋል፤
(ሪፖርተር ጋዜጣ) :- የሃይማኖት መሪዎች የ2002 ምርጫን አስመልክቶ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ነገ በምርጫ ቦርድ ጽሕፈት ቤት እንደሚያነጋግሯቸው ታወቀ፡፡

የሃይማኖት አባቶች ምርጫውን ሰላማዊ ለማድረግ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር የሚነጋገሩ ሲሆን፤ የኦርቶዶክስ፣ የካቶሊክ፣ የፕሮቴስታንትና የእስልምና እምነት መሪዎች መሆናቸው ታውቋል፡፡ 

የሃይማኖት መሪዎች የጠሩትን ስብሰባ አስመልክተን ያነጋገርናቸው የፖለቲካ ፓርቲዎቹ የተለያየ አስተያየት ሰንዝረዋል፡፡(Pictures: Courtesy of Addis Fortune).

May 11, 2010

ቅ/ሲኖዶስ ሰባክያንንና ዘማርያንን የተመለከተ ያወጣውን ሕግ ለሚመለከታቸው አካላት አስተላለፈ


(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 10/2010)፦ ቅ/ሲኖዶስ ባለፈው ዓመት ያወጣውን ስለ ሰባክያንና ዘማርያን የተመለከተውን መመሪያ በማጠናከር ፈቃድ ሳይኖራቸው ስለሚሰብኩ እንዲሁም በሊቃውንት ጉባዔ እና በሚመለከታቸው የቤተ ክርስቲያን አካላት ሳይታዩ ስለታተሙ ሕትመቶች ጉዳይ ለመንግሥት አቤቱታ አቀረበ።

May 10, 2010

የሰው ዛፍ እንትከል

(ከወርቅነሽ ቱፋ)
 የአብነቱ እውቀት የቅኔ የድጓ ያቋቋሙ አፈር፣
የመጽሐፉ ቤት ያሬዳዊ ዜማ እንዳይሸረሸር፣

ምድረ በዳ እንዳይሆን።

በፈረሰው በኩል ለመቆም እንትጋ፣
የእጃችን እንቁ ጠፍቶ ይቀርና እንዳንሄድ ፍለጋ::

ተነበው ተነበው ማያልቁቱ መጣፍ እኒያ ሊቃውንቱ፣
ሊኖሩ ይገባል ትውልድን ሊተኩ ሊቀጥል ትውፊቱ።

ተዋህዶን ብለው ተደጃ ተጥለው ስንት ሊቅ ያፈሩ፣
ማዕረጋችን ናቸው 'ሚቆጠሩ ቅርሶች አባቶች ይኑሩ።

ወስብሃት ለእግዚአብሔር

የዳላስ ቅ/ሚካኤል ጉዳይ

  (ደጀ ሰላም፤ ሜይ 10/2010)፦ የዳላስ ቅ/ሚካኤል ምእመናን ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዳይገቡ በፖሊስ ያባረራቸው ቦርድ ላይ ጊዜያዊ የእግድ ብይን ("temporary restraining order") ከፍርድ ቤት በማስወጣት ወደ ቤተ ክርስቲያን የመግባታቸውን መብት አስከበሩ፤ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ምእመን የተገኘበት ስብሰባም አካሄዱ። የአስተዳደር ቦርዱ በበኩሉ ባለፈው እሑድ ለተፈጠረው ትርምስ  (Video) “ማኅበረ ቅዱሳንና የወያኔ ደጋፊዎች” ያላቸውን ምእመናን ወንጅሎ “የማዳግም ሕጋዊ እርምጃ የሚወስድ መሆኑን” በበተነው መግለጫ አስታውቋል።
(ዝርዝሩን ይጠብቁ)

May 8, 2010

Greek Orthodox Church ready to stand by the people in tough times

(WCC: 06.05.10):- The Church of Greece is getting ready to assist the Greek people to face the consequences of tough economic measures taken by the government, a church official attending an ecumenical gathering in Geneva has said.

The Archbishop of Athens and All Greece and Primate of the Autocephalous Orthodox Church of Greece, Hieronymos II, met on Tuesday, 4 May with the country's Prime Minister George Papandreou to express the church's willingness to support the Greek people during the difficult times ahead, said Rev. Fr Gabriel Papanicolaou. A church official, Papanicolaou is attending a 4-6 May gathering of churches' ecumenical officers organized by the World Council of Churches.

May 6, 2010

“ነገር በምሳሌ፣ ጠጅ በብርሌ” እንዲሉ እነሆ ጥሩ ምሳሌና ጥሩ መልእክት

(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 5/2010)፦ ይህንን አጭር ምሳሌና ማብራሪያ ያገኘነው ከአቶ መስፍን አግዴ የፌስቡክ ገጽ ላይ ነው። መልእክቱ ግሩም ሆኖ ስላገኘነው ለደጀ ሰላማውያን ለማካፈል ወደድን። በግራም በቀኝም ለምንሰማቸው የቤተ ክርስቲያናችን ችግሮች፣ መፍትሔውን ከሌላ ወገን ለምንጠብቅ ዳተኞች ጥሩ አስተማሪ ሆኖ አግኝተነዋል።
---------------------------
ጌታ ለአራት ሰዎች ቤቱን እንዲያፀዱለትና እንዲጠብቁለት ነገራቸው። እነዚህ ሰዎች ሁሉምሰው፣ አንድሰው፣ የሆነሰው እና ምንምሰው ይባላሉ። ታዲያ “ሁሉምሰው” አንዲህ ሲል አሰበ። “የሆነሰው ሊያፀዳው ይችላል። እኔ ግዴለም ወደ ሥራዬ ልሒድ” ብሎ ወደራሱ ጉዳይ ሄደ። “የሆነሰው”ም በበኩሉ “በርግጠኝነት አቶ አንድሰው ይሰራዋል” በማለት ሳያፀዳው ቀረ። አቶ አንድሰው ግን “አቶ ምንምሰው ቢሰራው ይሻላል” በማለት እሱም እንደሌሎቹ ወደራሱ ሥራ ሄደ። ምንምሰው ግን በሀገሩ ስላልነበር ቤቱ ሳይፀዳ ቀረ። ጌታ ሲመለስ ቤቱ ሳይፀዳ ሲያገኝ በማን እንዲፈርድ ታስባላችሁ?

ማኅበረ ቅዱሳን ዲያቆን በጋሻውን ከሰሰ


(አዲስ አድማስ ጋዜጣ; May 02, 2010 )፦ በአዲስ አበባ እና በተለያዩ የአገሪቷ ክልል ከተሞች እየተዟዟረ የሚሰብከው ዲያቆን በጋሻው ከስብከተ ወንጌልና ሐዋርያዊ ተልዕኮ መምሪያ ፈቃድ ውጪ በድሬዳዋ ከተማ በቅዱስ ገብርተ ክርስቲያን ባደረገው ሰበካ “ማኅበረ ቅዱሳኖች የተለያዩ ወንድሞችን ደም የሚመጡ፣ ደማቸውንም በጽዋ ተቀብለው የሚጠጡ ናቸው» በማለት ሕጋዊ ፈቃድ ተሰጥቶት የሚንቀሳቀስን ተቋም ስም አጥፍቷል በሚል ማኅበሩ ክስ መስርቷል።  በማኅበረ ቅዱሳን የድሬዳዋ ማዕከል፣ ሰባኪው በማኅበሩ ላይ ያደረጉት ሕገ ወጥ ስም ማጥፋት በሕግ አግባብ ታይቶ ሊቀጡ ይገባል የሚል አቋም ስላለው በድሬዳዋ ከተማ ቤተ ክርስቲያኑ በሚገኝበት አካባቢ ባለው ሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ክስ መመስረቱን አስታውቋል።

May 5, 2010

“ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ትሰመይ፣ ቤቴ የጸሎት ቤት ትባላለች”

(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 5/2010)፦ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በመዋዕለ ትምህርቱ በአንዱ፣ ቀራጮች፣ ነጋዴዎችና ቀማኞች መቅዱሱን ባረከሱበት ወቅት፣ በጅራፍ እየገረፈ ባባረራቸው ጊዜ የተናገረው አምላካዊ ቃል “ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ትሰመይ” የምትለው ናት። (ማቴ. 21፡13፤ ማርቆስ 11፡17፤ ሉቃስ 19፡46) ያንን ዘመን የሚያስታውሰን ድርጊት በየጊዜው የሚከሰት ቢሆንም ባለፈው እሑድ በዳላስ ቴክሳስ ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን የተፈጠረው እና አንዳንድ ምእመናን ቀርጸው የያዙት ቪዲዮ ደግሞ የጌታን ቃል ድጋሚ እንድናስታውሰው ያደርገናል። ከሚገርመው ነገር አንዱ በዚህ ሁሉ ጩኸትና ግርግር መካከል “አድንኑ አርዕስቲክሙ ቅድመ እግዚአብሔር አምላክነ፤ ራሳችሁን በአምላካችን በእግዚአብሔር ፊት ዝቅ ዝቅ አድርጉ” እያለ ዲያቆኑ ሲያውጅ መስማት ነው።

May 3, 2010

ዳላስ ቅ/ሚካኤል በብጥብጥ እየታመሰ ነው


  • ሁለት ካህናቱ ተባረዋል፣ ምእመናን በፖሊስ ከቤተ ክርስቲያን ተይዘው ወጥተዋል፤
(ደጀ ሰላም፣ ሜይ 3/2010)፦ በዳላስ ቴክሳስ የሚገኘው የደ/ምሕረት ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አዲስ የተመረጠው ቦርድ ሁለት አገልጋይ ካህናቱን ካባረረ በኋላ እሑድ ሜይ 2/2010 ዕለት ደግሞ ድርጊቱን የተቃወሙ ምእመናንን በፖሊስ እያስያዘ ሲያስወጣ መዋሉ ተሰምቷል። 
የዳላስ ቅ/ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ለረዥም ጊዜ በተለያዩ ቡድኖች መካከል በተነሣ ውዝግብ የፍርድ ሒደት ላይ የሚገኝ ሲሆን አዲስ የተመረጠው ቦርድ ካህናቱን በማባረር በቤተ ክርስቲያኑ ያለውን ውጥረት ከፍ አድርጎታል ተብሏል። አሁን በሥልጣን ላይ ያለውም ሆነ ከዚህ በፊት የነበረው ቦርድ “ገለልተኛ” የሚባለውን የዚህን ቤተ ክርስቲያን ገንዘብ ያባክናሉ እየተባሉ ከመወንጀላቸውም በላይ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ያልሆኑ ፕሮቴስታንቶች ሳይቀሩ በቦርድ አባልነት ያሉበት እንደሆነ ምእመናን ይናገራሉ። (ፎቶ፦ ከግራ ወደ ቀኝ ቀሲስ መስፍን እና መ/ሣ አወቀ)


አባቶችን የማስታረቅ ሌላ ጥረት ተጀምሯል

(ደጀ ሰላም፤ ሜይ 2/2010)፦ በስደት ከኢትዮጵያ ወጥተው በአሜሪካ እና በሌሎች አገሮች የሚገኙትን አባቶች እና ቅዱስ ፓትርያርኩን ለማስታረቅ ሙከራ እየተደረገ መሆኑ ታወቀ።

May 2, 2010

ቅ/ሲኖዶሱ የአቡነ ሳሙኤልን ጉዳይ አላነሣም

(አዲስ አድማስ፤ ሜይ2/2010)፦ ሰሞኑን በተካሄደው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ መንፈቃዊ ጉባኤ እልባት ያገኛል ተብሎ የተጠበቀውን የብፁዕ አቡነ ሳሙኤል እና የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጉዳይ "ለግንቦቱ ምርጫ ትኩረት እንዲሰጥ" በሚል ሳይነሣ እንደቀረ ተጠቆመ። ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሲኖዶሱን ሲከፍቱም ሆነ ሲዘጉም "ለምርጫው በሰላም ተጀምሮ መጠናቀቅ ትኩረት እንዲሰጡ" ሊቃነ ጳጳሳትን አሳስበዋል። በግል አስተያያት የሰጡን ሊቃነ ጳጳሳት በበኩላቸው ስላልተነሱት የሀገረ ስብከቱና የአቡኑ እንዲሁም የሽሬ ሀገረ ስብከትና ተያያዥ ጉዳዮች የሞቀ ክርክር እንዳያደርጉ አጀዳዎቹ በይደር እንዲቆዩ ከመንግስት አካላት ማሳሰቢያ እንደተሰጣቸው ጠቁመዋል።

የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ


ዲስ አበባ, ሚያዝያ 23 ቀን 2002 (ኢዜአ) - የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ የተለያዩ የሀገሪቱን ልማትና ብልጽግና የሚያስገኙ እንዲሁም የቤተ ክርስቲያኗ አገልግሎቶችን የሚያበረክቱ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ፡፡

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)