February 21, 2010

“አርማጌዶን” የስብከት ካሴት ስለ እርሱ እንደሚናገር ዲ/ን በጋሻው ተናገረ፤ የመልስ ቪሲዲ እያዘጋጀሁ ነው አለ

(ደጀ ሰላም፤ ፌብሩዋሪ 21/2010)፦ “አርማጌዶን” በሚል ርዕስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ እንቅስቃሴ በመዛመት ላይ መሆኑን በማስጠንቀቅ በተሰራጨው ሲዲ ውስጥ በቀጥታ ስም ተጠርቶም ባይሆን የተጠቀስኩት “እኔ ነኝ” ሲል ዲ/ን በጋሻው ደሳለኝ ለ”ሮያል” መጽሔት ተናገረ። በቂም በበቀል የተነሣሣው ዘመድኩን ለግል ጥቅሙ እንድሠራለት የጠየቀኝን ባለመቀበሌ ሊበቀለኝ ስለፈለገ እንዲህ አድርጓል ሲል የተናገረው በጋሻው ይህንን “ደረጃውን ያልጠበቀ” ያለውን ስብከት የሚቃወም “አውሬው ለምን ይቆጣል?” በሚል ርዕስ ቪሲዲ እያዘጋጀ መሆኑን ተናግሯል።

ቃለ ምልልሱን ያደረገው የ“ሮያል” መጽሔት ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹሩቤ (shurubew@yahoo.com) ዲ/ን በጋሻው ምን ያህል ታላቅ ሰው መሆኑን ለመግለጽ ቃላት ሲያጥሩት ቆይተው እርሱ ጋዜጠኛው ደግሞ ለአንባብያን ባለው ከፍተኛ ታዛዥነት ዲ/ን በጋሻውን ያህል ታላቅ ሰው አይወጡ ወጥቶ፣ አይወርዱ ወርዶ ቃለ ምልልስ እንዳደረገው ይገልጻል። በክህነት ዓለም ላሉ የቤተ ክርስቲያን ሰዎች ተደርጎ በማይታወቅ የቃላት ሙገሳ ጋጋታ የተጨናነቀው ይህ መጽሔት ከዚህ በፊትም (ልክ የዛሬ ዓመት በ2001 ዓ.ም) ዲ/ን በጋሻውን ቃለ ምልልስ አድርጎ እንደነበር ተጠቅሷል። መጽሔቱን በዋና ሥራ አስኪያጅነት የሚመራው መኮንን ደሳለኝ የዲ/ን በጋሻው ወንድም እንደሆነ ይነገራል።

51 comments:

SendekAlama said...

ባዕዳን ሰዎችም ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ገብተዋል ኤር 51፣51

እባካችሁ እናንት «ዲያቆናት» ስለተቀበላችሁት አደራና ስለማላችሁት መሃላ ብላችሁ ቤታችንን አታምሱት !!!እንዲህ ብር ብር እናዳላችሁ ብር አድርጎ ከነስም አጠራራችሁ ሊሰርዛችሁ በሚችል አምልክ ቤት የምትሸቃቅጡት ይብቃችሁ! በየዋህነት ኪሱንና ልቡን ስጥቶ በሚከተላችሁ ምዕመንም ሕይወት አትጫዎቱበት። ኧረ በመድኃኔዓለም ተውን! ኧረ የምህረት ያለህ! ኧረ ምድረ ቀሳጢ ሲጫዎትብን የሚታደገንን ለመላክ አምላክ ምነው ዘገይህብን? ባዕዳን እኛን መስለው የእኛን ማዕረግ ይዘው በቤተ መቅደሳችን ገብተው ሲያምሱን የፍዳ ዘመናችንን ምነው አረዘምክብን?

Anonymous said...

ምኲራብ
ጌታ ቤቱን ያጸዳበት እለት

Anonymous said...

አንተ ማን ነህ?ብለው ይጠይቁት ዘንድ ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋውያንን በላኩበት ጊዜ፥ የዮሐንስ ምስክርነት ይህ ነው።

መሰከረም አልካደምም፤ እኔ ክርስቶስ አይደለሁም ብሎ መሰከረ።

እንኪያስ ማን ነህ? ኤልያስ ነህን? ብለው ጠየቁት። አይደለሁም አለ። ነቢዩ ነህን? አይደለሁም ብሎ መለሰ።

እንኪያስ። ማን ነህ? ለላኩን መልስ እንድንሰጥ፤ ስለራስህ ምን ትላለህ? አሉት።

እርሱም። ነቢዩ ኢሳይያስ እንዳለ። የጌታን መንገድ አቅኑ ብሎ በምድረ በዳ የሚጮኽ ሰው ድምፅ እኔ ነኝ አለ።

ዲ/ን በጋሻው ደሳለኝ
ማን ነህ?
ስለራስህ ምን ትላለህ?

Anonymous said...

ፐፐፕ....
እንዲህ ወዝ በወዝ ያደረገው እውን የሚያስተምረውን ቃለ እግዚአብሔር እየኖረው ስለሆነ ይሆን????????
በጣም አምሮበታል... ካይን ያውጣህ በሉልኝ...

Anonymous said...

I can't wait to hear what "Diakon" Begashaw is going to say. I am sure it's going to be full of insults and white lies with a purpose of covering up or attention diverting.
Tsegur kemelase yinekel, I am 101% sure. What do you expect from these guys who have no clue of what Sirptuality is?
Please go to this link and hear him boasting " Leka egna benewedk hulachehum tewedkalachu".
http://www.youtube.com/watch?v=F_5FlHdQOUc

Terunetu sle temeretut sweoch " Kenochu yaterlau" .. Amen

Anonymous said...

Your jealousy is driving U nut U calling name just because Begashaw shines U out U are on real maddens that is Ur problem.
One day in GOD's Will, truth will be revealed he is son of tewahedo who is sent to save so many souls.

U preach hatred he preach God who is Love.can't U open Ur eyes how jealousy is driving U to the edge,

God forbid U. Don't confuse the innocent tewahedo followers.
U have Ur agenda don't use the name of tewahedo to push it Ur personal hatred and jealousy.

Anonymous said...

temesgen!! i was sure begashaw wont let zemedkun to lie all tewhadedos! i cant wait to hear the truth in the VCD

Anonymous said...

can dejeselam report the whole interview please

Anonymous said...

You guys are trying to teach tewahedo church about LORD JUSUS CHRIST?You are funny.The way Begashaw calls LORD is NOT the way tewahedo addresses LORD.This is because either he is not learnt in the church or he does not believe in tewahedos teachings.
Our fathers are filled with politeness,but this guy says and acts just like a protestant pasteur.
If he claims to be ortodox he should follow orthodox way of teachings.
But I am angry at the leaders of the church.Having been watching all this,they have done nothing to control the quality of the church's teaching.

Anonymous said...

A GIFT FOR "EWENET"
A BIG GIFT FOR YOU. just listen the whole part (1-7) and you will have true live if you are ready to do so.IF YOU ARE REALY SEEK THE TRUE WAY OF GOD YOU WILL LOVE IT, OTHER WISE YOU WILL CRY IN YOUR WHOLE LIFE. our church needs 1000x1000 like Dn. begashaw. he is really gasha to our church. thank you for the "anontmous" abouve who bring this video clip.but i affraid he /she did listen the whole preach. it is a wonderful preach every body who want life should listen to this video.GOD HELP D. Begashaw.

http://www.youtube.com/watch?v=F_5FlHdQOUc

Anonymous said...

ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ይህ እውንትቱ የሚባለውን ወሸታም ማርልን ጤናውንም ስጠው።ጌታዬ ሆይ ያለ መስሎታልና አለመኖሩን አሳየው።
ወላዲተ አምላክ በምልጃሽ ተራጅው። ........................................................................................ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ይህ እውንትቱ የሚባለውን ወሸታም ማርልን ጤናውንም ስጠው።ጌታዬ ሆይ ያለ መስሎታልና አለመኖሩን አሳየው።
ወላዲተ አምላክ በምልጃሽ ተራጅው። ........................................................................................ጌታ እግዚአብሔር ሆይ ይህ እውንትቱ የሚባለውን ወሸታም ማርልን ጤናውንም ስጠው።ጌታዬ ሆይ ያለ መስሎታልና አለመኖሩን አሳየው።
ወላዲተ አምላክ በምልጃሽ ተራጅው። ........................................................................................

Anonymous said...

እግዚአብሄር በወደደና ባወቀ ረቂቅ በሆነ መንገዱ እናንተን ከሐገር አወጣችሁ እንጂ ያን ምስኪን የተዋህዶ አማኝ ታምሱት ነበር
ይህ ምስኪን ሰባኪ ወንጌል ምን ያድርገ ነው የምትሉት ወንጌልን በሰበከ ህዝብ እንዲድን በለፈለፈ ምን ያርጋችሁ ኢየሱስ ብሎ
ስላስተማረ ነው ችግራችሁ ዓለም ከዳነበት ስም ላይ ይሆን? የኢ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ራስ እኮ ክርስቶስ ነው ፡;
ምን ይደረግ? መዳንም በዚሁ ስም ነው ታዲያ እንዴት ትሆኑ?ለእናንተ ሲባል ምን ይደረግ ?
የግል የቅናትና የጥላቻ አጀንዳችሁን ለምን በሀይማኖቷ ስም እና ሽፋን ታካሂዳላችሁ? የተከደነን የሚከፍት የተደበቀን የሚገልጥ
የእስራኤል አምላክ ያጋልጠችኋል;;አሁንም ቢሆን በገዛ ብእራችሁ (ጽሁፋችሁ)ቅናታችሁ ተንቦግቦጎ እየተከሰተ ነው
ትንሽ እፈሩ;;እንዴት ጥላቻን ትሰብካላችሁ?አንድ ሰሞን ይሄንኑ የስም ማጥፋት ዘመቻችሁን በተወሰኑ አባቶች ላይ ስታካሂዱ እንደነበር
የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው፡; አሁን ደግሞ ተረኛው ዲ/በጋሻው ነው ደግሞ ለከርሞ ተረኛው ማን ይሆን?
ሽንፈት አናውቅም የንጉስ ልጆች ነን
በደም ተገዝተን ወራሾች የሆንን
በስሙ ብርታት በመስቀሉ ጉልበት
ይፈራርሳል የጠላት ሰገነት
ሕያው እግዚአብሔር ዝማሬ የሚደርሱትን እና የሚዘምሩትን ከጣእሙ የተነሳ አጥንትን የሚያለመልመውን ዝማሬ መላእክት
ያሰማቸው
ለዲያቆን በጋሻው እና ለመሰሎቹ እውነተኛ ወንጌላውያን ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡; መድሀኒተ ዓለም አብዝቶ ይጠብቃቸው ቅድስት ድንግል አትለያቸው፡;
እሽ ብትሉ ለእናንተም ማስተዋል ይስጣችሁ አ ሜ ን!

Anonymous said...

dear paster ewnet,
now,you talking.all of the sudden you took off your face mask and you told us exactly who you are as we suspect.

to be honest you don't have to confess.because every body knows you.now i am just give agreat appriciation for those true orthodox son's and prechers back in days. because if,they would n't had taken such a strong action on that time the peoples like paster ewnet would have succeed.

Anonymous said...

"Ewnet"
I read your comments every day and you are ትእብተኛ in front of almighty GOD. i am just wondering what you are in between tewahedos'. do you think we are blind? my be you think that but you are one of the few blind nontewahedo in this blog who plays zero sum game in his own life."...የኢየሱስ ሰላምና ጸጋ ይብዛልህ!" what do you think this 'ይብዛልህ' say about you? it says to me that
1. you are protestant
2. you beleive you are the most graceful who have enough grace and ready to go, which you are not. i hope you shouldn't make any accident to day and die at this time. i mean you don't have the power to say "ይብዛልህ." Jesus said " rasachewn kefkef yemiyadergu zikzik yilalu rasachewn zikzik yemiadergu kekef yilalu" so don't make your self above all and God will throw you under all at the last day.

Nabute said...

ለ ‘እውነትና’ (ሐሰት) ለመሰሎቹ

ከታች የተጻፈው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ለእናንተና ለመሰሎቻችሁ መናፍቃንና ተሃድሶዎች የተነገረ ነው።
ቤተክርስቲያንን በኑፋቄያችሁ ለማጥፋት/ለመለወጥ/ለማደስ ስንት ጊዜ እንቅልፍ አጥታችሁ ተቅበዘበዛችሁ። ነገር ግን ቤተክርስቲያን በእውነተኛው ክርስቶስ ደም ተመስርታለችና (የገሃነም ደጆች አይችሏትም ተብሎላታልና) እንደምኞታችሁ ልታጠፏት አልቻላችሁም። ይልቁንም እየሰፋች መጣች እንጂ። እናንተ ግን ሃሰተኛውን ክርስቶስን (አውሬውን) ተከትላችሁ ጠፋችሁ። አሁንም ሌሎች የዋሃንን በሚያቆላምጥ አፋችሁ ወደገሃነም ለመወርወር ብዙ ትደክማላችሁ። ነገር ግን የሚያያሳዝነው ከንቱ ድካም መሆኑና መጨረሻው ጥፋት መሆኑ ነው።

እባካችሁ ወደልቡናችሁ ተመለሱና ንስሃ ግቡ።


“የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ በውሥጣቸው ግን ነጣቂዎች ተኵላዎች ከሆኑ ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ።” ማቴ 7 ፤ 15

“ነገር ግን በመጨረሻው ቀን የሚያስጨንቅ ዘመን እንዲመጣ ይህን እወቅ። ሰዎች ራሳቸውን የሚወዱ ይሆናሉና፥ ገንዘብን የሚወዱ፥ ትምክህተኞች፥ ትዕቢተኞች፥ ተሳዳቢዎች፥ ለወላጆቻቸው የማይታዘዙ፥ የማያመሰግኑ፥ ቅድስና የሌላቸው፥ ፍቅር የሌላቸው፥ ዕርቅን የማይሰሙ፥ ሐሜተኞች፥ ራሳቸውን የማይገዙ፥ ጨካኞች፥ መልካም የሆነውን የማይወዱ፥ከዳተኞች፥ ችኩሎች፥ በትዕቢት የተነፉ፥ ከእግዚአብሔር ይልቅ ተድላን የሚወዱ ይሆናሉ፤ የአምልኮት መልክ አላቸው ኃይሉን ግን ክደዋል፤ ከእነዚህ ደግሞ ራቅ። ወደ ቤቶች ሾልከው እየገቡ፥ ኃጢአታቸው የተከመረባቸውን በልዩ ልዩ ምኞትንም የሚወሰዱትን ሁልጊዜም እየተማሩ እውነትን ወደ ማወቅ ሊደርሱ ከቶ የማይችሉትን ሞኞችን ሴቶች የሚማርኩ፥ ከእነዚህ ዘንድ ናቸውና። 8ኢያኔስና ኢያንበሬስም ሙሴን እንደ ተቃወሙት፥ እንዲሁ እነዚህ ደግሞ አእምሮአቸው የጠፋባቸው ስለ እምነትም የተጣሉ ሰዎች ሆነው፥ እውነትን ይቃወማሉ። ዳሩ ግን የእነዚያ ሞኝነት ደግሞ ግልጥ እንደ ሆነ፥ ሞኝነታቸው ለሁሉ ይገለጣልና ከፊት ይልቅ አይቀናላቸውም።” 2ኛ ጢሞ 3 ፤ 1-9

“ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና፤ ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ አልኋችሁ፥ አሁንም እንኳ እያለቀስሁ እላለሁ። መጨረሻቸው ጥፋት ነው፥ ሆዳቸው አምላካቸው ነው፥ ክብራቸው በነውራቸው ነው፥ አሳባቸው ምድራዊ ነው።” ፊልጵስዩስ 3 ፤ 18

Anonymous said...

እግዚአብሄር በወደደና ባወቀ ረቂቅ በሆነ መንገዱ እናንተን ከሐገር አወጣችሁ እንጂ ያን ምስኪን የተዋህዶ አማኝ ታምሱት ነበር
ይህ ምስኪን ሰባኪ ወንጌል ምን ያድርገ ነው የምትሉት ወንጌልን በሰበከ ህዝብ እንዲድን በለፈለፈ ምን ያርጋችሁ ኢየሱስ ብሎ
ስላስተማረ ነው ችግራችሁ ዓለም ከዳነበት ስም ላይ ይሆን? የኢ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ራስ እኮ ክርስቶስ ነው ፡;
ምን ይደረግ? መዳንም በዚሁ ስም ነው ታዲያ እንዴት ትሆኑ?ለእናንተ ሲባል ምን ይደረግ ?
የግል የቅናትና የጥላቻ አጀንዳችሁን ለምን በሀይማኖቷ ስም እና ሽፋን ታካሂዳላችሁ? የተከደነን የሚከፍት የተደበቀን የሚገልጥ
የእስራኤል አምላክ ያጋልጠችኋል;;አሁንም ቢሆን በገዛ ብእራችሁ (ጽሁፋችሁ)ቅናታችሁ ተንቦግቦጎ እየተከሰተ ነው
ትንሽ እፈሩ;;እንዴት ጥላቻን ትሰብካላችሁ?አንድ ሰሞን ይሄንኑ የስም ማጥፋት ዘመቻችሁን በተወሰኑ አባቶች ላይ ስታካሂዱ እንደነበር
የቅርብ ግዜ ትዝታችን ነው፡; አሁን ደግሞ ተረኛው ዲ/በጋሻው ነው ደግሞ ለከርሞ ተረኛው ማን ይሆን?
ሽንፈት አናውቅም የንጉስ ልጆች ነን
በደም ተገዝተን ወራሾች የሆንን
በስሙ ብርታት በመስቀሉ ጉልበት
ይፈራርሳል የጠላት ሰገነት
ሕያው እግዚአብሔር ዝማሬ የሚደርሱትን እና የሚዘምሩትን ከጣእሙ የተነሳ አጥንትን የሚያለመልመውን ዝማሬ መላእክት
ያሰማቸው
ለዲያቆን በጋሻው እና ለመሰሎቹ እውነተኛ ወንጌላውያን ቃለ ሕይወት ያሰማልን፡; መድሀኒተ ዓለም አብዝቶ ይጠብቃቸው ቅድስት ድንግል አትለያቸው፡;
እሽ ብትሉ ለእናንተም ማስተዋል ይስጣችሁ አ ሜ ን!A GIFT FOR "EWENET"
A BIG GIFT FOR YOU. just listen the whole part (1-7) and you will have true live if you are ready to do so.IF YOU ARE REALY SEEK THE TRUE WAY OF GOD YOU WILL LOVE IT, OTHER WISE YOU WILL CRY IN YOUR WHOLE LIFE. our church needs 1000x1000 like Dn. begashaw. he is really gasha to our church. thank you for the "anontmous" abouve who bring this video clip.but i affraid he /she did listen the whole preach. it is a wonderful preach every body who want life should listen to this video.GOD HELP D. Begashaw.

http://www.youtube.com/watch?v=F_5FlHdQOUc


thank you guys,,,this sibket change lifes!!

Anonymous said...

PLS LISTEN THE WHOLE SBKET!! HE IS NOT AFRAID TO TELL THE TRUTH! we need millions like him!! his speech is just the truth!! i am very very inspired by him!! elellelelelelelellelelelelewllelelelwellewlllellllleeeeeeeeeeeelll

Mar said...

Ewnet!?...Ha..Ha..Ha... anetene belo Ewnet. you are number one WESHETAME MENAFEKE. Don't try to hide your self yor ANEDEBET tola us already who you are. Yes you are the number one TELATE for our churich. Hay!..LAYER...you should to stop. Dear Dejeselamaweyan after this time this guy name is LAYER MENAFKE. When you responed for him use this name because of his personality i changed his name.

Anonymous said...

Dear Dejeselamaweyan

Can we read the full interview what he said for "Royal..."?

Anonymous said...

PLEASE CAN YOU POST THE WHOLE INTERVIEW!!!

Anonymous said...

Hey "LAYER MENAFKE" are you mad? because of we know already who you are? you do not need spend your time to tell for us about the BIBLE also do not try to hide your self in LORD word becaus YOUR OLDRE BROTHER DIVLE also apply the bible word we know who teach you. ...get out of on our way DIVLE.

Nabute said...

“ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ” ማቴ 7 ፤ 15

If u want to know who really the likes of 'EWNET' (actually HASET) and those of the influencial members of the fake synod (North America) please watch these video clips.

http://www.ethiotube.net/video/7935/Ethiopian-Orthodox-Tewahedo-Vs-Tehadiso-Part-116

Anonymous said...

how long our church be troubled by self oriented people inside the church.... oh God please provide us your true prophets and preachers. may it be your time to work for the church not us.

Anonymous said...

Dear DN Begashaw God will answer this just heads up, ignore this b/c they are gelious of hard work.

Wendeme keep quite and let God answer!!!

Tewahedo said...

የተዋህዶ ልጆች ንቁ እባካችሁ!!!
እውነትና መሰሎቹ እኮ ተልእኮአቸው ተሰናክሎባቸው ነው እንደዚህ የሚያሳብዳቸው አትፍረዱባቸው… ልብ ይስጣቸው ነው የሚባለው… እስቲ ቤተክርስቲያናችን በምን አይነት ፈተና ላይ እንዳለች አንድ ማስረጃ ልንገራችሁ….ግን ምን እስክንሆን የምንጠብቀው …?
የእነ በጋሻውና መሰሎቹ አላማ መስመር እየያዘላቸው መሆኑን የሚገልጽ ጽሑፍ ነው …ይኸውም
በመናፍቃኑ ሜታኖያ በሚባለው መጽሔታቸው ቁ 2 ታህሳስ 2ዐዐ2 ዓ.ም. ገጽ 23 ላይ እነዚህ “አለምን በወንጌል እና በመዝሙር ምድርን የሞሉት” ተብለው ከሚመሰክሩላቸው ዘማሪዎች ውስጥ አንዷ የሆነችው የምርትነሽን መዝሙር ለሃይማኖቶች እርቀ ሰላም ያደረገችውን አስተዋጾ ይተነትናል፡፡
የሃይማኖቶች ዕርቀ ሰላም በሚል ርዕስ ውስጥ እንዲህ ተገልጿል… “በዚህ ጽሑፍ ዛሬ የምናነሳው ጉዳይም በተለያዩ ጊዜያት ይህች ዘማሪት በለቀቀቻቸው መዝሙሮቿ እንዲት አድርጋ የኘሮቴስታንትና የኦርቶዶክስን የአንድነት መንገድ ለመክፈት ያደረገችውን አስተዋጽዎ ላይ በማተኮር ይሆናል፡፡”
ይልና…
“የሁለቱ ሃይማኖት አገልጋዩች በዚህ ሀቅ የመስማማት ግንዛቤ የበረቱ ይመስላሉ፡፡ ለዚህም አስረጅነት በየጊዜው የምናዳምጣቸው የስብከትና የዝማሬ ትሩፍቶቻቸው ይህንን እውነት በእርግጥ ማወጃቸውን ነው፡፡ የሁለቱ ሃይማኖቶች አገልጋዮች በህብራዊ የአገልግሎት ተመሳስሎ እንዴት አድርገው ልዩነታችውን እያጠበቡ እንደሚገኝ እንመለከታለን፡፡”… እያለ የተወሰኑ መዝሙሮቿን ግጥም አንድ በአንድ ይተነትነዋል እንግዲህ ይኼ የማን እና የማን ውጤት እንደሆነ በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡
ታዲያ የተዋህዶ ልጆች ወዴት እያመራን ነው? እስቲ እራሳችንን እንጠይቅ እንመርምር ….ዝም ብለን ካጨበጨበ ጋር አናጨብጭብ … ቀስ ብለው እኮ ሁሉንም ማለትም በጋሻውና ግብረአበሮቹን ቀስ በቀስ ቃለመጠይቅ ይደረግላቸዋል … ከዛም ቤተክርስቲያን የቀረው አንድ እግራቸው እዛው የመናፍቃኖቹ አዳራሽ ውስጥ እናገኘዋለን… እና አሁን እየሰሩ ያሉት ነገር ምን ያስደንቃል… ከፍሬያቸው ስለሚታወቁ… በማስተዋል እንመላለስ፡፡
ሙሉ ጽሑፉን ማንበብ ለምትፈልጉ በ neftalemb@yahoo.com ጻፉልኝ እልክላችኋለሁ፡፡
ሁላችንንም አምላከ ቅዱሳን ይጠብቀን!! በቸርነቱ ያስበን!!!
የእመቤታችን ፍቅሯን በልባችን እስከዘላለም ያኑርልን!!!
ቅዱሳን መላእክት በጠብቆታቸው አይለየን!!!
ጾመን ለመጠቀም ያብቃን!!!
አሜን!!!

Nabute said...

Tewahedo,
thank u for ur information. Even though we don't want it this is what was expected from their 'movement'. Let God uncovers everything for the sake of our true church nad the true followers.
And for those who r misled let Him show them the only true way andget themback to their ethernal home.

In the link below is the unsucessful movement of these ppl few years back.

“ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ” ማቴ 7 ፤ 15

If u want to know who really the likes of 'EWNET' (actually HASET) and those of the influencial members of the fake synod (North America) please watch these video clips.

http://www.ethiotube.net/video/7935/Ethiopian-Orthodox-Tewahedo-Vs-Tehadiso-Part-116

http://www.ethiotube.net/video/7754/Ethiopian-Orthodox-Tewahedo-VS-Protestant-Part-1-of-18

Birhanu Tadesse said...

በስመአብ ወወልድ ውመንፈስ ቅዱስ ፩ዱ አምላክ አሜን።

የመምህር (የዘማሪ ) ብቃቱ የሚታወቀው ትምህርቱ (ዝማሬው) ሰውን ወደ ንስሃ ፥ ወደ ቅዱስ ቁርባን መምራቱ እንጅ የመምህሩ ታዋቂነት (ዝና)፥ ተደማጭነቱም አይደለም። ማወቅስ እንደይሁዳ ማን ያውቅ ነበር?!
ደግሞስ ከእናንተ ውስጥ ጹሙ እያለ የማይጾም አለን?! አታመንዝሩ እያለስ የሚያመነዝርስ አለ ?!

ነገር ግን ሁሉም በአግባብ እና በስርአት ይሁን። ፩ኛ ቆሮ ፲፬፥ ፵
አባቶቻችሁ የሰሩትን የድንበር ምልክት አታፍርሱ መዝ ፳፪፥፳፭
ወሰናችሁን አትለፉ መዝ ፵፪፥፬
የእግዚአብሄርን ቃል የነገሩዋችሁን ዋኖቻችሁን፤ አባቶቻችሁን አስቡ። ዕብ ፲፫፥፯

መዝሙር ከዘፈን የተለየ ነው ና አለማውያን ለአለም በሚያንጎራጉሩበት ዜማ ሳይሁን ለእግዚአብሄር ለ ራሱ በተለየ ዜማ ነው። ብርሃን ከጨለማ የተለየ እንደሆነ መዝሙርም ከዘፈን ፥ ሽብሸባም ከዳንኪራ የተለየ ነው።
እግዚአብሄርስ የሰላም አምላክ እንጅ የሁከት አምላክ አይደለሁም ብሎአል እና።

ዘምሩ ለአምላካችን ዘምሩ ፤ ዘምሩ ለንጉሳችን ዘምሩ እግዚአብሄር የሁሉ ንጉስ ነውና በማስተዋል ዘምሩ። መዝ ፵፮፥፮-፯

ጌታ ሆይ ፥ ጌታ ሆይ ያለ ሁሉ መዝሙር አይደለም!።
በእንግዳ ትምህርት አትወሰዱ ልባችሁ በጸጋ ቢፀና መልካም ነው እንጅ በመብል አይደለም በዚህ የሚሰሩባት አልተጠቀሙም ዕብ ፲፫፥ ፯
ፈቃደ ስጋችንን ለ ነፍሳችን ስናስገዛ ቅዱን ስንደምንሆን ገላ ፭፥፲፮

ስለዚህ ችግር አለ(ሰው ያፈራው ጭፈራን ብቻ ነው)። ይህን ማስተካከል እንጂ መልስ መመላለስ የክርስቲያን ጸባይ አይደለም ። በገዛ ደሙ የዋጃትን የእግዚአብሄርን ቤተክርስቲያን ጠብቁዋት። ሃዋ ፳፰

እኛስ የተሰቀውን ክርስቶስ እንሰብካለን እንጂ የራሳችንን ስም አንሰብክም። ብዙሰባኪዎች አስተምረው ቀይረውኛል ለንስሃ ፥ ለ ቅዱስ ቁርባንም እንድደርስ እረድተውኛል።
ስማቸው ግን በምድራውያኑ ሳይሆን በሰማያውያኑ(በእግዚአብሄር እና በቅዱሳኑ)ይታወቃል።

ወስብሃት ለእግዚአብሄር ወለወላዲቱ ድንግል ወለመስቀሉ ክቡር።
አሜን"

mebrud said...

እንዲህ ሆነላችሁ: ባለፈው ጊዜ ይህን አስገራሚ ሲዲ (አርማጌዶን) ለመግዛትና ለማድመጥ(አዳምጦ ነው መፍረድ ብዬ) ከቤተክርስቲያን ደጃፍ ብፈልግ አዟሪዎች "ለምን ፈለግኸ ተከልክሏል እኮ" ሲሉኝ ተመስገን አዟሪዎች ከንግድ ውጪ ስርዓትን ያውቃሉ ማለት ነው ስል ዞር አልኩ ነገር ግን እግሬ ስር "የመስቀሉ ስር ቁማርተኞች" ከመጻሕፍት ጋር ተዘርግቶ ይሸጣል።ምን አይነት ተቃራኒ ነገር እንደሆነ ተመልከቱ።ብጹዓን ጳጳሳትን የሚሳደብ መጽሐፍ ህጋዊነት አግኝቶ ይሸጣል፣ይህን የሚተች ሲዲ ይከለከላል።ማነው ፈቃጁና ክልካዩ?ቅዱስ ሲኖዶስ(ሲኖዶሱማ ዝምታን መርጧል)?ምዕመናን?(ምዕመኑማ ግራ ተጋብቷል እነ'እውነት' በምድር ሲኖሩ ገና ብዙ ሰው ይደናገራል...እኔን ግር ይግባኝ ምስኪን ምዕመን)?በጋሻው?(በርግጥ ይሆናል በሮያል መጽሔት አትሽጡ የሚል መልዕክት ማስተላለፉን ልብ ይሏል)።
ወደ ሲዲው ልመለስ አርማጌዶንን ወድጄዋለሁ ዘመድኩን ዘመድህ ይብዛ።ውስጣችን ያረረበትን ነገር ገለጥኸው።
አንዳንዶችን እንደሚያስቆጣ ይታወቃል።ከዝምታ ግን ይሻላል።
እንግዲህ አባቶች ዝም ካሉ ግለሰቦች እንዲህ እውነቱን ይግለጡት እንጂ።አባቶች ዝምታችሁን ስበሩት።አለበለዚያ እነ "እውነት" እውነተኛ የወንጌል ሰዎች መስለው በጉን ከተኩላ ማኅበር ይደምሩታል።ይህ ደግሞ በሰማይ ያስጠይቃል።በጎችን አልጠበቃችሁም በሚለው ኃይለ ቃል።
ግን አንድ ጥያቄ መምረመር ግድ ይላል።የካሴቱን መሰራጨት አዟሪዎች ያልፈለጉበት ምክንያት ምንድነው?ወይም መከልከሉን ያስወሩት ለምን ይሆን።'ምድርን በዝማሬ የከደኑ' ካሴቶች ገበያ ላይ አሉታዊ ተጽዕኖ ይኖረው ይሆን?ይህን ያዳመጠ ምዕመን እንግዲህ ሊነቃ ነው።አግበስብሶ ካሴት መግዛት ሊኖርበት ነው።ሰባኪን ከአዋኪ ሊለይ ነው።ስለዚህ ገበያው ላይ ችግር ይፈጥራል።
ቤተክርስቲያን ሆይ ምዕመኑን ልትመሪው ሲገባ ይመራሽ ጀምሯል።ግን ወዴት ?ወደ ስጋ ወይስ የነፍስ ገበያ..."።
ይህ ፕሮቴስታት ምዕመኑን ከካቶሊክ ለመገንጠል የተጠቀመችበት አካሄድ አይደለምን?ህዝቡን ይመቸው እንጂ ወንጌል ተጣመመ አልተጣመመ ምን ችግር አለው...
ዋናው ጌታን ተቀበል እንጂ ስርዓት ተጠበቀ አልጠተበቀ ምን ችግር አለው...
ዋናው መንፈስ ቅዱስ ተሞላ እንጂ ብተደንስ ብታጓራ ምንችግር አለው...
ብትጾም ባትጾም ምን ችግር አለው? ነውኮ ነገሩ።
ህዝብን የመከተል አባዜ በፕሮቴስታን አየነውኮ።በክፍፍላቸው።
እመብርሃንን እኛ ልንደግመው አይገባም።
ክርክሩ በቤተክርስቲያን ልጆች መካከል የሚመስላችሁ ካላችሁ አትሳሳቱ።ይሄ የዘመድኩንና የበጋሻው ልዩነት አይደለም።
የተሃድሶና የተዋህዶ ግልጽ ልዩነት ነው።በየዋህነት በቤተክርስቲን ላይ ጦር እንዳንወረውር እናስተውል።
ቤተክርስቲያን የኦዲዮ ቪዲዮ፣የመጽሔትና ጋዜጣ ብሎም የሰባኪዎቿንና ዘማሪዎቿን እውነተኛነት እየገመገመች ሰርተፍኬት ካልሰጠች፣የወንበዴዎች ዋሻ መሆኗ ነው።
የሴንሰር ሺፕ(ቅድመ ግምገማ ጊዜው አሁን ነው)።
ማስመከሪያ ቤቶች ነበሩን አኮ።ዋሽራ፣ዲማ፣ባዕታ...።
ዘፈኑ እንኳን በethiopian idol ሲታረም ለዝማሬውና ለስብከቱ ሃይ ባይ ይጣ።ወይ መከራችን።
ይቆየን።

Unknown said...

ጌታ ደጉን ቀን ያምጣ ነው የሚባለው ሁላችንም መጀመሪያ የራሳችንን ጉድፍ እንመልከት እኛ ማነንና ነው ስሌላው የምንናገረው ለማንኛውም ሁሉንም ጌታ መድሃኒአለም ይፍታው አሜን

ዲዮስቆሮስ said...

አንዳንዶች ስለዲ/ን በጋሻው ማስረጃ የጠየቃችሁ አላችሁ ምነው ከፋችሁ ለምሣሌ # የኔ ናርዶስ የኔ ቤዛ በመዓዛ ልቤን ገዛ $የሚለው የዘርፌ መዝሙር ደራሲ #መጋቤ ሐዲስ$ ብሎ ባለመማር ቅሌት ራሱን የሾመው ዲ/ን በጋሻው የሐዲሳት መምህር ከሆነማ ምነው 1ኛ ጴጥሮስ 1-18 ላይ ያለውን ሳይማር ዘሎት ነው; አሃ አሃ አሃ…..ለድጋፍ የተሰጠው ስለሆነ ነው:: ቃሉ #የተቤዣችሁ በሚጠፋ በወርቅ ወይም በብር እንዳይደለ ታውቃላችሁ ነውርና እድፍ እንደሌለው እንደበግ ደም በክርስቶስ ክቡር ደም ነው እንጂ$ ይላል ታዲያ በክርስቶስ ደም ልባችን የተገዛ ሲሆን በመዓዛ ነው ማለት ትልቅ ምንፍቅና አይደለምን; አይ የኛ መጋቤ ሐዲስ ;!
ከምንፍቅና መንፈሶቹ አንዱ

Anonymous said...

TE:EVERYBODY:DO NOT USE THE WORDS OF GOD TO SUPPORT YOUR PERSONAL VIEWS AND COMMENTS!IT IS FORBIDDEN TO DO SO.

Anonymous said...

TO:EVERYBODY:DO NOT USE THE WORDS OF GOD TO SUPPORT YOUR PERSONAL VIEWS AND COMMENTS!IT IS FORBIDDEN.

LOZA said...

Oh..My God...I dont't know..before "WHO IS D.BEGASHEW". I thought he is a real TWAHEDO SUN but I was wrong. know something becoming clear fo me because of this... The writer name "EWENET" he is a real "MENAFKE" also he trying to tell us about D.BEGASHEW RELGIOUS and good personlity. That means D.Begashwe is.....?. Because "EWENET" he is not our churich member so why he likes D.BEGASHEW?....I am confused about him.

Tamrat said...

Dear Editor of Deje-Selam,
Can you put us the whole interview as usual?
Thx.

Tamrat
Holland

Anonymous said...

DO NOT USE THE WORDS OF GOD TO JUSTIFY YOUR PERSONAL VIEWS AND COMMENTS!

Nabute said...

WHAT IS THE ROOT OF THSES PROBLEM???
AND WHO R BEHIND ALL THESE???

CHECK THESE;

http://www.ethiotube.net/video/7935/Ethiopian-Orthodox-Tewahedo-Vs-Tehadiso-Part-116

http://www.ethiotube.net/video/7754/Ethiopian-Orthodox-Tewahedo-VS-Protestant-Part-1-of-18

Nabute said...

TO 'EWNET' AND HIS SUPPORTERS

DO U HAVE THE GUTS/BELIEF TO WATCH THESE AND DEFEND FOR UR 'FAITH'???
IF U R REALLY ORTHODOX U WILL NOT TALK THAT MUCH ABOUT THE SO CALLED 'ABUNE MELKETSEDEK' (ACTUALLY STRIPPED AND CALLED ABA HABTEMARIAM) AND ABA WELDETENSA THE SO CALLED 'YEZEMENU HAWARYA'.

BEGASHAW IS ALSO THEIR AGENT IN THE TRUE ORTHODOX TEWAHEDO (NOT THE FAKE ONE THAT IS TEHADISO).

TO KNOW MORE PLS WATCH THESE

http://www.ethiotube.net/video/7935/Ethiopian-Orthodox-Tewahedo-Vs-Tehadiso-Part-116

Anonymous said...

DEAR loza,
if you think "ewnet" is supporting Dn Begashaw you didn't understand what "ewnet" doing. he can't support begshw in breality because ewnet is menafik and begashaw is real orthodox. ewenet is messing in between us he real name might be wishet. he is a real protestant.

Unknown said...

‹d›እውነት ምን አይነት ነህ ንግግርህ እንዲህ የከረፋ ምን ሁነህ ነው፡፡የአባቶች አምላክ ያጋልጥህ፡፡ ማንነትህ በቅርብ መጋለጡ አይቀርም

Nabute said...

CONGRA'EWNET'

NOW U JUST REVEALED URSELF AS PENTE BCS U JUST USED THEIR WORDS (ORITAWIYAN)TO REFER TRUE ORTHODOX PREACHERS.

WE ALL KNOW THAT THOSE U MENTIONED HAVE BEEN MISCOMMUNICATED FROM THE TRUE CHURCH BCS OF THEIR HERETIC TEACHINGS.

ABA WELDETENSAY 'PREACH' US TO EAT ASAMA, HAYNA, KIMAL,.... LIKE PROTESTANT PASTORS.

'ABUNE MELKE TSEDEK' (ABA HABTEMARIAM) WROTE A BOOK THAT SAYS ARGANON MEANS ORGAN AND THEY INTRODUCED ORGAN TO THEIR 'CHURCH' LIKE PENTES. HE IS ALSO TRYING TO CHANGE KIDASE ZEMA USING ORGAN. (JUST LIKE THE PENTES ORDERED HIM TO DO SO)

PASTOR MELAKU AND PATOR LEULE KAL WERE ACTUALLY PENTES AND 'PREACHING' IN PENTES HALL FEW YEARS AGO. NOW THEY R REINSTATED AND CALLED ' KESIS' BY ABUNE MELKETSEDEK SO THAT THEY CAN SPREAD THEIR HERESIES MORE EFFECTIVELY TO THE YEWAH MEIMENAN.


NOW WE KNOW WHO U REALLY ARE.
WHY DID U TRY TO COVER URSELF IN THE ORTHODOX TEWAHEDO NAME THEN???
KEFIREYACHEW TAWKUACHEWALACHIHU TEBILOAL EKO.
ANTENIM KEFIREH AWEKINIH.

TO ALL THOSE WHO R IN THE TRUE RELIGION:-
NOW WE KNOW 'EWNET' (HASSET) THAT HE IS MENAFIK PENTE AND WHY DO WE WASTE OUR PRECIOUS TIME AND MORAL BY ARGUING WITH PENTES???
WE KNOW THAT WE CAN'T CHANGE THEM AS NO ONE CAN'T CHANGE SATAN TO BE A SAINT.

SO WE SHALL STOP DISCUSSING WITH THESE BANDAS OF PENTE.

I JUST STOP AND I WON'T WRITE U BACK TO DISCUSS WITH U 'EWNET'.

(BIRHAN KECHELEMA MIN HIBRET ALEW;
YEMIYAMINIS KEMAYAMIN MIN ANDINET ALEW; ORTODOX TEWAHEDOS KE PENTE/TEHADISO MENAFIKE MIN HIBRET LINOREW YICHILAL)


U WILL FIND MORE ON THESE @;

http://www.ethiotube.net/video/7935/Ethiopian-Orthodox-Tewahedo-Vs-Tehadiso-Part-116

Ankiro said...

I am so tired of this guy who calls himself 'ewnet'.
'Ewnet': All you do is label people 'Ferisawi - oritawi....' and you accuse people of calling you menafiq when everything you write is supporting and crying out 'Menafiq, Menafiq, Menafiq! - Not at least the Authentic EOTC teaching. Do you even understand what you are writing? I don't think you do. It seems like you are writing for yourself. 'Cause you might write something that readers might read!

You have your own blog, don't you? You have been nagging people to come to your blog. So, let me give you this simple advice: why don't you write all the crap you want on your own blog and stop grossing readers here? I am so turned of by your incessant and irritating, 'kind of stupid' (excuse the language) comments that I don't read them anymore. Do you get that ? I don't think you do. I know you will be back with your insults and blood thirsty comments. I think your heart is full of rage, vengeance. Otherwise, you could have been satisfied being just a menafiq.
You have to have everybody on your side or 'exterminate every opposition' if you could. That is not a healthy above all Christian like. Hope you understand my comment, but I don't think you will.
Accusing Mahibere Kidusan or some other EOTC body and its members for every topic! what is next?! - global warming, the H1N1 flu virus, economic problems..... That is so sickening.

Hope Deje selam Editor can do something about it otherwise more readers will be turned off.

God bless,

Melkam Werha (Abiy) Tsom,

Ankiro

ffffff said...

ዲ/ን በጋሻው ለመልስ መዘጋጀትህን ሰምተናል ምን ዓይነት መልስ እንጠብቅ፣ ለመጽሔቱ የሰጠኸው ቃለ ምልልስ በአንተና በዲ/ን ዘመድኩን መካከል ስላለው ግላዊ ግንኙነት ብቻ ነው እኔ ግን የምፈልገው የቀረበብህን ትችት ካልተቀበልክ ለምን እንዳልተቀበልክ አንድ በአንድ አስረዳን እንጂ የግላችሁ የሆነውን ምስጢር ለኛም ለቤተክርስቲያንም ምንም አያደርም፡፡ መቼም ፍጹም ነኝ እንደማትል እገምታለሁና የዘመድኩን መነሻ ምንም ይሁን ምን የምትቀበለው ትችት ካለም በግልጽ ንገረን፡፡
እግዚአብሔር ቤተክርስቲያንችንን ይጠብቅልን

seble said...

የውድቀት 15 ነጥቦች
ምክር ባትሰማም እንደ ምክር ለበጋሻው የተሰጠ ምክር
1. መጀመሪያ ማንም ሰው ህግና ስርዓት ሊያግደው ግድ ስለሆነ ለቤ/ክ ስርዓት አትገዛም
2. ለ ቤ/ክ ስርዓት አለመገዛትህ በራስህ እንድትዝ አድርጎአል
3. በራስህ ስትዝ መካሪና ገሳጭ ስለማትፈልግ መውደቅ ጀምረሀል
4. የመውደቅህ ጅማሬ ከ ቤ/ክ አስተምሮና ስርዓት መውጣት ሆነ
5. ስርዓተ ቤ/ክ መጣስ ድፍረት ፈጠረብህ
6. ዘማሪያንና ሰባኪያንን በግሩፕ ከፈልክህ
7. ወንጌልን ከህዝብ ማስተዋወቅ ሲገባህ (ሲገባችሁ) ራሳችሁን ማስተዋወቅ ጀመራችሁ
8. የአዲስ አበባ ህዝብ ስለማይመቸን በማለት ገጠሪን መበዝበዝ ጀመራችሁ
9. የገቢ ምንጫችሁን በ ቤ/ክ ላይ አደረጋቸሁ
10. በስብከቶችችሁ አባቶቻችንን ካህናትን እንድንጠላ ሞከራችሁ
11. ቤ/ክንን በዲኮር ዘጋችሁ
12. ህዝቡን ወደ አዳራሽ (ውጭ) አወጣችሁ
13. ገንዘብን በማስከፈል ወንጌልን መሸጥ ጀመራችሁ
14. ብር ሲበዛ ወንጌልን እንደፍላጎታችሁ ተረጎማችሁ
15. የስህተት ትምህርታችሁን ጀመራችሁ

አሁን ግን ነቃንባችሁ


በሚቀጥለው ደግሞ የስብከቶቻችሁን አይነትና ይዘት አቀርባለሁ

red said...

ሳታውቁ በስህተት አውቃችሁ በድፍረት ወንጌል እንሰብካለን በማለት ለወጣቱ ድፍረት እና ስርዓት አልበኝነትን ላስተማራችሁ ‹ሰባክያን› ፍሬዎቻችሁ የሰንበት ት/ቤትን መርሐግብር ትተው በየመንደሩ ቤት እየተከራዩ ‹ወንጌል› ማስተማር ጀምረዋል እንኳን ደስ አላችሁ፡፡ የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያን ወንጌል መስበክ የጀመረችው በዚህ ሁለት እና ሶስት ዓመት እያስመሰላችሁ ወጣቱ ጉባኤውን፤ስርዓቱን እና አባቶችን እንዲንቅ አድርጋችሁታል፡፡ እስከዚህ ጊዜ ድረስ በየዋህነት የምትነዱ ዙሪያችሁን እንድትመለከቱ እና እንድታስተውሉ ብቻ ነው የማሳስባችሁ፤ ሆን ብላችሁ ለምታውኩን ግን የቤተክርስቲያንን ታሪክ ተመልከቱ የመሰሎቻችሁ መጨረሻ ምን እንደሆነ/ነበረ፡፡
የቁርጥ ቀን እየመጣ ነው፡፡

Nabute said...

This will be the end of those who are against the true faith and order of the Orthodox Tewahedo Church.

http://www.ethiotube.net/video/7935/Ethiopian-Orthodox-Tewahedo-Vs-Tehadiso-Part-116

Tewahedo said...

ቃለህይወት ያሰማልን "red" በእውነት የልቤን ነው የተናገርከው፡፡እንዴ እኔኮ የሚገርመኝ አሁንም ወደልቡ መመለስ አቅቶት አዳራሽ ውስጥ ጉባኤ አዘጋጅተዋል… ወይ አለማስተዋል… ብቻ እግዚአብሔር የሁላችንንም መጨረሻ ያሳምርልን!!!

Anonymous said...

ምነው እያንዳንዱ ክርስቲያን እንደ ተሰሎንቄ ሕዝቦች ሳይሆን እንደ ቤርያ ሕዝቦች ልበ ሠፊ በመሆንና(ሐዋ ሥራ 17፡11) መጽሐፍትን በመመርመር የእግዚአብሔርን ቃል በሙሉ ፈቃድ ቢቀበልና ኢየሱስ ክርስቶስን በሙሉ ልብ ቢያምን?

" ሐዋ ምዕራፍ 17
1 በአንፊጶልና በአጶሎንያም ካለፉ በኋላ ወደ ተሰሎንቄ መጡ፥ በዚያም የአይሁድ ምኵራብ ነበረ።

2 ጳውሎስም እንደ ልማዱ ወደ እነርሱ ገባ፥ ሦስት ሰንበትም ያህል ከእነርሱ ጋር ከመጻሕፍት እየጠቀሰ ይነጋገር ነበር፤

3 ሲተረጉምም ክርስቶስ መከራ እንዲቀበልና ከሙታን እንዲነሣ ይገባው ዘንድ እያስረዳ። ይህ እኔ የምሰብክላችሁ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ ነው ይል ነበር።

4 ከእነርሱም አንዳንዶቹ ተረድተው ከሚያመልኩም ከግሪክ ሰዎች ብዙ ከከበሩትም ሴቶች ጥቂቶች ያይደሉ፥ ከጳውሎስና ከሲላስ ጋር ተባበሩ።

5 አይሁድ ግን ቀንተው ከሥራ ፈቶች ክፉ ሰዎችን አመጡ ሕዝብንም ሰብስበው ከተማውን አወኩ፥ ወደ ሕዝብም ያወጡአቸው ዘንድ ፈልገው ወደ ኢያሶን ቤት ቀረቡ፤

6 ባላገኙአቸውም ጊዜ ኢያሶንንና ከወንድሞች አንዳንዶችን ወደ ከተማው አለቆች ጎትተው። ዓለምን ያወኩ እነዚህ ወደዚህ ደግሞ መጥተዋል፥ ኢያሶንም ተቀብሎአቸዋል፤

7 እነዚህም ሁሉ። ኢየሱስ የሚሉት ሌላ ንጉሥ አለ እያሉ የቄሣርን ትእዛዝ ይቃወማሉ ብለው ጮኹ።

8 ሕዝቡና የከተማውም አለቆች ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ ታወኩ፥

9 ከኢያሶንና ከሌሎቹም ዋስ ተቀብለው ለቀቁአቸው።

10 ወዲያውም ወንድሞች ጳውሎስንና ሲላስን በሌሊት ወደ ቤርያ ሰደዱአቸው፥ በደረሱም ጊዜ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገቡ፤

11 እነዚህም በተሰሎንቄ ከሚኖሩት ይልቅ ልበ ሰፊዎች ነበሩና። ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን? ብለው ዕለት ዕለት መጻሕፍትን እየመረመሩ ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀበሉ።

12 ስለዚህም ከእነርሱ ብዙ፥ ከግሪኮችም የከበሩት ሴቶችና ወንዶች ጥቂት ያይደሉ፥ አመኑ።

13 በተሰሎንቄ ያሉት አይሁድ ግን ጳውሎስ በቤርያ ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ሰበከ ባወቁ ጊዜ፥ ወደዚያው ደግሞ መጡና ሕዝቡን አወኩ።

14 በዚያን ጊዜም ወንድሞቹ ወዲያው ጳውሎስን እስከ ባሕር ድረስ ይሄድ ዘንድ ሰደዱት፤ ሲላስና ጢሞቴዎስም በዚያው ቀሩ። "

ጌታ እግዚአብሔር ጊዜውን የወሬ ሳይሆን ቅዱሳት መጻህፍትን የማንበብና ነገሩ እንደዚሁ ይሆንን? እያሉ ዕለት ዕለት መጻሕፍትን በመመርመር ቃሉን በሙሉ ፈቃድ ተቀብሎ የመኖር ያድርግልን፡፡

Anonymous said...

እኔ ምንም አዲስ ነገር በጋሻው ይናገራል ብዬ አላምንም አልጠብቅም!ያው የተለመደ ድለላውን እና ፅርፈቱን ያሰማናል፡፡

ግን ግን ....ይሄ ሁሉ ሰው እንዲህ ስለ ቤተክርስቲያኑ ሲከራከር ሀሳቡን ሲገልፅ... በጋሻው የኢንተርኔት አክሰስ ያጣ ይመስላችሁዋል....በፍፁም፡፡
He is here discusing with us!
surprise!
His name is Ewnet.
I sware.

Unknown said...

oh zemedkun is doing all his best to decreas the famosity behind begashaw. but bugashaws supporter(jesus) have already selected him to carry his name and the gospel.

zemedkun also suggested that the song of zerfe kebede, yene nardos is a romantic song. haven't he read that jesus is "አኔ የሳሮኑ ጽጌረዳ የቆላ አበባ ነኝ"
gete hulachininm yasiben. bemihret na bechernetu yeorthodox tewahido betekristiann yasibat.
amen

Unknown said...

some people say that "Dn." Begashaw haven't finished his theology? is it true? If it is true, how he is teaching? i will say more for the future.

fikir said...

There are times when silence has the loudest voice. Fellow Christians please don't confuse us with big words, do you think that God will never see and hear what's going on in Our Church. Never, never and ever because Jesus Christ has given His life for the Church. Let's get out of this case, let the Almighty speaks. Please, let's take time to see and hear inward. I think the first virtue is to restrain the tongue; he approaches nearest to God who knows how to be silent, even though he is in the right. You are all saying that I'm the right and I'm defending the Tewahdo Church, but you are rather confusing the people. I don't think so this is right, let's learn from our Savior Jesus Christ. The Scripture says,
"When He suffered, He didn't threaten, but committed Himself who judges righteously."(1 peter 2:23) Let your fruits speak about yourselves. Please we need 'Big Silence' don't make useless noise! Dear Dns. Daniel, Zemedekun and Begashaw and others pronouncing the issue so high kindly,give us time until God reveals everybody. We really need 'Big Silence" Yeabatochachen Amlake Enat Tewahdo Bet-Kristiyanchenen Tebekelen! Amen!
Selam! Shalom!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)