April 1, 2010

በሊቢያ በኩል ጣሊያን ስለሚገቡ ኦርቶዶክሳውያን ስደተኞች እውነተኛ ታሪክ (ክፍል 2)


(በፈቃዱ ንጉሴ ዓለሙ)
... ከፕሮግራም በኋላ በባህር የመጡትን ወንድሞችና እህቶች ማነጋገር ፈልጌ አንዲት እህትን ጠየኳት እሷም በባህር ከመጡ ልጆች ጋር አገናኘችኝ። በርግጥ ብዙ ቢሆኑም ከብዙ 4 ብቻ ለማቅረብ ወደድሁኝ። አንብቡት፡- የመጀመሪያዋን እህት እነሆ::

"ሰፈሬ አውቶብስ ተራ አባቢ ነው። ከልጅነቴ ጀምሮ ማለትም ከ4-16 ዓመቴ በዲሱ ሚካኤል አገልግያለሁኝ።ከቤተሰቦቼ ጠፍቼ ነው የመጣሁት ምክያቱም አባቴ በጣም ሃይለኛ ነበርና። ከቤት እንድንወጣ በጭራሽ አይፈቅድልንም ነበር።
በሱዳን በኩል ወደ ውጭ መውጣት እንደሚቻል ከእህቴ ጋር ስለሰማን ከቤተሰባችን ተለይተን ለመጥፋት ወሰንን። በመተማ በኩላ በዛ ሱዳን ገባሁኝ። አባቴ ሱዳን መሆናችንን ሲሰማ ተቆጣ ባስቸይ እንድንመጣም አዘዘን። አባቴ በጭራሽ ፈቃደኛ ሊሆን አልቻለም።በርግጥ እኔ መመለስ ፈልጌ ነበር እህቴ ግን መሄድ እንዳለብን ስለነገረችን ተያይዘን ለመሄድ ወሰንን። ሱዳን ያሉ ወጣቶች የተጨመለለቀ ሕይወት ነው ያላቸው ምኑን እንደምነግርህ አላውቅም....። ብር አልቆብን ነበርና ከኢትዮያ ብር እስኪመጣልን ሱዳን 4 ቀን ተቀመጥን ከዚያም በኋላ ለደላላው የጠየቀው ብር ተከፍሎት ከሱዳን ወደ ሊቢያ ትርፓሊ በፒካፕ መኪና ሐራ በረሃን እያረጥን ጉዛችንን ቀጠልን በአጠቃላይ ቀኑን ሙሉ ስንጓዝ ቆይተን በ4ኛው ቀን በሰላም ገባን።
ሊቢያ ውስጥ 7 ወር ከቆየን በኋላ ወደ ጣሊያን በጀልባ ለመምጣት ወሰንን ግን በአንድ ጀልባ መሄድ እንደሌለብን ከ እህቴ ተስማምተን በተለያየ ጀልባ ጉዞችንን ለመቀጠል ከደላላሎች ጋር ተነጋገርን። እኔ ባለሁበት ጀልባ 35 ሰዎችን አሳፍሮ ነበር በጣም አስፈሪ ነበር። በሉ - ልነግርህ አልችልም ዋናው ነገር ደግሞ ጀልባችን ጊዜያዊ ሆና ነው የምትሰራው ይህ ማለት አንድ ጀልባ ሊኖራት የሚገባውን ነገር አላላችም በዚያ ላይ ጥቅጥቅ ብለን ነው የተቀመጥነው። ቀን 4 ሰዓት ላይ የተፈራው ማዕበል መጣ ማዕበሉ እጅግ አስፈሪ ነው በግምት እስከ አንድ ሜትር ድረስ ይሆናል ጀልባችንን ከዚህ ሲላት ወደ ጎን ትዋልላለች ግሞ ይመልሳትና ዘጭ ትላለች። በ እያንዳንዱ እንቅስቃሴ ልናችን በጣም ይመታ ነበር ከአሁን አሁን ምን ተፈጠር እያልክ ነው የምትቆየው "የመከራ ሌሊት አይነጋም" እንደሚባለው መድራሻችን ሩቅ ሆነብኝ። ከ4 ሰዓታት በኋላ ማዕበሉ አቆመልን ሁሉም ተመስገን አምላኬ ማለት ጀመረ። ከዚህ አስቸጋሪ ጉዞ በኋላ ሐምሌ 16 ጣሊያን ውስጥ ገባን። እህቴ ግን ተይዛ ተመልሳ ሊቢያ እስርቤት ገባች። የሊቢያ እስር ቤት በጣም አስቀያሚ ነው። በጣም ትታመም ነበር። አሁን ግን ጣሊያን መጥታለች ግን በእስር ቤቱ ምክያት አጠቃላይ ብዙ ጤና የላትም እንደውም በሚቀጥለው ዓመት እንጦጦ ኪዳነምህረት እንድትጸበል እያሰብኩኝ ነው አለችኝ።" እግዚአብሔር ይማርልሽ አልኳት። አሜን አለችኝ።

No comments:

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)