February 23, 2010

በዛሬው የየካቲት 16 የኪዳነ ምሕረት በዓለ ንግሥ ላይ ፀሐይ በቀስተ ደመና ተሸፍና ታየች፤ የምሕረት ያድርግልን


(ደጀ ሰላም፤ የካቲት 16/2002 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 23/2010) በዛሬው የየካቲት 16 የኪዳነ ምሕረት በዓለ ንግሥ ላይ ፀሐይ በቀስተ ደመና ተሸፍና ስትታይ ውላለች። ሸገር ሬዲዮ ዜናውን ከዘገበ በኋላ አንድምታውን እንዲያብራሩለት አንድ ባለሙያ ጠይቆ “ጉዳዩት እየተከታተሉት” መሆኑን መልሰዋል።

ክስተቱን ፎቶ ያነሣ “ሰሎሞን ታደሰ ሣህሉ” የተባለ አንድ ኦርቶዶክሳዊ በፌስቡክ ላይ
“ዛሬ በኮተቤ ኪዳነምህረት ቤተ ክርስቲያን ክብረ ባዓሏ ሲነግስ ከቤተ ክርስቲያኑ ጉልላት በላይ የቃል ኪዳኗ ቀስተ ደመና ታየ በላዔ ሰብእን (ሰው በላውን) ያስማረች እናታችን እኛንም በረድኤቷና በፍቅሯ በምልጃዋ አትለየን አሜን!!!”
ብሏል። አሜን ብለናል። ከአንድ ሺህ ቃላት፣ አንድ ፎቶግራፍ ማለት ይኸው አይደል?
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

+++
ኪዳነ ምሕረት
(www.mahiberekidusan.org)፦ ኪዳን የሚለው ቃል ተካየደ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ተማማለ፣ ተስማማ፣ ውል ገባ ማለት ነው፡፡ ኪዳነ ምሕረት ማለትም ደግሞ የምሕረት ቃል ኪዳን ማለት ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ስለሰው ልጆች ይቅርታ የገባላት ቃል ኪዳን ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት፣ ለሚያከብሩት፣ ለሚወዱትና ለሚወዳቸው ሁሉ በተለያዩ ጊዜያት ብዙ ኪዳናትን ሰጥቷል፡፡ በቅዱሳት መጻሕፍት ከሚጠቀሱት ውስጥ ለአብነት ያህል የሚከተሉትን እንመልከት፡፡


1- ኪዳነ ኖኅ
የሰው ልጆች በምድር ላይ እየበዙ በሔዱ ቁጥር ኃጢአታቸውም እንዲሁ እየበዛ በመሔዱ በውኃ መጥለቅለቅ እንዲጠፉ ባደረገ ጊዜ ጻድቁ ኖኅ የሚድንበትን መርከብ እንዲሠራ አዘዘው፡፡ ኖኅም እንደታዘዘው መርከብን ሥራ፡፡ በየወገናቸው ተባዕትና አንስት እየሆኑ በመርከብ ውስጥ ገብተው እንዲድኑ አደረገ፡፡ የጥፋት ውኃም ካለፈ በኋላ እንደገና እንዲበዙና ምድርን እንዲሞሏት እግዚአብሔር ፈቀደ፡፡ ምድርንም ዳግመኛ በንፍር ውኃ እንዳያጠፋት ለጻድቁ አባታችን ኖኅ ቃል ኪዳን ገባለት፡፡ ቃሉም እንዲህ የሚል ነበር፡፡ «ቃል ኪዳኔንም ለአንተ አቆማለሁ፤ ሥጋ ልባሽ ሁሉ ዳግመኛ በጥፋት ውሃ አይጠፋም፤ ምድርንም ለማጥፋት ዳግመኛ የጥፋት ውሃ አይሆንም፡፡ እግዚአብሔር አለ በእኔና በአንተ መካከል ካንተም ጋር ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ለዘላለም የማደርገው የቃልኪዳን ምልክት ይህ ነው፡፡ ቀስቴን በደመና አደርጋለሁ፡፡ የቃል ኪዳኑም ምልክት በእኔና በምድር መካከል ይሆናል፡፡» /ዘፍ.9:13-16/፡፡ ይህም ቃል የጸና ሆኖ ምልክቱ /ቀስተ ደመናው/ እስከ ዛሬ ድረስ በግልጥ ሲታይ ይኖራል፡፡

2- ኪዳነ አብርሃም
አብርሃም ከሣራ ልጅ ባለመውለዱ እያዘነ ሲኖር ከዕለታት አንድ ቀን እግዚአብሔር ተገልጦ «አብርሃም ሆይ አትፍራ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነው» አለው፡፡ እሱም « አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ ምን ትሰጠኛለህ ዘር አልሰጠኸኝም ወራሽም የለኝም» ባለው ጊዜ ልጅ እንደሚወልድ ዘሩም ከሰማይ ከዋክብት ከምድር አሸዋ እንደሚበዙና ከግብፅ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ያለውን ምድር ለዘሩ እንደሚያወርሰው ቃል ገባለት፡፡ አብርሃምም አምኖ ተቀበለ እንዲሁም ተፈጸመለት /ዘፍ.15:1.7/፡፡

3- ኪዳነ ዳዊት
በነቢዩ ዳዊት አፍ «ኪዳን ተካየድኩ ምስለ ኅሩያንየ፤ ከመረጥኋቸው ከወዳጆቼ ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ» መዝ 88:2 ፡፡ ካለ በኋላ ለእርሱም የሰጠውን ቃል ኪዳን እንመለከታለን ይኸውም ዳዊትን ከሌሎች ወገኖቹ አብልጦ በመረጠውና የብዙ ወገኖቹ መሪ አድርጎ ባስቀመጠው ጊዜ ዳዊት ለፈጣሪው ቅን አገልጋይና ፍጹም ታማኝ በመሆኑ ልበ አምላክ እስከመባል ድርሷል፡፡ «ለአገልጋዬ ለዳዊት ማልሁ ዘሩንም ለዘለዓለም አጸናለሁ» ብሎም ምሎለታል መዝ 88:5 ፡፡ ዘሩንም ለዘለዓለም አጸናለሁ ማለቱም ለጊዜው ለልጁ ለሰሎሞን ይሁን እንጂ ኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሱ ዘር ከምትሆን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ዓለምን ማዳኑን ሲያስረዳ ነው፡፡ ይህም አዳም በፈጸመው በደል በተጸጸተ ጊዜ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ የሚል ቃል ኪዳን ገብቶለት ስለነበር ጊዜው ሲደርስ ከድንግል ማርያም ተወልዶ ትንቢቱም እንደተፈጸመ ያረጋግጣል፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ለቀደሙት ቅዱሳን አባቶቻችን ያደረገው ቃል ኪዳን እጅግ ብዙ ነው፡፡ በዚህ ጽሑፋችን ውስጥ ማጠቃለል አይቻለንም፡፡ እናም ወደተነሳንበት ርዕሰ ጉዳይ በመመለስ ጌታችን ምደኃኒታችን ኢየሱስ ከርስቶስ ለእናቱ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሰጣታትን ቃል ኪዳን እንመልከት፡፡
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰው ልጆች ራሱን አሳልፎ በሰጠ ጊዜ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ነፍሱን በገዛ ፍቃዱ ከስጋው ከመለየቱ በፊት ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር /ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ/ ከመስቀሉ ሥር ስለነበር እናቱ ድንግል ማርያምን ያጽናናት ዘንድ «ነዋ ወልድኪ እነሆ ልጅሽ ወነያ እምከ፤ እነኋት እናትህ » በማለት አደራ ሰጥቶታል፡፡ /ዮሐ.19:26/ ዮሐንስም እመቤታችንን ወደ ቤቱ ወስዶ ካስቀመጣት በኋላ የእናትነት አንጀቷ አልችልላት ስላለ በየቀኑ እየሔደች በልጇ መቃብር በጎልጎታ ላይ እንባዋን እያፈሰሰች ትጸልይ ነበር፡፡ ከእለታት አንድ ቀን እንደተለመደው እያነባች ስትጸልይ ልጇ ክርስቶስ እልፍ አእላፋት መላእክትን አስከትሎ ወደ እርሷ ወረደ፡፡
«ስምሽን የጠራ፣ ቤተክርስቲያንሽን የሠራ፣ በስምሽ የተራበ ያበላ፣ የተጠማውን ያጠጣ፣ የታረዘውን ያለበሰ፣ ያዘነውን ያረጋጋ፣ ወይም ውዳሴሽን የጻፈ፣ ያጻፈ፣ ሴት ልጁንም ሆነ ወንድ ልጁን በስምሽ የሰየመውን ሁሉ እምርልሻለሁ» (ዘሰኔ ጎልጎታ) ሲል ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ ይህም የገባላት ቃል ኪዳን የጸና ነው፡፡ ጌታችን ምደኃኒታችን ኢየሱስ ከርስቶስ የተናገረውን የማያስቀር እውነተኛ አምላክ እንደሆነ በቅዱስ መጸሕፍ « አቤቱ የሰማይ አምላክ ሆይ ለሚወዱህና ትዕዛዝህን ለሚያደርጉ ቃል ኪዳንና ምህረትን የምትጠብቅ ታላቅና የተፈራህ አምለክ ሆይ...» ተብሎ ተጽፏል፡፡ እርሷም ልመናዋና ጸሎቷ ስለሰዎች መዳንና መመለስ ስለነበር አመስግና ቃል ኪዳኗን ተቀብላለች፡፡
ይህንንም ቃል ኪዳን የተቀበለችው ከክርስቶስ እርገት በኋላ የካቲት 16 ቀን ስለሆነ፤ ቤተክርስቲያን ባለበት ቦታ ሁሉ በተላቅ ድምቀት ሲከበር ይኖራል፡፡ ይህም ዕለት ከእመቤታችን ታላላቅ በዓላት አንዱ በመሆኑ ምእመናን ሁሉ በደስታና በተስፋ መታሰቢያዋንም በማድረግ ከላይ የተዘረዘሩትን ክርስቲያናዊ ተግባራት በመፈጸም ሊያከብሩት ይገባል፡፡
ለእርሷ የተሰጠው ቃል ኪዳን ለመላው ምእመናን ስለሆነ በእርሷ አማላጅነት ያገኘነውን ተስፋ ለመቀበል እኛ ደግሞ ለተጎዱትና ተስፋ ለሌላቸው ወገኖቻችን እንዲሁ አዛኞችና ሩኅሩሆች መሆን ይጠበቅብናል፡፡
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ተወልዶ ዓለምን በማዳኑ መድኃኔዓለም ተብሏል፡፡ እርሷም የዓለም ድኃኒት መገኛ በመሆኗ ቤዛዊተ ዓለም ተሰኝታለች፡፡ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ልናመሰግናት፣ የጸጋ ስግደት ልንሰግድላት፣ ልናከብራትና ልናገናት ይገባናል፡፡ ዛሬ በአፀደ ሥጋ ያለነው ብቻ ሳንሆን በእርሷ ተማጥነው በአማላጅነቷ ድነው በአፀደ ነፍስ ያሉት ነፍሳትም አንቺን ለፈጠረ ለእግዚአብሔር በሰማይ ምስጋና ይድረሰው፤ ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ሰው በመሆን በአንቺ ምክንያት የዘለዓለም ሕይወትን አገኝተናል እያሉ ሲያመሰግኑዋት ይኖራሉ፡፡
ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ቃል ኪዳን ጠብቀውና አክብረው ያለፉ ቅዱሳን አባቶቻችን የዘለዓለም ክብርን እንዳገኙ ሁሉ እኛም ቃሉን ብንጠብቅ ይጠብቀናል፡፡ ብናከብረው ያከብረናል፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔርንም ሆነ የድንግል ማርያምን ስም በመጥራትና በመሐላ የተዋዋልነውን ቃል ኪዳን የምናፈርስ፣በሐሰት የምንናገር በጥቅም ተደልለን ሌላውን የምንጎዳ ከሆነ የተሰጠንን ቃል ኪዳን ዘንግተናል፡፡
«የማይረባውን ቃል ይናገራሉ ቃል ኪዳን በገቡ ጊዜ በሐሰት ይምላሉ፡፡ ስለዚህ በእርሻ ትልም ላይ መርዛም ሥር እንደሚበቅል መቅሠፍት ይበቅልባቸዋል» ሲል ነቢዩ ሆሴዕ እንደተናገረው በምሕረት ፋንታ መቅሰፍትን በሥርየት ፋንታ መርገምን የምናመጣ እንዳንሆን መጠንቀቅ ይገባናል፡፡ ሆሴዕ 10:4
በዚህ ዓለም እርስ በእርሳችን የምናደርጋቸው ውሎችና ቃል ኪዳኖች ፈርሰው ቢገኙ ውል አፍራሽ ወገን በሕግ ፊት ቀርቦ በመረጃ ሲረጋገጥበት ቅጣቱን ተቀብሎ ውላቸው በሕግ የጸና እንደሚሆን ከእግዚአብሔርም የተቀበልነውን ቃል ኪዳን አፍርሰን ከተገኘን የሠራናቸው ክፉ ሥራዎች መረጃ /ምስክር/ በመሆን ያስፈርዱብናል፡፡ በወንጌል «ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም » ማቴ 24:35 ተብሎ እንደተጻፈ፡፡
ስለዚህ የቤተ ከርስቲያን ልጆች የሆንን ምእመናን በሙሉ ጌታችን ኢየሱስ ከርስቶስ ለእናቱ ለድንግል ማርያም በሰጣት ቃል ኪዳን መሠረት በመጠቀም በረከት ለማግኘት እንሽቀዳደም፡፡ ቃሉን ጠብቀን በሕጉ ጸንተን በመኖር በክርስቶስ ይቅር ባይነት በእመቤታችን ድንግል ማርያም አማላጅነት ዘለዓለማዊ ሕይወትን እንድንወርስ መልካም ፈቃዱ ይሁንልን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
አምላከ ሰማያት ወምድር

18 comments:

Anonymous said...

Cherentu yemayalekebet Amelak sele Enatu sele kidst dengel Mariam belo yemaren.
Where are all those people who write their opinion when our church has a problem? why dont they say something about this? lehulachenem netsuh lebonawn yadelen

Anonymous said...

Cherntu Yemayalkebet Amelak sele Enatu Sele Kidist Dengel Mariam belo Yemaren.Where are all thoase people who write their comments when our Church face a problem why dont they say some thing about this miracle.

Lehulachenem Nisthun Lebona yadelen

Anonymous said...

Thanks God

Dengel yanechi wuleta .........

HIWOT said...

DEJE TENAHU KOYICH KIDANMIHRTEN
TETSNANAHU RESAHU HAZENEN
YE AMILAKE ENAT EMBETACHIN
MOGES HUGNGN KERWE ZEMENEN
.....

Anonymous said...

ምንም፡የማይሳነው፡አምላክ፡እንዲሁ፡የይቅርታው
ን፡ብርሃን፡ልቦናችን፡ውስጥ፡ያብራልን።

ክፉውን፡ከኢትዮጵያ፡ምድር፡ነቅሎ፡ይጣልልን።

በምሕረቱ፡ዝናብ፡ከእድፋችንና፡ግድፈታችን፡
ሁሉ፡ያጽዳን።

ከአፋችንም፡ቅዱስ፡ቃሉና፡ምስጋናው፡ብቻ፡እንዲ
ንቆሮቆር፡ያድርግልን።

እመ፡ብርሃን፡የተዋሕዶ፡ኢትዮጵያን፡እንባ፡
ታብስልን።አሜን።

ክብርና፡ምስጋና፡ለመድኃኔ፡ዓለም፡ይሁን!

ሳሙኤል፡ዘአሰቦት።

Anonymous said...

On St Virgins Feast day (Kidane Mihiret), over her Church such kind of incident has a great meaning to the faithful. It is good news to me inspite of the ETV report.

By the way, do you remember about three or four years ago similar to this revelation in Addis Ababa. I guess it was after Fasika (I'm not sure about the exact time/date). Those who know it well please tell us.

Thanks.

Anonymous said...

ለግዚአብሀር የሚሳነው የለም
የእግዚአብሀር ስሙ ዛረም ነገም የተመሰገነ ይሁን.እመበታችን አማላጅነትዋ ከኛ አይለየን.የእግዚአብሀር ቃሉ ለዘላለም ነው. እኛ እንኩዋን አይተን ሳናይ ያመንን ነን.መጥሃፍ ቅዱስ በኢትዮጵያዊው ጃንደረባ አመካኝነት መስክሮልናል. ያልገባቸው ግን ለዚህም ጥቅስ ይፈሉግለታል. በየትኛው ክፍል አገኛትሁት ይሉናል. እንደ እስራኢላውያን በመንደራቸው ሳለ እንዳላመኑ እነዚህም ጥቅስ ካላገኜን ይህንን የታየውን የውሸት ነው ይላሉ. አለም መጨረሻዋ እየተቃረበ ነው. በመጨረሻ ግዘ ብዙ የሚያታልሉ እንደሚመጡና ብዙዎች እንደሚሰናከሉ ተጽፉዋል. ልብ ያለው ልብ ይበል

Nabute said...

Thanks to the Almighty God for His miracle.
And thanks to our Mother Saint Virgin Mary.

For those of us (real ethiopians) who believe in the intercession and support of Saint Mary this is not a big surprise. She has been doing great things throughout our life.

We praise God for His greatest gift (second to His ressurection) for us especially Ethiopians.

I am a bit amazed and surprised by the ETV news regarding this miracle. Actually no one expects more than that from this secular world.

Nabute said...

Thanks to the Almighty God for His miracle.
And thanks to our Mother Saint Virgin Mary.

For those of us (real ethiopians) who believe in the intercession and support of Saint Mary this is not a big surprise. She has been doing great things throughout our life.

We praise God for His greatest gift (second to His ressurection) for us especially Ethiopians.

I am a bit amazed and surprised by the ETV news regarding this miracle. Actually no one expects more than that from this secular world.

Ehetmicheal said...

emmmmmmm God is great.Thanks to Almighty God this days it is really to see this kind of "TAMER" I dont desrve to hear but GOD IS GREAT. DENGLE WELADIT AMALK ebaksh ande adregen.
Egizabher yemsegen Amen .

Anonymous said...

እግዚአብሄር ይመስገን ገና ብዙ ምህረት ደረግልናል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነት ብዙ ይሰራል እንደእናንተ በክፋት ና በዉሸት ሳይሆን በእዉነት ስለዚች ሐገርና ህዝቧ ለተዋህዶ ሀይማኖት የሚጨነቁ በጸሎት አምላክን የሚማጸኑ ጤዛ ልሰው ድንጋይ ተንተርሰው የሚማልዱ አባቶች አሉ የነሱ ጸሎት ገና ብዙ ያደርጋል፡;
እንጂ እንደናንተማ ሱባኤ አያግዳችሁ ፈሪሐ እግዚአብሄር አያውቃችሁ ለእኩይ ስራ ቆማችሁ ወንድም በወንድሙ ላይ እነዲነሳ እንደምታደርጉት ዘመቻና አማኙን ፈተና ውስጥ እንደመክተቻችሁ መድሀኒተዓለም ምንኛ በተቆጣ፡;

mekar said...

Cherinetu yemayalkibet Egziabher Amlak beenatu be dingil mariam lay adro limiren fekadu silehon yehin linishun neger aderege. Neger gin tininishoch bezenachew ye abuara kimichit alut. Libona yestilin. Cherinetu yamayalkibet erisu abizto yimaren. Hagerachini Yetebikilin.

Amen

Anonymous said...

God is good. He alone is truly and fully good. He is good without mixture of evil; in Him all evils disappears. From Him comes all good. All that is good not only comes from Him, but is also His presence. Where the good is, there God is present.'' -Paulos Mar Gregorios

Amen.

Anonymous said...

የምህረት ቃልኪዳን ሲታ....ይ ሰማያት ተቀደው
ፍጽም በሚያስደንቅ እጅግም በሚያምረው
በማርያም መቀነት በኖህ ምልክት ነው
ስትገለጽ በግብፅ እጅግ በሚያስፈራ በታላቅ ክብር ነው
በዚያ ለማመስገን ለማቅርብ ምስጋና ያልተመኘ ማን ነው?
ለምስጋና እንጂ ፍፅም ለመዘመር ሁሉም የተመኘው
በመንፈሳዊ ቅናት ሁሉም የተመኘው አንቺን ለማግኝት ነው
ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ ነሽ እና አማላጅ
ሰው ሁሉ ያመስግን ያድንቅ የአምላክን ስራ ዝማሬ ይታወጅ
ይህው በግልጥ ታይቶ የምህረት ቃልኪዳን
እጅግ በሚመስለው በታላቁ ነብይ በኖህም ቃልኪዳን
በአስራትሽም ሀገር ይህው ዛሬ ታየን
የልባችን ደስታ ምኞታችን ሞላን
ሁሌ በምልጃሽም እንዳየሽን አየን
ለዚህ ታላቅ ታአምር አይናችን ላሳየን
ፍጽም እናመስግን ከልባችን ሁነን
እናመስግን አንቺን ድንግል እናታችን
ነሽና ማደሪያው የማህሪው ጌታችን
የአንቺን ምስጋና የማይወደው ሰይጣን
ይህው ጀመረና ላማሳጣት አንችን
እጅግ ያውቃልና አስታራቂ እናት ርህርት መሆንሽን
በአሸዋም ላይ ቆመ ከርህርት ሊለየን
አለሙም ሹክ ይላል ድንገት በጆሮችን
ውሸት አይታክተው ይለናል ሪፍራክሽን
ምን አይነት ውሸት ነው ይሄው እየታየን
ሪፍራክሽን ነው ፍፅም ከተባልን
ለምን አሜሪካ አውሮፓስ አላየን
ለምን በአዲስ አበባ ብቻ በ16 ታየን
መተው ነው የሚሻለን የማናውቀውን
ብለው የለ ዝንጀሮ ታላቁን የሰው ልጅ እጅግ ክቡሩን
በአምላክም አምሳያ የተፍጠረውን
መሆኑን አልተረዱ መሳደብ አምላክን
አምሳያ ፈጣሪ የሰው ልጅ መሆኑን
ስለዚህ ውገኔ በ እምነትህም በርታ ፍጽም አመስግን
ሂድ አንተ ሰይጣን በሉት እንዳለን በቃሉ ጌታችን
አታስፈልገንም ከዚህ ጥፍ እንበለው እንዳባቶቻችን

maregne yekerebelgne said...

የምህረት ቃልኪዳን
የምህረት ቃልኪዳን ሲታ....ይ ሰማያት ተቀደው
ፍጽም በሚያስደንቅ እጅግም በሚያምረው
በማርያም መቀነት በኖህ ምልክት ነው
ስትገለጽ በግብፅ እጅግ በሚያስፈራ በታላቅ ክብር ነው
በዚያ ለማመስገን ለማቅርብ ምስጋና ያልተመኘ ማን ነው?
ለምስጋና እንጂ ፍፅም ለመዘመር ሁሉም የተመኘው
በመንፈሳዊ ቅናት ሁሉም የተመኘው አንቺን ለማግኝት ነው
ከፈጣሪ በታች ከፍጡራን በላይ ነሽ እና አማላጅ
ሰው ሁሉ ያመስግን ያድንቅ የአምላክን ስራ ዝማሬ ይታወጅ
ይህው በግልጥ ታይቶ የምህረት ቃልኪዳን
እጅግ በሚመስለው በታላቁ ነብይ በኖህም ቃልኪዳን
በአስራትሽም ሀገር ይህው ዛሬ ታየን
የልባችን ደስታ ምኞታችን ሞላን
ሁሌ በምልጃሽም እንዳየሽን አየን
ለዚህ ታላቅ ታአምር አይናችን ላሳየን
ፍጽም እናመስግን ከልባችን ሁነን
እናመስግን አንቺን ድንግል እናታችን
ነሽና ማደሪያው የማህሪው ጌታችን
የአንቺን ምስጋና የማይወደው ሰይጣን
ይህው ጀመረና ላማሳጣት አንችን
እጅግ ያውቃልና አስታራቂ እናት ርህርት መሆንሽን
በአሸዋም ላይ ቆመ ከርህርት ሊለየን
አለሙም ሹክ ይላል ድንገት በጆሮችን
ውሸት አይታክተው ይለናል ሪፍራክሽን
ምን አይነት ውሸት ነው ይሄው እየታየን
ሪፍራክሽን ነው ፍፅም ከተባልን
ለምን አሜሪካ አውሮፓስ አላየን
ለምን በአዲስ አበባ ብቻ በ16 ታየን
መተው ነው የሚሻለን የማናውቀውን
ብለው የለ ዝንጀሮ ታላቁን የሰው ልጅ እጅግ ክቡሩን
በአምላክም አምሳያ የተፍጠረውን
መሆኑን አልተረዱ መሳደብ አምላክን
አምሳያ ፈጣሪ የሰው ልጅ መሆኑን
ስለዚህ ውገኔ በ እምነትህም በርታ ፍጽም አመስግን
ሂድ አንተ ሰይጣን በሉት እንዳለን በቃሉ ጌታችን
አታስፈልገንም ከዚህ ጥፍ እንበለው እንዳባቶቻችን

Anonymous said...

Ethiopia shall soon stretch out her hands unto God.

Guad Mengistu said...

God love Ethiopia.

711/82 said...

yihn zena yaseman our lord bless us.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)