February 4, 2010

“አርማጌዶን” የተባለ አነጋጋሪ የስብከት ሲዲ ተለቀቀ


(ደጀ ሰላም፤ ፌብሩዋሪ 4/2010)፦ “አርማጌዶን” በሚል ርዕስ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አዳዲስ ሰባኪያን ዙሪያ የተዘጋጀ የስብከት ሲ.ዲ በአዲስ አበባ በሽያጭ ላይ መዋሉ ታወቀ።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ የአሰባበክ ዘዴ በተለይም ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ ከባህላዊ የዘፈን ስልት ጋር በሚስተካከል ዜማ መዝሙሮችን በማዘጋጀት እንዲሁም ስብከቶችን በስቱዲዮ ቀርጾ በማሰራጨት በታወቀው በዲ/ን በጋሻው ደሳለኝ እና በጓደኞቹ ላይ አነጣጥሯል የተባለው ይኸው ሲዲ በጉጉት ሲጠበቅ ቆይቶ አሁን በገበያ ላይ ውሏል። ዘመድኩን በቀለ በተባሉ ሰው የተዘጋጀው ይህ ሲዲ በዲ/ን በጋሻውና በእንቅስቃሴው ዙሪያ ቅሬታ የነበራቸውን በሙሉ በይፋ ተቃውሟቸውን እንዲያሰሙ በር ይከፍታል ተብሎ ይጠበቃል።

ዲ/ን በጋሻው “የመስቀሉ ስር ቁማርተኞች” በሚል ርእስ ባሳተማት ፓምፍሌት መሰል 100 ገጽ ባልሞላች መጽሐፍ ፓትርያርኩን በይፋ በመቃወሙ ለመታወቅ የበቃ ሲሆን በዚሁ ምክንያት ነው በተባለ ሰበብ ለሁለት ሳምንታት ለመታሰርም በቅቶ ነበር። ይሁን እንጂ “በሽማግሌዎች አቀራራቢነት” ነው በተባለ መልኩ ዲ/ን በጋሻው ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር የታረቀ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ “ቤተኛ” ለመሆን መብቃቱም ይነገራል። በዚህም ቤተኝነት ከዚህ በፊት በየትም ቦታ ሄዶ እንዳይሰብክ ተጥሎበት የነበረው ማዕቀብ የተነሣለት ሲሆን ያቋቋመው ማኀበርም በቅዱስ ፓትርያርኩ ትእዛዝ “ማኀበረ ማርያም” ተብሎ በቤተ ክህነቱ ፈቃድ እንዲያገኝ እንደተደረገ ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ።
224 comments:

«Oldest   ‹Older   201 – 224 of 224
dehna said...

dear w.gebriel what do you mean theology?

ወንጌል said...

ማህበረ ቅዱሳን እባካችሁ እስቲ አንድ ቀን እንኻን እስቲ ስለ ወንጌል ወይም ደሞ ስለ እግዚአብሄር ቃል ተናገሩ። እንደው እድሜልካችሁን የሰው ስም እያነሳችሁ ያለስም ስም እየሰጣችሁ እስከመቼ ትዘልቁታላችሁ ይህ እኮ ክርስትና አይደለም። ስለ ዲያቆን በጋሻው ማውራት ጽድቅነት አይደለም እንደውም መጽሀፍ ቅዱሱን እራሱን የምታውቁት አይመስለኝም። አጫጭር መረጃ ስለበጋሻው እና ስለ ግብረአበሮቹ ብለህ የለጠፍከው ሰውዬ ወይም ሴትዮ እንደው ጤነኛ አትመስሉኝም ብላችሁ ብላችሁ ደሞ በዘማሪ ዳግማዊ እና በአሹ መጣችሁ ደሞ? በቃ ለምን እግዚአብሄር ተመሰገነ ከሆነ ገና ምኑ ተነካና እድሜ ልካችንን እናመሰግነዋለን አዎ እናመሰግነዋለን ምን ትሆናላችሁ እንግዲህ? ዳግምዬ አይዞህ በርታ ዘምር ገና እንደ እያሪኮ ግንብ የማህበረ ቅዱሳንም ሴራ በመዝሙር ይፈራርሳል። እረ ደሞ ዝም ብል ይሻለኛል ሆ ነገ ደሞ የኔ ስም እዚህ ዌብሳይት ላይ እናዳላየው። እኔ ግን እነዚህ ማህበረ ቅዱሳን ነን ባዮች ግድ የላችሁም እንደው ሀይማኖት ያላቸው አይመስለኝም። እባካችሁ እንጸልይላቸው እውነት እና kiduel አይዣችሁ በርቱ

ቀሲስ ሰሎሞን ሙሉጌታ said...

We all EOT members do know well who Zemedkun is. And who his friends like "Bahtawi Gebremeskel" and "Dn Engida". We also have lots of evidences which exactly reflects they are really against our Church. The intention of Zemedkun is filling the economic gap he has these days and finishing the house he is constructing with the sale of his new CD - many are not willing to make him their distributor, ... lots of stories which is from who really know all of them. Behind him there is "Dn" Daniel Kibret who is a mater mind for Zemedkun, Zemari Mendaye, and some financers from Merkato negadewoch. In the other end there are Group of Draft drinkers in arat kilo who are composed of "Dn Paulos", "Dn Tadewos", ...

These are all peers who are standing in the awde mihrets of our church live their life with selling sibket, mezmur including Dn Begashaw.

Mahibere kidusan also looks for a means to recovery letting all the new comer church servants down as they consumed lots of their income from casettes, sibkets...

The whole reason behind is Jealousy and it would also be shame for real followers of our church to think Zemedkun someone who live for his word and his own. Now he is driven by "Dn Daniel, Dn Birhanu Admas... and some others and I am sure he will confess for what he did thinking of himself wrongly.

Let everyone be back to his mind. You can't find any you lead to follow your feelings, business plans,... Time is already went... We EOT members are awake and we know well our beloved church and who everybody really are.

Lib Yisten

Anonymous said...

What kind of expression is it በጋሻው ሰው ሰርቶ ለቤተ ክርስቲያን አድርሶ የለ????? Is not too much for him?

ewnet said...
This comment has been removed by the author.
ewnet said...

ዲክሽነሪ
1. የመቀሉ ስር ቁማርተኖች= የመስቀል ምልክት ይዘው ነገር ግን ኢየሱስን ያማይቀበሉ
2. ጸረ-ማርያም= ድንግል ማርያም ያልሆነችውን ያላደረገችዉን ህይወት መድሃኒት መጠለያ ጉልበት እረፍት ናት እያሉ ማስተማር ማምለክና መዘመር
3. ጸረ-ተዋህዶ= የተዋህዶ ስም ያላቸው ነገርግን በተዋህዶ አምላክ የሆነውን ኢየሱስ የሚለውን ስም መጥራት የማይችሉ
4. ጸረ-ኢየሱስ= ክርስቲያን ነን የሚሉ ነገር ግን የአምልኮ መልክ የሌላቸ ክርስቲያን የሚለውን ስም እንኳ ከማን እና እንዴት ለምን እና መቸ እንደተቀበሉ የማያውቁ
5. ጸረ-ቤተክርስቲያን= የክርስቲያኖች መሰባሰቢያ የሆነችዉን ቤት የጣኦት ማምለኪያ የጠንቋይ እና የጥንቆላ መጸሃፍ ማከማቻ የንግድ የስልጣን እና የፖለቲካ መድረክ እንድትሆን ማድረግ

ewnet said...
This comment has been removed by the author.
ewnet said...

የሚገርም አዲስ ዜና
ጉድ ፈላ ዛሬ ተስፋ ባደረኩባት በኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርቲያኔ ዲያቆን ያሬድ ገ/መድህን የተባለ ሰባኪ ያሳተመውን የቪሲዲ ቪዲኦ አይቸ እምነቴን እረገምኩ። እባካችሁ አንድ ነገር በሉኝ

Tewahedo said...

የተዋህዶ ልጆች ንቁ እባካችሁ!!!
እውነቱና መሰሎቹ እኮ ተልእኮአቸው ተሰናክሎባቸው ነው እንደዚህ የሚያሳብዳቸው አትፍረዱባቸው… ልብ ይስጣቸው ነው የሚባለው… እስቲ ቤተክርስቲያናችን በምን አይነት ፈተና ላይ እንዳለች አንድ ማስረጃ ልንገራችሁ….ግን ምን እስክንሆን የምንጠብቀው …?
የእነ በጋሻውና መሰሎቹ አላማ መስመር እየያዘላቸው መሆኑን የሚገልጽ ጽሑፍ ነው …ይኸውም
በመናፍቃኑ ሜታኖያ በሚባለው መጽሔታቸው ቁ 2 ታህሳስ 2ዐዐ2 ዓ.ም. ገጽ 23 ላይ እነዚህ “አለምን በወንጌል እና በመዝሙር ምድርን የሞሉት” ተብለው ከሚመሰክሩላቸው ዘማሪዎች ውስጥ አንዷ የሆነችው የምርትነሽን መዝሙር ለሃይማኖቶች እርቀ ሰላም ያደረገችውን አስተዋጾ ይተነትናል፡፡
የሃይማኖቶች ዕርቀ ሰላም በሚል ርዕስ ውስጥ እንዲህ ተገልጿል… “በዚህ ጽሑፍ ዛሬ የምናነሳው ጉዳይም በተለያዩ ጊዜያት ይህች ዘማሪት በለቀቀቻቸው መዝሙሮቿ እንዲት አድርጋ የኘሮቴስታንትና የኦርቶዶክስን የአንድነት መንገድ ለመክፈት ያደረገችውን አስተዋጽዎ ላይ በማተኮር ይሆናል፡፡”
ይልና…
“የሁለቱ ሃይማኖት አገልጋዩች በዚህ ሀቅ የመስማማት ግንዛቤ የበረቱ ይመስላሉ፡፡ ለዚህም አስረጅነት በየጊዜው የምናዳምጣቸው የስብከትና የዝማሬ ትሩፍቶቻቸው ይህንን እውነት በእርግጥ ማወጃቸውን ነው፡፡ የሁለቱ ሃይማኖቶች አገልጋዮች በህብራዊ የአገልግሎት ተመሳስሎ እንዴት አድርገው ልዩነታችውን እያጠበቡ እንደሚገኝ እንመለከታለን፡፡”… እያለ የተወሰኑ መዝሙሮቿን ግጥም አንድ በአንድ ይተነትነዋል እንግዲህ ይኼ የማን እና የማን ውጤት እንደሆነ በቀላሉ መረዳት ይቻላል፡፡
ታዲያ የተዋህዶ ልጆች ወዴት እያመራን ነው? እስቲ እራሳችንን እንጠይቅ እንመርምር ….ዝም ብለን ካጨበጨበ ጋር አናጨብጭብ … ቀስ ብለው እኮ ሁሉንም ማለትም በጋሻውና ግብረአበሮቹን ቀስ በቀስ ቃለመጠይቅ ይደረግላቸዋል … ከዛም ቤተክርስቲያን የቀረው አንድ እግራቸው እዛው የመናፍቃኖቹ አዳራሽ ውስጥ እናገኘዋለን… እና አሁን እየሰሩ ያሉት ነገር ምን ያስደንቃል… ከፍሬያቸው ስለሚታወቁ… በማስተዋል እንመላለስ፡፡
ሙሉ ጽሑፉን ማንበብ ለምትፈልጉ በ neftalemb@yahoo.com ጻፉልኝ እልክላችኋለሁ፡፡
ሁላችንንም አምላከ ቅዱሳን ይጠብቀን!! በቸርነቱ ያስበን!!!
የእመቤታችን ፍቅሯን በልባችን እስከዘላለም ያኑርልን!!!
ቅዱሳን መላእክት በጠብቆታቸው አይለየን!!!
ጾመን ለመጠቀም ያብቃን!!!
አሜን!!!

Anonymous said...

I read the comment posted by "Kesis
Solomon Mulugeta" I have a doubt that this is geniunely posted by Kesis Solomon. I have a feeling that some body else used his name. I know kesis Solmon Very well and I am sure the wordings are not his. I hope we will hear the truth from Kesis him self soon,
Chere yegetemen

Anonymous said...

ወንድሞችና እህቶች
ስለ አዘጋጆቹና ከበስተጀርባው አሉ ስለተባሉት ትተን በሲዲው ላይ የተባለው ነገር እውነት ነው ወይ ብለን እንጠይቅ….. መልሱ 90ፐርሰንቱ ትክክለኛ ሀቅ ነው፡፡ አላማው እኮ ከጥፋት እንዲታረሙ እንጂ እንዲገደሉ ወይም እንዲወገዙ አይመስለኝም፡፡ በጋሻው የተሰጠውን ጸጋ በብር ለውጧል፡፡ ይሄ ደግሞ መጨረሻው ምን እንድሚሆን ግልጽ ነው፡፡ ለማንኛውም ሚስጥራችንን በአደባባይ መውጣቱ ያሳዝነኛል፡፡
ገበየሁ ከአዋሳ

Anonymous said...

we are to young to give comments &suggestion but let the father of our church who has been devoted for the holly bible give comment & their suggestion why didn't we ask them?


egziabiher betekirstiyanachinin yitebikilin

Anonymous said...

lemin mahibere kidusan ena leloch gileseboch yitekesalu gudayu be zemedkun sibket aydele? new weysi lela tilacha new?
mahiberu yetekuakuamewu beEgziabiher fikad new
mahiberu yetekuakuamewu be 1 ena be 2 sewoch aydelem silezih pls leave it alone.

Anonymous said...

ear all I`m from dilla dp you know about the family of begashaw? he is from bad family in dilla for example his mothe is magician and palmist. in his praching of no.1 he said. አክስቴ ቤት ጨሌ አለ እቴቴ የምትባል፡፡ she is his mother she is smoker and addicted of ጫት ሲጋራ መጠጥ ወዘተ የቤቱን ሳያስተካክል በቤተ ክርስቲያንን ይረብሻል

Anonymous said...

Do you know what? the person who wrote about begashaw family, who are you telling about some bodys' bad history. Even his mum is as you said, does it really matter? let say he came from the idole worshipper family, however God saved him, GOD chose him to be his child and to save the other soul for example like you. please look at your face first in the mirror before you looked at someone face. God bless

hareg said...

ere ebakachihu enasitewul.. seyitan eko metekemia eyaregen new lemin anasitewulim lemin seyitan lay aninekabetim.. sile kirstos lisebek sigeba silesewoch anisiten eyaweran eko teshewedin ...

Geta yiridan

ewnet said...

ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6 17 የመዳንንም ራስ ቁር የመንፈስንም ሰይፍ ያዙ እርሱም የእግዚአብሔር ቃል ነው።
ልዚህ ነው የመጽሃፍ ቅዱስን ቃል ባለማዎቃችን ስለጌታ ሲነገርና ሲዎራ ግራ የምንጋባው። ይህ ብቻ አይደለም ግራ ከመጋባታችን እልፈን ያልሆነ ስም ለመለጠፍ የምንሯሯጠው። እግዚአብሄር መንፈስ ቅዱስ ሚስጥሩን ይግለጽልን አሜን!

Anonymous said...

"In Orthodox traditions start with ourselves"...bemil riese comment post siyaderg yenebere wendime...hulet commentochihin anbibe betam desse eyalegn temarkubachew...ketayun gin lagegn alchalkum...EBAKIHIN KECHALK LELOCHIM POST ADIRGILIGN...kalehiwot yasemalign. weyim be sami575@yahoo.com yalehin lakilign

Libona ysten!!!

Anonymous said...

guys are you Ethiopian especially kiduel, if you are real orthodox you understand our church and then you may comment on all side don't talk about begashaw or mahberekidusan in my believe you don't have any knowledge about both.both are working for church but one of them need a bit correction this may be solved if they come together and discuss on issue.if they are christian they may do it when God wills and pls. kiduel don't make your leader begashaw he is human being where is your savor Jesus?all others pls.let us check you we are to speak about begashaw or others? this is come because of our work.any way"Be hymanot bitnoru rasachihun mermiru" yemiyablechelich hulu werk aydelem.take care of your mouth and your life.

Anonymous said...

mechemche begashaw berasu gize maninetun geltual.yemiasazinew degafiwochu zarem orthodox new lilu yifeligalu.degimo lebegashaw minfikina yared yohanis ena ashenafi gebremarim tetwyakiwoch nachew.enezih nachew wanegna menafikan

Abebe said...

beyans 90% yemthonut protestant nachihu silebetekiristian titachihu lelataweralachihu.tisadebalachihu.kiristian malet kiristosawi malet new.

Andn said...

abizagochu yebegashaw degafiwoch tesadabiwoch nachew lemn yihon? kersu temrewt yihon?

Anonymous said...

i know that most of the comments are like months back but i would like to ask what is up with all this bad words and curses?do they glorify God?why do we have such a huge problem to have an open mind for things i mean if we put our priority to be God he will speak to our hearts and we know which one is right and which one is wrong.unluckily we dont have that we are lost reaally lost we put all this"ebrit " i think because we are empty inside but let me tell you brothers and sisters aytekemenen.egziabeherem ayekeberem .LEMEN ENECHENEKALEN? KE GETA YALHONE HULU AYESTENAM YEL YELE ENDE?this is what makes our religion mesakiya ena mesalekiya this is what makes our brothers and sisters to run away from our church .eseti egeziabeher yemikeberebet kehone enemeremer mejemeria what is it with all this ego?

Anonymous said...

እንደምን ሰንብታችዋል ደጀ ሰላማዊያን በቅድምያ የ ጌታችን ቸርነት የ ቅዱሳን በረከት የ እመበታችን ኣማላጅነት ከ ሁላችንም ጋር ይሁን በ መቀጠል የምላችው ቢኖር ኣሁን የምትሰጡትን ኣስተምህሮ ሁላችንም የ ኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ሰምተነዋል ባይባልም ጥቂቶቻችን አንበን የአላማውን መድረሻም ለመገንዘብም ችለናል በምትሰጡት በምታቀርቡት የተወሰኑ ቢቀበሉም የበዛነው ታ ኦ ሎ ጎ ስ ዘማሪ ዲ ያ ቆ ን ት ዝ ታ ው ሳ ሙ ኤ ል እና መጋቢ ሃዲስ በጋሻው ደሳለኝ በሰጡት መጽሃፍ ቅዱሳዊ ምላሽ ለመረዳት ችለናል እናም ይሄን ኢሰባዊ ድርጊት ተከትለው ለሚያምኑት ቸሩ ኣምላካችን የድንግል ማርያም ልጅ እውነታውን ይግለጽላቸው ለ መጋቢ ሃዲስ ድያቆን በጋሻውም የ እግዝያብሄር ቸርነት የ ድንግል ኣማላጅነት ኣይለይህ እያልኩ ሌሎችም ይህንን ተገንዝበው የሰጡትን የ ድያቆን በጋሻው መልክት በ ዩቱብ ገብተው ቢያዩት በቂና ከ በቂም በላይ ነው የሚል ግምት ኣለኝ የተሳሳተ መንገድ የሚጓዙትንም አግዝያብሀር ኣምላክ ቀናውን መንገድ ያሳይልን ኣሜን HILOM

«Oldest ‹Older   201 – 224 of 224   Newer› Newest»

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)