December 29, 2010

የአባቶች ዕርቀ ሰላም ንግግር በጥር ሊጀመር ይችላል


 • በንግግሩ ቅድመ ሁኔታዎች ስምምነት ላይ ከተደረሰ በሁለቱም ወገኖች የተላለፈው ቃለ ውግዘት ይነሣል
 • የዕርቀ ሰላም ንግግሩን የሚያስተናብሩ ሽማግሌዎች ተመርጠዋል
(ደጀ ሰላም፤ ዲሴምበር 29/2010 ታኅሣሥ 20/2003 .)በምዕራቡ ዓለም በስደት ከሚገኙት አባቶች ጋራ የሚደረገው የዕርቀ ሰላም ንግግር በመጪው ጥር ወር 2003 ዓ.ም አንድ የመገናኛ መድረክ በማመቻቸት እንደሚጀመር የቅዱስ ሲኖዶስ ምንጮች አመለከቱ፤ ቅዱስ ሲኖዶሱ ታኅሣሥ 13 ቀን 2003 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባ ‹‹በባሕር ማዶ በሚገኙት አባቶችም ዘንድ ተቀባይነት ይኖራቸዋል፤ የዕርቀ ሰላም ንግግሩን በገለልተኝነት ያስተናብራሉ›› ብሎ ያመነባቸውን ሦስት ሽማግሌዎችንም መርጧል፡፡

December 24, 2010

በአባቶች ዕርቀ ሰላም ጉዳይ የተነጋገረው የቅዱስ ሲኖዶስ አስቸኳይ ስብሰባ ተጠናቀቀ

 • በስደት በሚገኙት አባቶች የተሾሙትን ጳጳሳት ለመቀበል ስምምነት ላይ ተደርሷል
 • ቅዱስ ሲኖዶስን በመወከል የሚነጋገሩት የሰላም ልኡካን ተመርጠዋል
(ደጀ ሰላም፤ ዲሴምበር 23/2010 ኅሣሥ 14/2003 .) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በስደት ከሚገኙት አባቶች ጋራ የተጀመረውን የዕርቀ ሰላም ንግግር እና ድርድር ጉዳይ ለማስቀጠል በቀረበው ምክረ ሐሳብ (መርሐ ድርጊት) ላይ በመነጋገር ውሳኔዎችን አሳለፈ፡፡ ቅዱስ ሲኖዶስ ትናንት በመንበረ ፓትርያርኩ ባካሄደው የአንድ ቀን አስቸኳይ ስብሰባ በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በተመረጡት እና ሰባት ብፁዓን አባቶችን ባቀፈው ኮሚቴ በቀረበለት ምክረ ሐሳብ ላይ ጠንካራ ውይይት በማካሄድ አጽድቆታል፡፡ በኮሚቴው ከቀረቡት የምክረ ሐሳቡ ክፍሎች መካከል በምዕራቡ ዓለም በስደት በሚገኙት አባቶች የተሾሙትን 13 ጳጳሳት ስለመቀበል እና ቅዱስ ሲኖዶስን በመወከል በዕርቀ ሰላሙ ላይ ስለሚነጋገሩት ተደራዳሪ ልኡካን የተነሣው ሐሳብ የጋለ ክርክር እንደተካሄደበት ተዘግቧል፡፡

December 22, 2010

ጎንደር ጥምቀትን በካርኒቫል ደረጃ ልታከብር ነው

በሔኖክ ያሬድ
 (ሪፖርተር ጋዜጣ፤ Wednesday, 22 December 2010 11:14) ዓመታዊው የጥምቀት በዓል ለመጀመርያ ጊዜ በጎንደር በካርኒቫል ደረጃ ለአምስት ቀናት እንደሚከበር የጎንደር ባህልና ቱሪዝም መምርያ አስታወቀ፡፡ የመምሪያው ኃላፊ አቶ ጌታሁን ሥዩም ለሪፖርተር እንደገለጹት፣ ከዚህ ቀደም ከጥር 10 እስከ ጥር 12 ቀን ለሦስት ቀናት ይከበር የነበረው የከተራ ጥምቀት በዓል በሁለገብ ዝግጅቶች ለአምስት ቀናት በብሔራዊ ካርኒቫል ደረጃ ይከበራል፡፡

December 19, 2010

የቀድሞው መንግሥት ባለሥልጣናት ከገና በፊት ሊፈቱ ይችላሉ

(በታምሩ ጽጌና በዘካሪያስ ስንታየሁ ሪፖርተር ጋዜጣ፤ Sunday, 19 December 2010 12:31 ):-
በዘር ማጥፋት ወንጀል ተከሰው በሞት፣ በእድሜ ልክና በዓመታት እስር እንዲቀጡ የተወሰነባቸው የደርግ ከፍተኛ ባለሥልጣናት ለገና ሊፈቱ እንደሚችሉ ምንጮች ለሪፖርተር ገለጹ፡፡ በወቅቱ የፈጸሙትን የተለያዩ ወንጀሎችን በማመን እግዚአብሔርን፣ ሕዝብንና መንግሥትን ይቅርታ እንዲጠይቁ ከሁለት ዓመታት በፊት በኢትዮጵያ ላሉት የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን፣ በካቶሊካዊት ቤተክርስቲያን፣ በወንጌላዊት ቤተክርስቲያን መካነየሱስና በእስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሃይማኖት መሪዎች እንዲለምኑላቸው ባቀረቡት ጥያቄ መሠረት፤ የሃይማኖት መሪዎቹ መንግሥትን፣ ተጎጂዎችንና የተጎጂ ቤተሰቦችን በማነጋገር ይሁንታ በማግኘታቸው ሳይፈቱ እንደማይቀሩ ምንጮቹ ያላቸውን ግምት ተናግረዋል፡፡

የሃይማኖት አባቶች የቀድሞ የደርግ ባለሥልጣናትን ወክለው ይቅርታ አቀረቡ

(መ/ር መንግስተአብ አበጋዝ፤ ማ/ቅዱሳን ድረ ገጽ):- የአራት የሃይማኖት ተቋማት መሪዎች የቀድሞ የደርግ ባለሥልጣናትን የይቅርታ ጥያቄ ለኢትዮጵያ ሕዝብና መንግሥት አቀረቡ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ካቶሊካዊት ቤተ ክርስቲያን፣ የኢትዮጵያ ወንጌላዊት ቤተ ክርስቲያን መካነ ኢየሱስ እና የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የሃይማኖት መሪዎች ቅዳሜ ታኅሳስ 9 ቀን 2003 ዓ.ም በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ተገኝተው በሰጡት የጋራ መግለጫ ይህን የታሪክ ጠባሳ በአገራዊ ይቅርታና ዕርቅ መጨረስ ከሁሉ በላይ ታላቅ መንፈሳዊ አንድምታ ይኖረዋል ብለዋል።

December 16, 2010

መንፈሳዊ ኮሌጆቻችን የማዳከሙ አዲሱ ሴራና ተንኮል

(አዲሱ ተስፋዬ፤ ለደጀ ሰላም)፦ ባለፈው ወራት በቤተ ክርስቲያን ዙርያ መነጋገርያ ሆኖ የሰነበተው የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎች መንፈሳዊ ጥያቄና  የበጋሻው ክስ ጉዳይ መሆኑ ይታወሳል። ነገር ግን ደጀ ሰላምም ላይ ይሁን ሌሎች የቤተ ክርስቲያን ጦማሮች ላይ የጉዳዩን አሳሳቢነት ከመግለጥ ውጭ የችግሮቹን ሥረ-መሰረት ለማሳየት የተደረገ ሙከራ ጥቂት ነበር። የኛዎቹ ሚዲያዎች ቢተውትም ሌሎች ሚዲያዎች ግን በጉዳዩ ላይ አስገራሚ ምስጢሮችን አስነብበዋል።

Atlanta Abo, Blogging

In the Name of the Father, the Son and the Holy Sprit, one GOD Amen!
Dear Dejeselamawians,
I have seen your recent post regarding the blog sites by Kesis Yared and Kesis Dejene and comments posted to it. I just want to point  to you that Mekane Hiwot Abune Gebre Menfes Kidus EOTC in Atlanta has been operating its own blog site since Sept 11/ 2010 (may be a first for an EOT Church). 

December 9, 2010

የመልአከ ሰላም ደጀኔ ሺፈራው አዲስ የጡመራ መድረክ

መልአከ ሰላም ደጀኔ ከልጃቸው ከዲ/ን አትናቴዎስ ጋር
(ደጀ ሰላም፤ ዲሴምበር 9/2010፤ ኅዳር 30/2003 ዓ.ም)፦ በግሩም ስብከታቸው እና በጠንካራ ጽሑፎቻቸው ለረዥም ዘመን ምእመናንን በማስተማራቸው የሚታወቁት መልአከ ሰላም ደጀኔ ሺፈራው ከመስከረም 25 ቀን 2003 ዓ.ም (ኦክቶበር 5/2010) ጀምሮ አዲስ የጡመራ መድረክ (ብሎግ) በመክፈት አገልግሎት መስጠት ጀምረዋል። 


መልአከ ሰላም ደጀኔ ሺፈራው የሚያነሷቸው ርዕሰ ጉዳዮች በተለይም አሁን አሁን ከብዙ ሰባክያን አንደበት እና ከስብከት አደባባይ (ዐውደ ምሕረቶች) እየራቀ የመጣው የነገረ ሃይማኖት በተለይም የነገረ ቅዱሳን ጉዳይ በመሆኑ ደጀ ሰላማውያን በሙሉ እንዳያመልጣቸው ለማሳሰብ እንወዳለን።

የ"ፀረ-ሙስና" ቀን Anti-Corruption Day

(ደጀ ሰላም፤ ዲሴምበር 9/2010፤ ኅዳር 30/2003 ዓ.ም)፦ ኅዳር 30 (December 9) ቀን በዓለም ደረጃ የሙስና አስከፊነት የሚዘከርበት ("ፀረ-ሙስና") ዓመታዊ ቀን ነው። የችግሩ አስከፊነት በተለይም በታዳጊ አገሮች ዘርፈ ብዙ ችግሮችን የሚፈጥር ከመሆኑ አንጻር ለችግሩ ትኩረት መስጠቱ ተገቢ ነው። "ደጀ ሰላም" ማንሣት የፈለገችው ግን በጠቅላላው በኢትዮጵያ ስላለው ሙስና እና የንብረት ብክነት ሳይሆን ቤተ ክርስቲያናችንን ጠፍንጎ ስለያዛት ዝርፊያ እና የንብረት ውድመት ነው። ከላይ እስከ ታች በተዘረጋ የጉቦ፣ የሙስና እና የሀብት ዝርፊያ ዘመቻ ቤተ ክርስቲያናችን ችግር ላይ መውደቋን በተደጋጋሚ ስንዘግብ መቆየታችንን በማስታወስ መፍትሔው ግን አሁንም ሩቅ መሆኑን አበክረን እናስታውሳለን።

December 8, 2010

ከፍተኛ የመንፈሳዊ ትምህርት ተቋማቱ ትኩረትና ድጋፍ ይሻሉ


(ለደጀ ሰላም፤ ከቅ/ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት አንዱ)፦ ፕሮቴስታንቲዝም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንን አጥፍቶ ሀገሪቱን ለመረከብ ከአንድ ምዕት ዓመት በላይ የዘለቀ ጥረት አድርጓል፡፡ በዚህ ጥረቱ ከተከተላቸው እና እየተከተላቸው ካሉ ስልቶች አንዱ የቤተክርስቲያንን የክህነትና የስብከተ ወንጌል አገልገሎት እንዲሁም አስተደደር ለመቆጣጠር መሞከር ነው፡፡ በዚህ ስልት መሠረት የአብነት ትምህርት ቤቶቻችንን እና መንፈሳዊ ኮሌጆቻችንን ለመቆጣጠር በርካታ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡ ለዚህ ማሳያ የሚሆኑ ባለፉት ወራት በቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የተደረጉ እንቅስቃሴዎችን እናንሣ::

ገዳማትን እና አድባራትን ለመታደግ በለንደን የገንዘብ ማሰባሰብ ፕሮግራም ተካሄደ

(ለደጀ ሰላም ታምሩ ገዳ - ለንደን):- በኢትዮጵያ  ውስጥ  የሚገኙ  ገዳማት አድባራት እና የአብነት/ቤቶችን  (የቆሎ /ቤቶችንውድመት ለመታደግ የታቀደ  የገንዘብ  ማሰባስብ ፕሮግራም  ለንደን ውስጥ  ተካሄደ ፡፡ የፕሮግራሙ  ዋንኛ ተዋንያኖች ሆኑት የማኅበረ  ቅዱሳን  አባላት  ከዚህ ቀደም ያበረከቱት  እና አሁንም  እያበረከቱት ያለው አስተዋጽኦ  ለበርካታ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት  ተከታዮች ከፍተኛ አርአያ መሆኑ ተገለጸ፡፡

December 4, 2010

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አንድ ተማሪውን ከትምህርት አገደ

(ደጀ ሰላም፤ ዲሴምበር 4/2010 ኅዳር 25/2003 .) የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ አስተዳደር ጉባኤ ለአዲስ ተመዝጋቢ ደቀ መዛሙርት ባስቀመጠው መስፈርት መሠረት ‹‹ከተቋሙ የቅበላ መስፈርቶች አንዱ የሆነውን በሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ወይም በአጥቢያ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ የተፈረመበት የድጋፍ ደብዳቤ በተሰጠው ጊዜ ገደብ ውስጥ አላቀረበም፤ በድጋፍ ደብዳቤ ስም ያቀረበውም ማስረጃ ተቀባይነት የሌለው ነው፤ ከአንድ ወር በላይ በትምህርት ገበታው ላይ አልተገኘም››፣  ከሬጅስትራሩ፣ ከአካዳሚክ ዲኑ እና ከበላይ ሐላፊው ዕውቅና ውጭ ወደ ኮሌጁ በሕገ ወጥ መንገድ በመግባት ትምህርት ጀምሯል ያለውን አሰግድ ሣህለ የተባለ ተማሪ አገደ፡፡

December 3, 2010

ፍርድ ቤቱ በጋሻው ደሳለኝን በነጻ አሰናበተ

(ደጀ ሰላም፤ ዲሴምበር 2/2010፤ ኅዳር 23/2003 ዓ.ም)፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ማኅበረ ቅዱሳን የድሬዳዋ ማእከል የስም ማጥፋት ወንጀል ክስ የቀረበበት በጋሻው ደሳለኝ ከቀረበበት ክስ በነጻ ተሰናበተ፡፡ የድሬዳዋ አስተዳደር ካውንስል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ዛሬ ጠዋት ኅዳር 23 ቀን 2003 ዓ.ም ውሳኔ የሰጠው ተከሳሹ በጋሻው ደሳለኝ ሚያዝያ 19 ቀን 2002 ዓ.ም በሳባ ደብረ ኀይል ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን፣ “አንድ ማኅበር አለ - ማኅበረ ቅዱሳን የሚባል፡፡ ደም አፍሳሽ ማኅበር፣ የወንድሞችን ደም በጣሳ እየተቀበሉ ለመጠጣት የተዘጋጁ. . .” በማለት ያሰማው ንግግር “አያስከስስም” በሚል ነው፡፡ ውሳኔው ጉዳዩን በሚከታተሉ ሌሎች የፍትሕ አካላት እና የሕግ ባለሙያዎች ዘንድ ከፈጠረው መደናገር የተነሣ በጥንቃቄ እየተጤነ እንደሆነ ተገልጧል፡፡

November 27, 2010

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን የገንዘብ እና ንብረት ቆጠራ ላይ ጥብቅ መመሪያ ሰጠ


 • ለሊቀ ጳጳሱ ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ እና ለሥራ አስኪያጁ ንቡረ እድ  አባ ገብረ ማርያም አቀባበል ተደርጓል፡፡
 • አጥቢያ አብያተ ክርስቲያኑ ለሀገረ ስብከቱ ፈሰስ ማድረግ የሚጠበቅባቸው የ58 ሚሊዮን ብር ዕዳ ያለባቸው ሲሆን ሀገረ ስብከቱ ለጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ፈሰስ ማድረግ ከሚጠበቅበት የዘመኑ ገቢ የ13 ሚሊዮን ብር ጉድለት ተገኝቶበታል፡፡    
 • ‹‹ምእመናን ተቸግረው በሚሰጡት ገንዘብ መልሰው እንዲያዝኑ ልናደርጋቸው  አይገባም፡፡›› (ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ)
 • ‹‹ለቅጥር፣ ዕድገት እና ዝውውር አማላጅ የመላክ ጉዳይ አይቻለሁ፤ በግልጽ  ማስታወቂያ በሚወጣው መሠረት ከሚፈጸመው በቀር በምልጃ የሚደረግ ነገር  አይኖርም፡፡›› (ንቡረ እድ አባ ገብረ ማርያም)
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 27/2010፤ ኅዳር 18/2003 ዓ.ም)ትናንት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት የስብከተ ወንጌል አዳራሽ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ ጥሪ በተደረገላቸው የአዲስ አበባ ገዳማት እና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ የሰበካ ጉባኤ ጸሐፊዎች፣ ሒሳብ ሹሞች፣ የስብከተ ወንጌል ሐላፊዎች እና የምእመናን ተወካዮች በተገኙበት በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ለሆኑት ብፁዕ አቡነ ቀውስጦስ እና ለሥራ አስኪያጁ ንቡረ እድ አባ ገብረ ማርያም የአቀባበል እና የትውውቅ መርሐ ግብር ተካሂዷል፡፡

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመለሱ

(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 26/2010፤ ኅዳር 17/2003 ዓ.ም)የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ከኅዳር ስምንት ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ ትምህርት በማቆም እና ከምግብ ቤቱ አገልግሎት በመከልከል ባነሷቸው ችግሮች አፈታት ላይ ስምምነት ተደረሰ፤ ደቀ መዛሙርቱም ከትናንት ኅዳር 18 ቀን 2003 ዓ.ም ምሽት ጀምሮ በኮሌጁ የምግብ ቤት አገልግሎት መጠቀም መጀመራቸው ታውቋል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ከኮሌጁ አስተዳደር እና ቦርድ ጋራ ከስምምነት ላይ እንዲደርሱ ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉት የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ የነገረ መለኮት ምሩቃን ማኅበር እና ደቀ መዛሙርቱ አቤቱታቸውን ካቀረቡላቸው የውጭ አካላት አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ናቸው፡፡

November 24, 2010

መንፈሳዊ ኮሌጅ ተማሪዎቹ አድማቸውን ካላቆሙ ይባረራሉ አለ

 (በምዕራፍ ብርሃኔ፤ የሪፖርተር ጋዜጣ የኖቬምበር 24/2010 እትም):- የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ከህዳር 8 ቀን 2003 ዓ.ም. ጀምሮ የምግብና የትምህርት አድማ የመቱ ከመቶ በላይ የሆኑ ተማሪዎችን (ደቀመዛሙርት) ወደ ትምህርት ገበታቸው የማይመለሱና ከሆነና የኮሌጁን ምግብ የማይመገቡ ከሆነ፣ የኮሌጁን ንብረት አስረክበው ክሊራንስ በማስፈረም የትምህርት ተቋሙን በአስቸኳይ ለቀው እንዲወጡ ከትናንት በስቲያ አስታወቀ፡፡

November 20, 2010

ቤትህን አስተካክል


 "ሕዝቤ ሰንፈዋልና አላወቁኝም፤…። 
ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።" (ኤር.፬፡፳፪)
             
(አብርሃም ሰሎሞን)
በእጅህ ያኖርኩትን የብርሃን ፀዳል መቅረዙን
              ከስፍራው መጥቼ ሳልወስደው፣
ከዝናም በኋላ ደመናት ሳይሸሹ ፀሐይ
          ሳትጨልም ቀኑን ሳልጋርደው፣
ከማሳው ያለውን ፍሬ አልባ ዘርህን ማለዳ
       መጥቼ ከእርሻው ላይ ሳልነቅለው፣
የሰጠሁህን ሀብት ከመዳፍ ከጉያህ በአንድ
 ጀምበር እድሜ አውጥቼ ሳልጥለው፣
እፍ ያልኩበትን ነፍስ ከውስጥህ ለይቼ
          ወደነበረበት ስፍራ ሳልመልሰው፣
አእምሮ አለህና ነቅተህ ተዘጋጅተህ አደራህን
                ፈጽም አስተውል አንተ ሰው።

November 19, 2010

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጁ ደቀ መዛሙርት የምግብ ቤቱ ሐላፊ እንዲነሡላቸው ጠየቁ

(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 19/2010፤ ኅዳር 10/2003 ዓ.ም)የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት በምግብ አቅርቦት ጥራት፣ በጤና አገልግሎት ሽፋን፣ በሥርዐተ ትምህርት ጫና እና የደቀ መዛሙርት መማክርት መቋቋምን አስመልክቶ ለተቋሙ አስተዳደር ያነሷቸው ጥያቄዎች፣ “ወቅታዊ ምላሽ እና ተገቢ ትኩረት አልተሰጣቸውም” በሚል ከትናንት አንሥቶ በካፊቴሪያው ባለመመገብ እና ትምህርት በማቋረጥ የጀመሩትን ተቃውሞ ቀጥለው ውለዋል፡፡ ደቀ መዛሙርቱ ዛሬ ጠዋት የበላይ ሐላፊ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ጢሞቴዎስ እና ሌሎች የኮሌጁ አስተዳደር ሐላፊዎች በተገኙበት በተነሡት ጥያቄዎች ዙሪያ ውይይት ማድረጋቸው ተዘግቧል፡፡

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ለተቋሙ አስተዳደር የተለያዩ ጥያቄዎችን አቀረቡ


 • ‹‹60 ተማሪዎች ከምግብ ጋራ በተያያዘ የጤና ችግር ገጥሟቸዋል›› ተብሏል፤ 
 • ለኮሌጁ ዲግሪ እና ዲፕሎማ ዕውቅና የማይሰጡ ተቋማት አሉ፤
 • የኮሌጁ ቦርድ እና አስተዳደር ለተማሪዎች መማክርት ም/ቤት መቋቋም ፈቃድ ለመስጠት ተስኖታል፤
 • ደቀ መዛሙርቱ ያቀረቡትን ጥያቄ በመጠቀም “የራሳቸውን ዓላማ ለማስፈጸም የሚሹ አካላት ከድርጊታቸው ሊታቀቡ” እንደሚገባ ተገልጧል፤
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 16/2010፤ ኅዳር 7/2003 ዓ.ም) የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ደቀ መዛሙርት ከምግብ ጥራት፣ ከጤና እክል እና ከሚያገኙት የሕክምና ደረጃ፣ ከሥርዐተ ትምህርት ተገቢነት እና ከተማሪዎች መማክርት መቋቋም ጋራ በተያያዘ በኮሌጁ አስተዳደር ‹‹በአስቸኳይ ሊስተካከሉ ይገባሉ›› ባሏቸው ችግሮች ዙሪያ ተቃውሞ አንሥተዋል፡፡

November 17, 2010

የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ቤተ ክህነቱ ላለበት የአሠራር ብልሹነት ማሳያ ሆነ

 • የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር የሀገረ ስብከቱን ሊቀ ጳጳስ አስጠነቀቀ
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 16/2010፤ ኅዳር 7/2003 ዓ.ም) የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ጽ/ቤት የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት ለቤተ ክርስቲያኒቱ ልማት መሰናከል እና ለገጽታዋ መበላሸት ዕንቅፋት ሆኖ የሚገኘውን የቤተ ዘመድ አስተዳደር፣ ሙስና እና የሥነ ምግባር ብልሽት በአስቸኳይ እንዲያስተካክል አስጠነቀቀ፡፡ ‹‹ኅብረተሰቡ በሀገረ ስብከቱ ላይ የተቃውሞ ሰላማዊ ሰልፍ ለማድረግ ምክር ቤቱን እስከ መጠየቅ ደርሷል›› ያለው ጽ/ቤቱ “ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ” እስከ መባል የደረሰው የሰሜን ሸዋ ሀገረ ስብከት አስተዳደር በአፋጣኝ ይሻሻል ዘንድ የሀገረ ስብከቱ ሠራተኞች የሚፈጥሩት ጫና እና የኅብረተሰቡ ቁጣ እየተጠናከረ መምጣቱን ለሊቀ ጳጳሱ አስረድቷቸዋል፡፡ ችግሮቹ በምክክር የማይፈቱ ከሆነ ለሕዝቡ ምሬት ምላሽ ለመስጠት ጉዳዩ በሕግ አግባብ የሚታይ ይሆናል ብሏል አስተዳደሩ፡፡

November 16, 2010

አ.አ ዩኒቨርሲቲ መጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስን ዘከረ

 • የመጋቤ ብሉይ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ ፋውንዴሽን›› እንዲቋቋም ተጠይቋል
 •  ዝክሩ ለቤተ ክህነቱ ነቀፌታ(ተግሣጽ) ሆኖታል
 •  መጋቤ ምስጢር ወልደ ሩፋኤል ፈታሒ በዝክሩ ላይ ስለ መጋቤ ብሉይ ሰይፈ  አሟሟት የሰጡት እና ቤተ ክህነቱን የተቹበት ቅኔ ታዳሚዎችን አነጋግሯል
 • ዩኒቨርስቲው ዕውቀታቸው ለሀገር እና ለትውልድ የሚተርፉ ሌሎች ሊቃውንትንም አሥሦ የሚዘክርበት ‹‹አጉሊ መነጽር›› እንዲያደርግ ተጠይቋል
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 16/2010፤ ኅዳር 7/2003 ዓ.ም)የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሊቃውንት ጉባኤ መምሪያ ሐላፊ ለነበሩት እና ነሐሴ አንድ ቀን 2002 ዓ.ም መንሥኤው ባልታወቀ ድንገተኛ ዕረፍት ከዚህ ዓለም በሞት ለተለዩት ለሊቁ መጋቤ ሰይፈ ሥላሴ ዮሐንስ የመታሰቢያ መርሐ ግብር አካሄደ፡፡

November 15, 2010

በዱባይ ሻርጃ ለአንድ ወር የሚዘልቅ የስብከተ ወንጌል ጉባኤ ሊካሄድ ነው

 • በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የሊባኖስ እና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ አህጉረ ስብከታቸውን እያወኩ በሚገኙት ሕገወጦች  ላይ ርምጃ እንዲወሰድ ቋሚ ሲኖዶሱን በደብዳቤ ጠይቀዋል፡፡ 
 • ከሕገ ወጦቹ አንዱ የሆነው እና በአገር ውስጥ በስም ማጥፋት ወንጀል ክስ የተመሠረተበት በጋሻው ደሳለኝ ነገ ወደ ሥፍራው ይጓዛል፤
 • "የዱባይ ቅዱስ ሚካኤል የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን"  በሚል ጉባኤ ለማካሄድ የተዘጋጁት አካላት ሕገ ወጥ መሆናቸው ተገልጧል፤
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 14/2010፤ ኅዳር 5/2003 ዓ.ም)በተባበሩት ዐረብ ኤምሬቶች የሊባኖስ እና አካባቢው አህጉረ ስብከት ሥር በሚተዳደረው በዱባይ - ሻርጃ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ለአንድ ወር የሚዘልቅ የስብከተ ወንጌል ጉባኤ ተዘጋጀ፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር የስብከተ ወንጌል ጉባኤውን ለማስተዋወቅ ‹‹ሕዝቤ ሆይ ወደ ቤትህ ግባ›› በሚለው የነቢዩ ኢሳይያስ መሪ ቃል ባወጣው ፖስተር ላይ እንደተገለጸው፣ ጉባኤው የሚካሄደው በቅዱስ ሲኖዶስ ፈቃድ በሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዲሜጥሮስ ተባርኮ ወደ ሰዓሊተ ምሕረት ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የገባው የሊቀ መላእክት ቅዱስ ሚካኤል ታቦት ኅዳር 12 ቀን 2003 ዓ.ም ከመንበረ ክብሩ ወጥቶ የሚደረገውን ክብረ በዓል መሠረት አድርጎ ነው፡፡

November 14, 2010

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ወደ አሜሪካ ሄዱ

ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 13/2010፤ ኀዳር 4/2003 ዓ.ም)በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ጉባኤ የቅዱስ ጳውሎስ መንፈሳዊ ኮሌጅ ዲን ሆነው የተመደቡት ብፁዕ አቡነ ፋኑኤል ዛሬ ኅዳር 4/ 2003 .ም በዲሲና አካባቢው አቆጣጠር ከጠዋቱ 3 ሰዓት (9:00 AM) ዋሽንግተን ዲሲ  መግባታቸው ታወቀ:: ዳላስ ለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የደብረ ምረት ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ እና ጥቂት ምእመናን በቦታው በመገኘት አቀባበል ተደርጎላቸዋል:: የብፁዕነታቸው ወደ ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢው ሀገረ ስብከት መሄድ ሀገረ ስብከቱ እውቅና ይኑረው አይኑረው ለጊዜው ባይታወቅም፤ በአቀባበል ሥነ ርዓ ላይ ግን የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ አብሃም አልነበሩም::

November 13, 2010

በሐዋሳ ለብፁዕ አቡነ ገብርኤል ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው

 • ከ20 በላይ መኪኖች እና ሰባት ሞተረኞች ጥቁር ውኃ ላይ ተሰልፈው  ተቀብለዋቸዋል፤ ፓትርያርኩ አልተገኙም፡፡
 • ብፁዕነታቸው፣ ‹‹ውበት የሚኖረው በአንድነት ውስጥ በመሆኑ በኅብረት   አንድ ሆነን መገኘት ያስፈልገናል፤›› በማለት መክረዋል፡፡ 
 • ጥቂት ቲፎዞዎች ጥቁር ጨርቅ ሲያውለበልቡ ታይተዋል
 • እነ ያሬድ አደመ የተለቀቁት፣ ‹‹ዐቃቤ ሕግ የምርመራ ሂደቱን ከጊዜ ቀጠሮው  በፊት ማጠናቀቁን ሪፖርት በማቅረቡ የዋስ መብት ተጠብቆላቸው ነው›› ተብሏል፡፡
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 13/2010፤ ኀዳር 4/2003 ዓ.ም)በጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ የሲዳማ፣ አማሮ እና ቡርጂ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ሆነው የተመደቡት ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ዛሬ ረፋድ ላይ ሐዋሳ ከተማ ሲገቡ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡ ሊቀ ጳጳሱን ለመቀበል ከሀገረ ስብከቱ፣ ከአጥቢያ አብያተ ክርስቲያን እና ከምእመናን ተውጣጥቶ የተቋቋመው 40 አባላት እና ልዩ ልዩ ዘርፎች ባሉት የአቀባበል ኮሚቴ፣ ብፁዕ አቡነ ገብርኤል ከብፁዕ አቡነ ሕዝቅኤል፣ ብፁዕ አቡነ ያሬድ እና ብፁዕ አቡነ ሚካኤል ጋራ በሐዋሳ ከተማ መግቢያ - ጥቁር ውኃ አምስት ሰዓት ግድም ሲደርሱ በበጎ ፈቃድ በተሰለፉ ከኻያ በላይ መኪኖች እና ሰባት ሞተር ሳይክሎች በማጀብ ደማቅ አቀባበል ተደርጎላቸዋል፡፡

በሐዋሳ ቅ/ገብርኤል ውስጥ ብጥብጥ የፈጠሩት ተፈቱ


(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 12/2010፤ ኀዳር 3/2003 ዓ.ም) እሑድ ጥቅምት 28 ቀን 2003 ዓ.ም በሐዋሳ ደብረ ምሕረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም በተፈጠረው ዐምባጓሮ በሕጋዊ የገዳሙ ሰንበት ት/ቤት አባላት ላይ ከፍተኛ የድብደባ ጉዳት በማድረሳቸው ተከሰው የተያዙት ያሬድ አደመ እና ዓለምነህ ሽጉጤን ጨምሮ 11 ያህል ሰዎች ዛሬ ተፈቱ።

November 12, 2010

To Deje Selam: What Should We do?

To:    dejeselam@gmail.com       
(By Tewahedo)
Peace for All of You in The name Of Jesus Christ the Savior!
I agree and support DSs report about the abuse and disagreements in church but this is not the way to solve the problems of the church. If we want to solve the problems once and for all we need other mechanism. Shall we let DS and other Medias continue on the reporting this chaos’s, frustrations and divisions among Christians?

November 11, 2010

የሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ ሹመት እያነጋገረ ነው


ሊ/ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ
 • ‹‹በቅዱስ ሲኖዶስ ጥፋተኛ የተባለን ሰው ሹመት መስጠት ብቻ  ሳይሆን በሥራ መመደብ ስሕተት ነው፡፡››   (የቅዱስ ሲኖዶስ ዋና ጸሐፊ ተቃውሞ) 
 • በአስተዳደር እና አቅም ግንባታ መምሪያ ቦታ አዲስ ሹመት ተሰጥቷል
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 11/2010፤ ኀዳር 2/2003 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከትን በተመለከተ በቅዱስ ሲኖዶስ የተሠየመው አጣሪ ኮሚቴ ለጥቅምቱ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ባቀረበው ሪፖርት እንዲሁም በ29ው አጠቃላይ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ ስብሰባ ላይ በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ ዋና ሥራ አስኪያጅ ሪፖርት ውስጥ ተካትቶ በቀረበው የቁጥጥር አገልግሎት ሪፖርት ቃለ ዓዋዲውን ተከትሎ ከመሥራት እና መልካም አስተዳደርን ከማስፈን አኳያ በተገኘባቸው ከፍተኛ ግድፈት የተነሣ ከሥራ አስኪያጅነት ሐላፊነታቸው እንዲወገዱ፣ የፈጸሟቸው በደሎች ሁሉ ተጣርቶ በሕግ እንዲጠየቁ የተወሰነባቸው ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት በምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ማዕርግ የልማት ጉዳዮች ዘርፍ ሥራ አስኪያጅ ሆነው መሾማቸው ጥያቄዎችን እያስነሣ ይገኛል፤ በቤተ ክርስቲያኒቱ ወቅታዊ ችግሮች ዙሪያ በምእመኑ ዘንድ አንድ አቋም እና ግንዛቤ እየተፈጠረ የመጣበትን አትኩሮት ለማስቀየስ የሚደረግ ጥረት አካል ተደርጎም ተወስዷል፡፡

November 10, 2010

ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ከኦስትርያ መልስ


ርእሰ ዜና
 • ሊቀ ማእምራን ፋንታሁን ሙጬ በጠቅላይ ቤተ ክህነት የልማት ምክትል ዋና ሥራ አስኪያጅ ሆነው ተሾሙ፡፡ ቀደም ሲል ሊቀ ማእምራን ፋንታሁንን በጠቅላይ ቤተ ክህነቱ የአስተዳደር እና አቅም ግንባታ መምሪያ ሐላፊነት ለመመደብ በፓትርያርኩ ቀርቦ የነበረው ሐሳብ በዋና ሥራ አስኪያጁ በገጠመው ብርቱ ተቃውሞ ውድቅ እንደተደረገ ተገልጧል፡፡
 • የአስተዳደር እና አቅም ግንባታ መምሪያ ሐላፊ የነበሩት አቶ ደሳለኝ መኰንን ከሐላፊነታቸው በራሳቸው ፈቃድ ለቀዋል፤ ምክንያቱ ‹‹የተሻለ ሥራ እና ደመወዝ በማግኘታቸው ነው›› ተብሏል፡፡ (ዝርዝሩን እንመለስበታን)

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)