April 13, 2010

ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ለሕክምና ግሪክ ናቸው


(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 13/2010)፦ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ በግሪክ አገር ሕክምና በመከታተል ላይ ናቸው። 

አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ በጀርባቸውና በእግራቸው ላይ የሚሰማቸውን ሕመም መፍትሔ ለማግኘት ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ግሪክ ያቀኑ ሲሆን በመከታተል ላይ ያሉት ሕክምና ከረዳቸው እንደ ጥንቱ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ ለማገልገል ይቻላቸዋል ማለት ነው።
ብፁዕነታቸው ገጠር ከተማ ሳይሉ፣ በእግርም፣ በፈረስም፣ በመኪናም እየተዘዋወሩ ምዕመኑን በማገልገል የሚታወቁ አረጋዊ አባት ሲሆኑ ከልጅነት እስከ ዕርግና ቤተ ክርስቲያናቸውን ያገለገሉና በምዕመናኑ ዘንድ የሚወደዱ አባት ናቸው። ባለፈው ዓመት በቤተ ክህነቱ በተነሣው የሕገ-ቤተ ክርስቲያን ይከበር ጥያቄ መኖሪያቸው ከተደበደበውና አደጋ ከተጣለባቸው ብፁዓን አባቶች መካከል አንደኛው መሆናቸው ይታወሳል። ያንን ወንጀል የፈፀሙት ሰዎች ማንነት ሳይጣራ እስካሁን ቆይቶ እነሆ July ዓመት ይሞላዋል ማለት ነው። ቤተ ክርስቲያኒቱም ማዕከሏ የሆነው ጠቅላይ ቤተ ክህነት ከተደፈረና ሕገ ወጦች በሯን ከፍተው ሊቃነ ጳጳሳቷ ላይ አደጋ ከቃጡ ዓመት ሞላ ማለት ነው።

የኒህ ተወዳጅ አባ ጤንነት ለቤተ ክርስቲያን ጤናማ አገልግሎት ወሳኝ ነው። “ሳረጅ የምጦርበት ንብረት ልሰብስብ፣ የማርፍበት ቪላ ልሥራ፣ ገንዘብ በባንክ ላደራጅ” ሳይሉ እንደ ሐዋርያት ሕይወታቸውን ለቤተ ክርስቲያናቸው ሰጥተው የኖሩ እንደዚህ ዓይነት አባቶች በዕድሜና በጤና ምክንያት ጉልበት ሲያንሳቸው የመንፈስ ልጆቻቸው ከጎናቸው ሊቆሙላቸው ይገባል። የግሪክ ምዕመናንም ይህንኑ እንደሚያደርጉ ምንም ጥርጥር አይኖረንም። ደጀ ሰላምም ለብፁዕነታቸው ጤንነትንና ረዥም ዕድሜን ትመኛለች።

ቸር ወሬ ያሰማን፣ አሜን

13 comments:

denberu said...

ብፁዕ አባታችን እግዚአብሔር ምህረቱን ይላክልዎ

Anonymous said...

ብፁዕ አባታችን እግዚአብሔር ምህረቱን ይላክልዎ

Anonymous said...

በግሪክ ያሉ ምዕመናን ብቻ ሳይሆን ሁላችንም የበረከቱ ተካፋዮች
እንድንሆን መንገዱ ቢመቻች?

Anonymous said...

እግዚአብሔር ምህረቱን ይላክልዎ አባታችን!

አባግንባር said...

ለአባታችን እግዚአብሔር ምህረቱን ይላክላቸው፡፡
እንደዚህ ዓይነት አባት ማለት እኮ ብዙ ሺህ መጽሐፍትን የሚወክሉ ናቸውና እስቲ የምንችለውን እናድርግ፡፡

tad said...

I love him and I am the first hand witness for his authentic Gosple spreading dedication.
May God have mercy on him.

Anonymous said...

እግዚአብሔር ምህረቱን ይላክልዎ አባታችን!

Tsigemariyam said...

ብፁዕ አባታችን የምህረት አምላክ ምህረቱን ይላክልዎት
ጽጌ ማርያም

Mengina said...

መዝሙር 57
ለመዘምራን አለቃ፤ አታጥፋ። ከሳኦል ፊት ሸሽቶ በዋሻ በነበረበት ጊዜ፤ የዳዊት ቅኔ።

1 ማረኝ፥ አቤቱ፥ ማረኝ፥ ነፍሴ አንተን ታምናለችና፤ ጉዳት እስክታልፍ ድረስ በክንፎችህ ጥላ እታመናለሁ።

2 ወደሚረዳኝ እግዚአብሔር ወደ ልዑል እግዚአብሔር እጮኻለሁ።

3 ከሰማይ ልኮ አዳነኝ፥ ለረገጡኝም ውርደትን ሰጣቸው፤ እግዚአብሔር ቸርነቱንና እውነቱን ላከ።

4 ነፍሴን ከአንበሶች መካከል አዳናት። ደንግጬ ተኛሁ፤ የሰው ልጆች ጥርሳቸው ጦርና ፍላጻ፥ አንደበታቸው የተሳለ ሾተል ነው።

5 አምላክ ሆይ፥ በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል፤ ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትሁን።

6 ለእግሮቼ ወጥመድን አዘጋጁ፥ ነፍሴንም አጐበጡአት፤ ጕድጓድ በፊቴ ቈፈሩ፥ በእርሱም ወደቁ።

7 ልቤ ጨካኝ ነው፥ አቤቱ፥ ልቤ ጨካኝ ነው፤ እቀኛለሁ፥ እዘምራለሁ።

8 ክብሬ ይነሣ፥ በገናና መሰንቆም ይነሡ፤ እኔም ማልጄ እነሣለሁ።

9 አቤቱ፥ በአሕዛብ ዘንድ አመሰግንሃለሁ፥ በወገኖችም ዘንድ እዘምርልሃለሁ፤

10 ምሕረትህ እስከ ሰማይ ድረስ ከፍ ብላለችና፥ እውነትህም እስከ ደመናት ድረስ።

11 አምላክ ሆይ፥ በሰማያት ላይ ከፍ ከፍ በል፤ ክብርህም በምድር ሁሉ ላይ ትሁን።

Anonymous said...

የቤተክርስቲያናች (ኢ.ኦ.ተ.ቤ.ክ) ንብረት የሆኑት ንዋየ ቅድሳት ማለትም ከበሮ፤ ጸናፅል፤መቋሚያና እንዲሁም የተለያዩ አልባሳት በመናፍቃንና በተኩላዎች መሰረቃቸው ወይም መዘረፋቸው ታውቋል። ስለዚህ እነዚህን ንብረቶች በመናፍቃን እጅ ያየ ሰው ለፖሊስ ጥቆማ ቢያደርግ ወሮታውን ከእውነተኛው አምላክ ይቀበላል።

በአንጻሩ ሲዘረፉ በቸልተኝነት የተማለከተ ቅጣቱን ይቀበላል።

እረ የህግ ያለህ ተዘረፍን ???

የማቴዎስ ወንጌል 7፥15
“የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።”

ወደ ሮሜ ሰዎች 16፥18
እንዲህ ያሉት ለገዛ ሆዳቸው እንጂ ለጌታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ አይገዙምና፥ በመልካምና በሚያቆላምጥ ንግግርም ተንኮል የሌለባቸውን ሰዎች ልብ ያታልላሉ።

ወደ ፊልጵስዩስ ሰዎች 3፥19
መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው።

http://www.ethiotube.net/video/8669/Yetsidiq-Tsehay-Ethiopian-Gospel-Singers

Maraki Zegondar said...

May God be on his side!

Maryisaq said...

Btsue Abatachin EGZIABHIER mihiratun yilakilwot.
I know Abune Qerlos B4 16 years @ the holly day celebration of Gena in St. Lalibela when he led an oridinary serk program( at the eve) there & he gave the chance to the so called Bahitawi-Aba kaidane mariam.At the time it was incredible 4 me & my friends b/c we had long experience of dispute b/n bishops &' bahitawian' in our locality.During that time we admired his politeness.Shortly he is one of the strong (spiritually)fathers of our Church.
May the SAVIOR of our world give him health in my account, may he extend his life 4 us

Anonymous said...

may God save our father . he is well known for performing of z whole heart service in z ethiopian orthodox church.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)