January 27, 2010

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ከዛሬ ጀምሮ የሦስት ቀናት ሐዘን አወጀች(በታምሩ ጽጌ)
(ሪፖርተር ጋዜጣ)የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን፣ ንብረትነቱ የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሆነው አውሮፕላን ተሳፍረው፣ ከቤይሩት ወደ አዲስ አበባ በመብረር ላይ እንዳሉ፣ ምክንያቱ ባልታወቀ ሁኔታ በሜዲትራኒያን ባሕር ላይ ተከስክሶ ሕይወታቸው ባለፈው ኢትዮጵያውያንና የሌሎች ሀገራት ዜጎች የተሰማትን ሐዘን ምክንያት በማድረግ ከዛሬ ንጋት 12፡00 ሰዓት ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት የሐዘን ቀን ማወጇን አስታወቀች፡፡


ቤተ ክርስቲያኗ ባስተላለፈችው ሦስት የሐዘን ቀናት አዋጅ መሠረት፣ በሁሉም የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት ጠዋት ጠዋት ደወል እንደሚደወልና፣ ጸሎተ ፍትሐት እንደሚደረግ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅና የባሌ ሀገር ስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ይሥሐቅ አስታውቀዋል፡፡

የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን፣ በደረሰው ድንገተኛ አደጋ የተሰማትን ልባዊና ጥልቅ ሐዘን በመግለጽ፣ የሐዘን ቀናት እንዲታወጅ ትዕዛዝ ያስተላለፉት፣ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወፓትርያርክ ዘኢትዮጵያ፣ በደቡብ አፍሪካ በሐዋርያዊ ጉዞ ላይ ሆነው መሆኑን አቡነ ይሥሐቅ ተናግረዋል፡፡

..እግዚአብሔር በፈቀደው ቀን የሰው ልጅ ወደ ዓለም ይመጣል፡፡ በፈቀደው ቀን ደግሞ ይወስዳል እንጂ፤ በዓለም እስከ መጨረሻው ሊኖር አልተፈቀደም.. ያሉት ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ለጥር 17 ቀን 2002 ዓ.ም. አጥቢያ የደረሰውን ያልታሰበ አደጋ፣ በውጭ አገር ሆነው ሲሰሙ ልባቸው በሐዘን መነካቱን ገልጸዋል፡፡


በሀገር ውስጥ ያሉ እና በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ያሉ የተጐጂ ቤተሰቦች፣ በፍጹም ሐዘን ውስጥ በመሆን ተስፋ መቁረጥና ራሳቸውን መጉዳት እንደሌለባቸው ቅዱስ ፓትርያርኩ መልዕክታቸውን አስተላልፈው፣ ልዑል እግዚአብሔር መጽናናትን እንዲሰጣቸው ተማጽነዋል፡፡

በመልካም ስሙና አገልግሎቱ የሚታወቀውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ሠራተኞች፣ ኃላፊዎችና መላው የኢትዮጵያን ሕዝብ እግዚአብሔር መጽናናትን እንዲሰጣቸው እንደሚማፀኑ የገለጹት ፓትርያርኩ፤ የአደጋው ሰለባ የሆኑት ኢትዮጵያውያን አስከሬን ወደ አገራቸው ሲገባ ተገቢው መንፈሳዊ አቀባበል እንዲደረግላቸው፣ ከብፁዐን አባቶች፣ ከአዲስ አበባ አድባራትና ገዳማት ጋር በመሆንም በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ተገኝተው በጸሎት እንዲታሰብ ዝግጅት እንዲያደርጉ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል፡፡

የበረራ ቁጥሩ ኢት 409፣ 737 ቦይንግ በሆነው የኢትዮጵያ አውሮፕላን ውስጥ ተሳፍረው በመጓዝ ላይ የነበሩት 22 ኢትዮጵያውያን፣ 52 ሊባኖሳውያን፣ 8 የተለያዩ ሀገራት ዜጎች እና 8 የአውሮፕላን በረራ ሠራተኞች መሆናቸው ታውቋል፡፡
14 comments:

Anonymous said...

ሀዘን ማወጁ ጥሩ ነው። በ97 ምርጫ በእናት ሀገራቸው በገዛ ወንድሞቻቸው፤ በራሳቸው ገንዘብ በተገዛ ጥይት ለረገፉት ኢትዮጵያዉያን ስለምን የሀዘን አዋጅ ሳይታወጅ፧ስለምን መታሰቢያ ሳይደረግ? እግዚአብሔር አይታለልም!!!

Anonymous said...

It really sad story and should be thought in prayers.

Anonymous said...

እግዚአብሔር በዚህ አደጋ ህይወታቸውን ያጡትን ሁሉ ነፍስ ይማርልን፡፡ ቤተክርስቲያን የሀዘን ጊዜ ማወጇ ተገቢ ነው፡፡ ሁሌ መተቸት ብቻ ስራቸው ለሆኑትም እግዚአብሔር ልብ ይሥጣቸው፡፡

Anonymous said...

በቅድሚያ ነፍስ ይማር!

ስለቤተክሲያኗ አዋጅ ግን፦ ከልብ ከኾነ... (ታዲያ ከምን ሊኾን ይችላል? ማዘን የሚቻለው "በልብ" አይደለም እንዴ?)

በበኵሌ ቤተክሲያኗ አኹን ካለችበት ኹኔታ አንጻር፤ የሚከተለውን ጥያቄ በአዎንታ መመለስ የሚቻል አይመስለኝም፦

"ለመኾኑ ቤተክሲያኗ ከልቧ ናት ወይ? ልብ አላት ወይ?"

ይኽ ጥያቄ ባዎንታ ካልተመለሰ ደግሞ፦ አዋጁ "ካንገት በላይ" ደፋ ቀና ለማለት ነው። በቃ። ያውም ታይታው የሚያስገኘው ሥጋዊ (ፖለቲካዊ ወይም ሌላ) ጥቅም ተሰልቶ።

Anonymous said...

ቤተክርስቲያን የሀዘን ጊዜ ማወጇ ተገቢም ይበል የሚያሰኝም ነው። ወጥነት ግን ቢኖረው ደስ ይላል።በ97 ምርጫ ለሞቱት ወገኖች፤ በጂማና በተለያዩ ቦታዎች ለተሰዉት ክርስቲያኖች መች በቅጡስ ነፍስ ይማርስ ተባለ? ቤተክርስቲያን እናት ናት እናት ደግሞ አታዳላም ልጆቹዋን ሁሉ በአንድ አይን ነዉ ማየት ያለባት።መንግስት የጠላውን ጠልቶ መንግስት የደገፈውን ቢያራግቡት ዋጋ የለዉም ራስን ከመደለል ውጭ! በዚህ አደጋ ያረፉትን ነፍስ ይማር ለወዳጅ ዘመዶቻቸውም መፅፅናናቱ ይስጥልን።

Anonymous said...

why do think as a real religious leader? you blame and curse when the government orders you to do so.
but allmighty god knows what you are doing. you never ever hide from him.Did't you know howmany civel peaple were killed in 1997,and in Jimma ?why the church didn't annonce at that moment?

Girum said...

The cases in 1997 and in Jimma are different stories and already passed. The church should have denounced at that time as well but failed to do so.

But there is still time if the church wants to to do such things in the feature. Even thought we don't like them to happen again, they will come even in the feature. We need the church to act accordingly according to Holy Bible and Christian Teachings.

God Bless Ethiopia Forever

Anonymous said...

"He who is able to pray correctly, even if he is the poorest of all people, is essentially the richest. And he who does not have proper prayer, is the poorest of all, even if he sits on a royal throne."
St John Chrysostom

Prayer is the elevation of the mind and the heart to God in praise, in thanksgiving, and in petition for the spiritual and material goods we need. Our Lord Jesus Christ commanded us to enter into our inner room and there pray to God the Father in secret. This inner room means the heart, the core of our being.

The Apostle Paul says that we must always pray in our spirit. He commands prayer for all Christians without exception and asks us to pray unceasingly.

Orthodox Christians engage in both corporate and personal prayer. One’s individual prayer life is balanced with participation in the liturgical services of the Church where the whole community gathers for prayer and worship.

We are very sorry to hear the News of Ethiopian Airlines crash . May pleasant memories help to carry all the families through this difficult time. Our prayers and thoughts to the families of all. Memory be Eternal!

Anonymous said...

በ97 እና 98 የሕዝብን ንብረት በማውደም ሰላምን የነሳ ቦዘኔ በአርአያ ሥላሴ እንደመፈጠሩ በከንቱ መሞት ባይኖርበትም የቤተክርስቲያን ልጅ ነዉ ማለት ግን ፖለቲካን ከመስበክ አልፎ ቅድስት ቤተክርስቲያንን መሳደብ መሆኑን አስተውሉ ፡፡
ዓላማችሁ በስመ ክርሰትና ፖለቲካን መስበክ ከሆነ ግን ልፋታችሁ ያው እነደመሪዎቻችሁ ከንቱልፋት መሆኑን ተገንዝባችሁ አርፋችሁ ተቀመጡ፡፡
እንደ እኔ ግን አወዋጁ መልካም ነው ለሚገባው ሁሉም ይቀጥል እላለሁ፡፡
እግዚአብሔር ሆይ እውነተኛ ክርስቲያኖችን አብዛልን፡፡
አሜን
From
Ethiopia

Habesh said...

Its good to pray.
But I don't think it is a weather. There is no way of blowing on the air. I feel like it was planned. There was no thunder. No, technical problems don't blow an airplane on the air.
That is an organized attack.

Anonymous said...

The last Anony

If you are Christan, realy I feel sick to read that kind of words from you. You said 'Bozene' God knows who is bothene for our church and country.
let God return your heart to talk truth

Uk man

Anonymous said...

The last Anony

If you are Christan, realy I feel sick to read that kind of words from you. You said 'Bozene' God knows who is bothene for our church and country.
let God return your heart to talk truth

Uk man

Anonymous said...

vare good

Anonymous said...

what are those two flags and the candele? is that oromo flag or lebanon flag? if that is oromo flag, shame on you ethiopiawiyan!!
how could you compare yehager bandera and yekilel bandera?

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)