February 12, 2010

የመሐል ዘጌ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በእሳት ተቃጠለ ተባለ


(ደጀ ሰላም፤ ፌብሩዋሪ 12/2010)፦ በጣና ሐይቅ ዙሪያ ከሚገኙት የዘጌ ገዳማት መካከል አንዱ የሆነው የመሐል ዘጌ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ የካቲት 5 ቀን 2002 ዓ.ም ከቀኑ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ የአደጋዉ ምክንያት ባልታወቀ እሳት ሙሉ በሙሉ ወድሟል ሲል የማኀበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ ዘገበ።

እሳቱን ለማጥፋት በገዳሙ ዙሪያ የሚገኙ ምዕመናን ፣ በአካባቢው የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል እና ከባሕር ዳር ከተማ በጀልባ ተሳፍረው የሄዱ ምዕመናን ጥረት ቢያደርጉም የእሳቱን ቃጠሎ ለመከላከል እንዳልተቻላቸው ዜናው አትቶ አሁንም እሳቱ ከሰው ቁመት በላይ በመንደድ ላይ ነው ብሏል። እሳቱ በአፋጣኝ መገታት ካልተቻለ በመቀጠል የአቡነ በትረ ማርያምን ገዳምንም ሊያጠቃ ይችላል የሚል ስጋት ተፈጥሯል። ይህም ሆኖ በቦታው የተገኘው የመከላከያ ኃይልና ምዕመናን በአንድነት ሆነው በመካከል የሚገኙ ዛፎችን በመቁረጥ የአቡነ በትረ ማርያምን ገዳም ለማዳን በመጣር ላይ እንደሚገኙ በማኀበረ ቅዱሳን የባህር ዳር ማዕከልን ዋቢ አድርጎ ድረ ገፁ ዘግቧል።

++++
maregne yeqere belegne has left a new comment on your post "የመሐል ዘጌ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በእሳት ተቃጠለ ተባለ":

የዘጌ ገዳማት መካከል አንዱ የሆነው የመሐል ዘጌ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ የካቲት 5 ቀን 2002 ዓ.ም ከቀኑ 12፡00 ሰዓት (በ ኢትዮጲያ አቆጣጠር) ጀምሮ የአደጋዉ ምክንያት ባልታወቀ እሳት ሙሉ በሙሉ ወደመ።ይህ ግጥም መታሰቢያ ይሁንልኝ።
የመላእክት ዝማሬ የቅዱሳን ቦታ
ፍጽም ሰላም ያለው ለመንፍስ እርካታ
የአባቶቻችን ርስት የታቦታት ቦታ
ግርማ ሞገስ ያለው ይህን ላየው ላፍታ
ይሄው ተለወጠ ወደ ባዶ ቦታ
እርግጥ (ቅዱስ) መንፍስ አለ በቅዱሳን ቦታ
ይሄው በስንፍና እንደው በዝምታ
መጠበቅ ተስኖን ይህን ታላ...ቅ ቦታ
በእሳት አጣነው እንደው በቸልታ
ተባብረን ካልሰራን በፍቅር ሰላምታ
እጅ ለእጅ ተያይዘን በፍቅር አንድምታ
አንተ ትብስ ሆኖ ካልሆነ ይቅርታ
ከአሁኑ ይባስ ነው የነገ ዕጣፈንታ
ከእግዜር ካልተመለስን በፍጽም ይቅርታ
እንዴት ይምጣ ምህረት ከሃያሉ ጌታ
ወገኔ እንጸልይ ከጧት እስከ ማታ
ይመጣል ምህረት ከመሃሪው ጌታ
ቸርነቱ አያልቅም ካመንን በጌታ
ጌታ ሆይ አድነን እንደው በይቅርታ
አምላክ ሆይ ላክልን ፍጣኑን መከታ
ጊዮርጊስ በፈረስ ቅዱሳን በተርታ
ጌታ ሆይ አድለን ቅዱስ መንፈስህን እንድንበረታ
አሜን አሜን አሜን ::

Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)