February 15, 2010

“ቋሚ ሲኖዶስ” በብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ቀብር ጉዳይ ተነጋገረ

(ደጀ ሰላም፤ ፌብሩዋሪ 15/2010)፦ ባለፈው ቅዳሜ ፌብሩዋሪ 13/2010 ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስን አስመልክቶ “ቋሚ ሲኖዶስ” ዝግ ስብሰባ ማድረጉ ታወቀ። በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሰብሳቢነት ተደረገ በተባለው በዚህ ስብሰባ ቅዱስ ሲኖዶስ ከዚህ በፊት አስተላልፎት የነበረውን ውግዘት ለማንሣትና ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት አባት አስከሬንም በኢትዮጵያ እንዲቀበር እንዲፈቀድ ከስምምነት ተደርሷል ተብሏል። ውሳኔው ግን ገና ይፋ አልተደረገም።

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በፓትርያርክ ሹመት ጳጳሳቱ ለሁለት ከተከፈሉ ወዲህ ልዩነቱ በውግዘት ሳይነጻ ቆይቶ በስደት በአሜሪካ የሚገኙት አባቶች ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ “ኤጲስ ቆጶሳትን” ሾምን ካሉ በኋላ ውግዘቱ እንደተከተለ ይታወሳል።

“ቋሚ ሲኖዶስ” በዚህ ትልቅ ርእሰ ጉዳይ ላይ መወያየቱ ብዙዎችን እንዳስደሰተ “ደጀ ሰላም” የተረዳች ሲሆን የብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ሥርዓተ ቀብር በጵጵስና ክብር ዞረው በተማሩባት፣ በክህነት በከበሩባት፣ ቀድሰው ባቆረቡባት በሀገራቸው በኢትዮጵያ የሚካሄድ ከሆነ ቤተ ክርስቲያኑ በቅርብ ጊዜ የገጠማት አስተዳደርና የመከፋፈል ድቀት መድኀኒት ያገኛል ተብሎ ተስፋ እንዲጣል ያደርጋል።

ይሁን እንጂ ይህ መቀራረብና የስምምነት ዳር-ዳርታ ሁሉንም ላያስደስት እንደሚችል “የደጀ ሰላም” ተንታኞች የጠቀሱ ሲሆን “መለያየቱ እንጀራ የሆናቸው ቡድኖች” በጉዳዩ አይደሰቱም፤ በዚህም ነገሩ እንዳይሳካ ሳንካ እንዲገጥም ያደርጋሉ ብለዋል።

በርግጥም ቋሚ ሲኖዶሱ በዚህ ጉዳይ ላይ ተነጋግሮ ከሆነ ቅዱስ ፓትርያርኩም ሆኑ የቋሚ ሲኖዶሱ አባላት የሆኑት ብፁዓን አባቶች መመስገን እንደሚገባቸው “ደጀ ሰላም” ታምናለች። በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከጊዜያዊ ግርግር ባሻገር ያለውን የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ለመመልከት መቻል ትልቅ ጥበብ ነው። ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ዛሬ ያሉበት ሁኔታ ሳይሆን የትናንት አገልግሎታቸው ሳይዘነጋ በክብር ለአገራቸው አፈር እንዲበቁ ማድረግ ይገባል። በውጪ የሚገኙ “የቅርብ ነን” የሚሉ በሙሉም የብፁዕነታቸው የመጨረሻ ማረፊያ ኢትዮጵያ እንዲሆን፣ በሚገባቸው ክብር እንዲሸኙ በማድረግ በኩል አዎንታዊ በሆነ መልኩ ይተባበራሉ ብለን እንጠብቃለን። ልዩነቱ ይብቃ!!!! ግንቡ ይፍረስ!!!

“ደጀ ሰላም”ም ጉዳዩን እየተከታተለች መዘገቧን እንደምትቀጥል እያስታወቀች፤ ስለ ጉዳዩ ያላችሁን አስተያት በድምጽ መልእክት በመተው ወይም እንደተለመደው በመጻፍ ሐሳባችሁን እንድትገልፁ ትጋብዛለች።

21 comments:

Anonymous said...

በእርግጥም ቁዋሚ ሲኖዶስም ሆነ በየሃገረ ስብከቱ ያሉ ብፁዓን አባቶን በብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ዕረፍት የተሰማቸውን ሃዘን በመግለጽ ሥርዓተ ቀብራቸው በላላቅ የሊቀ ጳጳስ ክብር እንዲከናወን ስምምነት ላይ መድረሳቸው ተሰምቷል። እግዚኣብሄር እንህን ታላቅ አባት ለሃገራቸው ክብር እንዲያበቃልን ፈቃዱ ይሁን።

መልአከ ሳሌም አባ ገብረኪዳን እጅጉ said...

ሰላም ደጀ ሰላማዉያን ቸር ወሬ ያሰማችሁ የብፁዕ አቡነ ዜና የመጨረሻ እረፍት ኢትዮጵያ ቢሆን የሁላችንም ትልቅ ደስታ ነዉ የኢትዮጵያ ኦ/ተ/ ቤተ/ ቅዱስ ሲኖዶስም ይህን ቢያደርግና የብፁዕነታቸዉን ቀብር በክብር ቢያስፈጽም ትልቅ የጥል ግድግዳ ይፈርሳል ለቤተ ከርስቲያናችንም በጣም ትልቅ የታሪክ ሂደትም ነዉ የተለያየዉን ሕዝባችንንም የሚያቀራርብ ይሆናል ይኽንን ለማደናቀፍ በመካከላችን እየገባ የሚፈታተንን ክፉ መንፈስ እግዚአብሔር ያርቅልን ያባታችንንም ክቡር አጽማቸዉ በረከትም ስለሆነ በቅድስት ሀገራችን ኢትዮጵያ ማረፉን ያሰማን የቀሩትንም አባቶቻችን ዕርቀ ሰላም ወርዶ በህይወተ ሥጋ ለሀገራቸዉ እንዲበቁ እግዚአብሔርን ሁላችንም አጥብቀን በጸሎት እንጠይቅ እባካችሁ እግዚኦ እግዚኦ እንበል የብፁዕነታቸዉን ነፍስ ይማርልን በረከታቸዉ ይድረሰን አሜን፡፡

21_21 said...

የተባለውን እውነት ያድርግልን:: እግዝአብሔር ምክንያት ይኖረው ይሆናል:: ቤተ ክርስቲያን በክርስቶስ ሞት አይደል የተጠቀመችው? አባቶችኮ ሞታቸውም ለበጎ ነው::

Anonymous said...

hopefully this news will be true. our father will be burried in his beloved country. God guide our fathers once again.

Anonymous said...

This is good news.May Lord JESUS CHRIST make the death of his holiness a reason for reconciliation beteween our fathers here and there;and may He make it be the renaissnce of our church.

Unknown said...

አባታችን ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ለብዙዎቻችን መንፈሣዊ አባት ነበሩ:: በቅርብም ላወቅናቸው ጸጋ የተሞላባቸው የምንወዳቸው ሐዋርያ ነበሩ:: በእረፍታቸው ልጅ አባቱ ሲለየው የሚሰማው ሃዘን ይሰማኛል:: "የጻድቅ ሞቱ በሰማይ በእግዚአብሔር ፊት ክቡር ነው" ክቡር የሚለው ብዙ/ሙሉ ትርጉሙን አይሰጠንም: በዕብራይስጥ የተደረሰው የሚቀርበው ትርጉም רַב עֵרֶך "Precious in the sight of the Lord is the death of his saints". ይህም ማለት አባት የሚወደው የብርቅ ልጁ ከውጭ ወደቤት ሲመጣ እንደሚያስደስተው የጻድቅ ሞቱም በእግዚአብሔር ፊት ብርቅ ነው::

የብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ማፈፍ ለኛ ሃዘብ ቢሆንም በእግዚአብሔር ፊት ብርቅ ነው::

ብዙዎች "የብፁዕነታቸው የመጨረሻ ማረፊያ ኢትዮጵያ እንዲሆን" የሚሉ አሉ:: ለአንድ የወንገል ሐዋርያ አገሩ የግድ የተወለደበት ቦታ አይደለም:: እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ጴጥሮስ ጳውሎስ እንድርያስ ቶማስ ማርቆስ እንዲሁም ብዙዎች እኔ ብፁዕነታቸው አንደ ብፁዕ አቡነ ይሥሓቅ በስደት ባገለግሉበ አጽማቸው ቢያርፍ የበለጠ ክብር ነው::

"በኢትዮጵያ እንዲቀበር እንዲፈቀድ ከስምምነት ተደርሷል" የሚባልው ግን
የዘገየ መንፈሳዊነቱ የሚያጠያይቅ እንዳይሆን እፈራለሁ::

በዚህ አጋጣሚ ግን ስልጣን ፖለቲካ ሳይሆን የይቅርታ ምዕራፍ ተክፍቶ
ያጠፋ ከጥፋት ተመልሶ ለቤተ ክርስቲያን ለወንጌል አገልግሎት በመቆም በኢትዮጵያም በየአህጉሩ የተበተነውን የእግዚአብሔር ሕዝብ ለማገልገል መስማማት የበለጠ ነው እላለሁ::

Anonymous said...

Hmmmm

Namrud said...

አቤት እግዚአብሔር ቸርነቱ በኚህ ታላቅ አባት ዕረፍት ምክንያት ያልተነጋገሩት አባቶቻችን ሊነጋገሩ ይሆን ? ዕረፍታቸውን ብለው ውግዘት አንስተው እዚህ ያሉ አባቶች ደግሞ አሰከሬን ለመሸኘት ቢሄዱ እና በዛው እርቀ ሰላም ቢወርድ እስቲ ጸልዩ ለእርሱ የሚሳነው ነገር የለም።

s.A said...

yeabatnet fikrwo
lezelalem belbie tento
yinoral man yawukal
yetadik motu lekirston
yerso erefet degimo lelilochi
mihiret liho yichilal
S.A CALIFORIA

Sememen said...

Egziabher endiet endemisera,alamawm zewetr girum newnna ye abbatachinin arefte zemen lebeggo yadriglin!!!Dinghil hoy! zewetr bemiljash attleyin!!!
Geta hoy!beqa belen,amen.

Anonymous said...

This the time to everybody to compromise differences and come together to the renaissance of Tewahedo.In the name of our LORD JESUS CHRIST I beg you all our fathers here in USA and in Ethiopia and the faithfuls of Tewahedo in general to put aside any misunderstandings and animosity, and unite at this moment of sadness of his physical separation from us and time of rejoice of his going to his eternal home of his holiness abune Zenamarkos.Please,please please lets unite;it is only then GOD forgive us.

Anonymous said...

Dan I am so sorry about you! you seems you know but you know nothing. Abatachen yagerachew afere yefelegachewal. He diserve all respect by his own ppl on his own country. ante endewetahe kere
We pray God will do it. poletikegnaa nehe

Godolias said...

TEMESGEN AMLAKACHIN YECHEKENEN LIB ARARTEH KIN YADERGIH SIMH YIKBER YIMESGEN.

Anonymous said...

It is a brand new day for me to visit this site,I m like yours positive opnion about our curch.Yes, you guys are right !He deserve to buried at home with a big respect.Once again ,thank you for your positive idea.I think all media should write this kind positive news about our curch.

dr. zeBelay said...

He was good father, but it is not important for us to send his body to ethiopia. it will be shame on us.

Anonymous said...

ብጹዕነታቸው የሚቀበሩት ሲያትል ነው፡፡ ስደተኛው ሲኖዶስ የት ይቀበሩ የሚለው ያሳሰበው አይመስለኝም፡፡ የቀብሩን ጉዳይ በማስመልከት አሰተባባሪዎች ስም በኢትዮ ሚዲያ ላይ ሳነብ ትንሽ ስጋት ሽው አለብኝ፡፡ የፖለቲካ ሽታ፡፡ እግዚብሔር ያጽነናን፡፡
የቀብሩን መርኃ ግብር http://www.st-gebriel.org/MemorialService.pdf መመልከት ይቻላል፡፡

Anonymous said...

Dan is categorized in the 'tikefafel enibla' group.

Unknown said...

you still talk about unity.It is good to hear that but exile syonde refused the agreemnt to send him home.

The goveremnt of America didnt allow to lay him inisede the chruch.

At this point x-syond is deafted!but christeans hope unity forver.

they must think twice before they held thet body as a hostage.

Anonymous said...

His grace should rest in his coutry where so many saints rested.Where is he going to be rested if not in or in the vicinity of a church? In a cemetery where gays,lesbians,and others,etc buried?No way!If this is done,those who have done it are not really christians.
I am an ardent critic of aba paulos and the so called exile synod, because both are WRONG on what they have done to our church in the eyes of GOD and the churche's canon.Yet,this kind of time is a great opportunity to put behind past actions and rewrite history anew.GOD will never forgive anybody or any side who spoils this time of His mercy up on our church,ourselves and our country.If we are not willing to compromise and forgive,we should not expect others to do it,and we have not any moral or religious right to blame others on any issue.
May the Almighty GOD give us all the spirit of unity and love.

Unknown said...

Betsu Abatachin Abune Zena Markos yeagerbetun kemenfes kidus yeteleye sigawi kiber bfelegy noro gena duro wedeagerachew memeles yechilu nebere. negergen lebetekrstian keberena netsanet silu besidet norewal. yeaba paulos pletikawi tselotefetehate kemedrawi dance yeteley balemehune menfesawi keber yemeyasgengn aydelemena gregeru kertobachew beselamena begeleltegna senesereat beagerachew (yale aba paulos poletikawi musika) bekeberu des yel nebere. Amlake kidusan erefte mengiste semayaten yestelen.

keringeremew

Anonymous said...

menamentewoch nachihu. meleyayetu beabatochi becha neber yemimeslegne gin ezih blog bemtadergut yibsal. yehulunem sera egziabher yawuqewal. ahun enante medrawiwun tenegageru enji, menfesawinetun tewut. bezih belog aderaregachihu enquan lemenfesawi negeger kebrun letebeqe medrawi negegerm atebequm. keafachihu yemiwotaw yedurye, yebalegie, yesdadeg ayinet new. egziabher biete krstiyanachinen kendezih ayinetochu tebqlen.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)