March 28, 2010

"ዕንቁ" መጽሔት የደጀ ሰላምን ቃለ ምልልስ ምን ጭ ሳይጠቅስ አተመ


(ደጀ ሰላም፤ ማርች 28/2010)፦ "ዕንቁ" የተባለ አዲስ አበባ ውስጥ የሚታተም አንድ መጽሔት ዲ/ን ዳንኤል ክብረት ከደጀ ሰለማ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ እንደገና ሲያትም የደጀ ሰላምን ስም ሳያነሣ አልፎታል። በደፈናው “ዲ/ን ዳንኤል ቃለ ምልልስ ሰጥቷል” ብሎ ወደ ውይይቱ የገባው መጽሔቱ ደጀ ሰላም ያቀረበቻቸውን ጥያቄዎች ብቻ በማቅረብ፣ ማን ነው የጠየቀው የሚለው ሰርዞት አልፏል። መጽሔቱ  ለምን ይሄንን ለማድረግ እንደፈለገ ለጊዜው አላወቅንም።
እስካሁን እንዳየነው ጽሑፍ እየሰረቁ በማተም ብዙ ጊዜ የሚታሙት ከኢትዮጵያ ውጪ የሚታተሙ የአማርኛ መጽሔቶችና ጋዜጦች ነበሩ። ዛሬ ደግሞ በተገላቢጦሽ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚታተመው ዕንቁ መጽሔት የኮፒ ራይት መብትን ጥሶ ሥራችንን ወሰዶታል። መውሰዳቸው ባልከፋ፣ ያገኙበትን ግን ሊጠቅሱ ይገባ ነበር። አሁንም ለማስተካከል ይችላሉና እንዲያስቡበት እንመክራቸዋለን።

13 comments:

Anonymous said...

ya, they should at least write your name.

Melakeselam Gebreyesus said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሃዱ አምላክ አሜን።
ሀይማኖት ሲጎተቱ የሚጎተቱባት መንገድ አይደለችም

ይህንን ጽሁፍ ለመጻፍ ያነሳሳኝ አበይት ነገር ሰሞኑን እየተናፈሰ ለገበያ አገልግሎት እየተሰራጨ ያለው ወሬ አይሉት ዘገባ አደናጋሪ ክስተት ነው፡፡ በመሰረቱ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ “ከፍሬዎቻቸው ታውቋችዋላችሁ” ብሎ እንደነገረን የትኛው ፍሬ ከየትኛው ዛፍ እንደሆነ የዚህች ቅድስት እምነት ተከታዮች በትክክል እናውቃለን፡፡

ይህች ቅድስት እምነታችን በውዥንብርና በወሬ ወጀብ መሃል ስታልፍ ይህ የመጀመሪያው አይደለም የመጨረሻውም ይሆናል ተብሎ አይታሰብም፡፡ አይደለም ዛሬ እጅግ የምናከብራቸው የሀይማኖት አባቶች ቡድን ለይተው እርቅን ወዲያ ብለው የውስጥና የውጭ እየተባሉ አንዱ ተሳዳጅ ሌላው አሳዳጅ ሆነው ያለፉበትን መንገድ እድሜ ሰጥቶን ተመልክተናል፡፡ ከዚህም ባሻገር አሁን ቅድስት ቤተክርስትያናችንን እየመሩ ካሉት አባቶች መሃከል በመናፍቅነት የተወገዙ ስማቸው ጎድፎ “ከዲቁና እስከጵጵስና በክህደት ጎዳና” ተብለው በቤተክርስትያኒቱ ማተሚያ ቤት በወጣ ጋዜጣና መጽሄት መተቸታቸው የቅርብ ግዜ ትዝታ ነው፡፡

እና ዛሬ በእዚህ ሁለት “ሰባክያነ ወንጌል” መሃከል የተነሳው ቅራኔ በቤተክርስትያኒቱ ላይ የሚስከትለው ቅንጣት ታህል ተጽእኖ እንደሌለው ሁሉም የቤተክርስትያኒቱ ልጆች የሚረዱት ሀቅ ነው፡፡ “ወንጌል” ዛሬ የኑሮ መደጎሚያ አንድ የስራ ዘርፍ የንግድ መስክ ከመሆኑ አስቀድሞ እነ ፓፓ ሊዮንም የመንግስተ ሰማያት መግቢያ ቲኬት እየቸበቸቡ እንደከበሩ ታሪክ የሚነግረን እውነታ ነው፡፡

እውነት ነው ወንጌል ሲሰሟት ትጣፍጣለች፡፡ ልብን ታረሰርሳለች፡፡ ዓለምን አስረስታ የዘላለምን ሕይወት ታሳስባለች፡፡ ሀጢያትን አስትታ ወደ ጽድቅ መንገድ ትወስዳለች፡፡ ወደንስሃ ትጠራለች፡፡ እናም ይህችን ድንቅ ወንጌል እንዲሰብኳት እንዲናገሯት እና እንዲያስተምሯት አስቀድሞ የተጠሩ ኣባቶች አይደለም እንደዛሬ “ሰባክያን” በገንዘብና በጥቅም ሊለውጧት ቀርቶ፤ እንዲሁ በነፃ ለህዝቡ ሁሉ ከዓለም ጫፍ እስከ ዓለም ዳርቻ እንያደርሷት ነበር ትዕዛዙ፡፡ ከዚህም ባሻገር ወንጌልን ለዓለም እንዲያደርሱ የታዘዙት ቀደምት ንጹሃን አባቶች ቅያሬ ልብስ ስንቅና ብትር ጫማና ምንጣፍ አልነበራቸውም፡፡ እንዲይዙም አልተነገራቸውም፡፡

ታዲያ ዛሬ “ወንጌልን” እንደ ገቢምንጭ አድርገው እየሸቀጧት ያሉት ከዛም በጥቅም የተነሳ አንተመናፍቅ ነህ ያንተ ስብከት ህጸጽ አለበት እያሉ የሚራኮቱት ወገኖች ከመስመር የወጡና ተዉ ሊባሉ የሚገባ ይመስለናል፡፡ ይልቅ ጸጋውና ብቃቱ መጠራቱም አለን ካሉ በነፃ ያገኙትን ወንጌል በነፃ ያድሉን እንጂ ፤ በነጻ በተገኘች ወንጌል ላይ የጥቅም ግጭት አንስተው ባይጣሉ መልካም ነው፡፡ እኛን የሚስበን እኛን የሚማርከን እኛን የሚጎትተን የቅድስት ንጽህት የተዋህዶ እምነታችን ትምህርት እንጂ በድምጽ ማማር ወይንም በጥቅም በመቆርቆር የተፈጠረ አጉል ስብከት አይደለም፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ እንዳስተማረን ቅድስት እምነታችን በፍቅር የምትሰራ በፍቅር ሀይማኖት እንጂ በነቀፋና በጥላቻ የምትጎትት እምነት አይደለችም፡፡ እኛም የተዋህዶ እምነት ተከታዮች ማንም በስብከቱ ሲጎትተን የምንጎተት ሳይሆን በፍቅርና በይቅርታ ተስበን በቅድስት እምነታችን ጸንተን ዘላለማዊ ህይወትን ለመውረስ ያብቃን፡፡ ለሁላችንም የምነስተውልበት ልቡና ያድለን፡፡
ወስብሀት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር፡፡ አሜን፡፡

መላከ ሰላም ገብረ ኢየሱስ
ከሀገረ አየርላንድ

red said...

Dear Editor of ENQU, I think it is not delibrate mistake, how ever you should rectify this ASAP because DS deservs this, I do remember how you were yelling when your megazine is hijacked by the goverment for Tedy Afro's news case.

dani said...

እኔ እንደሚመስለኝ እንቁ መጽሔት ይሄን ያደረገው በቸልተኝነት አይመስለኝም::ሆን ብሎ ደጀ ሰላምን ለማበሳጨት የተደረገ ነገር ነው:: ከደጀ ሰላም ጋር ሰጣ ገባ ውስጥ በመግባት ለመታወቅ የፈለገ ይመስላል:: ይሄ ደግሞ ከበጋሻው ደሳለኝ የተማሩት ነገር ይመስለኛል:: በጋሻው ትልቅ ሰው ሰድቦ ለእውቅና እንደበቃ ሁሉ እንቁዎችም ደጀ ሰላምን አበሳጭቶ ለመታወቅ የፈለገ ይመስላል::ለማንኛውም ውጤቱን ወደፊት አብረን የምናየው ይሆናል::

Anonymous said...

Semonu semune himamat new! New! new neeeeew!

Anonymous said...

Wolete Mariam in Facebook:
Endemin alachihu deje selamoch.I like very much the conversation of you and Dn Danie kibret.I thank you very much for both of you.Egzabher rejim tenana Edme yistilin.I read ENQU and they have already write the source under the the page instead of writing on the begining of the coversation.That is their mistake.

But let us leave them such silly mistakes and let us take it positive.It is also good to write on their ENQU.So many people can read it and know the truth.

Bedigami Lehulachum Egzaber Yistilin

Anonymous said...

HIMAMATE MESKEL VIDEO LINK
http://www.ethiotube.net/video/8308/ETHIOPIAN-ORTHODOX-TEWAHEDO-HEMAMATE-MESKEL

Anonymous said...

please leave D.danel alone he is yezemenachin hawareyaw pawlos.

Anonymous said...

Dan'el Kibret mean "Mirt Eka" Just Like that "Hawariyaw Kidus Phawulos" ok [[Telat Yafral Gena!!!!!]]

Anonymous said...

ዲ. ዳንኤል ስራህን ፈጣሪ ድንግል ማርያም ትባርክህ! ስለ ጲላጦስ ስለጻፍከው ጽሁፍ
አንተ እርሱን አሳልፈው ቢሰጡት ባይሰጡት ምን አሳሰበህ እንኳን ድንግልን ተዉልህ እንጂ። እድሜ ለድንግል እጅህን ይዛ ወደገነት ታስገባሃለች። ብቻ እርሷ ላይ ያለህን እምነት አጠንክር እንጂ።እርስዋን አምኖ ማን አፈረ?አሁንም በርታ አይዞህ ኢየሱስ ጌታየ አምላኬ መድሃኒቴ የሚሉ ብዙ ሰዎች በተዋህዶ ውስጥ አሉና እነርሱን አሁኑኑ በህይዎት እያሉ ነው ማባረር ያለብህ።

Ehete micheal said...

Selam deje selamwoch
I read about this artice so what is wrong to post the interview? Like you hiding from peoples in cyber "ENQU" magazine did the same thing so in my view it doesnt matter who ever do that as far as it doesn't change the words & meaning as well.I am thinking like cristine/ postive/ don't take it negative way please.
God bless us Amen.
Ehete micheal

አግናጢዎስ ዘጋስጫ said...

ቢገባው ወንጌሉ


በደጀ ሰላም መስኮት ሁሌ ብቅ እያለ:
ሃሰት የሚዘራ አንድ አንድ ሰውዬ አለ:
እጠራጠራለሁ ስለርሱ ህሊና :
መልካሙን ከመጥፎ ከቶ አለየምና:
እውነትን መንጥረው ለህዝብ ባሳወቁ:
ወጣቱን ከተኩላ ነቅተው በጠበቁ
"ሰይጣኖች "እያለ እንድህ መሳደቡ:
አእምሮ ጎድሎታል ወይ ታውሯል ልቡ:
ጠላትን ውደዱ ቀድሞ እንደተባለ:
ማንም ይወደ ዋል በተዋህዶ ያለ:
አንድ ወቅት ሲገባው የቆመበት ቦታ:
እርሱው ይመለሳል ጠይቆ ይቅርታ:
ግን እስከዚያ ድረስ ሳለ በህይወ ቱ:
እንደ ወጣ እንዳይቀር ጠፍቶ ከበረቱ:
የተዋህዶ ልጆች ጸልዩ በእውነቱ:
የቆመበት እምነት የትም አያደርስም:
አፈር ትቢያ ሆኗል መስራቹ ሉተርም:
ቢሳደብም ቅሉ አውሬው አፉን ከፍቶ:
የገሃነም ደጆች አይችሏትም ከቶ:
ብላችሁ ንገሩት ለዚያ ለወንድሜ :
ቢገባው ወንጌሉ ቢያስተምረው እድሜ::

Anonymous said...

d/c Daneal keberet ,Yezemnachen kidus paulos ... kekkkkkkk!!! are you .......

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)