April 11, 2010

በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ተከበረ

(Mahibere Kidusan) ደቡብ አፍሪካ በሚገኙ ምእመናን በሦስት ነጥብ ስድስት /3 ነጥብ 6 ሚሊዮን ራንድ/ ተገዝቶ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በሚያመች መልኩ የተሠራው የፕሪቶሪያ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረትና ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤተ ተከበረ፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ፕሪቶሪያ የሚገኘው ይኸው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱ ጥር 16 ቀን 2002 ዓ.ም. በተከበረበት ወቅት
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ  ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ምክር ቤት ፕሬዝዳንት እና የዓለም ሃይማኖቶች ለሰላም ፕሬዝዳንት፣ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ የደቡብ እና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ እና ሌሎች ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናት አባቶች፣ መዘምራን ምእመናንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡

በደቡብ አፍሪካ የፕሪቶሪያ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ሕንፃ አሠሪ ኮሚቴ በዚሁ ወቅት ባቀረበው ሪፖርት፤ የእግዚአብሔርን ቃል እንማማር በሚል በአምስት የፕሪቶሪያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በትንሽ መኝታ ክፍል ሐምሌ 19 ቀን 1993 ዓ.ም. የተጀመረው እንቅስቃሴ እየጎለበተ መጥቶ የፕሪቶሪያ ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ጽዋ ማኅበርን በመመሥረት ከዚያም ፈቃደ እግዚአብሔር ሆኖ ይህ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ሊሠራ ችሏል፡፡

ከሁለት ዓመት በፊት ቤቱን ለመግዛት የተጀመረው እንቅስቃሴ ተጠናክሮ የተለያዩ ገቢ ማስገኛ ፕሮግራሞችን በማዘጋጀትና ምእመናንን በማስተባበር የሚፈለገው ገንዘብ ተገኝቶ በቸሩ እግዚአብሔር ፈቃድ እቅዱ እውን ሊሆን መቻሉን ከቦታው የደረሰን ሪፖርት ያስረዳል፡፡

በተጨማሪም የተገዛውን ቤት ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በሚሆን መልኩ ሠርቶ ለማዘጋጀት እንዲሁም ለቤተ መቅደሱ ንዋየ ቅድሳት ለማሟላት ወደ አንድ ሚሊዮን ራንድ ያህል ወጪ መደረጉን ሪፖርቱ አመልክቷል፡፡

ሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ ከግዢው ጀምሮ አስፈላጊውን በማሟላት ሥራውና ዝግጅቱ ሁሉ ፍጻሜ አግኝቶ ለአገልግሎት እስኪበቃ ድረስ ክትትልና ድጋፋቸው ያልተለየው የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ያዕቆብ እንዲሁም በደቡብ አፍሪካ ለሚገኙ ምእመናንና ምእመናት ሁሉ ኰሚቴው ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

6 comments:

አሐዱ said...

እንኳን ደቡብ አፍሪካ ገና መካ መዲና ላይ እናንፃለን ምን ይገርማል ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ገና አለም‹‹የክርስቲያን ደሴት›› ትሆናለች ሕዝብና አሕዛብ እጃቸውን በአፋቸው ጭነው የእግዚአብሔርን ስራ እስኪያደንቁ ድረስ፡፡ እግዚአብሔር ከእቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም በረከት ያካፍለን አሜን፡፡

አሐዱ

Teferi said...

We, who were there from the foundation of the congragation, learnt a lot of lesson from our God. There were a couple of times that we felt our dream will never come true but we the help of God and the intercession of our holy mother, everything is possible.

Again, bleesed be his name, our Lord.

Teferi from Pretoria

Teferi said...

We, who were there from the foundation of the congregation, learnt lots of lessons from our God. There were a couple of times that we felt our dream will never come true but with the help of God and the intercession of our holy mother, everything is possible.

Again, bleesed be his name, our Lord.

Teferi from Pretoria

fikir said...

I'd love to extend my gratitude for the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church Christian fellows in Pretoria. Congratulation once again, and blessed be His name, our Lord, as Scripture says,

"For it is God who works in you both to will and to do for His good pleasure."(Philip. 2:13) Here in Cape Town the Medhanyalem Gubaye was able to share all the joys and happiness with you. After the Pretoria Kidane Mehret Church Inauguration, His Holiness Abune Paulos along with Bishops stayed here in Cape Town for very few days in comforting us with sermons and benedictions of our Church Fathers. We were so grateful for their visiting the believes here in Cape Town, and His Holiness Abune Paulos also has contributed 1million birr for the Cape Town Medhanyalem Gubaye for buying our own Church, since we're worshiping God in renting hall.
To be continued!

fikir said...

The Committee along with brothers and sisters is labouring and praying to accomplish this wonderful idea. I beg in the name of the Cape Town Medhanyalem Gubaye, the whole Ethiopian Orthodox Church fellow Christians to be with us in praying, material and moral support.

I'd like to share with fellow Christians the short history of the Ethiopian Orthodox Church here in South Africa, especially in line with the Anti-Colonial and Anti-Apartheid struggle in the last quarter of the 19th century and half of 20th century. Let's keep in praying one another, May the Love of God and the intercession of Holy Virgin Mary be with our Church!
Selam! Shalom!
One of the Member!
University of Western Cape!

Anonymous said...

የመጀመሪያው ሐሳብ ሰጪ አኮራኸኝ ገና----------- መች ተነካና
ወንጌሉ በአለም ይሰበካል ‹‹ኢትዮጵያ ታበጽህ እደዊሐ ሐበ እግዚአብሔር››

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)