April 30, 2010

ቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ሥራ አስኪያጅ እና ፀሐፊውን መረጠ


(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 30/2010)፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በዓመት ሁለት ጊዜ ከሚያደርገው ስብሰባ ሁለተኛውን ዓመታዊ ጉባኤ በማካሄድ ብፁዕ አቡነ ፊሊጶስን የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ ብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤልን ደግሞ የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ አድርጎ መሰየሙ ታውቋል፡፡

በትንሣኤ 25ኛ ቀን በዋለው ርክበ ካህናት የተጀመረው ሁለተኛው ዓመታዊ ጉባኤ፣ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ  መሪነት፤ ከአገር ውስጥና ከውጭ ሀገራት በሚመጡ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ተሳታፊነት የሚካሔድ ሲሆን፤ በጉባኤው የቤተ ክርስቲያኗ የልማት ተግባሮች የሚተረጐሙበትና የተከናወኑትም የሚገመገሙበት እንደሚሆን ከጽሕፈት ቤቱ ያገኘውን መረጃ ጠቅሶ ሪፖርተር ጋዜጣ ረቡዕ ዕለት ዘግቦ ነበር፡፡

April 29, 2010

በሦስት ቋንቋዎች የተዘጋጀ “ዘመናዊ አማርኛ ቋንቋ ለልጆች ማስተማሪያ ዲቪዲ" በለንደን ሊመረቅ ነው


(ደጀ ሰላም፣ ኤፕሪል 28/2010)፦ በሦስት ቋንቋዎች የተዘጋጀ “ዘመናዊ አማርኛ ቋንቋ ለልጆች ማስተማሪያ” ዲቪዲ በለንደን እንደሚመረቅ የሥራው አዘጋጅ ኢንጂነር በላቸው ጨከነ በተለይ ለደጀ ሰላም በላኩት መግለጫ አስታወቁ። 
በተለያየ ዓለም ለተወለዱ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያን ለዘመኑ በሚመጥን መልኩ ይህን ፊደል እና ቋንቋ ለመማር በቂ መርጃ እንደሚሆን የተነገረለት ይህ ዝግጅት በመላው ዓለም ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን  እና ትውለደ ኢትዮጵያውያን  የአማርኛ ቋንቋ እና የኢትዮጵያውያን  ልዩ ታሪክ ለማስተማር እንደሚረዳ ተጠቁሟል።

April 26, 2010

የቤተ ክርስቲያን ቅን መሪ ቅዱስነታቸው አባ ሽኖዳ ስለምን አለቀሱ?


(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 26/2010)፦ ቅዱስነታቸው ፖፕ ሽኖዳ 3ኛ 117ኛው የግብጽ ኮፕት ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ናቸው። እንደተለመደው ከምእመናን ለሚቀርብላቸው ጥያቄ የሚመልሱበት የተለያየ ዝግጅት አላቸው። ከዝግጅቶቻቸው መካከል በየሳምንቱ በካይሮ በመንበረ ማርቆስ የሚያደርጉት አንዱ ነው። እነዚህን የምእመናን ጥያቄዎች So Many Years With The Problems Of People” በሚል ርዕስ እየታተሙ ለንባብ በቅተዋል። ጥያቄዎቹ ዶግማን፣ ሥርዓትን፣ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደርን የተመለከቱ ሊሆኑ ይችላሉ። በእጄ ገብተው ያነበብኳቸው እነዚህ መጻሕፍት ላይ እንደተመለከትኩት ከሆነ መልሶቻቸው የማያወላዱ፣ በአጭር አባባል ብዙ መልስ የሚሰጡ ናቸው። በቅርቡ ለተጠየቁት አንድ ጥያቄ ግን በቃላት መልስ ከመስጠት ይልቅ በእንባና በዝምታ መመለስን መርጠዋል። ከንግግራቸው በአጭሩ እንመልከት።

April 23, 2010

ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ሕክምና ላይ ናቸው፣ ታይላንድ

(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 23/2010)፦ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ታመው ባንኮክ ታይላንድ ሕክምና በመከታተል ላይ ናቸው። የጉራጌ፣ ሀድያና ስልጢ አህጉረ ስብከት ሊቀጳጳስ የሆኑት ብፁዕነታቸው በታታሪነታቸው ከሚመሰገኑ አበው መካከል አንዱ ሲሆኑ ባለፈው ዓመት በቤተ ክህነቱ በተነሣው የሕገ-ቤተ ክርስቲያን ይከበር ጥያቄ ሐምሌ 8 ቀን 2001 ዓ.ም መኖሪያቸው ከተደበደበውና አደጋ ከተጣለባቸው ብፁዓን አባቶች መካከል አንደኛው መሆናቸው ይታወሳል።

ያንን ወንጀል የፈፀሙት ሰዎች ማንነት ሳይጣራ እስካሁን ቆይቶ እነሆ ሐምሌ 2002 ዓ.ም ሲመጣ ዓመት ይሞላዋል ማለት ነው። ቤተ ክርስቲያኒቱም ማዕከሏ የሆነው ጠቅላይ ቤተ ክህነት ከተደፈረና ሕገ ወጦች በሯን ከፍተው ሊቃነ ጳጳሳቷ ላይ አደጋ ከቃጡ ዓመት ሞላ ማለት ነው።

April 19, 2010

“የኦርቶዶክስ ፎቶ-ባንክ አገልግሎት” (Orthodox Photo Bank Service):- ማስታወቂያ


(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 19/2010)፦ “ደጀ ሰላም” የጀመረችውን የድረ ገጽ ጡመራ እና የመረጃ ልውውጥ የበለጠ በማጠናከር ለመቀጠል እንድትችል አንባብያንን የሚከተሉትን ነገሮች ይልኩላት ዘንድ በትህትና ትጋብዛለች።  በቤተ ክርስቲያናችን ስለ ቤተ ክርስቲያናችን ወቅታዊ መረጃዎች የምናገኝበት ጠንካራ ድረ ገጽ ስለሌለን በዚህ ቴክኖሎጂ ዘመን ከሌሎች እህት አብያተ ክርስቲያናት ጋር ሲነጻጸር ወደ ሁዋላ ቀርተናል ማለት ይቻላል። ስለዚህ ይህንን ክፍተት መሙላት እንዲቻል “ደጀ ሰላም” “የኦርቶዶክስ ፎቶ-ባንክ አገልግሎት” ((Orthodox Photo Bank Service) ትጀምራለች። “ፎቶ ባንክ” ያልነው ፎቶዎችና ቅዱሳት ሥዕላት የሚጠራቀሙበት “ግምጃ ቤት” ለማለት ነው።

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ መምህር “በበጋሻው ሥራዎች ላይ ጥናት እያደረኩ ነው” አሉ

(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 18/2010)፦ በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ መምህር እና የጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የስብከተ ወንጌል መምሪያ ኃላፊ የሆኑት ዶ/ር አባ ኃ/ማርያም “አርማጌዶን” የሚለው የስብከት ሲዲን ተከትሎ በተነሣው የዲ/ን በጋሻው ደሳለኝ ሃይማኖታዊ “ሥራዎች” ዙሪያ ጥናት እንደሚያደርጉ መገለፁን “ያኔት” መጽሔት በሚያዚያ 2002 ዓ.ም እትሙ ዘግቧል። ይህ የተገለጸው ዲ/ን በጋሻው ከቅዱስ ፓትርያርኩ እና ከብፁዓን አባቶች ፊት በቀረበበት ወቅት ነው።

April 13, 2010

ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ ለሕክምና ግሪክ ናቸው


(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 13/2010)፦ የሰሜን ወሎ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የሆኑት ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ በግሪክ አገር ሕክምና በመከታተል ላይ ናቸው። 

አረጋዊው አባት ብፁዕ አቡነ ቄርሎስ በጀርባቸውና በእግራቸው ላይ የሚሰማቸውን ሕመም መፍትሔ ለማግኘት ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ግሪክ ያቀኑ ሲሆን በመከታተል ላይ ያሉት ሕክምና ከረዳቸው እንደ ጥንቱ ከቦታ ቦታ እየተዘዋወሩ ለማገልገል ይቻላቸዋል ማለት ነው።

April 12, 2010

“የሲዲ ስብከት በነጻ”

ሰላም ደጀ ሰላሞች፤
አንዲት መልዕክት ነበረችኝ። ትናንት በዳግማዊ ትንሣዔው ወደ ዋሺንግተን ዲሲዋ የቅ/ማርያም ቤተ ክርስቲያን የሄዱ ሰዎች ቅዳሴውን ጨርሰው ሲወጡ አንድ “ገጸ በረከት” ሲታደላቸው ነበር። ሥጦታው “የትምህርት ሲዲ” ሲሆን “ከኢትዮጵያ ዲ/ን በጋሻው ነው የላከላችሁ” እየተባለ በነጻ ይታደል ነበር። ጉዳዩን ቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር ይወቀው አይወቀው ግልጽ አይደለም። ከዐውደ ምሕረቱም ስለ ሲዲው የተባለ ነገር አልነበረም። ይኸው “ደህና” የሚለው የ/ን በጋሻው ስብከት ከአዲስ አበባ አቋርጦ በዲሲ ጎዳና በነጻ የሚሠራጭበት መንገድ ትንሽ ግር አሰኝቶኛል።

April 11, 2010

በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤት ተከበረ

(Mahibere Kidusan) ደቡብ አፍሪካ በሚገኙ ምእመናን በሦስት ነጥብ ስድስት /3 ነጥብ 6 ሚሊዮን ራንድ/ ተገዝቶ ለቤተ ክርስቲያን አገልግሎት በሚያመች መልኩ የተሠራው የፕሪቶሪያ ሐመረ ኖኅ ቅድስት ኪዳነ ምሕረትና ቅዱስ ዑራኤል ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤተ ተከበረ፡፡ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የደቡብና ምዕራብ አፍሪካ ሀገረ ስብከት ፕሪቶሪያ የሚገኘው ይኸው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴ ቤቱ ጥር 16 ቀን 2002 ዓ.ም. በተከበረበት ወቅት

ጥንታዊው የሌመን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በአደጋ ላይ ነው

(Mahibere Kidusan)  
በሰሜን ሸዋ ሰላሌ ሀገረ ስብከት ደገም ወረዳ የሚገኘውና በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ያሠሩት የሌመን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን በእርጅና ምክንያት በመፈራረስ ላይ ይገኛል፡፡  በ13ኛው መቶ ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ጻድቁ አቡነ ተክለሃይማኖት ስብከተ ወንጌልን ለማስፋፉት ሲዘዋወሩ ካሠሩአቸው አብያተ ክርስቲያናት መካከል አንዱ የሌመን ቅድስት ሥላሴ ቤተክርስቲያን መሆኑን ከሥፍራው ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የፍርኩታ ኪዳነ ምሕረት ገዳምን ለመታደግ የዕርዳታ ጥሪ ቀረበ

(Mahibere Kidusan) በሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት መንዝ ጌራ ምድር ወረዳ የምትገኘውን የፍርኩታ ጽርሐ አርያም መንበረ መንግሥት ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ጥንታዊት ገዳምን ለመታደግ የዕርዳታ ጥሪ ቀረበ፡፡ ገዳሟን ለማደስ የተቋቋመው ዐቢይ ኮሚቴ ለስምዐ ጽድቅ ጋዜጣ የላከው መረጃ እንደሚያመለክተው፤ ገዳሟ ከተመሠረተችበት 1450 ዓ.ም ጀምሮ  እስከ ዐፄ ኃይለሥላሴ ዘመነ መንግሥት ድረስ ትተዳደረበት የነበረ የራሷ መሬት ነበራት፡፡

April 9, 2010

እንኳን ለ“ዳግማዊ ትንሣኤ”ው ዋዜማ በደህና አደረሳችሁ


(ደጀ ሰላም፤ ኤፕሪል 9/2010)፦ ውድ ደጀ ሰላማውያን እንኳን ለዳግማዊ ትንሣኤው ዋዜማ በደህና አደረሳችሁ። ትንሣኤ በተለይም በእኛ በኦርቶዶክሳውያን ዘንድ በታላቅ ሁኔታ ነው የሚከበረው። ምዕራባውያን ግን ወደ ልደት (Christmas) ያደላሉ። የምሥራቅ ክርስቲያኖች (እኛ ኦሪየንታሎቹም ሆን ግሪኮቹ) ወደ ትንሣኤው አከባበር የበለጠ እናደላለን። ምክንያት? የክርስትና እምነት ከሌላው የምትለየው ሞትንና በመቃብር መበስበስን (ሙስና መቃብር) ደምስሶ በተነሣው ወልደ አብ ወልደ ማርያም የተመሰረተች ስለሆነች ነው። በበረት የተወለደው፣ በባሕረ ዮርዳኖስ የተጠመቀው፣ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን የገለጸው ጌታ እኩዮች አይሁድ እንደሰቀሉት ሞቶ ቢቀር ኖሮ የክርስትና ሃይማኖት ስም አጠራሩ በጠፋ ነበር።

April 4, 2010

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን/ ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሳ/ Khristós Anésti! Alithós

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን ... በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሠሮ ለሰይጣን ....................... አግዓዞ ለአዳም
ሰላም........................................... እምይእዜሰ
ኮነ ..................................... ፍስሐ ወሰላም::
ክርስቶስ ከሙታን ተለይቶ ተነሳ ........ በታላቅ ኃይልና ሥልጣን
ሰይጣንን አሰረው ................ አዳምን ነጻ አወጣው
ሰላም ................................... ከእንግዲህ
ሆነ ........................................ ደስታና ሰላም

April 1, 2010

በሊቢያ በኩል ጣሊያን ስለሚገቡ ኦርቶዶክሳውያን ስደተኞች እውነተኛ ታሪክ (ክፍል 2)


(በፈቃዱ ንጉሴ ዓለሙ)
... ከፕሮግራም በኋላ በባህር የመጡትን ወንድሞችና እህቶች ማነጋገር ፈልጌ አንዲት እህትን ጠየኳት እሷም በባህር ከመጡ ልጆች ጋር አገናኘችኝ። በርግጥ ብዙ ቢሆኑም ከብዙ 4 ብቻ ለማቅረብ ወደድሁኝ። አንብቡት፡- የመጀመሪያዋን እህት እነሆ::

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)