December 24, 2009

“እስክንድር ከሆንክ እንደ እስክንድር ተዋጋ፤ ካልሆነ ደግሞ ስሙን መልስ”

(አቤል ቀዳማዊ)
በሰሜን አሜሪካ የኢ/ኦ/ተ/ቤ ካህናትና ምዕመናን ጉባኤ መግለጫ ሳነብ የተዘበራረቀ ስሜት ተሰማኝ። ምክንያቱም በዘንድሮ ጉባኤአቸው ላይ ታሪካዊ ውሳኔ ያሳልፋሉ ብዬ ጠብቄ ነበረ። እነዚህ በተለያዩ ግዛት የሚገኙት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት በአስተዳደር ብልሹነት ምክንያት የአቡነ ጳውሎስ አስተዳደር እንደማይቀበሉ፤ ነገር ግን የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔዎች እንደሚቀበሉ በተለያዩ መድረኮች ሲገልፁልን ቆይተዋል። የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ በአንዳንድ ብፁአን አባቶች አማላካችነት ቤተ ክርስቲያናችን ከብልሹ አስተዳደር እንድትፀዳ ጥያቄው ቀርቦዋል። ይህም ጥያቄ በሒደት ላይ መሆኑን በተለያዩ የህዝብ መገናኛ ብዙሀን ሰምተናል። ታዲያ ችግራቸው የአስተዳደር ብልሹነት ከሆነ ጥያቄው አሁን በውስጥም ስለተነሳ “እኛም ከዚህ በፊት ያነሳነው ጥያቄ ስለሆነ ከእናንተ ጋር ነን፣ አብረንም እንዋጋዋለን” በማለት ግልፅ የሆነ ውሳኔ ለምን አላሳለፉም?።

እንግዲህ እነዚህ ተሰባስበዋል የተባሉት “ገለልተኞች” ነን ከሚሉት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት መሀከል በአንድ ቡድን የተሰሉፉ ናቸው። እዚህ ሰሜን አሜሪካ ውስጥ በይፋ የሚታወቁ ሶስት የአስተዳደር ዓይነት ያላቸው በኢ/ኦ/ተ/ቤ ስም የሚጠሩ አሉ። እነሱም “ገለልተኛ”፣ “ስደተኛ ሲኖዶስ” ነኝ ብሎ ራሱን የሚጠራው አስተዳደር የሚቀበሉ እና በኢትዮጵያው ቤተ ክርስቲያን አስተዳደር መዋቅር ስር የሚተዳደሩ ናችው። ይህ በስም ሶስት የአስተዳደር ዓይነቶች ምዕመናን ሁላችንም የምናውቀው ሲሆን፤ በውስጥ ግን እያንዳንዱ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን የራሱ የሆነ አስተዳደር እና የራሱ የሆነ ልዩ ፀባይ አለው።

ከዚህ በፊትም በዚሁ በደጀ ሰላም አስተያየት መስጫ ላይ እንደገለጽኩት እዚህ እኔ በምኖርበት ዋሽንግተን ዲሲ እና አካባቢዋ ማለትም ዲሲ፣ሜሪላንድ እና ቨርጂኒያ ላይ 18 (አስራ ስምንት) በኢ/ኦ/ተ/ቤ ስም የሚጠሩ አጥቢያ ቤተክርስቲያን ይገኛሉ። ከእነዚህም ውስጥ ስድስቱ “ገለልተኛ” ከሚባለው አስተዳደር የሚመደቡ ሲሆን፤ ነገር ግን ስድስቱም የራሳቸው የሆነ ልዩ ፀባይ እና እንዲሁም አስተዳደር ዓይነት አላቸው። ነገር ግን “ገለልተኛ” የሚለው ስም ብቻ አንድ ያደጋቸዋል። ከእነዚህም ውስጥ አንዱ አጥቢያ ብቻ ነው፤ ሰሞኑን በተካሄደው የካህናት እና ምዕመናን ጉባኤ ላይ የተሳተፈው። አምስቱ ግን አልተሳተፉም።
ታድያ ይህ ቅጥ ያጣ መለያየት መንስኤው ምን ይሆን? እውነት የፓትርያክ ጳውሎስ የአስተዳደር በደል? ወይስ ሌላ ጥቅም ፍለጋ? እንግዲህ “እስክንድር ከሆንክ እንደ እስክንድር ተዋጋ፤ ካልሆነ ደግሞ ስሙን መልስ” እንደሚባለው የኢ/ኦ/ተ/ቤ በማለት ስም ብቻ ይዞ ጉዞ እስከ መቼ?። መልሱን ለእናንተ ትቼዋለሁ።

16 comments:

Anonymous said...

የኢ/ኦ/ተ/ቤ በማለት ስም ብቻ ይዞ ጉዞ እስከ መቼ?። I believe the synodos should take a serious look in to the name specially for those that is under it's umbrella.

1=If Abune Paulos give 100.000 to lawyer here in america he will be glad to fight and get our church name to were it belongs not....
2=In regarding the Geliltegna the same thing should hapen to them too they are not different from the synodos here in america.
3= All those sunday school members who particpate in those church weather it is Gelilitegna or ye-americawi synodos,they should separate them selves.

Anonymous said...

ከላይ በቀረበው መጣጥፍ ውስጥ : ምን መልእክት ለማስተላለፍ እንደተፈለገ ግልጽ ባይሆንልኝም ::

ከተነሱት ነጥቦች ውስጥ ትንሽ ለማለት ያህል

1. ከኢትዮጵያ ውጭ ባሉ አገሮች (በተለይም በሰሜን አሜሪካ) ያለችው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን በሶስት ዓይነት አስተዳደሮች
"""(በኢትዮጵያ ሲኖዶስ,በስደተኛ ሲኖዶስ, እና ገለልተኛ በሚሉ አስተዳደሮች)""" እንደምትመራ የአደባባይ ምስጢር ነው ::

እነዚህም :
በኢትዮጵያ ሲኖዶስ እመራሁ የሚለው በራሱ በሶስት አይነት የተከፋፈለ ነው
ይኸውም

አንደኛው :
በትግራይ ተወላጆች ብቻ የሚመራውና ከፖለቲካው ጋር የተጣበቀው

ሁለተኛው :
መሀል ሰፋሪው (ማንም ፓትርያርክ ይሁን የቤተ ክርስቲያናችን መሰረት አገራችን ነው የሚል

ሶስተኛው ደግሞ :
መነሻውን አዲስ አበባ ያደረገውና የድርጅቱ ዋና ጽ/ቤት እንዳይዘጋበት (በአገር ውስጥ ሲኖዶስ ስር ነን የሚለውን ስም) እንደመያዣነት ብቻ የሚጠቀምበት :
በተጨማሪም : በቤተ ክርስቲያኗ ስም ከቀረጥ ነጻ ሆኖ ስለሚነግድባት : ስሟ የግድ የሚያስፈልገው :
የራሱ የሆነ ድብቅ አጀንዳና የተለየ ዓላማ ይዞ የሚንቀስ : ጭራውና ስሙ ብቻ ቤተ ክሕንት ውስጥ የተጎለተ :
ሙሉ አካሉና መንፈሱ ግን ከውጭ የሆነ : """"ማኅበረ ቅዱሳን""" የሚባለው ድርጅት....

ሁለተኛው አስተዳደር

በስደተኛው ሲኖዶስ ስር ነን የሚለውና : በጎንደር ተወላጆች መስራችነትና አንቀሳቃሽነት የተደራጀው ቡድን : (እንደ ግንቦት 7.... ፕሮግራም)ማንኛውንም መንገድ ተጠቅሞ የአባ ጳውሎስን (የትግራይን)አመራር ገልብጦ ጎንደርን በቤተ ክሕነቱ ውስጥ ለመትከል ደፋ ቀና የሚለው ቡድን

ሶስተኛው ቡድን ደግሞ

ራሱን ገለልተኛ ብሎ የሚጠራው : በመሀል አገር (በተለይ በሰሜን ሸዋ)ተወላጆች የተደራጀውና : """የሸዋ ቡድን"" የሚለው እውነተኛ ስሙ እንዳይታወቅበት ሌት ከቀን የሚፍጨረጨረው የባሰ ጠባብ ቡድን ነው :

የዚህ ቡድን አካሄድ ከሁሉም የሚከፋው ደግሞ
ሌሎቹን ""ዘረኞች ናቸው : የአስተዳደር ችግር አለባቸው ወዘተ ...""' እያለ : እሱ ግን ጭፍን ዘረኝነትን ከማንም በላይ የሚያራምድ :

"""በኢትዮጵያ (የመንግስትም ሆነ የክህነት) በትረ ስልጣን ከሸዋ ተወላጅ መውጣት የለበትም""" እያለ የሚቃዥ ከንቱ ህልመኛ :
በማኅበረ ቅዱሳን መስራቾችና አመራሮች የእጅ አዙር ድጋፍና : የውስጥ ቅንጅት ያለው ትምክህተኛ ጠባብ የማፍያ ቡድን ነው ::

ይቀጥላል

Anonymous said...

The answer for your question in the article/comment above is as follows:
It has become clear now that our church is totally controlled by the ruling clique in Addis. In the recent annual submit of the holy synod Aba Paulos called for a special force to terrorize those who raised questions about his ability to lead the church.The occassion has been proved that even if Aba Paulos is gone, the situation in our church will not change unless the political leadership is also gone.The so called administration problems come from not only from Aba Paulos,but we were able to confirm that the hands of the palace are also heavily involved.
Running around the bush can not solve the problems in our church.We need to talk the truth our hearts tell us,all of us including the writer of the above comment,who either scared to tell the truth or is part of those who rely on their gun,know full well.
During a meeting that took place to discuss the disagreements between MK and head of sunday school division of the church,the national security advisor-Abay Tsehaye,was heard warninig MK representatives that the government would take action if they,MK members, do not stop indicating weaknesses of the churche's leadership and ofcourse,practically speaking,to stop become good christians who care about their church.The killings of christians,the burning of churches,deprivation of christians' right to build churches,conduct conferences,celebrate holidays,etc are said by the government to be inciting conflict. And yet, the sad part of all this is that everybody including MK seems to have accepted the threat, and now become tigers against those who refuse to collaborate with our church destroyers.
One should not think that the daispora will succum to the curses of our country and our church and become part and parcel of the evil doers.Instead, we call up on all true christians to join us in the struggle to bring about change to our church and to our country. Long live tewshedo! Long live Ethiopia!

Anonymous said...

Abel,
Thank you for your thoughts. First of all, you are being to kind in stating that there are 3 types of Ethiopian Orthodox Churches in the US/diaspora. Unfortunately, and as you know, the number is two vast, and its getting even worse. My question is similar to yours, how long will EOTCs churches in the diaspora continue in their rebellion? Their rebellion is not against the government or a tribe, or a Patriarch, but against God. The true enemy of the Church always comes from within as in the case of Judah and Arius and others like them, some rebelled knowingly and some unknowingly. The enemy of the Ethiopia Orthodox Church is the one who seeks to change the doctrines or the canons of the Church, period. Therefore so called EOTCs in or out of Ethiopia who as a whole or as individuals disobey the dogmas and canons of the Church are in a state of rebellion against the True Church which will stand the test of time. All those who flow on their path, knowingly and unknowingly need to wake up, in the Gospel our Lord and Savior, warns us to Wake up! non of us know when we will be called, what a shame it would be if we were called out of this life and were questioned "why did you rebel? why did you exile yourself from the Church?" will our answer be sufficient? what will it be? tribal issues, political issues, administration issues... do we believe our answer will be sufficient to God who is Spirit and Love? Do we have a spiritual issue? So what is the solution? It is not complicated, seek the Church that is under the EOTC, who is connected to the Holy Synod in Ethiopia, and is KNOWN by the Holy Synod in Ethiopia. Make sure this connection is not just based on calling the Patriarchs name in the Kidase, but that the Church is fully administered by the EOTC administration. This means it is recognized by the Archdiocese of the EOTC in its region, and that its clergy commissioned by the EOTC administration. There is NO USE in saying "we follow the decisions of Holy Synod (Addis Ababa)" but the Holy Synod, which is represented by the Archbishop in the region of the parish does not recognize this Church. Recognize means validate its authenticity. We are in God's mercy, let us not waste our time relying on our own intelligence. Let us rely on our Father, King Christ, Emmebetachen, Saints Teklehaymanot, and our fathers and mothers of the past and present who are truly guided by God's Holy Spirit. I hope this for me and all of us..."watch and pray lest ye fall into temptation."

Anonymous said...

Abel,the undercover eprdf cadre,what ever you say we will not collaborate with enemies of our country and our church!We follow all dogma and sacraments of our church, Tewahedo,but we will not accept Aba Paulos and epdrf.They are the causes of all this mess in our church.And believe it or not they will both go soon, and Tewahedo and Ethiopia will once again shine high over their enemies.

Anonymous said...

"Not every one that saith unto me, Lord, Lord, shall enter into the kingdom of heaven; but he that doeth the will of my Father which is in heaven.
Many will say to me in that day, Lord, Lord, have we not prophesied in thy name? and in thy name have cast out devils? and in thy name done many wonderful works?
And then will I profess unto them, I never knew you: depart from me, ye that work iniquity". Mathew 7:21-23

"A new command I give you: Love one another. As I have loved you, so you must love one another. 35By this all men will know that you are my disciples, if you love one another". John 13: 34-35

Belachew AA said...

That is meaningless hope. We do know this the dream that you have been dreaming for a long time. Truest me, your meaningless dream will be vanished. You said," And believe it or not they will both go soon, and Tewahdo and Ethiopia will once again shine high over their enemies" I think you are you crazy. Aren’t you? Let me ask you this: could you please tell me where they will go? And do you think they are not Ethiopians? Are you coming to remove them from Ethiopia? Or just you are dreaming or wishing? You know nothing about Orthodox that’s why you said “We follow all dogma and sacraments of our church,” according to the Orthodox Teaching there is no church and sacraments without bishops, archbishops and patriarch. I do know your wish and dream, the reason why you want to separate from the holy Orthodox Church is; because patriarch Paulos and Ato Melas are not from Shiwa.
Anyway may God open your internal ear to hear the word of GOD.

Anonymous said...

We do not support Aba Paulos and eprdf's head not because they are not from shwewa nor because I believe in race,but it is because they hurt our church and our country. As to your question where they would go, they vwill go from their positions.They are ofcourse Ethiopians,but bad citizens who did harm to their country and our church.It is only for this reason the daispora rejected them. We come here from different parts of Ethiopia,and 95%of us oppose those people you mentioned their names.It is their erroneous policis that created the slaughtering of our brothers and sisters at the hands of extremists in Jimma and other places.It is these same people who are the causes of today's mess in our church.Aren't they? If we investigate why the mess occured,we can get the answer.In 1991 when eprdf seized power in Addis,its supporters here started to separate themselves from other Erhiopians saying that they would have mass sevices in their own language not in Amharic 'neftegnas'language;hence started establishing churches based on ethinicity-like the leaders at home.And Aba paulos came to power with controvertial issues sourrounding the legality of his patriarchate followed by his weak,nepotic,leadership and political affiliation to the ruling group.Then the churches in daispora preferred to stay out of the game,but firmly assuring that the holy synod of the church is in Ethiopia,and yet could not collaborate with those who did not care for the unity of the church and the country.In addition,it was not clear who the true patriarch of the church was until the consecration of bishops outside Ethiopia.Therefore,the so called 'independent' churches has become to mean independent from the dispute who the true patriarch was and a decision not to support those who mismanage the church and divide the country along ethnic/blood lines.However,regarding the dogma and sacraments of Tewahedo,it is actually these churches that strictly practice them except mentioning Aba paulos's name.That,ofcourse, should not have been a big deal,as it is a sign of opposition to his mismanagement and silence when people are slaugterd, his handing over of innocent students who harbour the churh to escape eprdfs' murderers,the list is on and on.... But instead of correcting mistaks, they always say it is because we are from the north-Tigray.It is not at all.It is their wrong doings that made them unacceped. people

Belachew said...

First of all I would like to say sorry to say that, I think you are foolish enough. You do not know anything about Ethiopia and Ethiopians and you know nothing about the holy bible. Read this from what you said.” If we investigate why the mess occured, we can get the answer.In 1991 when eprdf seized power in Addis,its supporters here started to separate themselves from other Erhiopians saying that they would have mass sevices in their own language not in Amharic” as long as I do live in Ethiopia. I cannot say your saying is false or true. Even it is true, do you think or believe having mass service in Tigrigna or Oromigna is wrong? Are you trying to say Amharic is a divine word or Amharic is the only Language in E thiopia? O!! Lord have mercy upon him” (her) if you are Christian, please read the holy bible. We are ordered to preach the holy gospel to the nations in their own Language not in one Language. I do know you now, who you are and where you are come from. I do understand why you are hate Abune Paulos and Ehadeg. Look at what you said again: “Then the churches in daispora preferred to stay out of the game, but firmly assuring that the holy synod of the church is in Ethiopia, “my goodness!! Are you saying that the Holy Synod can exist without a Patriarch? If you say yes. How can it be? You see! How foolish you are? Don’t be crazy, without a patriarch there is no synod or church. Take my advice, without accepting the holy synod of Ethiopia; saying that “the holy synod is in Ethiopia” it is meaningless. It is better to accept the synod which was established in the United States of America.
Before pointing your one finger at a person. Remember!! Three of your fingers are pointing at yourself. and do not forget what your forefathers had done? Believe it or not everything comes from Tigray or started in it. Without Tigray there is no Ethiopia. Ethiopia is Tigray and Tigray is Ethiopia,
May God bless you all
I am Belachew from Ethiopia

Anonymous said...

Selam brother Belachew, it is true Tigray is Ethiopia and without it there will not be Ethiopia.Do not try to picture me as if I said it otherwise and hate Tigray.That is the the tactic of eprdf.For true, no Ethiopian hates Tigray and the people.But we detest the stinky ethnic politics being implemented by some people born in that region,not by the whole Tgray population.Whenever epdrf is critcized for its wrong politics it changes the topic as though that criticism comes from those who hate Tigraians.This is the tactic of those handful cliques who try to get cheap support from the people.But it would have been better if they had taken lessons and correct their weaknesses.My brother, can you stop for a while and think? Atse Hailesilassie reigned almost 50 years,but he failed to correct some mistakes,handing over power to somebody.As a result, he paid the ultimate sacrifice.Mengistu did the same,and now also the people who have taken over their throne could not learn from their predecessors. Thus,the same will happen to them.I am happy we talked about this matter here on DS which one day, hopefully in the near future, we will refer to what we said.
Regarding you qusetions that if there could be a church without a patriarch.The answer is No,but we do not accept a patriach who does not care about his sheep,church and country.He who is not a voice for the voiceless,He who rely on gun.
As to the use of languages,I did not say Amharic is a divine language,and I believe that everybody is served well in his mother tongue.But this should not be the basis of division.Today's America has become like this prosperous and powerful because the people who came here from different parts of the world put first their country and unity. If the Norwegians said no to English,the German origins said the same,the French, the Japanese,the Spanish,etc all said no to English,they would have been like us,beggars! Don't you feel shame after 20 years of taking over the position of those who were blaimed for starving the people, now those in power do the same? Given the advancement of the day and time difference, the crimes perpetrated by present ones are actually worse than the formers.
Reminder:I have family members from Tigray too.So do not use that old fashion tactic because they are from this or that region.The people who say ethnic politics is dangerous and advocate the unity of Ethiopia,their references are those Emperors and Queens the majority of whom were from Tigray-from Abraha and Atsibeha to Yohannes the 4th. Unlike the present ones they were NOT narrow-minded ethnocentric leaders.
I said all these because the problems in our church can only be resolved if and only if the palace is also cleaned.We have recently witnessed that 'if the father is touched,the son is also touched.'

Unknown said...

“Abel,the undercover eprdf cadre,what ever you say we will not collaborate with enemies of our country and our church!We follow all dogma and sacraments of our church, Tewahedo,but we will not accept Aba Paulos and epdrf”.

ወንድሜ የኢ/ኦ/ተ/ቤ ዶግማ እስተቀበልን ድረስ ከእነ አባ ጳውሎስ ምንም አንድነት አይኖረንም ብለዋል። የእኔ ጥያቄ ደግሞ በዲያስጶራ ሚስጥራተ ቤተ ክርስቲያን እና ቀኖና ቤተ ቤተ ክርስቲያን እየተፋለሱ ናቸው። አውቀንም ይሆን ሳናውቅ ከሚጥራተ ቤተ ክርስቲያን እና ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ወጥተናል። የኢ/ኦ/ተ/ቤ የሚለው ስም ግን ይዘነዋል።

“የትኛው ሚስጥራተ ቤተ ክርስቲያን አፈለስን”? ብለውም ይጠይቁኝ ይሆናል። ይህም የአባባይ ሚስጥር ነው። ሁላችንም እንደምናውቀው ከሰባቱ ሚጥራተ ቤተ ክርስቲያን አንዱ ሚስጥረ ሜሮን ነው። ቤተ ክርስቲያናችን እስከ ቅርብ ግዜ ድረስ ከቅብጥ ወይም ከግብጽ መንበረ ማርቆስ ከሆነችው ቤተ ክርስቲያን እያስመጣች ትጠቀም ነበረ። አሁን ግን በራሷ መንበር ማፍላት ጀምራለች። ሜሮን የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ሊቃነ ጳጳሳት በአንድ ላይ ሆነው አፍልተው ለየ ሀገረ ስብከታቸው ይከፋፈላሉ። አዲስ ቤተ ክርስቲያን ሲታነጽ፣ ክህነት እና በቤተ ክርስቲያን ያሉት ንዋያተ ቅዱሳት የሚከብሩት በሜሮን ነው። በ40 እና በ80 ቀን ህፃናት ሲጠመቁ ማህተመ መንፈስ ቅዱስ የሚቀበሉት በሜሮን ነው። ቅዱሳን ሐዋርያት በአንድሮተ እጅ ፀጋ መንፈስ ቅዱስ ያሳድሩ እንደነበረ ቅዱስ ወንጌል ይነግረናል። ነገር ግን የአማኙ ቁጥር እየበዛ ሲመጣ በቅዱሳን ሐዋርያት እግር የተተኩ አባቶችህ ሚስጥረ ሜሮን እንደሰሩልን የቤተ ክርስቲያን ታሪክ ይነግረናል። ጳጳሳት ልክ እንደ ቅዱሳን ሐዋርያት ፀጋ መንፈስ ቅዱስ በአንብሮተ እጅ ማሳደር እንደሚችሉ ሐዋርያዊት ቤተ ክርስቲያናችን ታስተምራለች። ሜሮን ቄስ ለአዲስ አማኝ በጥምቀት ጊዜ ሲቀባ ልክ ጳጳሱ በአንብሮተ እጅ እንዳደረገው እንደሚቆጠር ቤተ ክርስቲያናችን በሚስጥራተ ቤተ ክርስቲያን ትምህርቷ ታስተምራለች። ሜሮን አይደገምም በጥምቀ ክርስትና ጊዜ ብቻ ይፈፀማል።

እኔ በምኖርበት አካባቢ 18 አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት እንደሚገኙ ባለፈው ፅሑፌ ላይ ገልጬዋለሁ። ከእነዚህ ውስጥ በግለሰዎች በአባ ኤገሌ ወይም በአቶ ኤገሌ የሚተዳድሩ ሲሆኑ፤ በየትኛወም መዋቀር ከሊ ቃነ ጳጳሳት ጋር አይገናኙም። መዋቅር እንኳ ባያገናኛቸው በግል ደረጃ ከጳጳሳት ጋር አይገናኙም። እንዲሁም “ገለልተኛ” ነን ከሚሉትም መሀከል በምንም ታምር ቤተ ክርስቲያናቸው ውስጥ ጳጳሳት ሊገቡ እንደማይችሉ ተናግረዋል። ታዲያ በእነዚህ እና በሌሎችም አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት ሚስጥራት ቤተ ክርስቲያን እየተፋለሰ አይደለም ብሎው ይገምቱ ይሆን?። መልሱን እርሶ ይመልሱት። እኔ እርሶ እንደሚሉት የአቡነ ጳውሎስም ሆነ የአቶ መለስ ፍርፋሪ ፈላጊም አይደለሁም። ነገር ግን ሐዋርያዊት፣ ጥንታዊት እንዲሁም ታሪካዊት ለሆነችው የኢ/ኦ/ተ/ቤ እድገቷን ከሚመኙ እንዲሁም ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ይጠበቅ ብለው ከሚጮሁ ወገን ነኝ።
አቤል ቀዳማዊ

Anonymous said...

Selam wendime Abel,just like you I also want to see our church united.But why do you think God turned away his eyes from us this long? Because, before His eyes we do not speak the truth.Abel could you write some points regarding what Aba Paulos failed EOTC? You see, as a true christian you should criticize all indifferently.I do not want our church remain like this nor do I blaim those who rejected irresponsible church leaders.What needs to be fixed is the cause of the problem.A certain disease cures only if the right medicine is used.And ofcourse it is martydom to refuse those who are guided by the spirit of the false messaih who is given power over ethnicity and language- see Revelation.It is this spirit that leads people in the palace now.And those who support and do not oppose this spirit of 'hasawi messih'should also be rejected.That is why they do not want correct their setbacks,rather sniff to avenge those who come up with a solution to problems in our church.
The realty:Under Eotc churches here in the US are not in any way better or different from those commonly called 'geleltegna'!Infact,in the services they give and number of EOTC followers they serve,the Geleltegnas are much better and have much bigger congregation.The same is true in obeying and violating the churche's sacraments- so called under eotc ones do not care about sacraments as long as they get supporters.99% of them are lead by people from the same region.This is true before GOD.
Concerning confirmation,some of those called under EOTC,conduct sevices in protestant and other denominations hall before the owners start their programs let alone to have churches blessed by confirmation.
Please write what you think Aba paulos's fault are and the very causes of such a mess in our church.May God enlighten your heart,and give you the courage to speak the truth.

Unknown said...

Dear my brother in Christ,here is some of the recent articles of mine about H.H Abune Paulos. Then gudge who am i? i am not supporter of him. My voice is to speak out the truth what i know about our Church. i am not said those the church 'under cover on EOTC' in USA only calling Abune Paulos name are not violeting church's sacraments,they are in the same spot to others. i will come soon by another articles of the truth what i believe about this Apostlic EOTC.

(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 18/2009)
(አቤል ዘቀዳማዊ እንደጻፈው)
እንግዲህ የዛሬው የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ የእናተው ዘገባ ካየሁ በኋላ፤ ከራሴ ጋር ብዙ ጥያቄዎች በማንሳት ተከራከርኩና ህገ ቤተ ክርስቲያንም ማገላበጥ ጀመርኩ ።
ከጥያቄዎችም መካከል፦
• የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የቤተ ክርስቲያኒቱን ሕግ ያውቁታል ወይስ አያውቁትም ?
• የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ያለባቸው ኃላፊነትስ በትክክል ተረድተውታል ወይ?
• ከዚህ በኋላስ ሊቃነ ጳጳሳቱ በምን ሞራል ነው ልጆቻቸው መባረክ የሚችሉት?
• ለቤተ ክርስቲያኒቱ ህግና ሥርዓት ተቆርቃሪዎች እውነተኞቹ ነገር ግን በቁጥር ትንሽ የሆኑት የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት እንዴት ከሕዝበ ክርስቲያኑ ጋር ሊገናኙ ይችላሉ?

እስቲ ቅዱስ ፓትርያርኩም ሆነ ብዙዎቹ የቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የማይቀበሉት ህገ ቤተክርስቲያን ስለ ፓትርያርክ ስልጣንና ተግባር ምን ይላል? ለዚሁ ጥያቄ መልስ ለማግኘት በራሳቸው በቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ተቀባይነት ያላገኘውን ህገ ቤተክርስቴያን ካነበብኩት ላካፍላችሁ
1. ፓትርያርክ ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ ነው (ሕገ ቤተክርስቲያን 1991)
2. ፓትርያርክ የቅዱስ ሲኖዶስና የቋሚ ሲኖዶስ ስብሰባዎችን ይመራል
3. በቅዱስ ሲኖዶስ መመሪያ ለብፁዓን ጳጳሳት የሊቀ ጵጵስና መዓረግ ይሰጣል
4. ለታላላቅ ገዳማት አበ ምኔቶችና በሀገረ ስብከቱ ለተመረጡ ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች የመዓረግ ስም ይሰጣል
5. ከቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጡና የተላለፉ ሕጎች፤ ደንቦች፤መመሪያዎችና ልዩ ልዩ ውሳኔዎች በተግባር መዋላቸውን ይከታተላል
የፓትርያርክ ከስልጣን መውረድስ ህገ ቤተክርስቲያን ምን ይላል?


ፓትርያርኩ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ከተሾመ በኋላ የተቀበለውን ኃላፊነት በመዘንጋት፦
• የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያንን ትምህርተ ሃይማኖት የሚያፋልስ፤ቀኖና ቤተክርስቲያንን የሚያስነቅፍ ተግባር ፈጽሞ ከተገኘ
• በፍትህ መንፈሳዊ አንቀጽ አምስት ከቁጥር 172 እስከ 208 በተደነገገው መሰረት በደለኛ ሆኖ ከተገኘ
• በኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በ1991 በወጣው ሕገ ቤተክርቲያን አንቀጽ 13 ንዑስ አንቀጽ ሰባት መሰረት በተሾመበት ቀን የገባው ቃለ መሐላ ያልጠበቀ እንደሆነ
በአጠቃላይ ታማኝነቱ፤መንፈሳዊነቱና አባትነቱ በካህናትና በምእመናን ዘንድ ተቀባይነት ያጣ ሆኖ ቤተክርስቲያንን የሚያስነቅፍ መሆኑ በትክክል ከተረጋገጠ ከስልጣኑ ይወርዳል። በሱ ምትክም ሌላ ተመርጦ ይሾማል። ፓትርያርክ እስኪሾም ግን ዐቃቤ መንበረ ፓትርያርክ ይመረጣል። የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ያወጣው ሕገ ቤተክርስቲያን 1996 አንቀጽ 16
ሕገ ቢተክርስቲያን ይህ ሆኖ ሳለ የአሁኑ ፓትርያርክ ከላይ የተጠቀሱት ህጎች ሁሉ እያፈረሱ፤ እኛም እያየነቸው የቅዱስ ሲኖዶሱም አባላት እያዩዋቸው እስካሁን ድረስ በዝምታ ታልፈዋል። ከዚ በኋላስ መፍትሔው ምንድ ነው? ተስፋ ቆርጦ መተው ወይስ ከጥቂቶቹ ለሕገ ቤተክርስቲያን ተቆርቋሪ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት ጋራ አይዞዋችሁ እኛም ከጎናችሁ ነን በማለት መስራት? መልሱን ለውድ ደጀ ሰላማውያን/ት በመተው አንድ ነገር ግን ላሰምርበት እወዳለሁ የኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን በፓትርያርክ ላይ ፓትርያርክ የሚል ህግም ደንብም የላትም።
እግዚአብሔር ተዋህዶ ሃይማኖታችን ይጠብቅልን!!! አሜን

(አቤል ወለቴ)
በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ሥር የሰደደውን የአስተዳደር ችግር ለማስወገድ ተጀምሮ የነበረው እንቅስቃሴ “ለመጨረሻ ጊዜ መፍትሄ ያገኝ ይሆን?” በማለት የተዋሕዶ ልጆች በያሉበ በተስፋ ሲጠባበቁት የቆየው የወርኃ ጥቅምት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ብዙዎቹም የተጠቀሱት ችግሮች መፍትሄ ሳይገኝላቸው በድጋሚ ለግንቦቱ ምልዓተ ጉባኤ አስተላልፎታል።

በሐምሌ ወር በአሜሪካ ድምጽ ሬድዮ እና በሌሎችም የሕዝብ ግንኙነት ጣቢያዎች እንደሰማነው ብፁዓን አባቶች ቅዱስ ፓትርያርኩ ላይ አንስተውት የነበረው መሠረታዊ ጥያቄ ተድበስብሶ ታልፏል። ይህንንም ጥያቄ ባነሱት ብፁዓን አባቶች ላይ ጥቃት ያደረሱት የቤተ ክህነቱ ተናካሾች ለፍርድ አልቀረቡም።

የቤተ ክርስቲያኒቱን ዘመንን ያልዋጀ ብልሹ እና ኋላ ቀር የአስተዳደር ችግር መፍትሄ ከማበጀት ይልቅ፤ የግለሰቦች ፀብ በማስመሰል አለባብሰው በይቅርታ አልፈውታል። ይቅር መባባሉ መልካም ቢሆንም መሠረታዊ እና መልስ ይሹ ለነበሩት የአስተዳደር በደል ጥያቂዎች ግን ምላሽ ማግኘት ነበረባቸው። ሚሊየነር ከሆነው ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጋር ተያያዥነት ያለው የብፁዕ አቡነ ሳሙኤል ጉዳይ ሶስት ሙሉ ቀን ፈጅቶ፣ ብፁዕነታቸውም ጊዜያዊ የሥራ መደብ አግኝተው፣ ችግሩም በዘላቂነት ሳይፈታ አሁንም ለግንቦቱ ምልዓተ ጉባኤ መተላለፉን ሰምተናል።
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ከሌሎች ሀገረ ስብከቶች በተለየ ሁኒታ በሕገ ቤተክርስቲያን ልዩ ትኩረት ተሰጥቶት ሕግ ቢቀመጥለትም ሕጉም በትክክል እየተተረጐመ አይመስልም። ሕገ ቤተክርስቲያን “የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤት በ1991 ዓ.ም ቅዱስ ሲኖዶስ ባወጣው ሕገ ቤተክርስቲያን አንቀጽ 35/ ንዑስ አንቀጽ 3 መሰረት የሚመራ የአስተዳደር ዐቢይ ኮሚቴ አለው። ዐቢይ ኮሚቴው በቅዱስ ሲኖዶስ ይሰየማል” ይላል።
የዐቢይ ኮሚቴው አባላት፦
• ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት የሚመረጡ ሦስት ሊቃነ ጳጳሳት ወይም ጳጳስት፣
• ከጠቅላይ ቢተክህነት ሶስት አባላት፣
• ከአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሚመረጡ ሦስት አባላት፣
• በድምሩ ዘጠኝ አባላት ይኖሩታል።
የዐቢይ ኮሚቴው ሰብሳቢ በቅዱስ ሲኖዶሱ ከተመረጡት ሊቃነ ጳጳሳት ወይም ጳጳስ ወይም የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ይሆናል። የዐቢይ ኮሚቴው የአገልግሎት ዘመን ሶስት ዓመት ሲሆን እንደ አስፈላጊነቱ የኮሚቴው አባላት በሙሉ ወይም በከፊል ለተጨማሪ ሦስት ዓመት ብቻ ሊመረጡ ይችላሉ። ዐቢይ ኮሚቴው ተጠሪነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ ይሆናል።
የተቀመጠው ሕግ ይህ ሆኖ ሳለ ቅዱስ ፓትርያርኩ ግን ሀብታሙን (ሚሊየነሩን) የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት “የራሴ ሀገረ ስብከት ነው” በማለት ፈላጭ ቆራጭ የአገዛዝ ክንዳቸው ሲሰነዝሩበት ይታያሉ።

Unknown said...

Continued....
(አቤል ቀዳማዊ ወለቴ)
(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 16/2009):- “የራሱን ሀብትና ማንነት የማያከብር ሕዝብና ተቋም በቁሙ የሞተ ነው” በሚል በነመራ ዋቀዮ ቶላ የቀረበውን ጽሑፍ ሳነብ ልቤ እጅጉን ተነክቷል። ይህንኑ የደጀ ሠላም ጦማሪ ሀሳብ መነሻ በማድረግ እኔም መጦመር እንኳ ባልችልም ስሜቴን ግን ለመግለጽ ብዕሬን ለማንሳት ተገድጃለሁ። ባለፉት 40 ዓመታት ቤተ ክርስቲያናችን የአስኳላውን ትምህርት ተምሬያለሁ በሚለው በማርክሳዊና በሌኒናዊ ትውልድ እጅጉን ተፈትናለች። እንዲሁም አሁንም ‘በተረፈ’ ኮሚኒስቶች እየተፈተነችም ትገኛለች።

ማርክሳዊ እና ሌኒናዊ ፍልስፍና ምንም እንኳ በየክፍለ ዓለማት የሚገኙት የእምነት ተቋማት በሙሉ (ከእስልምና በስተቀር) ፈተና ቢሆንም፤ እንደ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ግን የተፈተነ የለም። ሌኒን ተወልዶ ያደጉባት እንዲሁም ለዚሁ ፍልስፍና መሠረት የሆነችው ሀገር ሩሲያ ወይም ‘የሩሲያ ቤተ ክርቲያን’ እንኳን እንደ ኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አልተፈተነችም ቢባል ማጋነን አይሆንም። እንግዲህትውልዱን ለመውቀስ አቅሙም ችሎታውም የለኝም፤ ነገር ግን ታሪክ በራሱ ጊዜ ይወቅሳቸው ይሆናል። የዚሁ ጽሑፌ ዋና ዓላማ ግን ‘ተረፈ’ ኮሚኒስቶች ከቤተ ክርስቲያናችን ላይ በትራቸውን እንዲያነሱ ለማስገንዘብ ነው። ቤተ ክርስቲያን ይህንን ትውልድ በማጣቷ ለሁላችንም የእግር እሳት ቢሆንብንም አሁንም በዚሁ ዘመንም ቤተ ክርስቲያኒቱን ማሳደድ አለማቆማችውና እንዲሁም ደግሞ ሁለተኛ ትውልድ እንድናጣ እየተደረገ ያለው እንቅስቃሴ ግን የበለጠ ያበሳጨኛል።

ለመሆኑ ኮሚኒስቱ ትውልድ በኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያደረሰው ጥፋት ሳያንሰው አሁንስ ቢሆን ምን እያደረሰ ነው? እስቲ ከብዙ በጥቂቱ፦

1. በማርክሳዊና ሌኒናዊ ፍልስፍና የተዋጠው ትውልድ የቤተ ክርስቲያኒቱን ፓትርያርክ ጨምሮ አያሌ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያንን በግፍ ገድሏል፤ አስሯል፤ አሳዷል። በዚህም ብቻ አላበቃም። ቤተ ክርስቲያን ለብዙ ዘመናት ያፈራችውን ንብረትና ሀብት ወርሷል፤ በብዙ በገንዘብ የማይተኩ ንዋያተ ቅድሳት ዘርፏል።

2. የቀድሞው የቤተ ክርስቲያኒቱ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ከመንበራቸው እንዲወርዱና እንዲሁም ከወረዱ በኋላም ከሀገር እንዲሰደዱ አድርጓል። የመጀመሪያው ኮሚኒስት የደርግ መንግሥት ፓትርያርኳን በግፍ ገደለ፤ሁለተኛውና ወይም አሁን ያለው ኮሚኒስቱ መንግሥት ደግሞ ፓትርያርኳን ከመንበራቸው እንዲወርዱ አደረገ። እንግዲህ ቅዱስ ፓትርያርኩ ከመንበራቸው ከወረዱ በኋላም ተቀማጭነቱ ሀገረ አሜሪካን ያደረገው ሌላኛው ኮሚኒስት ቡድን ደግሞ ቅድስት ሀገራቸውን ጥለው እንዲሰደዱ አድርጓቸዋል። ከተሰደዱ በኋላም የራሳቸው ሲኖዶስ እንዲያቋቁሙና ቤተ ክርስቲያኒቱ ለሁለት እንድትከፈል እዚሁ አሜሪካን ሀገር ያሉት ‘ተረፈ’ ኮሚኒስቶች በአማካሪነትና በዋና ተዋናይነት አስተዋፅዖ አድርገዋል።

3. አሁን በሥልጣን ላይ ያለው ‘ተረፈ’ ኮሚኒስት ቡድን ቤተ ክርስቲያንን ማሳደድ አላቆመም። ባለሥልጣናቱ ቤተ ክርስቲያን የሌላትን ተቀጽላ ስም እየሰጡ “የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የነፍጠኞች ዋሻ ናት” በማለት ሲያንቋሽሹ ሰምተናቸዋል። እንዲሁም ልጆቿዋ በተለያዩ አካባቢዎች በአክራሪው የእስልምና ቡድን በግፍ ሲታረዱባት ተገቢውን ፍርድ ሳያገኙ ቤተ ክርስቲያንን “ምንም አታደርገንም” ብለው በዝምታ አልፈውታል። እነዚህ ኮሚኒስት ባለሥልጣናት በዚህ ብቻ አላቆሙም። ቤተ ክርስቲያን ለኢትዮጵያ ያበረከተችውን በርካታ አስተዋጽዖ ወደ ኋላ በመተው ባገኙት አጋጣሚ ሁሉ ለኢትዮጵያ ድህነት ቤተ ክርስቲያንን ተጠያቂ ሲያደርጉ እንሰማቸዋለን።

4. ይኸው ኮሚኒስቱ ትውልድ በውጪው ዓለም በተለይም በአሜሪካን ሀገር ቤተ ክርስቲያን ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን ውጪ እንድትመራ አድርጓል። ቤተ ክርስቲያን ያስቀመጠችውን ከራሷ ቀኖና ወይም ‘ከሰበካ ጉባዓኤ አስተዳድር’ ውጪ ቦርድ የሚል ስያሜ በመስጠትና እንዲሁም ገለልተኛ አስተዳደር በሚል ተቀጽላ ቤተ ክርስቲያን እንዲቋቋም አድርጓል። ይህም ብቻ አይደለም ኮሚኒስቶቹ በባለቤትነት የሚያስተዳድሩት የግላቸው ቤተክርስቲያንም አቋቁመዋል።

ከላይ እንደጠቀስኩት አሁንም በድጋሚ መጥቀስ የምፈልገው የዚህ ጽሑፍ ዓላማ እነሱን ለመውቀስ አይደለም። ነገር ግን የዚሁ ፍልስፍና ተዋናዮች እያወቁም ሆነ ሳያውቁ እያደረጉት ያለውን ጥፋት እንዲያቆሙ ለመማፀን ነው። በስደት ላይ የሚገኙትም ‘ተረፈ-’ኮሚኒስቶች ጥንታዊቷንና ሐዋርያዊቷን ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያዊ ተልዕኮዋን በይበልጥ እንድታስፋፋ እንቅፋት ከመሆን እንዲቆጠቡ እለምናችኋለሁ።
ቸር ወሬ ያሰማን፣

Anonymous said...

Selam Abel, now you mentioned the true causes of the mess.what do you think the solution may be then?
I think those who disobey the church's and/or synod's decisions should be rejected. That is what has happened in the daispora.If the laity of EOTC at home also get freedom like we have here,the majority of them do not want his name be mentioned just like us, not because he is from Tigray,but he is not for the church and supporting what the Ethiopian people hate-ethnic politics .But he has the gun and gun bearers on his side.That is exactly what has happened in the recent meeting between MK and him.
Lets all unite in every way to free our church and our country.

decon mezegabu said...

my name is decon mezegabu, i like to give a comment about so colld a charch problem. i do not think our ortodox are in problem i think people are making thire owen opinion about it. Firest of all it is important to know where the problem started.wyane came and change the church low as the country fluge and sovernty lan. as true ortodox chrstina and a s a true follower of dogma and canone low we say no this is aginest our blive we like to keep our patriric as connon law says. to be with ethiopians or to be with wayne is up to the indeviduals, but history will juge evry body. now p/s do not give your own understanding just follow the canone low as ortodox. regarding synodos in exele we do not call synod in americ thats wynes system to confuse people. we call it the legetmet ithiopian ortodox holy synod.we say this becouse theire is un legtment one in addis ababa by force. thank you all. from canada.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)