April 30, 2010

ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ፀሐፊውን መረጠ


(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 30/2010)፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዓመት ሁለት ጊዜ ከሚያደርገው ስብሰባ ሁለተኛውን ዓመታዊ ጉባኤ በማካሄድ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤልን ደግሞ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ አድርጎ መሰየሙ ታውቋል፡፡

በትንሣኤ 25ኛ ቀን በዋለው ርክበ ካህናት የተጀመረው ሁለተኛው ዓመታዊ ጉባኤ፣ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ  መሪነት፤ ከአገር ውስጥና ከውጭ ሀገራት በሚመጡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ተሳታፊነት የሚካሔድ ሲሆን፤ በጉባኤው የቤተ ክርስቲያኗ የልማት ተግባሮች የሚተረጐሙበትና የተከናወኑትም የሚገመገሙበት እንደሚሆን ከጽሕፈት ቤቱ ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ ሪፖርተር ጋዜጣ ረቡዕ ዕለት ዘግቦ ነበር፡፡
በዚህ ስብሰባው ቅዱስ ሲኖዶሱ ጥቅምት 11 ቀን 2002 ዓ.ም በተካሄደው ዓመታዊ አንደኛ ጉባኤ ላይ ተጀምረው ሳይጠናቀቁ በቀሩ ዐበይት ጉዳዮች ላይ በመምከር መፍትሔ እንደሚሰጥ አንዳንድ አባቶችን ጠቅሶ የዘገበው ሪፖርተር፣ ጥቅምት 11 ቀን 2002 ዓ.ም. በተካሄደው ጉባኤ ላይ በ18 አጀንዳዎች ላይ ተመካክረውና መክረው በ17ቱ ላይ ውሳኔ ካስተላለፉ በኋላ፣ "አቡነ ሳሙኤል የት ይመደቡ?" የሚለው ሐሳብ ውሳኔ ሊያገኝ ባለመቻሉ እስከ ሁለተኛው ዓመታዊ ጉባኤ ድረስ የቤተ ክርስቲያኒቱ የልማትና ክርስቲያናዊ ተራድኦ ኮሚሽን ጊዜያዊ ሊቀ ጳጳስ ሆነው እንዲቆዩ መወሰኑን ጋዜጣው አስታውሷል፡፡

ቅዱስ ፓትርያርኩ በሰኔ ወር የጣሊያን መንግሥት ባደረገላቸው ግብዣ መሠረት ወደ ጣሊያን ሲያመሩ፣ የአዲስ አበባ አገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ በነበሩት አቡነ ሳሙኤል ፊርማ የተለያዩ ደብዳቤዎች ለአድባራትና ገዳማት አስተዳዳሪዎች ተበትነው በቅዱስ ሲኖዶሱና በፓትርያርኩ መካከል ያለውን የውሳኔ ሰጭነት ሚና የሚያዛቡ ሆነዋል በሚል ውዝግብ መነሣቱንፓትርያርኩ ከመንፈሳዊ ጉዞአቸው ሲመለሱ አቡነ ሳሙኤልን ከሥራ በማገድ ሰባት አባቶች ያሉበት ኮሚቴ ተቋቁሞ፣ የአገር ስብከቱን የሒሳብ አያያዝ፣ የሠራተኛ ቅጥር፣ ምደባና ሌሎችንም በማጥናት ለጥቅምት ወር 2002 ዓ.ም. ዓመታዊ ጉባኤ ሪፖርት እንዲያቀርቡ ቢታዘዝም ባለ መድረሱ የተወሰኑ አጀንዳዎች ለሁለተኛው ዓመታዊ ጉባኤ መዛወራቸውን ሪፖርተርጠቅሷል፡፡
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)