December 27, 2009

የገናን በዓል በላሊበላ ከተማ በድምቀት ለማክበር ዝግጅት እየተካሄደ ነው

(WALTA ዋኢማ, Sunday, 27 December 2009):- የኢትዮጵያን መልካም ገጸታ ለመገንባት መጪውን የገና በዓል በድምቀት ለማክበር መዘጋጀቱን የላሊበላ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፤ ለበዓሉ ድምቀት የታላቁ ሩጫ መርሐ-ግብር እንደሚካሄድ ገለጸ።


የአስተዳደሩ ምክትል ከንቲባ አቶ ተስፋዬ ጌጤና የከተማው ባሕልና ቱሪዝም መምሪያ ኃላፊ አቶ በለጠ ወዳጄ ትናንት ለዋልታ እንዳስታወቁት፤ በየዓመቱ በላሊበላ ከተማ የሚከበረውን የገናን በዓል በተያዘው ወር መጨረሻ በደመቀ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው።

በተለይም ከመላው ዓለምና ከሀገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች ዓመታዊውን የገናን በዓል ለማክበር ወደ ላሊበላ የሚመጡ መንፈሳዊ ተጓዦችና ቱሪስቶች በዓሉን በሰላማዊና አስተማማኝ ሁኔታ እንዲያከብሩት ነዋሪውንና ፖሊስን ያሳተፈ የአካባቢ ጸጥታና ጥበቃ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።

በርካታ ምዕመናንም ወደ ላሊበላ ስለሚመጡና ለቀናት ስለሚቆዩ ሊፈጸሙ የሚችሉ የወንጀል ክሶችን አፋጣኝ ውሳኔ ለመስጠት እንዲቻል ጊዜያዊ የወንጀል ችሎት መቋቋሙንም ምክትል ከንቲባውና ኃላፊው ተናግረዋል።

አገልግሎት ሰጪ ተቋማትና ሆቴሎችም በዓሉን ምክንያት በማድረግ የአገልግሎት ዋጋ ጭማሪ እንዳያደርጉ ምክክርና ውይይት መደረጉን ገልጸው፤ በተለይም እንግዶች በአግባቡ የመኝታና የምግብ አገልግሎት እንዲያገኙ ከወትሮው በተሻለ ሁኔታ ለእንግዳ አቀባበል ሥርዓት ዘርግተዋል ብለዋል።

የከተማው የዘላቂ የንጹህ መጠጥ ውሃ ኘሮጀክት ግንባታ ተጠናቅቆ አገልግሎት መስጠት በመጀመሩ አስተማማኝ የውሃ አቅርቦት እንዳለም የከተማ አስተዳደሩ የሥራ ኃላፊዎች ተናግረዋል።

ለመጀመሪያ ጊዜ በላሊበላ ከተማ የሚካሄደው የታላቁ ሩጫ መርሐ-ግብርም ለበዓሉ ድምቀት እንደሚሰጥ ጠቁመው፤ የተሽከርካሪና የእግረኛ መንገዶችን ጨምሮ የአየር ትራንስፖርት ለተጓዦች አመቺ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

በበዓሉ ላይ ከስምንት መቶ ሺ እስከ አንድ ሚሊየን ሕዝብ ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ አመልክተው፤ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላቸውን ፍልፍልና ውቅር አብያተክርስቲያናትን ጨምሮ ዋሻዎች፣ የአካባቢው መልክዓ-ምድርና በላሊበላ ከተማ በ45 ኪሎ ሜትር ዙሪያ ያሉ የተፈጥሮ፣ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ቦታዎች እና መስህቦች እንዲጎበኙ ጥረት እየተደረገ ነው ብለዋል።

ባለፉት አምስት ወራት ላሊበላ ከተማንና በአካባቢው ያሉ የቱሪዝም ሃብቶችን ከጎበኙ 10 ሺ 769 የውጭ ሀገርና 4ሺ 989 የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ከ23 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የከተማው አስተዳደር ባህልና ቱሪዝም መምሪያ ሰሞኑን መግለጹ ይታወሳል።
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)