February 16, 2010

ቅዱስ ሲኖዶስ የብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስን ውግዘት አነሣ


(ደጀ ሰላም፤ ፌብሩዋሪ 16/2010)፦ ባለፈው ቅዳሜ ፌብሩዋሪ 13/2010 ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስን አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ ከዚህ በፊት አስተላልፎት የነበረውን ውግዘት ለማንሣትና ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት አባት አስከሬንም በኢትዮጵያ እንዲቀበር እንዲፈቀድ ከስምምነት መድረሱ ታውቋል። ውሳኔው ይፋ በተደረገበት በዛሬው ቀን እንደተረጋገጠው ከሆነ ውግዘቱ የተነሣው ከዚህ ዓለም ድካም አረፍተ ሞት ለገታቸው አባት ብቻ ነው።

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በፓትርያርክ ሹመት ጳጳሳቱ ለሁለት ከተከፈሉ ወዲህ ልዩነቱ በውግዘት ሳይነጻ ቆይቶ በስደት በአሜሪካ የሚገኙት አባቶች ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ “ኤጲስ ቆጶሳትን” ሾምን ካሉ በኋላ ውግዘቱ እንደተከተለ ይታወሳል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ትልቅ ርእሰ ጉዳይ ላይ መወያየቱ ብዙዎችን እንዳስደሰተ “ደጀ ሰላም” የተረዳች ሲሆን የብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ሥርዓተ ቀብር በጵጵስና ክብር ዞረው በተማሩባት፣ በክህነት በከበሩባት፣ ቀድሰው ባቆረቡባት በሀገራቸው በኢትዮጵያ የሚካሄድ ከሆነ ቤተ ክርስቲያኒቱ በቅርብ ጊዜ የገጠማት የአስተዳደርና የመከፋፈል ድቀት መድኀኒት ያገኛል ተብሎ ተስፋ እንዲጣል ያደርጋል።

ይሁን እንጂ ይህ መቀራረብና የስምምነት ዳር-ዳርታ ሁሉንም ላያስደስት እንደሚችል “የደጀ ሰላም” ተንታኞች የጠቀሱ ሲሆን “መለያየቱ እንጀራ የሆናቸው ቡድኖች” በተለይም የዚህ የመከፋፈል አባዜ ግንባር ቀደም መሪ ናቸው የሚባሉ አንዳንድ አባቶችና የፖለቲካ ትኩሳት ያላቸው ሰዎች በጉዳዩ አይደሰቱም፤ በዚህም ነገሩ እንዳይሳካ ሳንካ እንዲገጥም ያደርጋሉ ብለዋል።

በርግጥም ቅዱስ ሲኖዶሱ በዚህ ጉዳይ ላይ ተነጋግሮ በመወሰኑ ቅዱስ ፓትርያርኩም ሆኑ የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት የሆኑት ብፁዓን አባቶች መመስገን እንደሚገባቸው “ደጀ ሰላም” ታምናለች። በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከጊዜያዊ ግርግር ባሻገር ያለውን የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ለመመልከት መቻል ትልቅ ጥበብ ነው። ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ዛሬ ያሉበት ሁኔታ ሳይሆን የትናንት አገልግሎታቸው ሳይዘነጋ በክብር ለአገራቸው አፈር እንዲበቁ ማድረግ ይገባል። በውጪ የሚገኙ “የቅርብ ነን” የሚሉ በሙሉም የብፁዕነታቸው የመጨረሻ ማረፊያ ኢትዮጵያ እንዲሆን፣ በሚገባቸው ክብር እንዲሸኙ በማድረግ በኩል አዎንታዊ በሆነ መልኩ ይተባበራሉ ብለን እንጠብቃለን። ል ዩነቱ ይብቃ!!!! ግንቡ ይፍረስ!!!

40 comments:

Anonymous said...

It is great news,but the fake synod created by undercover heretics like melaku,leulekal,and others says that he is going to rest in Texas.I was hoping this would be a big opportunity to solve differences and bring up unity to our church.But I should have had a second thought that it could also be meant the death of undercover heretics who behind these fathers are always conspiring to dismantle our church. Whatever happens, now on these pseudo christians will never see that holy country again.Here now we are able to identify who the culprit is.His holiness has forgiven and lifted the condemnation,but the group here demonestrated its stubbornness.It is only to collect money from the people/those who go to their 'chrch' that they claim to be christians.So far I was criticizing aba Paulos,now on I will not blaim him.I now know the real cause of division is not only thirst for power,but heresy and may be even not believing in the existence of GOD on the part of these pseudo synod members.Shame on you all members of this fake synod.You are just like Juda who squanderred his chance of repentance.Even after Abune paulos is gone, nobody will allow you or accept you in that country.

tebarek said...

በግዚአብሔር መንግሥት መቀለድ በግዚአብሔር ላይ መዘበት እስከመቼ እንደሚቀጥል አላገባኝም
ወንድምን በህይወት እያለ ይቅር ማለት መፍታት እንደሆነ ጌታ አስተምሯል፤ ነገር ግን በዚህ አለም አስፈላጊነቱ ካብቃ በኋላ
ፈትቸዋለሁ ማለት የክርስቶስን ትምህርት ከንቱ ማድረግ ነው።

ይህች ቤተ ክርስቲያን ትለወጣለች ወደፊት በጌታ ወንጌል ሥር ትሆናለች የሚለው ተስፋችን እይተሟጠጠ ነው ።አሁን የምናየው የፖለቲካ አካሄድንና ብልጣ ብልጥነትን ብቻ ነው ።
ወንድምን በሕይወት እያለ አልፈልገውም ከሞተ ግን ሬሳውን እፈልጋለሁ ብሎ ምግለጫ ማውጣት ፖለቲካ እንጂ ክርስትና ሊሆን አይችልም።
ይህች ቤ/ክር/ በየጊዜው የምትፈጽማቸው ነገሮች እያደማን እንጂ እየፈወሰን አይደለም እኔና ይህ ትውልድ ቁስላችን የምሚደርቅበትን መንገድ መፈላግችን የማይቀር ነገር እየሆነ መጥቷል ።የሚሠራው ሁሉ መንፈሳዊ ሳይሆን አለማዊ ነው።

ትተዋቸው ወደ ሌላ አብያተ ክስቲያናት የሚሄዱወንድሞቻችንና እህቶቻችንን ደግሞ መናፍቅ እያሉ ይሳደባሉ እነርሱ ግን የፖለቲካ ሥራ እንጂ የኢየሱስ ክርስቶስን ሥራ ሲሠሩ ማየት ብርቅ ሆኖብናል።

እናምየሲኖዶሱ መግለጫ ምንም ዓይነት መንፈሳዊ ነገር የሌለበት
የፖለቲካ ሥራ ነው።
ጳጳሳቱ መንፈሳዊ ነን ካሉ የሞቱትን ሳይሆን በሕይወት ያሉትንስ ለምን ይቅር አላሏቸውም?
ውሸት ልጊዜው ቢያቆይ እንጂ እስከ መጨረሻ አያጸናም።

Anonymous said...

I am so amazed by how foolish the individual who wrote the previous posting. From what you posted it is obvious that you were with Aba Paulos to begin with. What are you trying to do? Have people believe you posting and follow your example? What a joke!!!!

If you summerize what Aba Paulos and the AA synod did is prove that the fact that they are not willing to deal with the church fathers in exile while they are alive. However, if they are welcome they are as long as they are dead. I must admit, it is also very Ethiopian to not deal with real issue while people are alive and then offer to jump in the MEKABIR when that someone is dead. We see that in our families and relationships ...

Remember, we all are Ethiopians and it is not the decision of the Synod in Ethiopia to allow of forbid any of us from deciding to be burried in the mother land, should that be our option.

There is no gain for Abune Zena if he goes to Ethiopia, but for the people who loved him, it makes every sense for his body to remain here. Aba Paulos needs the body for his political posture ...

Finally, I want to ask a silly question. There is one other Abune Zena in Ethiopia that Aba Paulos appointed bishop. In the church canon, you will not use a name of a living bishop unless you consider him dead and finished. So, Aba Paulos, who considered Abune Zena dead years ago, what business does he have with our beloved Abat? It would be very sad for the Abune Zena in Ethiopia to stand there and watch his name be called during the fithat service. Wouldn't it?

Anonymous said...

Selam Tebarek,short answer to your comment. In order to lift the condemnation of the rest of the fathers, there should be talk between them and the fathers in Ethiopia and they first need to relinquish this so called 'exile synod.This would be a good opportunity to do that,but the real players of all this mess undercover heretics did not want that to happen.'Regarding his grace the late abune zenamarkos,our church book 'fitha negest' orders the lifting of condemnation of a deceased bishop.
I am sure you or the fathers here who denied the peaceful rest of this father will feel remorse at the end of the day.

Anonymous said...

"Fight with the alive and make peace with the dead", I like it. I can assure those DS cadres that I will accept Abba Paulos's synod when Abba Paulos is dead. You like that?

Anonymous said...

'The benefit of being burried in Ethiopia?'
For true Tewahedo believers,resting in the soil where so many saints rested has mistrious,religious meanings.
We believe that the ashes of incense during liturgy,the soil in which holy water springs,saints burried,the caves saints prayed,their piece of garment/vestment,etc have healing power, and we get relief from our pain and sin. It seems you do not believe in this.Yes, you do not believe in unity.That's why I described those like you who aborted this chance of coming together for forgiveness undercover....
Is it ,perhaps, punishment by GOD not been allowed to rset in holy land-Ethiopia? He knows.

Anonymous said...

It is sad more than his death that he is going to be buried here.Even ordinary people's coffins are sent to their land of forefathers to rest.It is not foolishness or unreligious practice to do so.Any argument to defend this historical mistake of buring his grace here is nonesense.Both religious and cultural wise,it is WRONG! A SECOND DEADLY MISTAKE-the first one being establishing 'synod'.

Anonymous said...

It is sad to see this tragedy.i think,the decesion to buried Abune zena in Texas shows the deep hostility of American synod members to their Addis brothers.Any way we memnan are bleeding while non religious monks fight for supermacey.May be one day our church will become a super power in the world,We may not see that day because our heart is full of hostility and we have no room for peace and excuse.May God end this dark age

Anonymous said...

I hope the faithful will not tolerate this unEthiopian,unchristian and immoral measure of some who plan to resting his grace's body here.This action is out of touch of Ethiopians' norm by any parameter.And I believe that the majority of the people who really love his holiness abune ZenaMarkos will do something to convience the fathers here and those behind this shameful act to send his body to his native country Ethiopia for graceful,peaceful rest.

Sememen said...

Be ergitim chekkinew Abbatachinin ye qidstitun ager afer(Holy soil) ke kelekeluachew ,ezih yallut sewwoch lemecheresha gizie ke libbe yiwetalu!

Geta hoy! Ante libb sitachew,amen!!!

Anonymous said...

Is the disagreement of those people who are doing this act of burying his eminence here also with the soil of Ethiopia and Ethiopianity? It is so,I think.
I am stunned by their shameful action.
It is infact the tradition of many cultures too to send remains of people to their native country.Even ash of remains who burnt in accidents such as airplane crash,their body rest in their country of birth.
Shame,shame,shame....

Anonymous said...

Bemegemria ye Abatachenen nefes be Abrham,Yesak Yakob ategeb yanurelen elalehu.Keza beterefe gen mechem mut wekash ayargenena Aba Zena Markosem eko yechi betecrstian be andenetwa senta endatenor yebekulachewn astewsao maderegachen aneresa.Neger gin menalbat ahun yesemay abatachew fekad hono kehedu zend asmachewe enquan Be kidisst hager beyaref melakm neber neger gen hulgizem ye bete kristian andenet yemaywdu betat yemikoteru abatoch endene like selatnat habtemaram ena pastor melaku lefekedu alchalum.mine enlalen kidus paulos endalew manem yekome bemeslw endayewdek yetenkek newna lebonachewn geztew le betekristian andenet ye Abunen Zena mot mikniyat beyadergut teru neber.Lehulachnem lebonawen yeseten asrar bete krsianen yetalen

Anonymous said...

It is so funny.I am even laughing right now. I can't understand how these people are thinking. Are they going to say "Adminstration problem" not to send this father's body to holy land Ethiopia. Shame on the people, not only who decided to burry him in US, also the people who go to these churches. AWAGE... AWAGE...AWAGE... because of adminstration problem we have with Abune Paulos, Our dear Father's body is not going to Ethiopia. Does this father has any family who cares where his holiness's body should rest? I am sorry. Shame on those so called christians.

Anonymous said...

Dear Tebarek, do you know why the holy synod wegzetun yanesaw, because even though Abune zena Markos, did his part in dividing the church, recently he tried to contact the holy synod to make peaceful meeting. That counts. And may be if you don't know about 'Tselote fithat' ask if you go to church and if you can find a real Father who read 'Fitha Negest', that lifting of condemnation of a deceased bishop, is allowed, read, and if you don't know it is not sin, just ask. Thanks to our fathers who teaches us forgiveness.

Anonymous said...

መዊቶ ጻድቅ ይኮንን ረሲአነ

"ጻድቅ ሰው ከሞተም በሁዋላ በክፉዎች ላይ ይፈርዳል"

ወልደ ሚካኤል ዘጽርሐ ጽዮን said...

As pleasant as it feels hearing this good news, it is still painful to see this orthodox generation moving to deep separation based on ungodly thinking and imagination.

KaleHawaryat AA said...

“ሞቶሙ ለጻድቃን ሕይወቶሙ ( ዕረፍቶሙ) ውእቱ”

የብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ከዚህ ዓለም መለየት ለብፁዕነታቸው ታላቅ ዕረፍት ነው። ለእኛ ደግሞ ማስተማሪያ እንደሚሆን አምናለሁ። ምንም እንኳ ብፁዕነታቸው በተፈጠረው የምድራዊ አስተሳሰብ ግርግር ምንክንያት ወደ ውጭ አገር ቢሰደዱም ከዚህ ዓለም እስከ ተጠሩ ድረስ የነብራቸው መንፈሳዊ ሕይወት የተቀደሰ እንደሆነ ከማንም የተሰወረ አይደልም። አሁን ብፁዕነታቸው የት ይቀበሩ? ኢትዮጵያ ወይስ ሲያትል? የሚለው አባባል። እንደ ክርስትና እምነት ስንመዝነው መልሱ አጭር ነው። ይህም ሐዋርያ ወይም ክርስቲያን ይቅርና የሚቀበርበት ቦታ አግኝቶ ባያገኝም የትም ቦታ ቢወድቅ ወይም ቢቀበር የሚቀርበት ጥቅም የለም። ኢትዮጵያ ቢቀበሩ ምናልባት በሰው ሰውኛ አባባልና ብሎም ሰው በተወልደበት አገር ቢቀበር መልካም ነው ቢባልም። በምድራዊ አስተሳሰብ ካልሆነ በስተቀር ለሟቹ የሚሰጠው ጥቅም ይህ ነው ሊባል የሚችል ነገር የለም። እንደ ተባለው ግን አስከሬናቸው ወደ ኢትዮጵያ ቢመጣ መልካም ነው። ምናልባት ኢትዮጵያ ላለነው መልካም ሊሆን ይችላል። መቃብረ ቅዱሳን በረከት ነውና። ለእርሳቸው ግን ምንም የሚጨምርላቸው ነግር የለም። ሌላው ቅዱስ ሲኖዶስ ውግዘቱን ማንሳቱ ለብፁዕነታቸው ምንም ፋይዳ ባይፈይድላቸው ሰላምና ፍቅር እንዳይሰፍን ይጠሩ ለነበሩት አካላት ተስፋ የሚያስቆርጥና በሕይወተ ሥጋ ካሉት አባቶች ጋር እርቅ እንዲመሠረት በር ይከፍታል የሚል እምነት አለኝ።
የውግዘቱን መነሳት በቃለ እግዚአብሔር ሚዛን ከመዘነው ግን ቅደም ተከተሉን ያልጠበቀ ለይስሙላ የተደረግ ውሳኔ ነው ማለት ይቻላል። ምክንያቱም ይቅር ይቅር መባባል በሕይወት ሥጋ እያለን እንጂ ከሞት በኋላ የሚደርገው እርቅም ሆነ ከውግዘተ መፍታት ቀድሞም መሠረት ያለነበረው ውግዘት እንደ ሆነና ለይስሙላ እንደተደረገ ብቻ ያሳያል። ሌለው ቅዱስ ሲኖዶስ ውግዘቱን ማንሳት ያለበት ከሁሉም ላይ ነው እንጂ በሞት ከተለዩ አባት ብቻ መሆን የለበትም። በመሆኑም ቅዱስ ሲኖዶስ በጀመረው ቅዱስ ተግባር ጊዜ ሳይውስድ በውጭ ካሉት ሊቃነ ጳጳትና ካህናት ወዘተ. የሰላምና የፍቅር ጥሪ ሊያስተላልፍ ይገባል። ይህ ካደረግ ብቻ ነው። ትክክልነቱ የሚታወቀው እንጂ አሁን በወሰነው ብቻ ትክክል ሠራ ለማለት አያስደፍርም። ስለዚህም ሁላችን የተለያዩ አባቶቻችን ወደ ሰላም እንዲመጡና ዕርቅ እንዲመሠርቱ መጸለይና ድርሻችንም መወጣት ይጠበቅብናል። የብፁዕነታቸው በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን።
ቃለ ሐዋርያት ነኝ ከአዲስ አበባ

Anonymous said...

እኔ የማይገባኝ የአባታችን ኢትዮጵያ ሄዶ ማረፍ ለኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ የሚሰጠው ጥቅም ምንድን ነው? ለእኔ እንደሚገባኝ የሚሰጠው ጥቅም ያለ አይመስለኝም ነገር ግን ለእርሳቸውም ሆነ ተምረው እዚህ ለደረሉባት ቤ/ክ በተጨማሪም ለአገለገሉትም ሕዝብ ታላቅ ክብር ከማጎናጸፉ በስተቀር። ስለዚህ አሁንም ፖለቲካና ሃይማኖትን ለይተው ለማየት ላልታደሉት አስተያየት ሰጪዎች የምለው ነገር ቢኖር ምናል ቤተክርስቲያንዋን ለቀቅ ብታደርጉ? "የፖለቲካ አካሄድ" ምናምን እረ ተው ይበቃል.ሲሆን ሲሆን የተወሰነው ውሳኔ ይበል የሚል ነው ማለት ኣና ለቀጣዩ በህይወተ ለሚኖሩትም አባቶች ይሄው መቀራረብ እንዲቀጥል መጸለይና መምክር ሲገባ የምን በሚነድ እሳት ላይ ጋዝ ማርከፍከፍ ነው. እባካችሁ ይሄ ነገር ይብቃን። አምላክ ያስበን

21_21 said...

ሰላም ወገኖቼ! ብፁዕ አባታችን እንደ ሐዋርያትና ሰማዕታት የትም ቢቀበሩ ለሳቸው ለውጥ ላይኖረው ይችላል:: ነገር ግን 1:1 የቅዱሳን ቦታዎች ለምሳሌ ደብረ ሊባኖስ ቃል ኪዳን ያለው ቦታ ነው ይባላል እንኩዋን እንዲህ ዓይነት የቤተ ክርስቲያን አባት ይቅርና በዚያ የተቀበረ ሁሉ ነፍሱ ይማራል የሚል ቃል ኪዳን አለና እንዴት ታዩታላችሁ?

nafkoteyegetalij@gmail.com said...

እውነትም ቃለ ሃዋርያት እግዚአብሔር አብዝቶ ይባረክህ እንዳንተ አይነት ሰዎች ይብዙ

ሙሉ በሙሉ ከአንተ ሃሳብ ጋር እስማማለሁ

"የውግዘቱን መነሳት በቃለ እግዚአብሔር ሚዛን ከመዘነው ግን ቅደም ተከተሉን ያልጠበቀ ለይስሙላ የተደረግ ውሳኔ ነው ማለት ይቻላል። ምክንያቱም ይቅር ይቅር መባባል በሕይወት ሥጋ እያለን እንጂ ከሞት በኋላ የሚደርገው እርቅም ሆነ ከውግዘተ መፍታት ቀድሞም መሠረት ያለነበረው ውግዘት እንደ ሆነና ለይስሙላ እንደተደረገ ብቻ ያሳያል። ሌለው ቅዱስ ሲኖዶስ ውግዘቱን ማንሳት ያለበት ከሁሉም ላይ ነው እንጂ በሞት ከተለዩ አባት ብቻ መሆን የለበትም። በመሆኑም ቅዱስ ሲኖዶስ በጀመረው ቅዱስ ተግባር ጊዜ ሳይውስድ በውጭ ካሉት ሊቃነ ጳጳትና ካህናት ወዘተ. የሰላምና የፍቅር ጥሪ ሊያስተላልፍ ይገባል። ይህ ካደረግ ብቻ ነው። ትክክልነቱ የሚታወቀው እንጂ አሁን በወሰነው ብቻ ትክክል ሠራ ለማለት አያስደፍርም። ስለዚህም ሁላችን የተለያዩ አባቶቻችን ወደ ሰላም እንዲመጡና ዕርቅ እንዲመሠርቱ መጸለይና ድርሻችንም መወጣት ይጠበቅብናል። የብፁዕነታቸው በረከት ከሁላችን ጋር ይሁን።
ቃለ ሐዋርያት ነኝ ከአዲስ አበባ"

Anonymous said...

I do not think they are beurying him hear they will put him in a museum so every body is going to vist his body untill one person from Gonder held the patriaric postion then they will take him back to eth to burry him .That is wierd.Any way since the synod is under control of some kahinat meahiber like u know no need to call their name they will never think right.

Anonymous said...

'Kalehawariat and Ewunet' your comments clearly tell how much ignorants you are at Orthodox teachings.According to your saying,I was able to infer that pilgrimage to Jerusalem where Lord JESUS CHRIST was born,taught,crucified,buried and resurrected is useless.Poor!Your belief, for sure, is not Tewahedo.You are caught in your words and notion that saints do not intercede.But they do both before and after death.Soil from Elsa's grave raised a dead body!How many holy fathers/saints rested in Ethiopia?So many.Just like lucky ones get buried in Holy Land,for those of us who believe in the healing power of saints,their remains and their intercession,resting beside them gives healing to our soul.
As to the lifting of the condemination,what the holy synod has done is right.The fathers here in north America did historical mistakes by establishing a 'synod' which is illegal and ordained bishops.They first need to renounce this act of violation of the church's canon.Instead, they preferred to commit a third historical,deadly mistake by planning to rest Aba Zenamarkos's body here.
Regarding the comparison with the early christians,
this immoral act can not be compared to the lives of marthyrs or the apostles.Those forefathers of ours were murdered by the enemies of CHRIST then.This is a totally different era.Anything that we do now is our own choice.The choice you people made is WRONG and UNFORGIVABLE! What
You are saying in action is that even with death, when people traditionally and religiously forgiven each other,we never forgive.You are judged now for you do not believe in the Son of the Father.Yes you are HERETICS!Yes you are anti-tewahedo!You DO NOT like Ethiopia,you do not like even its soil!There is no other reason to justify this act of shame.

Anonymous said...

ሰላም ደጀስላም!!!

እናንተ ለሞተ ሰው አዝናችሁ ሳይሆን የፖለቲካ እንጀራችሁን ለማብሰል ጥሩ አጋጣሚ ያገኛችሁ ይመስላል።

እውነተኞች ብትሆኑ ኖሮ ይህን መወያያ መድረክ ስትከፍቱ አድሎአዊነታችሁን ከመግቢያው ባላስቀመጣችሁ ነበር።

ለመሆኑ ህግ የጣሰው በጠመንጃ አፈሙዝ ኦርቶዶክሳዊ ቀኖናን ጥሶ የተቀመጠ በለጠመንጃ፤ የፖለቲካ ቁማርተኛ ነው ???ወይስ ተሳዳጅ ምስኪን አባቶች ናቸው። ምነው ካለፈው ብትማሩ። ስንት ስታጎበድዱ ኖራችሁ መጨረሻ ብትንትናችሁን ስላወጧችሁ አሁን ይህችን ቀዳዳ አገኛችሁና አኒህን ቅዱስ አባቶች ህግ የጣሱ እያላችሁ፤ ኤጲስ ቆጶሳትን የሾሙ እያላችሁ ታናፍሳላችሁ። ዎዮላችሁ !!!

ይህች እናት ሐገራችን ኢትዮጵያ አሁን የባለ ታጣቂዎች ብትሆንም ጊዜው ሲፈቅድ ግን የዜጎቿ ትሆናለች።

ለማጠቃለል ግን ውግዘትን በተመለከተ የተወገዙት አቡነ ጳውሎስ እንጅ እነ አቡነ ዜና አይደሉም ። የተወገዘ እንዴትስ ፍታት ሊፈታ ይችላል። ቅዱሱ አባት በተቀደሱት አባቶች ነው የሚጸለይላቸው።
ተግባባን።

ካሰባችሁ ደማቸው ሜዳ ላይ በሲይፍ የተቀላውን ባህታዊ ፈቃደን ውግዘት አስነሱላቸው።

ነገ ደግሞ እነዶክተር ብርሃኑ ጥፋታቸው ይቅርታ ተደርጎ ሞት ቅጣት ተነሳላቸው ስትሉ እንሰማ ይሆናል። በጠላት ወረራ ጊዜ ባንዳነት።ት ነበር ሀገራችን የጎዳት ከዋናው ጠላት በበለጠ። አሁንም ባንዳነት ይቁም።

ኢትዮጵያ በእግዚአብሄር ፈቃድ ትንንሳኤዋን እናያለን። ያኔ ከትዝብት ለመዳን አሁን ከባንዳነት መኮብለል ያስፈልጋል።

ሁሉም ያልፋል።

Ethio Coup plotter said...

በቅድሚያ አቡነ ፓውሎስና ጓደኞቻቸው ከነብስ ገዳዮች ጋር የተባበሩ ወንጀለኞች ናቸው። እነሱን ብሎ አወጋዥ እና ውግዘት አንሽ?

Anonymous said...

You have made it clear that you hate Ethiopia.For real you do not like that holy country.Ethio coup plotter and the anonymous above him, you are hopless creatures.You and your likes are behind the fathers here to serve Ethiopia's enemies who are also our church's enemies.You traded the love of your country with a piece of burger and your religion to heresy.Shamful!

Anonymous said...

ጥሩ ብለሃል!

መጀመሪያ ከራስህ ተሟግተህ እውነቱን ተናገር
ጋሻ ጃግሬነትህ የትም አያደርስም
ከመሆን በስተቀር የህሊና ሸክም!

ተሳስታችሁ እንኳ ወያኔነትን መኮነን እንደ ሃጢያት የምትቆጥሩ ተገፊዎችን ስትኮንኑ በዎያኔነት ጥላ ስር ተከልላችሁ ስለመሆናችሁና ያ በሜዳ ላይ እየተቀላ ደመ ከንቱ የሆነውን ኢትዮጵያዊ ሁሉ የማሰቢያ ጊዜ ማጣታችሁ ያሳዝናል።

ሁሉም ያልፋል

Anonymous said...

Who do hate? Individuals or their deeds?You hate people,I hate their wrong deeds.In christ I love you,but I disagree with your idea/belief as it is unEthiopian,unorthodox.By the way,you changed the topic to silly political comments.When are you going to come to your conscience?
Their mistakes can not make you mistake right.

Anonymous said...

AMEZING

"ቃለ ሐዋርያት ነኝ"ከአዲስ አበባ RASUN "KEF KEF YEMIADERG ZIKZIK YILAL, RASUN YEMIAWARD GIN KEFKEF YILAL." SAY MOT KEMOTE YADNEN

Anonymous said...

I am so glad I do not have to deal with this loud mouth uneducated and yet who claim to know everything.

They are quick to open their filthy mouth to condemn and insult others as "ignorant" "fools" “unEthiopian” “unorthodox”

They preach us Orthodoxy and yet their knowledge is shallow.

Some keep on saying “holy Ethiopia” where millions are perishing because of hunger and many millions are still not preached the Gospel of Jesses Christ. They’re bickering & fighting among themselves, like their fathers and their fathers before them, making it possible for Muslims to overtake and decimate Christian Ethiopia.

The Church and all of us should work and pray for true Shepard because those we see to day, as Saint Paul said, they “ seek their own, not the things which are Jesus Christ's, Phil. 2.20, 21.

Anonymous said...

ጋሽ ቃለ ሃዋርያት ወይም እውነት ለምን ሁለት አስፈለገህ ።

gonderawit said...

እውነት
አስር አይነት ስም መጠቀም አንተነትህን አይለውጠውም። ባንተ ጭንቅላት ሰውን ማታለል ትንሽ ሳይከብድህ ይቀራል ብለህ ታስባለህ።

nafkoteyegetalij@gmail.com said...

አሁንም ነገም ለዘለዓለም
ቃለ ሃዋርያት እግዚአብሔር ይባርክህ እንደሱ በትህትና ማውራት እግዚአብሔር ያድለኝ እሱን ባረገን ግን እሱነሃ ካላችሁኝ የማሀበረ ሰይጠን ርዝራዦች አይደንቀኝም ምክንያቱም እዚህ ብሎግ ላይ ስም እየለዋወጠ 15 አይነት ጽሁፍ የሚጽፈው እራሱ ባለቤቱ አቶ ዳንኤል ክስረት እንደሆነ በመረጃ አውቃለሁ ትንሽ የሚቃወሙዋችሁ አንድ አይነት ሲሆንባችሁ ትደነግጣላች ጥሩ ጭንቅላቶች አነድ አይነት ሃሳብ ያፈልቃለሁና እባካችሁ የአፍኒንና የፊንሃስ ልጆች ከፊታችን ዘወር በሉ
በነገራችን ላይ አዎ እይንዳንድሽ ኢትዮጵያን የምትወጂ ከሆነማ ለምን በስደት መውጣትስ አስፈለኘ ወሬ ከማውራት ወደ ሃረግ ባት መግባ!

ለነገሩ ከምድረ ጨዎ ጋር አፍ መካፈት ዋጋ የለውም

አንድ ወንድሜ አስቀምጦታል በስደት ያለው ሲኖዶስ ህጋዊ እንደመሆኑ መጠን ከህገ ወጡ ጋር በጭራሽ መደራደር አይችልም መጀመሪያ እነዚያኛዎቹ ህጋዊ መሆን ይጠየቅባቸዋል ወትሮ እንደአንዳን ለሆዳቸው ያደሩ ሌቦች ሃሳብ ምን አለበት ቢታረቁ ይላሉ ደደቦች በስደት ያሉት አባቶች የግለሰብ ጸብ የላቸውም ከሃገራቸው የወጡት ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተጣሰ ብለው ነው እንግዲህ እስከምናየው ድረስ እውነተኛወ ሲኖዶስ ግልጽ ነው አንዱ በሊቀ ካህኑ በኢየሱስ ይመራል አንዱ ደሞ በሊቀ ካህኑ በመለስ ዜናዊ የመራል ስለዚህ ቀኑ እስከሚነጋ ምረጫው የናንተው ነው።
ይቆየን

Kalehawaryat AA said...

እውነት!
እባክህ እውነትን አያውቁም ተዋቸው፡ እነዚህ እውነትን አውቀውና በእውነት አምነው፤ እውነት ነፃ እስከ ምታወጣቸው ድረስ ዓይነ ህሊናቸው የታወረ ስለ ሆነ እንደ እነዚህ ከመሳሰሉ ሰዎች ብዙም አትድክም። ነግር ግን ኃላፊነት ተሰጥቶናልና ተግባራቸውን እየተጸየፍን

Kalehawaryat AA said...

እውነት!
እባክህ እውነትን አያውቁም ተዋቸው፡ እነዚህ እውነትን አውቀውና በእውነት አምነው፤ እውነት ነፃ እስከ ምታወጣቸው ድረስ ዓይነ ህሊናቸው የታወረ ስለ ሆነ እንደ እነዚህ ከመሳሰሉ ሰዎች ብዙም አትድክም። ነገር ግን ኃላፊነት ተሰጥቶናልና ተግባራቸውን እየተጸየፍን እውነትን አውቀው ወደ እውነት እስከሚመለሱ ድረስ ልንጸልይላቸው ይገባናል።
ሰላማዊ የሆነው ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላሙን ያብዛልን። በድጋሜ ቃለ ሐዋርያት ነኝ ከአዲስ አበባ

nafkoteyegetalij@gmail.com said...

አሜን ቃለ ህይወት እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል!!!
አይዞህ በርታ

ሃይላeዝጊ said...

ሕግ ጥሶ ሕግ አስከባሪ መሆን ይቻላልን????

ሀገር ቤት አለሁ የሚለው በነ አባይ ፀሀይ የሚመራው ሲኖዶስ ቀኖና አፍርሶ በዎያኔ የሚመራ፤ ኤርትራን ያስገነጠለ፤ ባህታዊ ፈቃደስላሴን በታቦት ፊት በጥይት ያስገደለ፤ በአደባባይ እየሱስ ህዝብ ሲጨፈጨፍ ዝም ብሎ የተመለከተ፤ በዪሀንስ ወልደነጎድጓድ የሚያስቀድሱ ምእመናንን በዎታደር ያስደበደበ፤ ነፍስ አድኑን ብለው የተጠጉ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ለደብዳቢ ፖሊስ አሳልፎ የሰጠ፤ በ97 በግፍ ለተጨፈጠፉት ወገኖች ጸሎተ ፍትሃት ያላደረገ፤ ለሀገር ተቆርቁረው የዎያኔን ግፍ ተቃውሞ ያሰሙትን የወገን ልጆች ያለአግባብ ሲታሰሩ ያላወገዘ፤ የሲኖዶስ አባላት ነን ተብየዎች በጥቅም ምክነያት ተጋጭተው ቤታቸው በወታደር ሲደበደብ በጥንት ቅዱሳን አባቶች ተከብሮና ተቀድሶ የነበረውን ቤት የወሮበላ መናሃሪያ ሲሆን ጥፋተኞች ለፍርድ አለመቅረባቸው የቅርብ ጊዜ አሳዛኝ ትዝታ ነው።
የሲኖዶስ አባላት ነን ተብየዎችም በየጊዜው በንጽህና ጉድለት የሚከሰሱ ወንጀለኞች ናቸው። ገመናቸውን አደባባይ አውጥተው መጽሀፍ እያሳተሙ ሲሰዳደቡ ማየት ለቤተክርስቲያኗ ክብር አለመቆማቸውን የሚያሳይ ነው።
ታዲያ እንዲህ ያሉ ቅንጣት ክህነታዊ ሞራል የሌላቸው ናቸው በስደት ያሉትን ብጹዓን አባቶች አወገዝናችሁ፤ ፈታናችሁ እያሉ የየሚባርቁብን።

ቸር ይግጠመን!

ኃይለእዝጊ

tirukal said...

huletum yetewgagezu silehonu khuletum ga
menor aychalm geleltegna none yemilut sayshalu aykerum libonaye yetekebelachew tinish enesun new balesinodos none yemilut gin kihnetachewn bemewgagez silaserut liasrum lifetum aychilum bemejemeria enersu erasachew mefetatat alebachew eskezaw gin mistrate betekirstian lemefesm geleltegna none yemilut yishalalu mikneyatum yetewegz yelebachewm yebezuwochum kihnet babune baslios yetesete new techenke techenke efoy yalkubet mela yih new bekagne huletegna ketewgagezut betekirstian heje alkafelm simotu mazene silemayker personal erdatayen alnefgachewm
yemiasabd gira yemigeba guday new woy geta bimetana bigelaglen minalebt

Nabute said...

“ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ” ማቴ 7 ፤ 15

If u want to know who really the likes of 'EWNET' (actually HASET) and those of the influencial members of the fake synod (North America) please watch these video clips.

http://www.ethiotube.net/video/7935/Ethiopian-Orthodox-Tewahedo-Vs-Tehadiso-Part-116

Anonymous said...

I grew up in a Church that goes back more than thousand years in its existence. My ancestors for generations served as priests traveling from one part of the country to the other carrying the 'Tabot' and the cross. They only served God by rejecting what their contemporaries pursued in life such as power, wealth and fame. Today, I am a bystander and spend my days wondering if this is the Church that my ancestors gave their whole life for. I am disgusted by those stories of individuals who have to do nothing with the Church and the message it is carrying. Our ancestral Church became the playground of people who once denied the existence of God and attempted to destroy it. They are fomenting hate and bitterness among servants of God and its people. Please get out of the Church and fight elsewhere and leave the Church alone. As our holy fathers may have some disagreements between them and they also are capable of how to resolve it. They know forgiveness because they are serving the forgiving God. Above all this is very clear to them. The disagreement between those who serve in the Church and those lay individuals who bring their issues into the Church are completely different. Be ashamed of yourself and stop meddling. With your hateful language you are only serving the devil and not God. Our fathers abroad and those who are within the country understand each-other and are choosing forgiveness over bitterness. They are visiting and exchanging messages in a manner expected from spiritual leaders. I admire all of them. May God protect the Orthodox Church!

Anonymous said...

Ebakacehu, wedemisirak temeliketu. you all wasting your time through "gunch alfa weg". yemedan kenieko ahun newu! silemin letelat fanta tisetalachihu, gobez?. besewu layi mefired deg ayidelem, hulum endesiraw yikefelewal enji sewu maninim ayikonnm. Please wederasachin enimelket. Ye'ethiopia betekiristian menfesawi bereket ke'egna alfo lehulum alem yiterfal. this is only the treaky from the very enemy of tsion i.e. satinael. when we come to the mother church, we must put-off our unpolished shoes. egna bemayitekimen neger sinikeraker alemu hulu titon berere. ebakachihu mi'emenan ahununu yeliyunetin menfes ke'egna enarik. betekiristian andit nat!

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)