April 12, 2010

“የሲዲ ስብከት በነጻ”

ሰላም ደጀ ሰላሞች፤
አንዲት መልዕክት ነበረችኝ። ትናንት በዳግማዊ ትንሣዔው ወደ ዋሺንግተን ዲሲዋ የቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን የሄዱ ሰዎች ቅዳሴውን ጨርሰው ሲወጡ አንድ “ገጸ በረከት” ሲታደላቸው ነበር። ሥጦታው “የትምህርት ሲዲ” ሲሆን “ከኢትዮጵያ ዲ/ን በጋሻው ነው የላከላችሁ” እየተባለ በነጻ ይታደል ነበር። ጉዳዩን ቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር ይወቀው አይወቀው ግልጽ አይደለም። ከዐውደ ምሕረቱም ስለ ሲዲው የተባለ ነገር አልነበረም። ይኸው “ደህና” የሚለው የ/ን በጋሻው ስብከት ከአዲስ አበባ አቋርጦ በዲሲ ጎዳና በነጻ የሚሠራጭበት መንገድ ትንሽ ግር አሰኝቶኛል።
ከዚህ በፊት ደጀ ሰላም በተደጋጋሚና በሰፊው እንዳስነበበችን፣ በአንድ መጽሔትም ላይ “ስብከቶች የፕሮቴስታንት ቅላፄ እየያዙ” እየመጡ መሆናቸው እየተነገረ ባለበት በአሁኑ ወቅት ሲዲዎችን ወደ ውጭ እየላኩ “እወቁኝ” ማለቱ የጤና አልመሰለኝም።  እናንተስ ምን ትላላችሁ? ሌሎች ደጀ ሰላማውያንስ?

ወለተ ማርያም (ከዲሲ)
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)