February 14, 2010

ሰበር ዜና/Breaking News - አሜሪካ የሚገኙት ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ አረፉ


(ደጀ ሰላም፤ ፌብሩዋሪ 13/2010)፦ ከሀገራቸው በስደት ወጥተው በአሜሪካ ይኖሩ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ዛሬ ማረፋቸውን የቅርብ ምንጮች ገለፁ። የፓትርያርክ ለውጥ ከተደረገበት ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ በስደት የነበሩት ብፁዕነታቸው ዛሬ ያረፉ ሲሆን ዕረፍታቸው የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ሲናፍቁ ለነበሩ በሙሉ ታላቅ የቅስም መሰበርን ፈጥሯል።

ብፁዕነታቸው በዘመናዊው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ይከበሩና ይወደዱ ከነበሩ አባቶች አንዱ የነበሩ ሲሆን በተለይም የቅርብ ጓኛቸውና የሃይማኖት ወንድማቸው የነበሩት ታላቁ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የሚያደንቋቸው አባት እንደነበሩ ይታወቃል።

ብፁዕነታቸው በቤተ ክህነት ፖለቲካ ተጠልፈው የ”ስደተኛው ደጋፊ” ከመሆናቸው በስተቀር በቤተ ክህነቱ አበው መካከል ለተፈጠረው ልዩነት መፍትሔ ይሆናሉ ተብለው ተስፋ ይጣልባቸው ነበር።

የብፁዕነታቸውን ነፍስ በደጋጎቹ አባቶች ሀገር፣ ከአባቶቻችን ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር ያድርግልን፤ አሜን
24 comments:

መልአከ ሳሌም አባ ገብረኪዳን እጅጉ said...

የብጹዕ አቡነ ዜና ማርቆስን ማረፍ ሰምተን በሁኔታዉ በጣም በጣም ነዉ ያዘነዉ እግዚአብሔር ላገራቸዉ አፈር ቢያበቃቸዉ በጣም ደስ ባለን ነበር አሁንም ያባታችን በረከት ይድረሰን ለቀሩትም ለሀገራቸዉ መሬት እገዚአብሔር ያብቃቸዉ የአባታችንን ነፍስ በመንግስቱ ይቀበልልን።

Anonymous said...

May GOD give him eternal rest and his death be a reason to bring back unity for our church.

Anonymous said...

Sad news. Satan planted this big wall of division among the fathers which deprived most of us in both side of the insel the chance to to get to know our fathers in depth and learn from them. It was my longer wish to sit beneath his father and hear most importantly his experience as a church leader during the Dergue period. I still wish to meet the rest of the father who has the same level of experience.

May his soul rest in peace, Amen!

derek said...

How sad news!
Oho Almighty!give rest to his soul in paradise besides of Abraham, Isaak & Israel.

Dereje

Holland

21_21 said...

Nefsachewun ymarlin. He did a lot for our church from the very beginning. But what is the reason for his death?I mean is it a normal death or something else?

Maryisaq said...

The death of our father Abune Zenamarkos is very sad news.As per informations from Dejeselam large number of followers of our Church were put strong trust on his role to bring a solution 4 the exiting conflict bln our fathers, unfortunately he dead.However,GOD will prepare another Abune Zenamarkos 4 his own mission(2 regulate the conflict)because "EGZIABHIER erasun yalemlikt aytewum" .Any ways if he was with that holly idea his blessed soul went to her Shepherd.Finally, let me ask U who knows sth:-is it a natural death?
May his soul rest in the hands of GOD.

Anonymous said...

please every body who had chance to comunicate with peoples around try to send the body of our holly father to ethiopia.
May God give him him eternal rest.

ሰይፈ ሚካኤል said...

አምላክ ሆይ የአባታችንን ንፍስ ተቀበልልን...
እኛን ልጆችህንም ያለኣባት አንቀር ዘንድ ላሉት ልቦና ሰጥተህ በፍቅርና በሰላም በቤትህ ሰብስበን
ሳይማሩ ሊቅ, መምህር,... መባባል እየገነነ በሔደበት ዘመን ሃይ የሚል አባት አታሳጣን

መዘሙረ ዳዊት said...

መዘሙረ ዳዊት

በማህበረ ቅዱሳን ተቀነባብሮ በዘመድኩን በቀለ አፈ ቀላጤነት ያስደመጣችሁን የስም ማጥፋት ዘመቻ ኢክርስቲያናዊ ድርጊት፣ አንገት የሚያሰደፋ አሳፋሪ የሆነ በምቀኝነት ላይ የተመሰረተ ዘመቻ እንደሆነና ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን አስባችሁ እንዳልሆነ ጠንቅቀን እናውቃለን !
ስለዚህ እባካችሁ እርስ በርስ ከመካሰስ ይልቅ ሁላችንም ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን መሰራት የሚገባንን በጊዜያችን ሰርተን እንለፍ;; የጠላት መሳለቂያ አታድርጉን ;;

Anonymous said...

Realy sorry...

Is that the title we are discussing now - ato "Mezimur"?....why you mix two unrelated things?

Please let us comforting each other on the death of our Father!

Unity1 said...

Our Lord and Saviour Jesus Christ, please put his soul next to Abraham, Isaak & Israe.

hiwot said...

May God rest him in peace.
May this be a reason for other fathers to end the separiton of our church. I wish his body rest in Ethiopia.

Nefes Yemar said...

le Abatachen nefes yemar belanale...bezum selemalawuqache bezu metsaf alefelegem... I fell that is realy sad news...

I like to say to Mezemur Dawit... please do not write what is not similar to the story... it is nothing to do with the issue right here. please open up your mind.

Rest in peace.
Thanks

Unknown said...

Breaking news
The effort to rest his body in Jerusalem failed as Abune Paulos refused after he called Abune Matyas> Abune Samuel is here since yesterday and he agreed too not to transfer him from Seatle to Jerusalem.
By the way why people try to transfer him it is butter to burry him there.

Namrud said...

የብፁዕ አቡነ ዜና ዕረፍት የቤተክርስቲያናችን ትንሳኤ ይሆናል ብለን
እናምናለን።በጌታ ሞት ሄሮድስ ከጲላጦስ እንደታረቁ። አበው ይብቃን ማሩን እና ታረቁ ሞት አይቅደማችሁ። አደራ የአባታችንን አጽም እዚህ እንዳታሳርፉ ያዕቆብ ለዮሴፍ እንዳማለው እንማጸናችኋለን ከአባቶቻቸው ጋር እንዲከማቹ አጽማቸውን ወደ ሀገር ቤት ሸኙ እርግጠኛ ነኝ በሙት አካል ላይ እትከራከሩም የአቡነ ይስሐቅ ስህተት እንዳይደገም።
የአባታችንን ነፍስ ከደጋጎቹ ይደምርልን።

Anonymous said...

+++
አይይይይይይይ
ሰዉ ከንቱ ፣
ምነዉ ሞት ላይቀር ያ ሁሉ መከፋፈል
ኸረ በድንግል አባቶቻችን ይኸ ነገር በተራ የሚደርስ ነዉና ከዛ በፊት እባካችሁን ቤተ ክርስቲያቻችንን አንድ አድርጉልን

አባታችን የአብርሃም አምላክ ነፍስዎን በገነት ያኑርልን

SendekAlama said...

+++

የቤተ ክርስቲያናችን አባቶች እርስ በእርሳቸው ከማዕርጋቸው ተሰራርዘው አቶ እገሌና አቶ እገሌ በተባባሉበትና ልጆችን ያለ አባት ባስቀሩበት ርምጃቸው ለሁለቱም ወገኖች ያልታያቸው እንዲህ አይቀሬው ሞት ሲመጣ የህዝብን ጥያቄን መመለስ ከባድ እንደሆነ ነው። እንደ መንደር ኮበሌ - በመቃብሬ አትቁም በመቃብርህ አልቆምም- አይነት እልህ ተጋብተው ከዕርቅ በፊት አረፈተ ዘመን ሲገታን እንኩዋን አባ ጳውሎስ ሌላው ቢቀር እንኩዋን በዚህ ምክንያት ሊመጣ ስለሚችል የዕርቅ መንፈስ ሲሉ ለክብር ቀብር እጃቸውን ቢዘረጉ ምን አለበት? በውጭ ያለችውን ቤተ ክርስቲያንን ፓትርያርክ የመሆን ህልማቸው እስኪሳካላቸው ድረስ አግተው የያዙዋት አባ መልከጼዴቅስ ምናለ ድካምና መከራ ነው በተባለለት ዘመናቸው አምላካቸውን አሳዝነው ከመሞት ይልቅ ይህ ክስተት ለእርሳቸው ደወል ሆኖ ተንስዑ ቢላቸው?

Anonymous said...

Well it is very sad newes,but his body should not rest in Ethiopia or Eyersualem.He (abune zena markos)did participate in breaking our one synodos in to 2 so he has to pay the price,let him be barried in kidist Hager Seatle or wt ever states here in america,i believe Abune Paulos did the wright thing to deny his berrial in Eyersualem or ethiopia.They thought that this day will never come,they were spoiled by LA tehadiso movement organized by Abba Welditinsae and both"churches"in la they were talking trash about our church in their as they called it good times,i bet they bending now to the only synodos in addis ababa.

Anonymous said...

denver
The Lord is our shipered we have no fears even if we walked through the shadow of death. As the Lord Jesus is taking one of His sons, we ask Him to give us wisdom to understand death. No one has died in Jesus but has eternal life. So, my sisters and brohers in ethiopia and abroad, let us rejoice the death of our father Abune ZeneMarkos. Sing a song to God, give thanks to Him for giving us such strong man in His faith. May the Lor give us some one like him. Lord I thank you for not foresaken Ethiopia. Unite us God, please give us back the love of our forefathers. I love you all.

ብርሃኑ said...

እግዚአብሔር አምላክ ነፍሳቸውን ይማርልን፡ ወደ ቤተመንግስቱም ይውሰድልን።

ብዙ የማናውቃቸው አባቶቻችን አገር ቤትም ሆኑ በስደት ስላሉ፡ ውድ ደጀሰላማውያን በዚህ በጾም ጊዜ በጎ የሆነውን የህይወት ታሪካቸውን ብታስተዋውቁን ምን ያህል መንፈሳችንን ለማጠንከር በረዳን ነበር። የሚሰድቡን፡ የሚጠሉን፡ የሚያቃጥሉንና የሚገድሉን ሞልተዋል፡ ወራቱን፡ አመቱን ሙሉ እናያቸዋለን፡ እንሰማቸዋል... ስለዚህ በእግዚአብሔር፡ በዚህ በተቀደሰ ጊዜ ፡ በትህትና ሊያስለቅሱንና ሊያስደስቱን፡ ተስፋ ሊሰጡን፡ ትብብርና ፍቅር ሊፈጥሩልን የሚችሉትን ሃሳቦች ብታቀርቡልን ምን ያህል ባስመሰግናችሁ።

nafkoteyegetalij@gmail.com said...

አይ ተዋህዶ ምን ይሆን መጨረሻሽ?
በጌታችንን እና በደመድኃኒታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ውድ ወንድሞቼ ለምትሆኑ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን በሙሉ።

የጌታ ፍቃድ ይሁን ብለን ዝም አልን።

በእውነት የታላቁ አባታችን የብፁዕ አበነ ዜና ማርቆስ እረፍት እጅጉን አሳዛኝና ቅስም የሚሰብር ዜና ቢሆንም የምናዝነው በሞት ስለመለየታቸው ሳይሆን የሚናፍቁትን የቤቱ ክርስቲያን አንድነት ሳያዩት በማለፋቸው እና ይኸቺ አይዞሽ ባይ የሌላት የጌታ ሙሽራ አባቶች እያሉቁ ብቻዋን በመቅረቷ ነገ በኛ ላይ ወይም በእምነታችን ላይ ይደርሳል ብለን የምንፈራው አስከፊ ጨለማ መታየት ስለጀመረ ነው። በእውነት ብጹዕ አቡነ ዜና ማርቆስን ለማታውቋቸው ወይም እናንተ በሰይጣን ጆሮ ያልሆነ ነገር ነው ተብላችሁ ሰምታችሁ ሳታቋቸው ለቀራችሁ ሁሉ የሳቸው ማንነት ፈጽሞ በኔ በጨዋው አንድደበት ሊነገር አይችልም። ግን አንድ ነገር አውቃለሁ ታላቁ በጸሎት የጠገው ዛፍ ከተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን መሃል ተገነደሰ። እንግዲህ የምናመለከው አምላክ ስራው ድንቅ ስለሆነ ለቀሩት እውነተኛ የተዋህዶ ልጆች ሰላም ይስጥልን ይቺ ቤተ ክርስቲያን በጥቅም ፈላጊዎች ምክንያት ስትዋዥቅ የሚያያት እሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ሰላም ይስጣት በተለይም በስደት የሉት አባቶች ጠዋት ማታ በባዕድ ምድር ህዝቡን እየመሩ ጠዋት ማታ ቀና ደፋ እያሉ የሚያዩ የልብ ህሊና የተነሳቸው ግለሰቦች ስማቸውን እያጠፉ በብዙ ፈተና ሊፈትኗቸው ወደዱ ነገር ግን የሚያመልኩትን አምላክ ፈጽሞ ስለሚያውቁት ከቶም ከያዙት አላማ ስደትና መከራ ሳይገድባቸው በስደት ያለችውን ቤተ ክረስቲያን እዚህ አድርሰዋል አንድ የሚያሳዝነኝ ነገር ግን ቢኖር በስደት ልባቸውን በጦር ወግተን አድምተነው ይቅርታ ሳንጠይቃቸው ቀስ እያሉ እያንቀላፉ ነው። ይኸቺ ቤተ ክርስቲያን 3 ፓትሪኮችን አርዳ በልታ አንድን ዋሻ ለዋሻ በማሳደድ ላይ ያለች እንደሆነች አለም የሚያውቀው ጸሃይ የሞቀው እውነት ነው። ማለትም ከወስጥ አዋቂዎች በተረዳነው መሰረት ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ባስሊዎስን ገድላ ታላቁን ብጹዕ አቡነ ቴዎፍሌዎስን በገመድ አንቃ ወይኒ ቤት ጣለች ቀጥሎም በጹዕ አቡነ ተክለሐይማኖት ከመከራው ብዛት እራሳቸውን በርሃብ ከዚህ አለም አሰናበቱ አሁን ደሞ ልተገላቸው ፈልጋ በእግዚአብሔር ጥበብ በስደት ያሉትን አባት ከምደራቸው አስወጥታ በማሳደድ ላይ ትገኛለች ታዲያ እነዚህ አባቶች የኼን ያህል ተገፍተው እውነት እኔና እናንተ በሰላም እናድር ይሆን???? ተስፋችን እለት ተዕለት እየደበዘዘ መጣ እርስ በዕርሳችን እንደ ባቢሎን ህዝብ በቋንቋ ተለያይተን የዕርቅ ቃል ፈጽሞ አልሰማ ብሎናል አሁንም በስደት ያሉት አባቶች ከአንድ አገር ወደ አንድ አገር ሲባክኑ በየ አየር ማረፊያው መስቀል አውልቁ ፈረጅያ ፍቱ ቆብ አውልቁ እየተባሉ ምንም ያህል በስደት ላለው ህዝብ ጠዋት ማታ የሚያዩትን መከራ በልባቸው በማድረግ ተመስገን እያሉ ኖሩ እንዲሁም እግዚአብሔር እሰከፈቀደው ድረስ ይኖራሉ አባቶቻችን የህንን አስከፊ ስደት ህይወት ብለው የያዙት የግል ጸብ ስላላቸው ሳይሆን በስተት ላይ ስተት አይደገም ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተጣሰ ብለው ነው። በእርግጥ በኢትዮጵያ የሉ የቀደሙት አባቶችም በሚታወቅና በማይታወቅ ምክንያት በየዕለቱ ኪዚህ አለም እያንቀላፉ ነው ታላለቆቹና ለቤተ ክርስቲያን አንድነት ደፋ ቀና የሚሉት ቶሎ ሲጠፉ እናያለን ወስጡን የሚያውቅ ንጹህ አብሃሪ ቅዱስ አምላካችን እውነቱን ይመርምር እኔስ የመፍረድ መብት የለኝም። እንግዲህ አባቶቻችንን በስደት እንደወጡ ከሆነ የሚያልፉት ቀኑ ሲነጋ እንደ እስራኤል ልጆች አጽማቸውን ይዘን እንገባለን እንጂ እውነት ለመናገር ከሆነ ለትንሹም ለትልቁም ነገር ብለው ገና ለገና ሞትን ፈርተው ወደ ክህደት አይመጡም አሁንም ቢሆን ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ተጥሷል ህጋዊውና ትክክለኛው የቤተ ክርስቲያናችን አባት ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆራዎስ ፓትርያሪክ ዘኢትዮጵያ ናቸው እነዲሁም ህጋዊው ሲኖዶስ እሳቸው የሚመሩት ነው ብለው ለእውነተኛና ትክክለኛ በሆነ አላማ በስደት ይገኛሉ እውነቱ ይሄ ነው ቢጣፍጠንም ቢመረንም። የብጹዕ አባታችንን አስከራን ማረፍ አስመልክቶ እየሩሳሌም መቀበር ፈልገው እምቢ ተባሉ ብላችሁ በሬ ወለደ ላወራችሁት አዘንኩላችሁ እንደውም ምን ያህል እውነት እንደሆነ ባላውቅም ከአቡነ ማቲያስ እንደሰማሁት ከሆነ በኢትዮጵያ የሚገኙ አባቶች ተሰብስበው በተፈጸመው አደጋ እጅጉን አዝነው እንደውም ውግዘቱን አንስተው ብጹዕ አባታችንን በክብርና በፍቅር አስከሬናቸውን እንደሚያሳርፉ ነው የነገሩኝ ስለዚህ እባካችሁ የክፋት ልጆች ሰይፉን ወደ ሰገባው መልሱት ከግለሰብ ጥቅም ይልቅ የቤተ ክርስቲያን አንድነት ብልጫ ይኑረው አሁንም በህይወት ያሉን አባቶቻችንን እድሜ ይስጥልን ከቶም በእምነታቸው ላይ ክህደት ሳያደርሱ ላመኑበት አላማ የተሰቀለውን ክርስቶስን እያዩ የመጣውን መከራ ልክ እንደ አባቶቻቸው እንደሚቀበሉ እምነቴ ነው። ሰው በህይወት እያለ ታላቅ ስራ ከሰራ እምነቱንም ከጠበቀ የትም ተቀበረ የትም ለኔ ዋናው ነፍሱ በአምላክ እጅ መሆኗ ነው ሰለዚህ ስለ አፈር የሚጨነቁ በሚጨነቁበት አፈር እነሱ ይገቡበታል አምላክ የፈቀደውና ያዘዘው ግን ከመሆን ፈጽሞ አይቀርም ይህንን አምናለሁ
እግዚአብሔር አምላክ ቤተ ክርስቲያናችንን ከወስጥ ጠላት ይጠብቃት የአቡነ ዜና ማርቆስ በረከት በሁላቸንም ላይ አድሮ በይቅርታና በፍቅር ወደ ቀደመው ፍቅር ይመልሰን።

እምናውቀው ነገር ቢኖር አባታችን የሰማዩን ህየወት በምድር እየኖሩ ተለማምደውታል አዲስ ነገር የለውም የት እንደሚሄዱም ልባችን በእምነት ጽኑ ነው።

የሚያመልኩት አምላክ ከሁሉም ይበልጣል እና

ይቆየን

ለአዘንን ሀሉ መንፈስ ቅዱስ መጽናናትን ሰቶን እጅ ለእጅ ተያይዘን ተከባብረን እንድንኖር ይርዳን።

ሰላም ሁኑ
አስተዋይ ልብ ያድለን

gelila said...

በመዓቱ ምህረቱን ያደርጋል እና እርሱ በአባታችን ዕረፍት ምናልባትም አባቶች ተቀራርበው የጠቡ ግድግዳ ይፈርስ ይሆናል
ከዚያም ሁላችን ወደ ዕኢረፍት እንወጣና አብያተ ክርስቲያናቱ በሰው ስም መጠራታቸው ቀርቶ እንደ ቀደመው በእግዚአብሔር ስም ይጠራሉ የጳውሎስ እና የመርቆርዮስ ከመባል እንተርፍ ይሆን እንደ ቸርነቱ በቃችሁ ይበለን።

Anonymous said...

"ፈጽሞ በኔ በጨዋው አንድደበት ሊነገር አይችልም"

ANTEN BELO CHEWA!

የአባታችንን ነፍስ ከደጋጎቹ ይደምርልን።

getanew said...

yedesta new weys yahazen

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)