April 19, 2010

“የኦርቶዶክስ ፎቶ-ባንክ አገልግሎት” (Orthodox Photo Bank Service):- ማስታወቂያ


(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 19/2010)፦ “ደጀ ሰላም” የጀመረችውን የድረ ገጽ ጡመራ እና የመረጃ ልውውጥ የበለጠ በማጠናከር ለመቀጠል እንድትችል አንባብያንን የሚከተሉትን ነገሮች ይልኩላት ዘንድ በትህትና ትጋብዛለች።  በቤተ ክርስቲያናችን ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ መረጃዎች የምናገኝበት ጠንካራ ድረ ገጽ ስለሌለን በዚህ ቴክኖሎጂ ዘመን ከሌሎች እህት አብያተ ክርስቲያናት ጋር ሲነጻጸር ወደ ሁዋላ ቀርተናል ማለት ይቻላል። ስለዚህ ይህንን ክፍተት መሙላት እንዲቻል “ደጀ ሰላም” “የኦርቶዶክስ ፎቶ-ባንክ አገልግሎት” ((Orthodox Photo Bank Service) ትጀምራለች። “ፎቶ ባንክ” ያልነው ፎቶዎችና ቅዱሳት ሥዕላት የሚጠራቀሙበት “ግምጃ ቤት” ለማለት ነው።
ጥቅሙ ምንድር ነው?፦ አባቶቻችንን በስም ብቻ ሳይሆን በመልክም እናውቃቸዋለን፣ ቅዱሳት ቦታዎቻችንን እንመለከታቸዋለን፣ ታሪክ እናስቀራለን። ለምሳሌ በቅርቡ በእሳት የወደመው የመሐል ዘጌ ቅ/ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን አሁን የተረፈን ፎቶው ብቻ ነው። ፎቶ ባይኖረው ምን እንደሚመስል ላናውቀው እንችል ነበር። ስለዚህም ነው “ከአንድ ሺህ ቃላት፣ አንድ ፎቶ” የሚባለው።

ፎቶግራፎች፦ ፎቶዎቹ ቤተ ክርስቲያናችንን፣ ሃይማኖታችንን፣ በጠቅላላው ክርስቲያናዊት ኢትዮጵያን የተመለከቱ መሆን አለባቸው።
 1. የገዳማትና አድባራት ፎቶዎች፣
 2.  የአብያተ ክርስቲያናት ፎቶዎች፣
 3.  የብፁዓን አባቶች ጳጳሳት ፎቶዎች፣
 4. የካህናት አባቶች ፎቶዎች፣
 5. የቅዳሴና ሌሎች የጸሎት ላይ ፎቶዎች፣
 6. የበዓላት ፎቶዎች (መስቀል፣ ጥምቀት፣ ንግሥ፣ የገዳማት ጉዞዎች) ወዘተ
 7.  ቅዱሳት ሥዕላት (የእግዚአብሔር፣ የእመቤታችን፣ የሰማዕታት፣ ጻድቃን፣ ቅዱሳን፤ የመላእክት)
 
ማስገንዘቢያ፦
 • ፎቶዎቹ የእናንተ ከሆኑ የእናንተ መሆናቸውን፣ ካልሆኑ ደግሞ ምንጫቸውን ጥቀሱ፣
 • ምርጥ ፎቶዎችን በአሸናፊነት እናወጣለን፤
 • ፎቶዎቹ የሰዎች (ምሳሌ አባቶች)፣ የቦታ (ቅዱሳት መካናት)፣ የገዳማትና አድባራት እንዲሁም አብያተ ክርስቲያናት ከሆኑ ስማቸውንና የት አካባቢ እንደሚገኙ ግለፁ፣
 • ፎቶዎቹን በ  dejeselam@gmail.com  አድራሻ ላኩልን፣
 • ለመላክ ችግር ከገጠማችሁ ቴክኒካዊ ድጋፍ እናደርጋለን።
እግዚአብሔር ይርዳን።

Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)