April 11, 2010

የፍርኩታ ኪዳነ ምሕረት ገዳምን ለመታደግ የዕርዳታ ጥሪ ቀረበ

(Mahibere Kidusan) በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት መንዝ ጌራ ምድር ወረዳ የምትገኘውን የፍርኩታ ጽርሐ አርያም መንበረ መንግሥት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ጥንታዊት ገዳምን ለመታደግ የዕርዳታ ጥሪ ቀረበ፡፡ ገዳሟን ለማደስ የተቋቋመው ዐቢይ ኮሚቴ ለስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ የላከው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ ገዳሟ ከተመሠረተችበት 1450 ዓ.ም ጀምሮ  እስከ ዐፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ድረስ ትተዳደረበት የነበረ የራሷ መሬት ነበራት፡፡

ይሁንና ገቢ ይገኝበት የነበረው መሬት በደርግ ዘመን በመወረሱ በገዳሙ ያገለግሉ የነበሩ መነኮሳት በችግር ምክንያት ገዳሙን ጥለው በመውጣታቸው ገዳሟ ተዘግታ ቆይታለች፡፡ እንደዚሁም ትታወቅበት የነበረው የመጻሕፍት፣ የዜማና ቅኔ ተማሪዎች በዚሁ ችግር ምክንያት ሊበተኑ መቻላቸውን የገዳሙ ታሪክ ያስረዳል፡፡

በመሆኑም ስለሃይማኖታቸውና ስለ ታሪክ የተቆረቆሩ የቤተክርስቲያን ልጆች ተሰባስበው ተዘግታ የቆየችውን ጥንታዊት ገዳም ለማደስና ወደነበረችበት የገዳምነት ሥርዐት ለመመለስ ኮሚቴው አቋቁመው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ፡፡

መረጃው እንደሚያመለክተው፤ ኮሚቴው ሊሠራ ካሰባቸው የልማት ሥራዎች መካከል የአብነት ትምህርት ቤት መክፈት፣ ዘመናዊ ቤተመጻሕፍት፣ የስብሰባና የስብከተ ወንጌል ትምህርት መስጫ አዳራሽ መገንባት ናቸው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም ለገዳሟ የገቢ ማስገኛ የንብ ማነብ፣ የወፍጮና የዳቦ ቤት ሥራ ፕሮጀክት ማከናወን ይገኙበታል፡፡

ለዚህ የተቀደሰ ዓላማ ሕዝበ ክርስቲያኑ በዕውቀት፣ በገንዘብ፣ በጉልበትና በቁሳቁስ ድጋፍ እንዲያደርግ ዐቢይ ኮሚቴው በቅድስት ኪዳነ ምሕረት ስም ይጠይቃል፡፡

ጥንታዊቷ የፍርኩታ ጽርሐ አርያም መንበረ መንግሥት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ገዳም ከኢትዮጵያና ከውጭው ዓለም ቅዱሳን አባቶች ወደ ገዳሟ በመጉረፍ በምንኩስና በጾም በጸሎት ተወስነው ኖረውባታል፡፡

ከነዚህም ቅዱሳን አባቶች መካከል ግብጻዊው አባ እጨጌ ዮሐንስ ከሰማይ የወረደውን መስቀል ይዘው የኢትዮጵያን ምድር ለአምስት ዓመታት ያህል በመዘዋወር አምልኮ ጣኦትን ሲዋጉና ክርስትናን ሲያስፋፉ ቆይተው ለሃምሳ ዓመታት በዚችው ገዳም ጾም ጸሎት በማድረግ እንደኖሩ መረጃው ጠቁሞ ሲያርፉም የተቀበሩበትን ቦታ አፈር በመውሰድ በርካታ ሕሙማንን እየተፈወሱ ይገኛሉ፡፡

ገዳሟን እንደ ኢትዮጵያዊው ጻድቅ ሰማዕት ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ ያሉ ታላላቅ አባቶች እንዳስተዳደሯት ኮሚቴው ለዝግጅት ክፍሉ የላከው መረጃ ያመለክታል፡

2 comments:

Dagnu said...

This is a great movement forword pls lets know the body to contact for assisting the action. Mehabere Kidusan you should know that you are the right God prepared peaople to do this kind of works . Dont be dicouraged by the works of enemies(devils) pls you should know that people will be by your side whatever good things you do to save the charch. and its identity. Go for!

Kedane Miheret Tirdachu!

አሐዱ said...

ቅድስት ድንግል ማርያም ባወጣነው ትተካልን ያለንን ከመተባበር ወደኋላ አንበል የመዳኛችንን መንገድ ያበዛልን እግዚአብሔር ይመስገን በቅዱሳን ስም እንኳን መታሰቢያ ቤተከርስቲያን ያሰራ ይቅርና ቀዝቃዛ ውሃ የሰጠ ታላቅ ዋጋ አለውና ለበረከት እንትጋ

አሐዱ

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)