February 28, 2010

ክርክሩ ቀጥሏል፤ የሚበጀንን እንምረጥ

በአንባብያን ጥያቄ መሠረት የዲ/ን በጋሻውን ቃለ ምልልስ አፈላልገን አግኝተናል። ተከታተሉት።


(ደጀ ሰላም፤ ፌብሩዋሪ 27/2010)፦ የ“አርማጌዶን” ነገር ከተነሣ ወዲህ በኢትዮጵያ በሰባክያን፣ በዘማርያንና ጊዜ-ፈጠር (ዘመነኞች) የሆኑ አገልጋዮችን የተመለከተው ውይይት ቀጥሏል። ከኢትዮጵያ ውጪም “ደጀ ሰላም” በከፈተቻቸው መድረኮቿ አማካይነት ውይይቱ ቀጥሏል። የነገሩ ባለቤቶች የሆኑት ሰዎችም በየመጽሔቱ የየራሳቸውን ማለት ጀምረዋል። አስቀድሞ ዲ/ን በጋሻው፣ አሁን ደግሞ መምህር ዘመድኩን የየራሳቸውን ብለዋል። እናንተ ደጀ ሰላማውያን ሁለቱንም ተመልክታችሁ አስተያየታችሁን ትሰጣላችሁ። ደጀ ሰላም የሁለቱንም ወገን ታስተናግዳለች። ለቤተ ክርስቲያናችን የሚበጀውን እንድንወስድ፣ ስንዴውን ከእንክርዳዱ እንድንለይ ትመክራለች።
እነሆ!!!February 24, 2010

ስለ ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ የቀብር ሥፍራ የአንባብያን ድምጽ (Poll)

(ደጀ ሰላም፤ የካቲት 16/2002 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 23/2010)፦ የብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስን እረፍት ከሰማንበት ጊዜ ጀምሮ እርሳቸውን የተመለከቱ የተለያዩ ዜናዎች ስናስነብብ መቆየታችን ይተዋሳል። የቀብር ሥፍራቸውን በተመለከተ “ቅዱስ ሲኖዶስ የብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስን ውግዘት አንስቶ ሥርዓተ ቀብራቸው በኢትዮጵያ እንዲፈጸም፣ አስከሬናቸውም ለጵጵስናቸው በሚገባ ክብር፣ አበው ጳጳሳት በሚያርፉበት በመ/ፀ/ቅ/ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን እንዲያርፍ ወስኗል። በዚሁ በአሜሪካን አገር እንዲቀበሩ የሚፈልጉም አሉ። እርስዎስ በየት እንዲፈጸም ይመርጣሉ?” በሚል ባዘጃነው የድምጽ መስጫ (ፖል) 518 ሰዎች የተሳተፉ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ 434ቱ (83%) አዲስ አበባ ቢቀመሩ እንደሚመርጡ ሲጠቁሙ፣ 84ቱ (16%) ደግሞ እዚሁ አሜሪካ እንዲቀበሩ እንደሚሹ መልስ ሰጥተዋል። መቸም ያለነው ነጋ ጠባ ፖል (Poll) በሚሰበሰብበት "በሰለጠነው ዓለም" ነውና በተለይም ውሳኔው በእጃቸው ያለ ወገኖች ይህንን ቁጥር ከግምት ያስገቡት ዘንድ እንጠቁማለን።

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

February 23, 2010

በዛሬው የየካቲት 16 የኪዳነ ምሕረት በዓለ ንግሥ ላይ ፀሐይ በቀስተ ደመና ተሸፍና ታየች፤ የምሕረት ያድርግልን


(ደጀ ሰላም፤ የካቲት 16/2002 ዓ.ም፤ ፌብሩዋሪ 23/2010) በዛሬው የየካቲት 16 የኪዳነ ምሕረት በዓለ ንግሥ ላይ ፀሐይ በቀስተ ደመና ተሸፍና ስትታይ ውላለች። ሸገር ሬዲዮ ዜናውን ከዘገበ በኋላ አንድምታውን እንዲያብራሩለት አንድ ባለሙያ ጠይቆ “ጉዳዩት እየተከታተሉት” መሆኑን መልሰዋል።

ክስተቱን ፎቶ ያነሣ “ሰሎሞን ታደሰ ሣህሉ” የተባለ አንድ ኦርቶዶክሳዊ በፌስቡክ ላይ
“ዛሬ በኮተቤ ኪዳነምህረት ቤተ ክርስቲያን ክብረ ባዓሏ ሲነግስ ከቤተ ክርስቲያኑ ጉልላት በላይ የቃል ኪዳኗ ቀስተ ደመና ታየ በላዔ ሰብእን (ሰው በላውን) ያስማረች እናታችን እኛንም በረድኤቷና በፍቅሯ በምልጃዋ አትለየን አሜን!!!”
ብሏል። አሜን ብለናል። ከአንድ ሺህ ቃላት፣ አንድ ፎቶግራፍ ማለት ይኸው አይደል?
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

+++
ኪዳነ ምሕረት
(www.mahiberekidusan.org)፦ ኪዳን የሚለው ቃል ተካየደ ከሚለው የግእዝ ግስ የወጣ ሲሆን ትርጉሙም ተማማለ፣ ተስማማ፣ ውል ገባ ማለት ነው፡፡ ኪዳነ ምሕረት ማለትም ደግሞ የምሕረት ቃል ኪዳን ማለት ነው፡፡ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ለእመቤታችን ድንግል ማርያም ስለሰው ልጆች ይቅርታ የገባላት ቃል ኪዳን ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለሚፈሩት፣ ለሚያከብሩት፣ ለሚወዱትና ለሚወዳቸው ሁሉ በተለያዩ ጊዜያት ብዙ ኪዳናትን ሰጥቷል፡፡ በቅዱሳት መጻሕፍት ከሚጠቀሱት ውስጥ ለአብነት ያህል የሚከተሉትን እንመልከት፡፡


1- ኪዳነ ኖኅ
የሰው ልጆች በምድር ላይ እየበዙ በሔዱ ቁጥር ኃጢአታቸውም እንዲሁ እየበዛ በመሔዱ በውኃ መጥለቅለቅ እንዲጠፉ ባደረገ ጊዜ ጻድቁ ኖኅ የሚድንበትን መርከብ እንዲሠራ አዘዘው፡፡ ኖኅም እንደታዘዘው መርከብን ሥራ፡፡ በየወገናቸው ተባዕትና አንስት እየሆኑ በመርከብ ውስጥ ገብተው እንዲድኑ አደረገ፡፡ የጥፋት ውኃም ካለፈ በኋላ እንደገና እንዲበዙና ምድርን እንዲሞሏት እግዚአብሔር ፈቀደ፡፡ ምድርንም ዳግመኛ በንፍር ውኃ እንዳያጠፋት ለጻድቁ አባታችን ኖኅ ቃል ኪዳን ገባለት፡፡ ቃሉም እንዲህ የሚል ነበር፡፡ «ቃል ኪዳኔንም ለአንተ አቆማለሁ፤ ሥጋ ልባሽ ሁሉ ዳግመኛ በጥፋት ውሃ አይጠፋም፤ ምድርንም ለማጥፋት ዳግመኛ የጥፋት ውሃ አይሆንም፡፡ እግዚአብሔር አለ በእኔና በአንተ መካከል ካንተም ጋር ባለው በሕያው ነፍስ ሁሉ መካከል ለዘላለም የማደርገው የቃልኪዳን ምልክት ይህ ነው፡፡ ቀስቴን በደመና አደርጋለሁ፡፡ የቃል ኪዳኑም ምልክት በእኔና በምድር መካከል ይሆናል፡፡» /ዘፍ.9:13-16/፡፡ ይህም ቃል የጸና ሆኖ ምልክቱ /ቀስተ ደመናው/ እስከ ዛሬ ድረስ በግልጥ ሲታይ ይኖራል፡፡

2- ኪዳነ አብርሃም
አብርሃም ከሣራ ልጅ ባለመውለዱ እያዘነ ሲኖር ከዕለታት አንድ ቀን እግዚአብሔር ተገልጦ «አብርሃም ሆይ አትፍራ እኔ ለአንተ ጋሻህ ነኝ ዋጋህም እጅግ ታላቅ ነው» አለው፡፡ እሱም « አቤቱ እግዚአብሔር ሆይ ምን ትሰጠኛለህ ዘር አልሰጠኸኝም ወራሽም የለኝም» ባለው ጊዜ ልጅ እንደሚወልድ ዘሩም ከሰማይ ከዋክብት ከምድር አሸዋ እንደሚበዙና ከግብፅ እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ያለውን ምድር ለዘሩ እንደሚያወርሰው ቃል ገባለት፡፡ አብርሃምም አምኖ ተቀበለ እንዲሁም ተፈጸመለት /ዘፍ.15:1.7/፡፡

3- ኪዳነ ዳዊት
በነቢዩ ዳዊት አፍ «ኪዳን ተካየድኩ ምስለ ኅሩያንየ፤ ከመረጥኋቸው ከወዳጆቼ ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ» መዝ 88:2 ፡፡ ካለ በኋላ ለእርሱም የሰጠውን ቃል ኪዳን እንመለከታለን ይኸውም ዳዊትን ከሌሎች ወገኖቹ አብልጦ በመረጠውና የብዙ ወገኖቹ መሪ አድርጎ ባስቀመጠው ጊዜ ዳዊት ለፈጣሪው ቅን አገልጋይና ፍጹም ታማኝ በመሆኑ ልበ አምላክ እስከመባል ድርሷል፡፡ «ለአገልጋዬ ለዳዊት ማልሁ ዘሩንም ለዘለዓለም አጸናለሁ» ብሎም ምሎለታል መዝ 88:5 ፡፡ ዘሩንም ለዘለዓለም አጸናለሁ ማለቱም ለጊዜው ለልጁ ለሰሎሞን ይሁን እንጂ ኋላ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከሱ ዘር ከምትሆን ከቅድስት ድንግል ማርያም ተወልዶ ዓለምን ማዳኑን ሲያስረዳ ነው፡፡ ይህም አዳም በፈጸመው በደል በተጸጸተ ጊዜ ከልጅ ልጅህ ተወልጄ አድንሃለሁ የሚል ቃል ኪዳን ገብቶለት ስለነበር ጊዜው ሲደርስ ከድንግል ማርያም ተወልዶ ትንቢቱም እንደተፈጸመ ያረጋግጣል፡፡
እግዚአብሔር አምላክ ለቀደሙት ቅዱሳን አባቶቻችን ያደረገው ቃል ኪዳን እጅግ ብዙ ነው፡፡ በዚህ ጽሑፋችን ውስጥ ማጠቃለል አይቻለንም፡፡ እናም ወደተነሳንበት ርዕሰ ጉዳይ በመመለስ ጌታችን ምደኃኒታችን ኢየሱስ ከርስቶስ ለእናቱ ለእመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም የሰጣታትን ቃል ኪዳን እንመልከት፡፡
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለሰው ልጆች ራሱን አሳልፎ በሰጠ ጊዜ በመስቀል ላይ ተሰቅሎ ነፍሱን በገዛ ፍቃዱ ከስጋው ከመለየቱ በፊት ይወደው የነበረው ደቀ መዝሙር /ዮሐንስ ፍቁረ እግዚእ/ ከመስቀሉ ሥር ስለነበር እናቱ ድንግል ማርያምን ያጽናናት ዘንድ «ነዋ ወልድኪ እነሆ ልጅሽ ወነያ እምከ፤ እነኋት እናትህ » በማለት አደራ ሰጥቶታል፡፡ /ዮሐ.19:26/ ዮሐንስም እመቤታችንን ወደ ቤቱ ወስዶ ካስቀመጣት በኋላ የእናትነት አንጀቷ አልችልላት ስላለ በየቀኑ እየሔደች በልጇ መቃብር በጎልጎታ ላይ እንባዋን እያፈሰሰች ትጸልይ ነበር፡፡ ከእለታት አንድ ቀን እንደተለመደው እያነባች ስትጸልይ ልጇ ክርስቶስ እልፍ አእላፋት መላእክትን አስከትሎ ወደ እርሷ ወረደ፡፡
«ስምሽን የጠራ፣ ቤተክርስቲያንሽን የሠራ፣ በስምሽ የተራበ ያበላ፣ የተጠማውን ያጠጣ፣ የታረዘውን ያለበሰ፣ ያዘነውን ያረጋጋ፣ ወይም ውዳሴሽን የጻፈ፣ ያጻፈ፣ ሴት ልጁንም ሆነ ወንድ ልጁን በስምሽ የሰየመውን ሁሉ እምርልሻለሁ» (ዘሰኔ ጎልጎታ) ሲል ቃል ኪዳን ገብቶላታል፡፡ ይህም የገባላት ቃል ኪዳን የጸና ነው፡፡ ጌታችን ምደኃኒታችን ኢየሱስ ከርስቶስ የተናገረውን የማያስቀር እውነተኛ አምላክ እንደሆነ በቅዱስ መጸሕፍ « አቤቱ የሰማይ አምላክ ሆይ ለሚወዱህና ትዕዛዝህን ለሚያደርጉ ቃል ኪዳንና ምህረትን የምትጠብቅ ታላቅና የተፈራህ አምለክ ሆይ...» ተብሎ ተጽፏል፡፡ እርሷም ልመናዋና ጸሎቷ ስለሰዎች መዳንና መመለስ ስለነበር አመስግና ቃል ኪዳኗን ተቀብላለች፡፡
ይህንንም ቃል ኪዳን የተቀበለችው ከክርስቶስ እርገት በኋላ የካቲት 16 ቀን ስለሆነ፤ ቤተክርስቲያን ባለበት ቦታ ሁሉ በተላቅ ድምቀት ሲከበር ይኖራል፡፡ ይህም ዕለት ከእመቤታችን ታላላቅ በዓላት አንዱ በመሆኑ ምእመናን ሁሉ በደስታና በተስፋ መታሰቢያዋንም በማድረግ ከላይ የተዘረዘሩትን ክርስቲያናዊ ተግባራት በመፈጸም ሊያከብሩት ይገባል፡፡
ለእርሷ የተሰጠው ቃል ኪዳን ለመላው ምእመናን ስለሆነ በእርሷ አማላጅነት ያገኘነውን ተስፋ ለመቀበል እኛ ደግሞ ለተጎዱትና ተስፋ ለሌላቸው ወገኖቻችን እንዲሁ አዛኞችና ሩኅሩሆች መሆን ይጠበቅብናል፡፡
መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከእርሷ ተወልዶ ዓለምን በማዳኑ መድኃኔዓለም ተብሏል፡፡ እርሷም የዓለም ድኃኒት መገኛ በመሆኗ ቤዛዊተ ዓለም ተሰኝታለች፡፡ ስለዚህ ከእግዚአብሔር ቀጥሎ ልናመሰግናት፣ የጸጋ ስግደት ልንሰግድላት፣ ልናከብራትና ልናገናት ይገባናል፡፡ ዛሬ በአፀደ ሥጋ ያለነው ብቻ ሳንሆን በእርሷ ተማጥነው በአማላጅነቷ ድነው በአፀደ ነፍስ ያሉት ነፍሳትም አንቺን ለፈጠረ ለእግዚአብሔር በሰማይ ምስጋና ይድረሰው፤ ከሥጋሽ ሥጋ ከነፍስሽ ነፍስ ነሥቶ ሰው በመሆን በአንቺ ምክንያት የዘለዓለም ሕይወትን አገኝተናል እያሉ ሲያመሰግኑዋት ይኖራሉ፡፡
ከእግዚአብሔር የተሰጣቸውን ቃል ኪዳን ጠብቀውና አክብረው ያለፉ ቅዱሳን አባቶቻችን የዘለዓለም ክብርን እንዳገኙ ሁሉ እኛም ቃሉን ብንጠብቅ ይጠብቀናል፡፡ ብናከብረው ያከብረናል፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔርንም ሆነ የድንግል ማርያምን ስም በመጥራትና በመሐላ የተዋዋልነውን ቃል ኪዳን የምናፈርስ፣በሐሰት የምንናገር በጥቅም ተደልለን ሌላውን የምንጎዳ ከሆነ የተሰጠንን ቃል ኪዳን ዘንግተናል፡፡
«የማይረባውን ቃል ይናገራሉ ቃል ኪዳን በገቡ ጊዜ በሐሰት ይምላሉ፡፡ ስለዚህ በእርሻ ትልም ላይ መርዛም ሥር እንደሚበቅል መቅሠፍት ይበቅልባቸዋል» ሲል ነቢዩ ሆሴዕ እንደተናገረው በምሕረት ፋንታ መቅሰፍትን በሥርየት ፋንታ መርገምን የምናመጣ እንዳንሆን መጠንቀቅ ይገባናል፡፡ ሆሴዕ 10:4
በዚህ ዓለም እርስ በእርሳችን የምናደርጋቸው ውሎችና ቃል ኪዳኖች ፈርሰው ቢገኙ ውል አፍራሽ ወገን በሕግ ፊት ቀርቦ በመረጃ ሲረጋገጥበት ቅጣቱን ተቀብሎ ውላቸው በሕግ የጸና እንደሚሆን ከእግዚአብሔርም የተቀበልነውን ቃል ኪዳን አፍርሰን ከተገኘን የሠራናቸው ክፉ ሥራዎች መረጃ /ምስክር/ በመሆን ያስፈርዱብናል፡፡ በወንጌል «ሰማይና ምድር ያልፋሉ ቃሌ ግን አያልፍም » ማቴ 24:35 ተብሎ እንደተጻፈ፡፡
ስለዚህ የቤተ ከርስቲያን ልጆች የሆንን ምእመናን በሙሉ ጌታችን ኢየሱስ ከርስቶስ ለእናቱ ለድንግል ማርያም በሰጣት ቃል ኪዳን መሠረት በመጠቀም በረከት ለማግኘት እንሽቀዳደም፡፡ ቃሉን ጠብቀን በሕጉ ጸንተን በመኖር በክርስቶስ ይቅር ባይነት በእመቤታችን ድንግል ማርያም አማላጅነት ዘለዓለማዊ ሕይወትን እንድንወርስ መልካም ፈቃዱ ይሁንልን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር
አምላከ ሰማያት ወምድር

“አርማጌዶን” ስብከትን በተመለከተ በድምጽ የተሰጡ አስተያየቶች (Part 3)February 21, 2010

“አርማጌዶን” የስብከት ካሴት ስለ እርሱ እንደሚናገር ዲ/ን በጋሻው ተናገረ፤ የመልስ ቪሲዲ እያዘጋጀሁ ነው አለ

(ደጀ ሰላም፤ ፌብሩዋሪ 21/2010)፦ “አርማጌዶን” በሚል ርዕስ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ ኦርቶዶክሳዊ ያልሆነ እንቅስቃሴ በመዛመት ላይ መሆኑን በማስጠንቀቅ በተሰራጨው ሲዲ ውስጥ በቀጥታ ስም ተጠርቶም ባይሆን የተጠቀስኩት “እኔ ነኝ” ሲል ዲ/ን በጋሻው ደሳለኝ ለ”ሮያል” መጽሔት ተናገረ። በቂም በበቀል የተነሣሣው ዘመድኩን ለግል ጥቅሙ እንድሠራለት የጠየቀኝን ባለመቀበሌ ሊበቀለኝ ስለፈለገ እንዲህ አድርጓል ሲል የተናገረው በጋሻው ይህንን “ደረጃውን ያልጠበቀ” ያለውን ስብከት የሚቃወም “አውሬው ለምን ይቆጣል?” በሚል ርዕስ ቪሲዲ እያዘጋጀ መሆኑን ተናግሯል።

ቃለ ምልልሱን ያደረገው የ“ሮያል” መጽሔት ጋዜጠኛ ሚሊዮን ሹሩቤ (shurubew@yahoo.com) ዲ/ን በጋሻው ምን ያህል ታላቅ ሰው መሆኑን ለመግለጽ ቃላት ሲያጥሩት ቆይተው እርሱ ጋዜጠኛው ደግሞ ለአንባብያን ባለው ከፍተኛ ታዛዥነት ዲ/ን በጋሻውን ያህል ታላቅ ሰው አይወጡ ወጥቶ፣ አይወርዱ ወርዶ ቃለ ምልልስ እንዳደረገው ይገልጻል። በክህነት ዓለም ላሉ የቤተ ክርስቲያን ሰዎች ተደርጎ በማይታወቅ የቃላት ሙገሳ ጋጋታ የተጨናነቀው ይህ መጽሔት ከዚህ በፊትም (ልክ የዛሬ ዓመት በ2001 ዓ.ም) ዲ/ን በጋሻውን ቃለ ምልልስ አድርጎ እንደነበር ተጠቅሷል። መጽሔቱን በዋና ሥራ አስኪያጅነት የሚመራው መኮንን ደሳለኝ የዲ/ን በጋሻው ወንድም እንደሆነ ይነገራል።

ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ሲታወሱ፦ ዝግጅት በአሜሪካ ድምጽ (VOA)፣ ቅንብር በደጀ ሰላምFebruary 19, 2010

ቅዱስ ሲኖዶስ “የብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስን ውግዘት ማንሣቱን”፣ በኢትዮጵያ እንዲቀበሩ መፍቀዱንም አንቀበለውም - በአሜሪካ የሚገኙት አባቶች


(ደጀ ሰላም፤ ኤብሩዋሪ 18/2010)፦ ባለፈው ቅዳሜ ፌብሩዋሪ 13/2010 ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስን አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ ከዚህ በፊት አስተላልፎት የነበረውን ውግዘት ለማንሣትና ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት አባት አስከሬንም በኢትዮጵያ እንዲቀበር መፍቀዱን እንደማይቀበሉ በአሜሪካ የሚገኙት አባቶች አስታወቁ። የአሜሪካ ድምጽ ሬዲዮን ዝግጅት ያዳምጡ፤ መግለጫውንም ያንብቡ


February 16, 2010

ቅዱስ ሲኖዶስ የብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስን ውግዘት አነሣ


(ደጀ ሰላም፤ ፌብሩዋሪ 16/2010)፦ ባለፈው ቅዳሜ ፌብሩዋሪ 13/2010 ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስን አስመልክቶ ቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ ከዚህ በፊት አስተላልፎት የነበረውን ውግዘት ለማንሣትና ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት አባት አስከሬንም በኢትዮጵያ እንዲቀበር እንዲፈቀድ ከስምምነት መድረሱ ታውቋል። ውሳኔው ይፋ በተደረገበት በዛሬው ቀን እንደተረጋገጠው ከሆነ ውግዘቱ የተነሣው ከዚህ ዓለም ድካም አረፍተ ሞት ለገታቸው አባት ብቻ ነው።

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በፓትርያርክ ሹመት ጳጳሳቱ ለሁለት ከተከፈሉ ወዲህ ልዩነቱ በውግዘት ሳይነጻ ቆይቶ በስደት በአሜሪካ የሚገኙት አባቶች ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ “ኤጲስ ቆጶሳትን” ሾምን ካሉ በኋላ ውግዘቱ እንደተከተለ ይታወሳል።

ቅዱስ ሲኖዶስ በዚህ ትልቅ ርእሰ ጉዳይ ላይ መወያየቱ ብዙዎችን እንዳስደሰተ “ደጀ ሰላም” የተረዳች ሲሆን የብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ሥርዓተ ቀብር በጵጵስና ክብር ዞረው በተማሩባት፣ በክህነት በከበሩባት፣ ቀድሰው ባቆረቡባት በሀገራቸው በኢትዮጵያ የሚካሄድ ከሆነ ቤተ ክርስቲያኒቱ በቅርብ ጊዜ የገጠማት የአስተዳደርና የመከፋፈል ድቀት መድኀኒት ያገኛል ተብሎ ተስፋ እንዲጣል ያደርጋል።

ይሁን እንጂ ይህ መቀራረብና የስምምነት ዳር-ዳርታ ሁሉንም ላያስደስት እንደሚችል “የደጀ ሰላም” ተንታኞች የጠቀሱ ሲሆን “መለያየቱ እንጀራ የሆናቸው ቡድኖች” በተለይም የዚህ የመከፋፈል አባዜ ግንባር ቀደም መሪ ናቸው የሚባሉ አንዳንድ አባቶችና የፖለቲካ ትኩሳት ያላቸው ሰዎች በጉዳዩ አይደሰቱም፤ በዚህም ነገሩ እንዳይሳካ ሳንካ እንዲገጥም ያደርጋሉ ብለዋል።

በርግጥም ቅዱስ ሲኖዶሱ በዚህ ጉዳይ ላይ ተነጋግሮ በመወሰኑ ቅዱስ ፓትርያርኩም ሆኑ የቅዱስ ሲኖዶሱ አባላት የሆኑት ብፁዓን አባቶች መመስገን እንደሚገባቸው “ደጀ ሰላም” ታምናለች። በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከጊዜያዊ ግርግር ባሻገር ያለውን የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ለመመልከት መቻል ትልቅ ጥበብ ነው። ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ዛሬ ያሉበት ሁኔታ ሳይሆን የትናንት አገልግሎታቸው ሳይዘነጋ በክብር ለአገራቸው አፈር እንዲበቁ ማድረግ ይገባል። በውጪ የሚገኙ “የቅርብ ነን” የሚሉ በሙሉም የብፁዕነታቸው የመጨረሻ ማረፊያ ኢትዮጵያ እንዲሆን፣ በሚገባቸው ክብር እንዲሸኙ በማድረግ በኩል አዎንታዊ በሆነ መልኩ ይተባበራሉ ብለን እንጠብቃለን። ል ዩነቱ ይብቃ!!!! ግንቡ ይፍረስ!!!

“የት ይቀብሩ ይሆን?” - “ቤተ ክርስቲያን አሁን አንድ ትሆን ይሆን?” - ምኞት ወይስ ተስፋ?


(ከ-ዘክርስቶስ)
ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ አረፉ። በጣም አዘንኩ። በተለይ የቤተ ክርስቲያንን አንድነት እውን ሆኖ ሳያዩ ወይም እውን እንዲሆን ሳያደርጉ …ብቻ እንዲሁ ቤተ ክርስቲያን ለሁለት እንደተከፈለች ማረፋቸው ሐዘኔን እጥፍ ድርብ አደረገው። ከዛ ተረጋግቼ ሳስብ ደግሞ የት ይሆን የሚቀበሩት የሚለው ማሰብ ጀመርኩ።
ይህን ጥያቄ ማንሳቴ ራሱ አናደደኝ። ለምን ማንም የፓለቲካ ችግር ያለበት ሰው እንኳን በሕይወት ዘመኑ ወደ አገር ቤት መሄድ ባይችል ቢያንስ ሲያርፍ ኢትዮጵያ ሄዶ ይቀበር ይሆን ወይ የሚለው ጥያቄ እንደ ጥያቄ ራሱ አይነሳም። የብፁዕ አባታችን በምንም ዓይነት መለኪያ የፓለቲካ ችግር ካለበት ወይም ከነበረበት ሰው ጋር አይወዳደርም አይነጻጸርም። ግን ምን ላድርግ የሃይማኖት አባቶች ከፓለቲከኞች የባሰ ልብና አእምሮ በያዙበት ዘመን አፍን ሞልቶ ይህ ይሆናል ማለት አለመቻሌ ያው የጋራ ችግራችን አስከፊነት ምልክት ነው።

ችግሩን ያባባሰውና የት እንደሚቀበሩ ጥያቄ እንዲሆን ያደረገው ደግሞ “አገር ቤት ያሉት አባቶች እንዴት ነው የሚያዩት?” የሚለው በአንድ ወገን “ከዛም ውጪ ያሉት አባቶችስ ምን ይሆን የሚወስኑት?” የሚለው በሌላ በኩል እየተጨነቅን እያለ አገር ቤት ያሉት አባቶች የነበረው ውግዘት አንስቶ የአባታችን ቀብርም በኢትዮጵያ እንዲሆን መወሰኑን ሰማን። በጣም ደስ አለኝ። አዲስ ተስፋ ታየን ወይም አማረን። እኝህ አባት ተወዳጅ ሰለነበሩ “ምናልባት በሕይወታቸው ሲመኙት የነበረውን አንድነት ዕረፍታቸው ምክንያት ሆኖ ቤተ ክርስቲያን አንድ ትሆን ይሆን?” የሚለው ተስፋዬ ለመለመ - እንደሌላው ሰው ሁሉ ማለት ነው።
የእሳቸው ተዋድጅነትና ወቅቱ “የትና እንዴት ይቀበሩ?” ይሆን የሚለው “አሁን ቤተ ክርስቲያን አንድ ትሆን ይሆን?” ከሚለው ጋር ተያያዘ። እናም “ውጭ ያሉት አባቶች ምን ይሉ ይሆን?” እያልን ምንስ ማድረግ አለብን እያልን መጨነቅ ያዝን። ከዛም ውጭ ባሉት አባቶች የአባታችንን ዕረፍት በተመለከተ የወጣ መርሐ ግብር ላይ “ወደ ተዘጋጀላቸው ማረፊያ” ይሄዳሉ የሚል አነበብን። መርሐ ግብሩ የቀብር ሥነ ሥርዓት አይልም። “ወደ ተዘጋጀላቸው ማረፊያ” ማለት ምን ማለትና የት ይሆን ስንል አሰብን። ያው አገር ቤት ካሉት አባቶች ጋር ገና እየተነጋገሩ ስለሆነና ስላልወሰኑ ይሆናል ብዬ አሰብኩ ወይም ማሰብ ፈለግኩ።
በቅርብ የምናውቀው ሰውን ሞት መስማት የሆነ በጎ የማሳሰብ፣ ልብን የማለስለስ ነገር ስለሚያመጣ በዛ ላይ የሃይማኖት አባትነታቸው ተጨምሮ ኧረ እኛም እኮ ነገ እንደዚሁ ነን እና እስቲ ይህን አጋጣሚ ለአንድነት እንጠቀምበት ይላሉ ከሚለው ምኞትና ተስፋ ጋር በዛ ላይ ደግሞ በባህላችንም በሥርአታችንም እንኳን አቡነ ዜና ማርቆስን ለመሰለ ሊቀጳጳስ ቀርቶ ለሌላውም ለቀብር በቦታውና በጊዜ መፈጸም ከምንሰጠው ትኩረት አንጻር ከአሁን አሁን አንድ ጥሩ ነገር እንሰማለን እያልን ጓጓን። እሳቸው አገር ቤት ሊቀበሩ ሲሄዱ ውጭ ያሉት እነ አቡነ መልከጺዴቅ አቡነ ኤልያስ እና ፓትርያርኩ አቡነ መርቆርዮስ አብረው ይሄዱና በዛው መነጋገር ይጀምራሉ የሚል ጉጉት ማለት ነው።
በዚህ ጉጉት ላይ እያለሁ ውሸት እንዲሆን የምመኘው አስደንጋጭ ነገር ውጭ ከሚኖሩት አባቶች አካባቢ ሰማሁ። አሁንም ውሸት እንዲሆን የምመኘው ቢሆንም እውነት እንዳይሆን እነዚህን አባቶች መለመን እንድንችልን የምንጓጓለት ነገር እንዲሳካ ለማድረግ የሰማሁትን ነገር ላስቀምጥ።
ያሰቡት የትም እንዲቀበሩ ሳይሆን ለረጅም ጊዜ (ለዓመታት) አስከሬን ማስቀመጥ የሚቻልበት ቦታ ለማቆየት ነው(እንደ ማቀዝቀዣ ቢጤ)። ይህንን ስሰማ መርሐ ግብሩ ላይ ለካ “ቀብር” የሚል ቃል ሳይኖር “ወደ ተዘጋጀላቸው ማረፊያ” በሚል የተገለጸው ለዚህ ነው አልኩኝ። እናም እንደገና እጅግ አዘንኩ። ብዙ ጥያቄዎች መጡብኝ ምን ለማለት ተፈልጎ ይሆን? ማንን ለመጥቀም? ማንን ለማስደሰት? ማንን ለመጉዳት? በየትኛው ልማድ መሠረት ተወሰነ? ማን ወሰነው? እጅግ አፋጣኝና ወሳኝ መልስ የሚያስፈልጋቸው ጥያቄዎች።
እነ አቡነ መልከ ጼዴቅና እነ አቡነ ኤልያስ ለራቸው ይህን ነው የሚመኙት? አይመሰለኝም። ወይም እንዲመኙ አልፈልግም። ታዲያ ምን ነካቸው? የምንመኘው የቤተ ክርስቲያንስ አንድነት እሺ ይቅር ብፁዕ አባታችን በሕይወት ዘመናችን ሳሉ ሲረዷቸው የነበሩት የደብረ ሊባኖስ መነኮሳት ቢያንስ በክብር መቅበር አለባቸው እኮ። አረፉ ግን አልተቀበሩም? ካረፉ በኋላ ታገቱ ዓይነት አሠራር ምን ማለት ነው? ከላይ እንደተባለው መቼም ቢሆን አገር ቤት መግባት አይችሉም የሚባሉ ፓለቲከኞች ላይ እንኳን መድረስ የሌለበት ብቻ ሳይሆን ደርሶም የማያውቅ ነገር ብፁዕ አባታችን ላይ መድረስ የለበትም።
ውሸት በሆነ የሚለው ምኞቴ እንዳለ ሆኖ ይህንን ነገር ማጣራት እና እንዳይደረግም ማድረግ የሁላችንም ማለትም የቤተ ክርስቲያን አንድነት ይገደናል የምንል ወገኖች ኃላፊነት ነው፤ ጥረታችንም በሚቀጥሉት ሰዓታት ይጥበቅብናል።
የአባታችንን ነፍስ ከደጋጎቹ አበው ጋር ያቁምልን።
መንፈሳዊ ልብ ይስጠን።

February 15, 2010

“ቋሚ ሲኖዶስ” በብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ቀብር ጉዳይ ተነጋገረ

(ደጀ ሰላም፤ ፌብሩዋሪ 15/2010)፦ ባለፈው ቅዳሜ ፌብሩዋሪ 13/2010 ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስን አስመልክቶ “ቋሚ ሲኖዶስ” ዝግ ስብሰባ ማድረጉ ታወቀ። በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ሰብሳቢነት ተደረገ በተባለው በዚህ ስብሰባ ቅዱስ ሲኖዶስ ከዚህ በፊት አስተላልፎት የነበረውን ውግዘት ለማንሣትና ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩት አባት አስከሬንም በኢትዮጵያ እንዲቀበር እንዲፈቀድ ከስምምነት ተደርሷል ተብሏል። ውሳኔው ግን ገና ይፋ አልተደረገም።

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በፓትርያርክ ሹመት ጳጳሳቱ ለሁለት ከተከፈሉ ወዲህ ልዩነቱ በውግዘት ሳይነጻ ቆይቶ በስደት በአሜሪካ የሚገኙት አባቶች ቀኖና ቤተ ክርስቲያንን በመጣስ “ኤጲስ ቆጶሳትን” ሾምን ካሉ በኋላ ውግዘቱ እንደተከተለ ይታወሳል።

“ቋሚ ሲኖዶስ” በዚህ ትልቅ ርእሰ ጉዳይ ላይ መወያየቱ ብዙዎችን እንዳስደሰተ “ደጀ ሰላም” የተረዳች ሲሆን የብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ሥርዓተ ቀብር በጵጵስና ክብር ዞረው በተማሩባት፣ በክህነት በከበሩባት፣ ቀድሰው ባቆረቡባት በሀገራቸው በኢትዮጵያ የሚካሄድ ከሆነ ቤተ ክርስቲያኑ በቅርብ ጊዜ የገጠማት አስተዳደርና የመከፋፈል ድቀት መድኀኒት ያገኛል ተብሎ ተስፋ እንዲጣል ያደርጋል።

ይሁን እንጂ ይህ መቀራረብና የስምምነት ዳር-ዳርታ ሁሉንም ላያስደስት እንደሚችል “የደጀ ሰላም” ተንታኞች የጠቀሱ ሲሆን “መለያየቱ እንጀራ የሆናቸው ቡድኖች” በጉዳዩ አይደሰቱም፤ በዚህም ነገሩ እንዳይሳካ ሳንካ እንዲገጥም ያደርጋሉ ብለዋል።

በርግጥም ቋሚ ሲኖዶሱ በዚህ ጉዳይ ላይ ተነጋግሮ ከሆነ ቅዱስ ፓትርያርኩም ሆኑ የቋሚ ሲኖዶሱ አባላት የሆኑት ብፁዓን አባቶች መመስገን እንደሚገባቸው “ደጀ ሰላም” ታምናለች። በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ከጊዜያዊ ግርግር ባሻገር ያለውን የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ለመመልከት መቻል ትልቅ ጥበብ ነው። ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ዛሬ ያሉበት ሁኔታ ሳይሆን የትናንት አገልግሎታቸው ሳይዘነጋ በክብር ለአገራቸው አፈር እንዲበቁ ማድረግ ይገባል። በውጪ የሚገኙ “የቅርብ ነን” የሚሉ በሙሉም የብፁዕነታቸው የመጨረሻ ማረፊያ ኢትዮጵያ እንዲሆን፣ በሚገባቸው ክብር እንዲሸኙ በማድረግ በኩል አዎንታዊ በሆነ መልኩ ይተባበራሉ ብለን እንጠብቃለን። ልዩነቱ ይብቃ!!!! ግንቡ ይፍረስ!!!

“ደጀ ሰላም”ም ጉዳዩን እየተከታተለች መዘገቧን እንደምትቀጥል እያስታወቀች፤ ስለ ጉዳዩ ያላችሁን አስተያት በድምጽ መልእክት በመተው ወይም እንደተለመደው በመጻፍ ሐሳባችሁን እንድትገልፁ ትጋብዛለች።

“አርማጌዶን” ስብከትን በተመለከተ በድምጽ የተሰጡ አስተያየቶች

3.
+++
2.

1.

ለማንኛውም የዘመድኩን በቀለን ዝግጅት ለማዳመጥ የሚከተለውን ይጫኑ፦


አስተያየታችሁን በሁለት መልክ እንድትሰጡ ትጠየቃላችሁ።
1ኛ. ሁል ጊዜም እንደተለመደው በጽሑፍ፣
2ኛ. በአሜሪካ ለምትገኙ ደጀ-ሰላማውያን ደግሞ አስተያየታችሁን በድምጽ መተው ትችላላችሁ። ነጻ ነው።

ቸር ወሬ ያሰማን፣
+++

February 14, 2010

ሰበር ዜና/Breaking News - አሜሪካ የሚገኙት ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ አረፉ


(ደጀ ሰላም፤ ፌብሩዋሪ 13/2010)፦ ከሀገራቸው በስደት ወጥተው በአሜሪካ ይኖሩ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ ዛሬ ማረፋቸውን የቅርብ ምንጮች ገለፁ። የፓትርያርክ ለውጥ ከተደረገበት ከ1984 ዓ.ም ጀምሮ በስደት የነበሩት ብፁዕነታቸው ዛሬ ያረፉ ሲሆን ዕረፍታቸው የቤተ ክርስቲያንን አንድነት ሲናፍቁ ለነበሩ በሙሉ ታላቅ የቅስም መሰበርን ፈጥሯል።

ብፁዕነታቸው በዘመናዊው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ታሪክ ውስጥ ይከበሩና ይወደዱ ከነበሩ አባቶች አንዱ የነበሩ ሲሆን በተለይም የቅርብ ጓኛቸውና የሃይማኖት ወንድማቸው የነበሩት ታላቁ ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ የሚያደንቋቸው አባት እንደነበሩ ይታወቃል።

ብፁዕነታቸው በቤተ ክህነት ፖለቲካ ተጠልፈው የ”ስደተኛው ደጋፊ” ከመሆናቸው በስተቀር በቤተ ክህነቱ አበው መካከል ለተፈጠረው ልዩነት መፍትሔ ይሆናሉ ተብለው ተስፋ ይጣልባቸው ነበር።

የብፁዕነታቸውን ነፍስ በደጋጎቹ አባቶች ሀገር፣ ከአባቶቻችን ከአብርሃም፣ ከይስሐቅና ከያዕቆብ ጋር ያድርግልን፤ አሜን
February 12, 2010

የመሐል ዘጌ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በእሳት ተቃጠለ ተባለ


(ደጀ ሰላም፤ ፌብሩዋሪ 12/2010)፦ በጣና ሐይቅ ዙሪያ ከሚገኙት የዘጌ ገዳማት መካከል አንዱ የሆነው የመሐል ዘጌ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ የካቲት 5 ቀን 2002 ዓ.ም ከቀኑ 12፡00 ሰዓት ጀምሮ የአደጋዉ ምክንያት ባልታወቀ እሳት ሙሉ በሙሉ ወድሟል ሲል የማኀበረ ቅዱሳን ድረ ገጽ ዘገበ።

እሳቱን ለማጥፋት በገዳሙ ዙሪያ የሚገኙ ምዕመናን ፣ በአካባቢው የሚገኘው የኢትዮጵያ መከላከያ ኃይል እና ከባሕር ዳር ከተማ በጀልባ ተሳፍረው የሄዱ ምዕመናን ጥረት ቢያደርጉም የእሳቱን ቃጠሎ ለመከላከል እንዳልተቻላቸው ዜናው አትቶ አሁንም እሳቱ ከሰው ቁመት በላይ በመንደድ ላይ ነው ብሏል። እሳቱ በአፋጣኝ መገታት ካልተቻለ በመቀጠል የአቡነ በትረ ማርያምን ገዳምንም ሊያጠቃ ይችላል የሚል ስጋት ተፈጥሯል። ይህም ሆኖ በቦታው የተገኘው የመከላከያ ኃይልና ምዕመናን በአንድነት ሆነው በመካከል የሚገኙ ዛፎችን በመቁረጥ የአቡነ በትረ ማርያምን ገዳም ለማዳን በመጣር ላይ እንደሚገኙ በማኀበረ ቅዱሳን የባህር ዳር ማዕከልን ዋቢ አድርጎ ድረ ገፁ ዘግቧል።

++++
maregne yeqere belegne has left a new comment on your post "የመሐል ዘጌ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን በእሳት ተቃጠለ ተባለ":

የዘጌ ገዳማት መካከል አንዱ የሆነው የመሐል ዘጌ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ዛሬ የካቲት 5 ቀን 2002 ዓ.ም ከቀኑ 12፡00 ሰዓት (በ ኢትዮጲያ አቆጣጠር) ጀምሮ የአደጋዉ ምክንያት ባልታወቀ እሳት ሙሉ በሙሉ ወደመ።ይህ ግጥም መታሰቢያ ይሁንልኝ።
የመላእክት ዝማሬ የቅዱሳን ቦታ
ፍጽም ሰላም ያለው ለመንፍስ እርካታ
የአባቶቻችን ርስት የታቦታት ቦታ
ግርማ ሞገስ ያለው ይህን ላየው ላፍታ
ይሄው ተለወጠ ወደ ባዶ ቦታ
እርግጥ (ቅዱስ) መንፍስ አለ በቅዱሳን ቦታ
ይሄው በስንፍና እንደው በዝምታ
መጠበቅ ተስኖን ይህን ታላ...ቅ ቦታ
በእሳት አጣነው እንደው በቸልታ
ተባብረን ካልሰራን በፍቅር ሰላምታ
እጅ ለእጅ ተያይዘን በፍቅር አንድምታ
አንተ ትብስ ሆኖ ካልሆነ ይቅርታ
ከአሁኑ ይባስ ነው የነገ ዕጣፈንታ
ከእግዜር ካልተመለስን በፍጽም ይቅርታ
እንዴት ይምጣ ምህረት ከሃያሉ ጌታ
ወገኔ እንጸልይ ከጧት እስከ ማታ
ይመጣል ምህረት ከመሃሪው ጌታ
ቸርነቱ አያልቅም ካመንን በጌታ
ጌታ ሆይ አድነን እንደው በይቅርታ
አምላክ ሆይ ላክልን ፍጣኑን መከታ
ጊዮርጊስ በፈረስ ቅዱሳን በተርታ
ጌታ ሆይ አድለን ቅዱስ መንፈስህን እንድንበረታ
አሜን አሜን አሜን ::

February 11, 2010

“አርማጌዶን” በድምጽ የተዘጋጀውን ስብከት ያዳምጡ እና አስተያየቶን ይስጡ!!!

• በተባባሪ የደጀ-ሰላም አንባብያን ርዳታ ስብከቱን አግኝተናል!!
(ደጀ ሰላም፤ ፌብሩዋሪ 10/2010)፦ የዚህን ስብከት ዜና ካወጣንበት ካለፈው ሳምንት ጀምሮ ጉዳዩን በተመለከተ የተለያዩ አስተያየቶች ሲሰጡ ቆይተዋል። ከ107 በላይ መልእክቶችና አስተያየቶች መሰጠታቸውን ዜናው ሥር ያለው መቁጠሪያ ያመለክታል። ሁሉም አስተያየት ደረጃውን የጠበቀ እና ለውይይት የሚጋብዝ ባይሆንም ከሞላ ጎደል ግን ጥሩ ሐሳቦች የተንሸራሸሩበት ነው ማለት ይቻላል።

የተወሰኑ ደጀ-ሰላማውያን “እባካችሁ እንደዚህ ዓይነቱን ነገር እንተወው” ሲሉ ሌሎቹ ደግሞ “ውይይቱ መጀመሩ ጥሩ ነው ነገር ግን አዘጋጁ ዘመድኩን በቅንዓት ያደረገው ነው” ይላሉ፤ ሌሎች ደግሞ ነገሩን ከማ/ቅዱሳን ጋር በማገናኘት እነርሱ ሥራ ነው ብለዋል። ወዘተ ወዘተ በሁሉም በሁሉም ግን ስለ ዲ/ን በጋሻው ትምህርቶች፣ መዝሙሮች እና መጽሐፎች መነጋገር ገና አልጀመርንም። እስቲ “አርማጌዶን”ን እናዳምጥ እና ውይይቱን ከስድብና ስም ከመጥራት በተሻለ እንወያይበት።

ለማንኛውም የዘመድኩን በቀለን ዝግጅት ለማዳመጥ የሚከተለውን ይጫኑ፦
zSHARE - armagedon.mp3

አስተያየታችሁን በሁለት መልክ እንድትሰጡ ትጠየቃላችሁ።
1ኛ. ሁል ጊዜም እንደተለመደው በጽሑፍ፣
2ኛ. በአሜሪካ ለምትገኙ ደጀ-ሰላማውያን ደግሞ አስተያየታችሁን በድምጽ መተው ትችላላችሁ። ነጻ ነው።

ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

February 4, 2010

“አርማጌዶን” የተባለ አነጋጋሪ የስብከት ሲዲ ተለቀቀ


(ደጀ ሰላም፤ ፌብሩዋሪ 4/2010)፦ “አርማጌዶን” በሚል ርዕስ በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አዳዲስ ሰባኪያን ዙሪያ የተዘጋጀ የስብከት ሲ.ዲ በአዲስ አበባ በሽያጭ ላይ መዋሉ ታወቀ።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአዲስ የአሰባበክ ዘዴ በተለይም ከዚህ በፊት ባልተለመደ መልኩ ከባህላዊ የዘፈን ስልት ጋር በሚስተካከል ዜማ መዝሙሮችን በማዘጋጀት እንዲሁም ስብከቶችን በስቱዲዮ ቀርጾ በማሰራጨት በታወቀው በዲ/ን በጋሻው ደሳለኝ እና በጓደኞቹ ላይ አነጣጥሯል የተባለው ይኸው ሲዲ በጉጉት ሲጠበቅ ቆይቶ አሁን በገበያ ላይ ውሏል። ዘመድኩን በቀለ በተባሉ ሰው የተዘጋጀው ይህ ሲዲ በዲ/ን በጋሻውና በእንቅስቃሴው ዙሪያ ቅሬታ የነበራቸውን በሙሉ በይፋ ተቃውሟቸውን እንዲያሰሙ በር ይከፍታል ተብሎ ይጠበቃል።

ዲ/ን በጋሻው “የመስቀሉ ስር ቁማርተኞች” በሚል ርእስ ባሳተማት ፓምፍሌት መሰል 100 ገጽ ባልሞላች መጽሐፍ ፓትርያርኩን በይፋ በመቃወሙ ለመታወቅ የበቃ ሲሆን በዚሁ ምክንያት ነው በተባለ ሰበብ ለሁለት ሳምንታት ለመታሰርም በቅቶ ነበር። ይሁን እንጂ “በሽማግሌዎች አቀራራቢነት” ነው በተባለ መልኩ ዲ/ን በጋሻው ከቅዱስ ፓትርያርኩ ጋር የታረቀ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ “ቤተኛ” ለመሆን መብቃቱም ይነገራል። በዚህም ቤተኝነት ከዚህ በፊት በየትም ቦታ ሄዶ እንዳይሰብክ ተጥሎበት የነበረው ማዕቀብ የተነሣለት ሲሆን ያቋቋመው ማኀበርም በቅዱስ ፓትርያርኩ ትእዛዝ “ማኀበረ ማርያም” ተብሎ በቤተ ክህነቱ ፈቃድ እንዲያገኝ እንደተደረገ ውስጥ አዋቂዎች ይናገራሉ።
February 3, 2010

Ethiopian women: trafficked and trapped in Lebanon


by Marian
(Blogher)You have to search hard and then read between the lines to find anything about the tens of thousands of African women - mostly Ethiopian - currently trapped in Lebanon in the midst of the humanitarian disaster caused by Israel's overwhelming and prolonged military assault. Just to interject a piece of traditional wisdom about this deadly turn in the "Mideast (read Palestinian) conflict": Two wrongs don't make a right. What I find just as sad as whole-scale cross-border fighting is that even before these missile and rocket attacks began these women already were trapped in a largely ignored humanitarian disaster - in Lebanon and elsewhere in the Middle East. What other African countries likely have citizens trapped in Lebanon's man-made tragedy? Somalia, Burundi, and probably even Nigeria. On Wed., 19 July from relative safety in a Beirut underground parking garage, BBC News showed the unidentified face of a lone displaced Ethiopian woman. She appeared to be 40ish and seemed to be wearing a blue maid's uniform. Obviously distressed, she stood against a cement pillar, covering her mouth with her hand. In that moment my impression was she seemed alone, even among the people - mostly Lebanese - also sheltering there and milling around her.

It was a few years ago while living in Nairobi, in east Africa, that I first learned that Ethiopian women were being trafficked to Lebanon, including for prostitution.

Blogher's own JaninSanFran's Happening Here blog has an entry on foreign workers trapped in Lebanon - "Foreign nationals under the Israeli gun". Jan's post includes the BBC's own chart showing numbers of other countries' nationals in Lebanon (attached below). Five of the six countries have populations traditionally, and not always accurately, identified as white or only slightly more vaguely "European". The same groups are euphemistically referred to as "westerners". The sole exception on the BBC list is the Philippines.

In spite of the obvious geography of the current crisis - i.e., the so-called Middle East adjoins Africa - for some reason there is far more awareness of the thousands of "guest workers" in Lebanon from Asia - Sri Lanka and Philippines in particular - yet next to nothing on persons from countries virtually next door to the west and south of Egypt. That would be Africa. In the midst of shelling and lack of electricity, food and water, and uneven evacuations by other countries of their nationals, virtually all these Africans and Asians remain stranded: unaided or somehow 'beyond the reach' of assistance by their own governments (or in Somalia's case transitional, interim government ).

Ethiopian writer Bathseba Belai corroborates the broader issues of trafficking as she writes about the "forgotten diaspora" of Ethiopian women labour migrants in the Middle East.

According to the U.S. State Department's 2005 Lebanon human rights report, from July 2004 the Lebanese government quit issuing visas to Ethiopian migrant workers. "... the SG [Lebanese police known as the "surete general"] stopped issuing visas to migrant workers from Ethiopia because Ethiopian authorities could not guarantee that adequate safeguards against fraud in the recruitment of these women for work in Lebanon were being taken."

State Department's Ethiopia human rights report for the same year goes into detail:
"... Young Ethiopian women were trafficked to Djibouti and the Middle East, particularly Lebanon, the United Arab Emirates, Saudi Arabia, and Bahrain for involuntary domestic labor. A small percentage were trafficked for sexual exploitation to Europe via Lebanon.
How many women equal "a small percentage"?


"... Private entities arranged for overseas work and, as a result, traffickers sent women to Middle Eastern countries--particularly Lebanon, Saudi Arabia, Bahrain, and the United Arab Emirates--as domestic or industrial workers. These women typically were trafficked through Djibouti, Yemen, and Syria. The chief of the investigation and detention center in Lebanon reported in October [2005] that 30 thousand Ethiopian women worked in Beirut, the vast majority of whom were trafficked. ... Approximately 50 percent of these women were not able to return legally to their home country. ...
Somali Islamists al-Shabab 'join al-Qaeda fight'

(BBC): Somali Islamist rebel group al-Shabab has confirmed for the first time that its fighters are aligned with al-Qaeda's global militant campaign. The group said in a statement that the "jihad of Horn of Africa must be combined with the international jihad led by the al-Qaeda network". Meanwhile, several people have died in fighting in Mogadishu after government troops shelled militant positions. Islamist insurgents control much of southern and central Somalia.

The government, which is backed by the UN and African Union, holds sway only in a small part of Mogadishu. Despite repeated accusations by the US that al-Shabab is linked to al-Qaeda, the group denied the connection in a recent interview with the BBC.
The BBC Somali service's Mohamed Mohamed says it is the first time the group has officially confirmed its fight is linked to al-Qaeda.

'Financer of terrorism'
The group's statement also announced that its militants had joined forces with a smaller insurgent group called Kamboni.

The group, based in the southern town of Ras Kamboni, was previously allied to Hizbul-Islam - another militant group fighting the government. Kamboni is led by Hassan Turki, a militant the US accuses of being a "financer of terrorism".

Al-Shabab said it was trying to unite all Islamist forces to create a Muslim state under its hard-line interpretation of Sharia law. The group, which controls swathes of Somalia, has carried out public beheadings and stonings.

'Human shields'
Meanwhile in Mogadishu reports said at least eight civilians were killed in fighting overnight. "Our team collected eight bodies of civilians who were killed in the shelling and 55 others who were injured, some of them seriously," health official Ali Musa told the AFP news agency. Militants had launched an artillery attack on the presidential compound, and government and African Union forces responded with several mortar shells.

AFP quoted an unnamed police official accusing the rebels of hiding in civilian areas and using "human shields". Somalia has been wracked by violence for much of the past 20 years. It has not had a functioning central government since 1991.
Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)