January 10, 2010

መፍትሔዬ:- የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዲያስጵራው ዓለም ለምትገኝበት ትርምስምስ

(አቤል ቀዳማዊ qedamawi@live.com)
ሰሞኑን ባቀረብኩት የቤተ ክርስቲያናችን ችግር ላይ አንዳንድ ጽሑፉን ያነበቡ ደጀ ሰላማውያን “የምናውቀውን ችግር ደግመህ ለምን ትነግረናለህ? መፍትሔው ነው የጠፋው” በማለት ስለጠየቁኝ፤መፍትሄ እንኳን ባይሆን ለመወያያ ይሆነን ዘንድ አንዳንድ ነጥቦች ለማስቀመጥ ተገድጃለሁ። በቤተ ክርስቲያናችን ላይ እኛው የፈጠርነው ይህ ሁሉ ትርምስምስ በዘለቂው ለመፍታት “ከ40 ሚሊዮን የተዋህዶ ልጆች መሀከል በደጀ ሰላም ድረ ገጽ የምንወያይ ሰዎች ብቻ ልንፈታው አንችልም” የሚሉ ደጀ ሰላማውያን ሊኖሩ ይችላሉ፤ ለእግዚአብሔር ምን ይሳነዋል በቅንነት እና ለእውነት ከተወያየን እንፈታዋለን የሚል ተስፋ አለኝ። ለእኔ የታዩኝ አንዳንድ ለችግሮቹ መፍትሄ ይሆናሉ የምላቸው ነጥቦችን ለውይይት እንዲያመቸን አቅርቢያለሁ። እንግዲህ ስህተት ካለም እያረማቹኝ በጎደለውም እየሞላችሁበት፤ የሚከተሉትን ሀሳቦች በያለንበት እንድንወያይበት ለመጠቆም ሞክሬያለሁ፦

፩.ከእረኞቻችን ምን ይጠበቃል?
እዚህ ላይ ለውይይት እንዲያመቸን “ገለልተኛ” ነን የሚሉና በቦርድ የሚመሩት በተለያየ መልኩ በግለ-ሰዎች ሥር ያሉት፣ እንዲሁም ደግሞ “በኢ/ኦ/ተ/ቤ ሥር” ነን የሚሉት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ውስጥ ያሉት ዕረኛቻችንን ብቻ ይመለከታል። “በስደተኛው ሲኖዶስ” አስተዳደር ውስጥ እንመራለን ለሚሉት ዕረኞቻችን በተመለከተ በሌላ ግዜ እመለስበታለሁ። እረኞቻን ብዬ እንደ መፍትሔ ሀሳብ ያስቀመጥኩት ከዲያቆናት እስከ ሊቃነ ጳጳሳት ድረስ ነው። እንግዲህ ስለ ቤተ ክርስቲያን ስተዳደራዊ መዋቅር አስፈላጊነት፤ መጽሐፍ ቅዱሳዊነት እና ሐዋርያዊ አመጣጥ ለዕረኛቼ መናገር “ለቀባሪ አረዱት” ሥለሚሆንብኝ ለእነሱ ትቼዋለሁ። ቤተ ክርስቲያን አንድነቷን ጠብቃ ለትውልድ እንድትተላለፍ አንድ አስተዳደራዊ መዋቅር መኖር ግድ ነው እንደምትሉኝ አልጠራጠርም። ስለዚህ በተለያየ ሁኔታ አሁን ላለንበት ትርምስምስ “በገለልተኛ” እና በግለስዎች ያሉት አጥቢያ አብያተ ክርስቲያናት ምክንያታቸው የአባ ጳውሎስ የአስተዳደር በደል መሆኑ የአደባባይ ሚስጥር ነው። ይህን የአስተዳደር በደል ፈርቶ መሸሽ ማለት ለእኔ ቤተ ክርስቲያን ስትበደል “እኔ ይመቸኝ እንጂ የሯሷ ጉዳይ” ማለት ይመስለኛል።

በእኛ ከአስተዳደሩ ሸሽቶ መውጣት አባ ጳውሎስ ምን ተጎዱ? ቤተ ክርስቲያናችንስ ምን ተጠቀመች? ይህ እንግዲህ ዕረኛቻችን በሚገባ መወያየት ያለባቸው ጉዳይ ይመስለኛል። ነፃነት ያለበት ሀገር ውስጥ ስለሆንን በመዋቅሩ ሥር እንኳን ሆንን አባ ጳውሎስን መቃወም አንችልም ወይ? እንደ ኢትዮጵያው እዚህ ሀገር ደብር አስተዳዳሪውን እንደተፈለግ ያለ ህጉ ማዘዋወር የሚችሉ ይመስሏችኋል? አይመስለኝም። ታድያ ምንድ ነው የሚያስፈራን? ነፃነት በሌለበት ሀገራችን እንኳ በቅርቡ በአርባ ምንጭ እና በአክሱም ከታማዎች ህግ በማያዘው መሰረት በተነሱት አስተዳዳሪዎች ምክንያንት የተከሰቱት የምዕመናን ተቃውሞዎች ማስታወስ ይቻላል። ስለዚህ “ሥጋችሁን እንጂ ነፍሳችሁ መግደል ለማይችሉት አትፍሩ” የሚለው አምላካዊ ትዕዛዝ የተዘነጋ ይመስለኛል። “ቦርድ ያባርረኛል” ብሎ መፍራት ቢያባርርስ፤ ዕረኞች ከተወያያችሁበት ቦርዱ አሐዱ አብ ቅዱስ አይልም እኮ። ስለዚህ ከላይ መጀመሪያ ላይ የጠቀስኳቸው ሦስቱንም አስተዳደር ሥር የሚገኙ ዕረኞቻችን ለእውነት ብለው ወደ ልባቸው መመለስ ያለባቸው ይመስለኛል። የመደራደሪያው ጊዜም አሁን መስሎ ይታየኛል። እኛው የፈጠርነው ችግር እኛው ካልፈታነው ልጆቻችን ይፈቱታል ብዬ አልጠብቅም። “የመቅደስ አገልግሎት እስከተሟላ ድረስ የቤተ ክርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር በዲያስጵራው ዓለም ለምን ያስፈልገናል”? የሚሉ ዕረኞች ብዙ ጊዜ ያጋጥሙኛል። ይህ ግን በቤተ ክርስቲያን ላይ መቀለድ ያስብላል። ድርድሩ እንዴት ይጀመር ለሚለው ለእናንተው እተወዋለሁ።
እዚህ እኛ ያለንበት ሀገር ላይ አስተዋዮቹ አባቶቻችን ያስረኩቡንን የቤተክርስቲያን የአስተዳደር መዋቅር ጠብቀን ብንሄድ ቤተ ከርስቲያናችን ምን ጠቀሜታ ታገኛለች? ቢባል፦
 የቀደሙት አባቶቻችን በሀግራችን ኢትዮጵያ ላይ የአብነት መማሪያ ትምህርት ቤቶች ገንብተው እንዳስረከቡን ሁሉ፤ እኛም እዚሁ ሀገር ላይ ለሚቀጥለው ትውልድ ይሚሆን ዘንድ የአብነት ት/ት መማሪያ ሥፍራዎችን ገንብተን ማስቀመጥ እንችል ነበረ። እዚህ ሀገር ላይ ቤተ ክርስቲያናችን የ50 ዓመት ዕድሜን አስቆጥራለች፤ በዚህ ዕድሜዋ ግን በሳምት አንድ ቀን ከሚሰጠው የቅዳሴ አገልግሎት ውጪ ለትውልዱ የሚተላለፍ ምንም የተሰራ ነገር የለንም። አንዳንድ አካባቢዎች በብድር የተለያዩ ህንፃዎች ተገዝተው ሊሆን ይችላል፤ አንድ ላይ ብንሆን ግን በ50 ዓመት ዕድሜ ከዛ ያለፈ መስራት በቻልን ነበር።
 በአንድነት ጥላ ሥር ብንሆን ሌሎች አሀት አብያተ ክርስቲያናት እንደሚያደርጉት እኛም ያላመኑት አፍሪካውያንን ወንድሞቻችን እያስተማርን የእግዚአብሔር መንግስት ለዓለም እንዲዳረስ በሚገባ መንቀሳቀስ እንችል ነበረ።
 ለዘመኑ ቴክኖሎጂ ቅርበት ላይ ስለሆንን ለሌሎች አህጉረ ስብከቶቻችን ምሳሌ መሆን እንችል ነበረ።
እረኞቻችን እነዚህን ሀሳቦች ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ራሳቸው ለውይይት ማዘጋጀት ያለባቸው ይመስለኛል።
፪. ከሰንበት ት/ት ቤት ወጣቶች ምን ይጠበቃል?
ስንዱ እመቤት የሆነችው የኢ/ኦ/ተ/ቤ የሰንበት ትምህርት ቤት አስፈላጊነት እና ዓላማው በህግ ደንግጋ አስቀምጣልናለች። ቃለ ዓዋዲው ስለ ሰንበት ት/ት ቤት ዓላማ ሲገልጽ “የኢ/ኦ/ተ/ቤ እምነትና ሥርዓት ተጠብቆ ሳይለወጥ ሳይበረዝ ከትውልድ ወደ ትውልድ እንዲተላልፍ ማድረግ” ይላል። ስለዚህ አንድ የሰንበት ት/ት ቤት አባል ይሄ ሁሉ የቤተ ክርስቲያን አደራ ተሸክሞ ይኖራል ማለት ነው። እዚህ ሀገር የምንኖር የሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ከቀደሙት አባቶቻችን የወረስነውን የቤተ ከርስቲያን አስተዳደራዊ መዋቅር መጠበቅ ከእኛ ምን ይጠበቃል? ቢባል፦
 ስለምናገለግልበት አጥቢያ አብያተ ቤተ ክርስቲያን በሚገባ ማወቅ፤ የአጥቢያ ቤተ ክርስቲያኑ መተዳደሪያ ደንብ “ምን ይላል”? ብሎ በሚገባ መፈተሽና በመተዳደሪያ ደንቡ ላይ ከህገ ቤተ ከርስቲያን እና ከቃለ ዓዋዲው ጋር የሚጋጭ ነገር ካለ እንዲስተካከል ለሚመለከተው አካል ጥያቄ ማንሳት።
 በሳምንት አንድ ቀን ከምንዘምረው የመዝሙር አገልግሎት በተጨማሪ ሌሎች ሥራዎችን ለመጀመር በአካባቢያችን ከሚገኙት አሀት አብያተ ክርስቲያናት ሰንበት ትምህርት ቤት ወጣቶች ጋር ልምድ በመቅሰም ለትውልድ የሚተላለፉ ሥራዎች ለመጀመር መዘጋጀት።
፫. ከምዕመናን ምን ይጠበቃል?
ቤተ ክርስቲያናችን ከቅዱስ ፓትርያርኩ እስከ ምዕመናን ድረስ በየደረጃው የሥራ ድርሻ ከሙሉ ሀላፊነት፤ መብት እና ግዴታ ጋር አስቀምጣለች። ሁሉም እኩል የሚዳኝበት በየደረጃው የሯሷ ህግም አላት። አለመታደል ሆኖ ግን እዚህ እኛ ያለንበት ሀገር ብቻም ሳሆን ሀገር ቤትም ጭምር ምዕመናኑ ቤተ ክርስቲያን የሰጠችን መብቶችና ግዴታዎች ብዙውን ግዜ እየተወጣን አይመስለኝም። የዲያስጶራው የቤተክርስቲያናችን ትርምስምስ በዘላቂ እንዲፈታ ከምዕመናን ምን ይጠበቃል?
 የቤተ ክርስቲያን ጉዳይ ላይ የተወሰኑ ሰዎችን ብቻ ይመለከታል የሚለው አስተሳሰብ መላቀቅ ያለብን ይመስለኛል። ክርስቶስ በደሙ የመሰረታት የቤተ ክርትስቲያናችን ጉዳይ ለሁላችንም እኩል ይመለከተናል። ሥለዚህ ስለምንገለገልበት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በሚገባ ማወቅ አለብን። መተዳደሪያ ደንቡ ምን ይላል? ቤተ ክርስቲያኑ በማን ሥም ነው ያለው? እስከ መቼ ድረስ ከቤተ ክርስቲያን ተገንጥሎ ይቆያል? የሚለው በሚገባ ማወቅ ያለብን ይመለኛል።
 በኢትዮጵያ ሀገራችን ነፃነት ስለሌለ በየ ዘመኑ የሚነሱ ፖለቲከኞች እንድፈልጉት በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ ቢጫወቱም፤ እዚህ ሀገር ግን ነፃነት ሥላለን የምንገለገልበት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የፖለቲከኞች ዓላም ማስፈፀሚይ እንዳትሆን መከላከል መቻል። የቤተ ክርስቲያኒቷን ቀኖና እና ሥርዓት እንዲተገበር የራስ ጥረት ማድረግ።

26 comments:

gorgoreyos said...

I agree you.

nafkoteyegetalij@gmail.com said...

ጥንቸል
የሰው
ጥንቸል ነህ አንተን ብሎ መካሪ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አንዳንድ ካንሰር የሆኑ የውሸት ካህናት በዙባትና እነሱንመሰል ምዕመናን አሳደጉ ችግሩ እዛ ጋር ያበቃል ሁሉም ሰው ከሊቅ እስከ ደቂቅ ወደ ህሊናው ሲመለስ ያን ቀን ለቤተ ክርስቲያን ሰላም ይሆናል እንደኔ እንደኔ እውነተኞ ከፍሬያቸው ያስታውቃሉ ስለዚህ እነሱን ይዤ እሄዳለሁ በተረፈ

በማያገባህ ወስጥ ገብተህ አታንቦራጭቅ
እራስህን መርምረ

ይቆየን
ድሮም የማህበረ ስብስብ ከማወናበድ በቀር ቁም ነገር የለውም የለመዳችሁት ላይ ደንሱ

ጥንቸሎች

Anonymous said...

For ewnet

endante yalute nachewe betekirstianen lematefate yemchekulute....eske leande kenem beyone mindeken positive neger endyaseb adergewe.

Anonymous said...

Do not think for a second that as long as EPRDF and Aba Paulos are in power unity of our country and our church is possible.They and their policies are the causes of all the messes,the rest are results.So the solution is not what you wish,but to unite against these curses of our country and our church in every way possible,in prayer and other ways.
The churches in the daispora are Tewahedo churches,and they are not as you try to describe them outside of the church! The services given in every respect are acording to tewahedo's dogma and canon.But no name mentioning of Aba Paulos,no appointments of priests and deacons by him,no support to eprdf.If these things were there the churches are 'under the synod' according to Abel Kedamawi.You are so funny Abel.Are you telling us to cooperate with those people who are engaged in destroying our church and our country ?
Since Aba Paulos come to power:
1.For the first time in the history of Ethiopia the number of Muslims plus none orthodox has become bigger than the number of tewahedo followers.
1.Since the invesion of Gragn Tewahedo believers were slaughtered in such big numbers and tewahedo churches burnt at the hands of extremists
3.Tewahedo believers were executed by epdrf forces in several towns and places related to church matters
4.So many church fathers were persecuted, displaced and fired from their positions to fill them with relatives and servants of the group in power in the palace.
on and on .............
He did some good things too.But he is there to do ONLY good things;thus he does not get credits for that.
Therefore it would be better if you write how we can get rid of the causes of our disunity instead of wasting time on the impossible and untrue,unjust accussations of those who are rejecting the evil.

ዘፍሬምናጦስ said...

ኤልሻዳይን ይዘን ለምን ሁሉንም ነገር የማትቻል እናደርገዋለን? እንደኔ ግን አቤል ያነሳውን ሀሳብ አንስቶ መወያየት መልካም ነው እላለሁ:: በስድብ ግን መንንም አናስተምርም እናበሳጭና የበለጠ እናተራምስ እንደሆነ እንጂ::
የእናንተው መልካም ዜና መስማት ከሚናፍቀው ደካማ ወንድማችሁ
ከኢትዮጵያ

Orthodox Unit said...

አቤል ቀዳማዊ ያነሳኸው ነጥብ ጥሩ ነው። ሁልጊዜም ችግሮችን በመወያየትና በመነጋገር መፍታት ይቻላል። ባይቻል እንኳን የሐሳቡ ልዩነት ምን ላይ እንሆነ አውቆ ለመፍታት የሚያስችል ሐሳብ ማምጣት ይቻላል።

አቶ እውነት ግን ምን አይነት ሰይጣን ቢገባብህ ነው ሰው ማስታረቂያ ነገር ሲያቀርብ እንተ ወደ ስድብ የምትቀይረው? ሰው ሲወያይ ነው ወደ ህሌናው ሊመለስ የሳተው ሊያስብና ሊጸጸት የሚችል። እግዚአብሔር በሰዎች አድሮ መክሮ ነው እኮ ወደ እውነት የሚመልስ እንጂ ዝም ብሎ የሚሆን ነገር የለም።

ለሰላም ለፍቅር ለመነጋገር ለመወያየት ልባችን ሁልጊዜም ቅንና ክፍት መሆን ይጠበቅበታል። ማነኛውም አይነት ችግር በመወያየት ሊቀል ይችላል ያው አንዱ ሌላ አላማ ከሌለው። እንኳን እኛ እርስ በእርሳችን ይቅርና ዛሬ በምስራቅና በኦሬንታል ኦርቶዶክሶች መካከል እንኳን ቤተ ክርስቲያንን ወደ አንድ ለማምጣት ውይይቶች እየተካሄዱ ይገኛሉ። ስለቤተ ክርስቲያን ስናስብ ሰፋ አድርገን የነገንም ጭምር ማሰብ አለብን። ዝም ብሎ ለአንድ አጥቢያ ለአንድ ቄስ ወይም ለአንድ ማህበር በማሰብ የቤተ ክርስቲያንን ራዕይ ሊሆን የሚችለውንና መስራት የሚገባንን መልካም ስራ ሳንሰራ እንዳንቀር አጥብቀን ልናስብበት ይገባል ባይ ነኝ።

ሰላም ሁኑ፡ ኦርቶዶክስ ዮናት ነኝ።

Anonymous said...

የተወደድክ አቤል ቀዳማዊ የቤተ ክርሰቲያናችንን ችግር እንፍታ በማለት አስተያየት በመሰጠተህ አመሰግንሃለሁ፡፡
በተጨማሪም በፖለቲካ ተቃኝቶ ሰላም የማይታሰብ መሆኑን ደጀ ሰላማውን እንድትገነዘቡልኝ አወዳለሁ፡፡ ሁለቱንም በቅርብ ሰለማውቃቸው ነው፡፡
በጣም ያሳዘነኝ ነጥብ ቢኖር ግን የአክሱምን ባላውቅም የጳጳስ ብሎም የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ እኔን አያዘኝም በማለት ቤተ ከክርስቲየያንን በዓለም ፍርድቤት የሞገቱትን ሰው፡፡ አካሄድዎ ከስርዓት ውጭ ነው ያሉዋቸውን ምሰኪን ካህናትንና ምዕመናንን በዱርየዎች ያሰደበደቡን የዓመፅ አባትን ያለ ህግ ተባረሩ ሰትለን አንድም ሰዎች ተሳስተው የተዛባ መረጃ ሰጥተውሃል ወይም እንድጠረጥርህ እገደዳለሁ፡ በማፈንገጥስ አንድነት የት ነው የታየው?
Please Abel
ከየት መጡ?
ከመጡስ በኃላ ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ውጭ ምን ሰሩ?
ከተባረሩ በኃላስ ማን ገር ሂደው ምንን ጠየቁ ማንስ የጠየቁትን ከለከላቸው?
ወ.ዘ.ተ የመሳሰሉትን ከተለያየ አቅጣጫ የያሉት ስዎችን(የቅርብ አዋቂዎችን)በመጠየቅ
ወንድሜ አቤል ስለ ሰውየው በቂ መረጃ አግኝተህ ደጀ ሰላማውንን ይቅርታ እንደምትጠይቀን ተሰፋ አደርጋለሁ

of EOTC
From
Arbamich
Ethiopia

Unknown said...

ለምን እንደ አባቶቻችን አንሆንም ለምን ለኃይማኖታችን አንሞትም ጌታ ለእኛ ከሞተልን እኛስ ለምን ለኃማኖታችን አንሞትም አባቶቻችን ኦርቶዶክስ ይሻር ካቶሊክ ይሁን ሲባል ለሃይማኖታችን እንሙት አሉ እንጂ ሌላ ቤተክርስቲያን እንክፈት አላሉም በሃማኖት ምክንያት ከሀገር አልወጡም እና ከአሁኖቹ አባቶች ምን እንጠብቃለን ከእኛስ ከምዕመናን ምን ይጠበቃል እባኳችሁ የምንወያየው ጉዳይ ስለ አንዲት ሃማኖትና ቤተ ክርስቲያን ነው መሰዳደብ ይቅርና ሁላችንም የሚጠበቅብንን የተሰጠንን መክሊት እናትርፍ የሌላውን መክሊት እየተመለከትን ከምንጠፋ ከሁሉም በላይ ለሰው መጥፊያ እንዳንሆን እንጸልይ እኛ በስጋ አይናችን ማየት ከተሳነን ሁሉ እርሱ ፈጣሪያችን እግዚአብሔር ከመጠፋፋት ይጠብቀን የተከፋፈለ መንግስት ይጠፋል እንደተባለው እኛም ካልነቃን ለልጆቻችን ምንም የምናወርሳቸው ሃይማኖት አይኖረንም እኛም እራሳችን ግራ ገብቶናልና እግዚአብሔር በይቅርታው ይጎብኘን አሜን

nafkoteyegetalij@gmail.com said...

በመጀመሪያ ለኔ ጥንቸል ማለት ስድብ አይደለም!
ጥንቸል ማላት በጣም ሃይለኛ የማትያዝ ሯጭ ማለት ነው ፡)
ለማንኛውም በጽሁፌ ያስቀየምኩችሁ በሙሉ በጣም ይቅርታ ብዙ ነገር ወስጤ ስላለና አንዳን ሰዎች ማን ነበሩ? እንዲሁም የወደፊት አላማቸው ምን እንደሆነ ስለማውቅ ነገሮችን መያዝ አቅቶኝ ነው
ግን ስለእውነተኛው እውነት የምንነጋገር ከሆነ በፍቅርና በማስተዋል ለመጻፍ እሞክራለሁ በነገራችን ላይ የማንንም ህሊና ለማድማት ወይም ሁን ብዬ ንግግራችሁን ለማበላሸት የምፈልግ ሰው ወይም ግለሰብ አይደለሁም ነገሩ እንዲህ ነው

እወነተኛዋን እውንተ ከፈለግን ወገንተኝነት ዘረኝነት መከፋፈል መሰዳደብ መጠላላት እኔ ከሌላው የበለጠ አውቃለሁ ማለት በሰው ላይ መፍረድ ይቅር አለመባባል እልኸኛነት የስለጣን ጥምና የክርስቶስን አምላክነት መዘንጋት መቆም አለበት ሁላችንም እነዚህን ካደረግን እወነተኛዋን እወነት ካለችበት በህብረት ማውጣት እንችላለን። ማንም ማህበር ማንም ግሩፕ ማንም ዘማሪ ማንም ዲያቆን ማንም መምረህር ማነም ቄስ ማንም መነኩሴ ማንም ቆሞስ ማነም ኤጲስ ቆጶስ ማንም ሊቀ ጳጳስ ማንም ፓትርያሪክ እንዲያዝን እንዲለይ አንፈልግ ሁሉንም አቻችለን አንተ ትብስ እኔ ተባብለን ለክርስትናችን ብንቆም ይበጃል አዎ እናውቃለን ብዙ ጥፋት ጠፋ ብዙ ብዙ ግን ስለጥፋቱ በመለያየት በመሰዳደብ በመወቃቀስ መፍትሄ አይገኝም! ይቅር በመባባል እነጂ
ኢየሱስ ክርስቶስ ለቤተ ክርስቲያን ሰላም ይስጥ እኔስ ወስጤ ደክሟል አምላክ ሃይማኖታቸንን በላም ይጎብኛት አባቶቻችንን እና ምዕመናኖቻችንን ሁሉ በፍቅር አንድ ያድርግልን ኢትዮጵያ አገራችንን ይባርክልን

ይቆየን

ለይቅርታ አንሸነፍ ዝቅ ማለት ማሸነፍ ነውና!

Anonymous said...

Thank you for posting an important/ obvious and urgent issue. We shall not delay or wait for someone else to speak. Some forget that Ethiopia Orthodox Sinodose can only be under Ethiopia's Orthodox church in Ethiopia. How can Ethiopian Orthodox sinodose be in United States...then it will be United States Orthodox Sinodose.. I am sorry to say this but it just doesnt make sense even using simple common sense. For those that are continously bitter about the Patriarch Abune Paulos..let me ask..who isn't??? we all are and it is very obvious that Ethiopia Orthodox Tewahedo is growing downhill since not much is being accomplished by Our Patriarch. But if we continue to separate because of such issue, then Our church will even more progress downhill since we can not get anything done by our disunity.
So I beg for the sake of our fore fathers and Unity, lets forgive bitterness..and do not associate that with being naive. We are all aware of the problem of our Sinodose in Ethiopia and corruption of the government in the church. But we need to overcome these obstacles thru Unity. May God bless Orthodox Tewahedo and Ethiopia!

Unknown said...

i agree with u. Egzyabere yebarke/shi "How can Ethiopian Orthodox sinodose be in United States...then it will be United States Orthodox Sinodose.."

Anonymous said...

How partial some of you are!
Aba Paulos left the church and immigrated to USA during dergue.Aba Merquorios did the same.
If we criticize we should be impartial.As christians we should always speak the truth and fear GOD.
Yes we need to forgive one another,but we have to abandon the wrong actions and deeds first.Forgiveness does not mean accepting someone's wrong and allow him to continue his bad deeds.
Question to Abel:What do you mean when you say we need to unite? Is that saying those churches that do not mention Aba Paulos's name to mention? or Is that you mean let every church register under eotc and Aba Paulos evict all of us like he did to our holy father Abune Yishaq who can be called the real Apostle of his time.
It is aba yishaq and aba gorgorios ii who are real apostles of eotc in the last 40 years.
Let their prayer save our church,our country and us all.

amanawi said...

ጎበዝ እንዴት ነው ነገሩ የተነሳው ርዕሰ ጉዳይ ወቅታዊና አስፈላጊ ቢሆንም ይህ ጉዳይ ለውይይት ቅርቶ ለወሬ እንኩዋን እንዳይነሳ የሚሹ ጥቂት ጥቅመኞች መኖራቸው የተዘነጋችሁ መስሎኛል በዛ ላይ አጽራረ ቤተ ክርስቲያን ቤተ ከርስቲያናችን እዚህ አይነቱ ምስቅልቅል ውስጥ በመግባትዋ ሰርግና ምላሽ ላይ መሆናቸውንም ልብ ማለት ተገቢ ነው
መልከ ጥፉን በስም ይደግፉ እንዲሉ አበው የሀሰቱ ጎተራ በእውነት ስም ተሸፍኖ ስለመጣ ኦርቶዶክሳዊ እንዳይመስላችሁ ጌታ የበግ ለምድ ለብሰው ከሚመጡባችሁ ነገር ግን ነጣቂ ከሆኑ ተኩላዎች ተጠበቁ እንዳለው ተኩላ በበግ ለምድ ተደብቆ ወደ ኦርተዶክሳውያን ብሎግ በረት መግባቱን አላወቃችሁም ለማለት ሳይሆን ለማስገንዘብ ያህል ነው
አቤል ቀዳማዊ በእርግጥ ስሙን እንደያዝክለት እንደየዋሁ አቤል በቅን ህሊና ተነሳስተህ ያቀረብከው የመወያያ ርዕስ እንደሆነ እገምታለሁ ከላይ እንደገለጥኩት ላንዳንዶች አይነኬ ነገርና መፍትሄውም እንደሰማይ የራቀ ተደርጎ ቢታሰብም እኔ ግን መነሳትና መወያየት እንዳለብን አምናለሁ የብዙ ማይልስ መንገድ በአንድ እርምጃ ይጀመራል እንደሚባለው
በሰሜን አሜሪካ ሆነ በአጠቃላይ በዳያስጶራው ቤተ ክርስቲያኒቱ አሁን ለገባችበት ቀውስ ተጤቂው ማን ነው?ለሚለው የአንበሳውን ድርሻ የሚወስድ ግለሰብ በእኔ በኩል የለም አሁን ኑሩዋቸውን በሰሜን አሜሪካ ያደረጉት የቀድሞው ፓትርያርክም አሁን በመንበሩ ላይ ተሰይመው ያሉት ፓትርያርክም ሁለቱም የበኩላቸውን አስተዋጽኦ አድርገዋል እንጂ ዋነኛ ተጠያቂ አይደሉም በውጭ ያለችው ቤተ ክርስቲያን አሁን ላለችበት መመሰቃቀል ዋነኛው መንስኤ በግብጻውያን አመራር ለዘመናት ተይዞ የነበረው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አስተዳደር በባለሀገሮቹ መንፈሳዊ መሪዎች ከተያዘ አጭር ግዜ በመሆኑ በልምድ ማነስ የተፈጠረ ክፍተትና ከዚያውም ጋር ተያይዞ በሀገሪቱ የተከሰተው ኮምኒስታዊ ስርዓት ያስከተለው መለያያት ያመጣው ነው በአጭር አነጋገር ለመጠቅለል የቤተ ክርስቲያኒቱ አስተዳደር ቀድሞ የቤተ ክርስቲያኒቱን አስተዳደራዊ መዋቅር ባለመዘርጋቱ ከቤተ ክርስቲያኒቱ መለየት የማይሻው ምእመን የፖለተካ አላማ ኖሩዋቸው ይክፈቱት የቤተክርስቲያን ፍቅር አስገድዱዋቸው ለግዜው በእርጋጠኝነት ልናውቀው ባልቻልነው ምክንያት በተከፈቱለት አብያተ ክርስቲያናት በመሰባሰብ አምልኮቱን መፈጸም ጀመረ
የኮምኒስትን አስተምህሮ ከመጽሀፍ ቅዱስ አስተምህሮ ጋር እያጣቀሱ የሚያስተምሩ ንብርብሬ ካህናት በምድረ ኢትዮጵያ በመከሰታቸውና የነበረው ርእዮተ ዓለምም ከካፒታሊስቱ ስርዓት ጋር ምንም ዓይነት ንክኪ እንዳይኖር የሚሻ በመሆኑ ቤተ ክህነትም እንደአሁኑ ሁሉ የስርዓቱ አቀንቃኝ ስለነበረች በዲያስፖራው በተለይ የካፒታሊስቱ ጎራ ተብለው በተፈረጁት ሀገራት ያለችው ቤተ ክርስቲያን ከእናት ቤተ ክርስቲያን ፍጹም እየራቀች መጣች ምንም እንኩዋን መዋቅርዋን ለመዘርጋት ሊቃነ ጳጳሳትን ቀድማ የመደበች ቢሆንም ቀደም ብዬ በጠቀስኩት የልምድ ማነስና በተፈጠረው የፖለቲካ ቀውስ ጳጳሳቱ በግል የሚጠቀስ ስራ ከመስራት ውጪ የቤተ ክርስቲያኒቱን መዋቅር የሚያጠናክር ስራ ለመስራት የሚያስችል ሁኔታ አልነበረም
አያ ደርግ ተገርስሰው አያ ኢሀድግ ሲተኩ በዲያስፖራው ያለችው ቤተ ክርስቲያን ሁኔታ ከድጡ ወደ ማጡ ሆነ ፓትርያርክ አባ መርቆርዮስ የኢሀድግን ዛቻ መሰረት አድርገው የሀገሬ የወንዜ ሰዎች የሚሉዋቸው ከጎናቸው ያሉ ጳጳሳት በመከሩዋቸው ምክር መሰረት በህመም ምክንያት አድርገው ፕትርክናቸውን በፈቃዳቸው አሳልፈው ሰጡ ተባለና ቆይተው በኬንያ አድርገው አሜሪካ ገቡና ህጋዊ የሚል ቅጥል ተቀጥሎላቸው መንበራቸውን አሜሪካ ማድረጋቸውን ይፋ ሲያደርጉ በአሜሪካ ያላቸው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ፖለቲካ አቡዋረው ቦኖ ብዙዎችን ለያየ ለዚህኛው የአንበሳውን ድርሻ የሚይዙት ታሪክ በክፋት የሚያነሳቸው የዚህ ዋነኛው አቀንቃኝ አባ ሀብተ ማርያም ወርቅነህ መሆናቸው በምድረ አሜሪካ ከአበሻው አልፎ ነጩም እስፓኒሹም አፍሪካ አሜሪካዊውም ሌላውም ያወቀው ይመስለኛል ይህችን ቤተ ክርስቲያን ሳልከፍል ብቀር እንትፍ ብለው ምራቃቸውን ተፍተው ከሀገር እንደውጡ የሚያውቁዋቸው ይናገሩላቸዋል እናም ያሰቡትን ከግብ ካላደረሱ እረፍት የላቸውም የተባሉት አባ ሀብቴ አቡነ መርቆርዮስን ሌት ተቀን ወጥረው ጳጳሳትን በመሾማአቸው የቤተ ክርስቲያኒቱን አንድነት እመቀመቃት ውስጥ ከተቱት
በዚህ ጉዳይ ውስጥ የአቡነ ጳውሎስም ድርሻ ከአባ ሀብተ ማርያም የተናነሰ አይደለም አቡነ መርቆርዮስ ወደ ሀገር እንዳይመለሱም በቅድስት ሀገር ኢሩሳሌምም በለው ገዳማችንም በጾምና በጸሎት ተወስነው እንዲቀመጡ ቀረባን ባጠቃላይ እርቅ የተባለውን ሁሉ እየገፉ የውጮቹን ጳጳሳት ለዚህ ያበቁዋቸው እርሳቸው ናቸው

እንግዲህ እስከአሁን ባጭር የገለጥኩት በዲያስፖራው ያለችው ቤተ ክርስቲያን አሁን ላለችበት ቀውስ ባለድሻዎች እነማን እንደሆኑ ለማመልከት ሲሆን ዋነኛዎቹ በከፈቱት ቀዳዳ ሌሎች በምእመንነት ያሉት ገብተው ለሚፈልጉት ቦለቲካ ማቀንቀኛ አድርገው ተጠቅመውባታል አሁንም እየተጠቀሙበት ነው

Anonymous said...

Do not mix the cause with the effect,Abel.
'The churches in daispora become harbours to politiacians,'you said.What about the church in Ethiopia? Is that only the opposition 'political' for you? Those who support the ruling group are also political!Do not try to deceive GOD!He knows you in and out.God knows you are working for the group in power in Addis.You can not escape from GOD's judgement.

Unknown said...

To the last Anonymou
Dear my brother in Christ please don't jugded somebody by just ego. Think twice before you speak out.I guss you are a new to this blog that's why you described me wrongly. Anyway i don't care what you said about me. i want to tell you the truth is i won't have any back interes from anybody. i am not supporter of Aba paulos or other groups you described.If you have time please read some of my articles about abs Paulos on this blog. My idea is we have to discuss about problem we faced in our church especially here in USA. All the problems are created by our not the next generations'. So, what i said and what i want to say now is we have to solve the problem we created. The next generation won;t be soleve the problem we created on our church. I hope so many of DS follower understand what i want to said. i we continue to speak out loudly abou the truth. i don't fear nobody for the truth. you can say as you like about myself but i couldn't stop to write what i abou the facts we have got from our forhfathers. We have a responsibility for the next generation and for our real Apostolic Tewahido Church. We will fight you those politician by the words of our God not only here in USA but also at back home.
Abel Qedamawi

tewahido said...

ኧረ በየንታ አምላክ የዳኛ ያለህ በምዕራብ ጎጃም ልዩ ስሙ አንጎት ሚክኤል የጨረቃ ከተማ ከ30 ዓመታትበላይ ጉባዔ ተክለው በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ የቅኔ ተማሪዎችን ቅኔ አስተምረው መርቀዋል
ታዲያ ምን ይሆናል ለእኝህ ታላቅ መምህር ውለታቸው እሥር መግባትሆነ ከመንግሥትም ሆነ ከቤተ ክህነት ምንም ዓይነት ክፍያ ስይኖራቸው በነፃ አገራቸውን ያገለገሉ ሊቅ ዓይነ ስውር መምህር
ናቸው ዕድሜአቸው 73 ሲሆን እኒህ ታላቅ ዓይነ ስውር ሊቅ
ሴት ደፈርክ ተብለው የሃኪምም ሆነ የሰው ማስርረጃ
ስይቀርብባቸው ባቃቤ ህጉ ተፅዕኖ 8ዓመት ተፈርዶባቸው መሪጌታ
አዕምሮ አመነ በፍኖተ ሰላም ማረሚያ ቤት ሆነው ሌት ከቀን በጠፋው ዓይናቸው እያለቀሱ ሀገራችንን እየመረቋት ነው እባካችሁ
ስልጣንና ልብ ያላቸሁ አስቧቸው አስቧውቸው ብርቱካንን ስታስታውሱ መሪጌታ አዕምሮ አመነን አትርሱ

Anonymous said...

You did not answer my question,Abel.What do you mean by lets bring unity?
Looking forward to hearing from you.

Berhanu said...

እንደምን ከረማችሁ እህቶችና ወንድሞች፡

የብዙዎቻችሁ ተቆርቋሪነት የተሞላበት አስተሳሰብና መፍትሄ ፈላጊነት በጣም የሚያስደስት ነው። በእውነት ለመናገር አገራችንም ሆነች ቤተክርስቲያናችን ብዙ ከፍተኛ እውቀት ያላቸውን ሰዎች አፍርታለች፡ ይህም ትልቅ ጸጋ ስለሆነ፡ ቸሩ እግዚአብሔር ምስጋና ይድረሰው።

በሁሉም አቅጣጫ ለተወጠሩብን ችግሮችና ፈተናዎች መፍትሄ ለማግኘት፡ እንደ እኔ ከሆነ፡ በጣም ቀላል ነው፡ ማለትም ቀላል የሆኑትን ወይም ኤሌሜንታሪ የሆኑትን ቅድመ ሁኔታዎች ለማሟላት ከቻልን መፍትሄውን ቶሎ የማናገኝበት ምንም ምክኒያት አይኖርም።

የመጀመሪያው ቅድመ ሁኔታ፡ እያንዳንዳችን እራሳችንን በንጹህ ልብ፡ በግልጽ መንፈስ መርምረን ምን እንዳለን፡ ምን እንደሚጎለን፡ ምን ዓይነት ሁኔታ ላይ እንደምንገኝ፡ ምን እንዳደረግን፡ ምን እያደረግን እንደሆነ፡ ባጠቃላይ ማንነታችንን በሚገባ ተገነዘብን ከመረመርን በኍላ ሁሉም ግልጥ ብሎ ስለሚታየን በቅዱስ መንፈስ እየተመራን ፈተናዎቹን ሁሉ ለማለፍ እንበቃለን።

ብዙ ጊዜ ቀላልና ትንሽ ነገሮች ሆነው የሚታዩን ነገሮች ናቸው ከፍተኛ የሆነውን አቀበት ሊያስወጡን የሚችሉት።

እስኪ፡ ከእኔ ጀምሮ፡ ሁላችንንም እንታዘብ፡ ለልደት በዓል የእንኳን አደረሳችሁ የእግዚአብሔር ሰላምታ ለመለዋወጥ ፈቀደኞች ሆነን ከምንገኝ፡ ዓለማዊ በሆኑት የፖለቲካ ሽኩቻዎች ገብተን መሳተፉን እንመርጣለን፡ ከመንፈስ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ጋር ሃርሞኒ በተሞላበት መንገድ በየጊዜው ከመነጋገር፡ የጠላቶቻችን የንትርክ መድረክ ላይ በመውጣት መንፈሳችንን እናደክማለን። ታዲያ ይህ ሁሉ ከቀን ወደ ቀን ሲጠረቃቀም፡ ወደላይ ይሄድና መሪዎቻችንን እንዲደነባበሩ አስተዋጽዖዎን እናበረክታለን።

የዚህች ጽሁፌ ዋና መልዕክት፡ እራሳችንን እንንከባከብ፡ በሁሉም መስክ ጤናማ የሆነ ኑሮ ለመምራት እንሞክር፡ ቀጥተኛውን መንገድ ሁልጊዜ እንምረጥ" የሚለው ነው።

ቸሩ እግዚአብሔር ከኛ ጋር ይሁን!

Anonymous said...

Is there any possible way that our fathers,aba Paulos,aba Merkorios,aba Gerima,aba Melketsedek,aba zena,aba Abraham,aba kewustos,aba Elyas meet together in the same room and forgive eachother?
I will do all my part to facilitate the meeting.I hope as matured,holy fathers they will not say NO to meet and forgive eachother so that GOD forgive them and their country and us all.What do you think? If they say no, we all will never be forgiven!

nafkoteyegetalij@gmail.com said...

የመጨረሻው Anonymous እግዚአብሔር ይባርክ አዎ አባቶቻችን በሰላም ለይቅርታ እንዲነሱና ይቅር እንዲባባሉ ነው እኛ መውጣት መውረድ ያለብን ደሞም እውነተኞቹ የተዋህዶ ልጆች ህልማቸው ይሔው ነው ይሄም ደሞ እውን ይሆናል ደስ ያማየላችሁ ሁሉ እፈሩ የእግዚአብሔር ሃይል ይበልጣልና አላማችን ከግብ ይደርሳል ውድ ወንድሜ ሆይ እኔ በስደት ያሉት አባቶች በሙሉ ሙሉ በሙሉ ለሰላም ድርድር ፍቃደኛ መሆናቸውን አረጋግጣለሁ ዋናው በኢትዮጵያ ባሉት አባቶች በኩል የሚደረገው የሰላም ፍላጎት ይወስነዋል ስለዚህ እውነተኞች ሁሉ ወደ አባቶቻችን እግር ወድቀን አልቅሰን ይታረቁ ዘንድ የበኩላችንን ድርሻ እንወጣ ከዚህ ውጪ አጉል ተቆርቁሪ እየመሰሉ በመሃበር ስም ወይም በመንግስትም ስም የተቀደሱ የተመረጡ አባቶቻችንን ገበና ሜዳ ለሜዳ መዝራት የካም ዘርነት ስለሆነ የካም ዘሮች ዘራችሁን ለዩ እኛ ግን ምንም ሆነ ምንም የያፌትና የሴም ዘሮች ለመሆን እራሳችንን ዝቅ እናደርጋለን ምንም እንካን የአባቶቻችን ጥፋት የሚያሳዝንና የሚያሳፍር ቢሆንም ስለምንወዳቸውና ስለምናከብራቸው ነገሩን ለአምላካችን ከማመልከት ውጪ ከቶ ሾተል አንመዝም

እግዚአብሔር በሃገር ወስጥም በስደትም ያሉትን አባቶቻችንን አንድ አድርጎ በሚያሳዝን መንገድ የተከፈለችውን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አንድ ያድርግልን

ይቆየን

Orthodox Unit said...

I agree with you Last Anonymous and Ewnet. We should work for that. We should work for real benefit of the church and Glory of God. Our fathers should learn from Russian Church. The Russian Church came to one after long period of splitting in their church.

This is the best solution for the church but I don't think Aba Paulos will be willing to do this.

Little John said...

Plese visit kidistselassie.org/files/mkrelated.pdf
you will see one of the ways to solve our church's problems especially, coused by people who don't care about the church but for their benefit only and menafikan.Bravo kidist selassie for showing your clear stand. I hope others will follow your role model.
selam...

Anonymous said...

Peace possible if and only if the bishops come together.
I agree and I support with all my heart, soul,thought.
God bless

Anonymous said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ
አሐዱ አምላክ አሜን፡፡

ዘመነ ዲዮቅሊጥያኖስ ዛሬ በኢትዮጵያ!

ለማንበብ

http://www.dskmariam.org/Whatnew/Meglecha%2007-07-2009.pdf

ከላይ ያለውን መጠቆምያ/ሊንክ/ ይጠቀሙ።

mebrud said...

አቤል በቅን ልቡና ተነሳስተህ ላቀረብከው ሀሳብ እግዚአብሔር ይስጥህ። ልንደግፈው የሚገባና የየበኩላችንን ድርሻ ልናበረክት ይገባል።ሲጀመር ጀምሮ ችግሩ የሚያመን ከሆነ መፍትሔው አይቸግርም ።አሁን የድፍረት ሓጢአት እየገዛን እንዳለ ስንከስ እንጂ በደለኛ ነኝ ስንል ባለመታየታችን ምክንያት የተረዳ ነው።አሁን እየታየኝ ያለው
1- ውስጣችን በቅናት አለመቃጠል።የዛሬው ቀላል ልዩነት ነገ ሊያመጣ የሚችለው የከፋ ቀውስ ከወዲሁ ያለማየት።
2- ለችግሩ መፍትሔ ከማቅረብ ይልቅ በችግሮች ዙሪያ መደራደር፡፡ችግሩን ማወሳሰብ
3- መፍትሔም እንዳለው ያለማመን።
4-የመናፍቃኑ፡የፖለቲከኛው፡የምንደኛው መፍትሔ እንዳይኖረው መትጋት የምዕመናችን ይህን ተንኮል ያለመረዳት።
አማናዊ የችግር ትንታኔህን ወድጄልሃለሁ መፍትሔውንም ወዲህ በል።
ለሚያምን ሁሉ ይቻል የለ እንመን ብቻ መፍትሔ አለው።እስቲ ነገራችን በትህትና ይሁንና ከዚያ መፍትሔውን ለባለቤቱ እንተወው።መሻት ብቻ ነው የሚፈለግብን፡
'እውነት' ሆይ ውሸትህን ይዘህ ጣልቃ ባትገባ ምናለ።አዛኘ ቅቤ አንጓች ሁንክብኝ።

ewnet said...

"አቶ" MEBURED ስራ ፈት መሰልከኝ

እስቲ ስለራስህ ተጨነቅ የኔ ቅቤ አንጋችነት ለኔ ነው አንተን አይመለከትህም

ማህበር ስል ምንው ነካ አረኩህ እንዴ ልክ ነገር ያዘለውን ልብህነ ሸንቆር አረኩት መሰለኝ አሁንም አይገባህም እነጂ እንዲገባህ ያህል በሃገር ወስጥም በስደትም ያሉት አባቶች በመንፈስ ቅዱስ ሃይል በፍቅር አንድ ሆነው እነደሚስማሙ አልጠራጠርም ድሮም ቢሆን ዋናው ነቀርሳ መሃል ላይ ሆኖ ነገር ሲያምታታ የነበረው ማህበር እራሱን ያውቃል ሰለዚህ ሳይጠሩህ አቤት አትበል ደሞም የጌታ መንፈስ በተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ የኖረው ማህበር ነኝ በዩ ከመጣ በሃላ ሳይሆን ገና ከጥንት ነው ወደፊትም ይኖራል ግን በማህበሩ ውስጥ እንዳንተ አይነት ጠባብ ሰዎች ካሉ አሁንም ቢሆን ባሉበት ይኑሩ እኛ የምንቀበለው ለይቅርታና ለሰላም ቅን ልቦና ያላቸውን ለጥቅማቸው ያልቆሙትን እውነተኛ የተዋሀዶ ልጆች ነወ አንተን አይመለከትህም መናፍቅ/አስመሳይ/ከሃዲ።
ይትባረክ እግዚአብሔር አምላክ አበዊነ
እግዚአብሔር ኢትዮጵያንና ህዝቧን ይባረክ

አሜን

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)