February 24, 2010

ስለ ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ የቀብር ሥፍራ የአንባብያን ድምጽ (Poll)

(ደጀ ሰላም፤ የካቲት 16/2002 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 23/2010)፦ የብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስን እረፍት ከሰማንበት ጊዜ ጀምሮ እርሳቸውን የተመለከቱ የተለያዩ ዜናዎች ስናስነብብ መቆየታችን ይተዋሳል። የቀብር ሥፍራቸውን በተመለከተ “ቅዱስ ሲኖዶስ የብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስን ውግዘት አንስቶ ሥርዓተ ቀብራቸው በኢትዮጵያ እንዲፈጸም፣ አስከሬናቸውም ለጵጵስናቸው በሚገባ ክብር፣ አበው ጳጳሳት በሚያርፉበት በመ/ፀ/ቅ/ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን እንዲያርፍ ወስኗል። በዚሁ በአሜሪካን አገር እንዲቀበሩ የሚፈልጉም አሉ። እርስዎስ በየት እንዲፈጸም ይመርጣሉ?” በሚል ባዘጃነው የድምጽ መስጫ (ፖል) 518 ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 434ቱ (83%) አዲስ አበባ ቢቀመሩ እንደሚመርጡ ሲጠቁሙ፣ 84ቱ (16%) ደግሞ እዚሁ አሜሪካ እንዲቀበሩ እንደሚሹ መልስ ሰጥተዋል። መቸም ያለነው ነጋ ጠባ ፖል (Poll) በሚሰበሰብበት "በሰለጠነው ዓለም" ነውና በተለይም ውሳኔው በእጃቸው ያለ ወገኖች ይህንን ቁጥር ከግምት ያስገቡት ዘንድ እንጠቁማለን።

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)