April 23, 2010

ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሕክምና ላይ ናቸው፣ ታይላንድ

(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 23/2010)፦ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ታመው ባንኮክ ታይላንድ ሕክምና በመከታተል ላይ ናቸው። የጉራጌ፣ ሀድያና ስልጢ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ የሆኑት ብፁዕነታቸው በታታሪነታቸው ከሚመሰገኑ አበው መካከል አንዱ ሲሆኑ ባለፈው ዓመት በቤተ ክህነቱ በተነሣው የሕገ-ቤተ ክርስቲያን ይከበር ጥያቄ ሐምሌ 8 ቀን 2001 ዓ.ም መኖሪያቸው ከተደበደበውና አደጋ ከተጣለባቸው ብፁዓን አባቶች መካከል አንደኛው መሆናቸው ይታወሳል።

ያንን ወንጀል የፈፀሙት ሰዎች ማንነት ሳይጣራ እስካሁን ቆይቶ እነሆ ሐምሌ 2002 ዓ.ም ሲመጣ ዓመት ይሞላዋል ማለት ነው። ቤተ ክርስቲያኒቱም ማዕከሏ የሆነው ጠቅላይ ቤተ ክህነት ከተደፈረና ሕገ ወጦች በሯን ከፍተው ሊቃነ ጳጳሳቷ ላይ አደጋ ከቃጡ ዓመት ሞላ ማለት ነው።

ቀደም ብሎ አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ በግሪክ ሕክምና እየተከታተሉ መሆናቸውን መዘገባችን ይታወሳል። ደጀ ሰላምም ለብፁዓን አባቶቻችን ጤንነትንና ረዥም ዕድሜን ትመኛለች።

ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)