December 19, 2009

የህንድ ቤተ ክርስቲያን ለእኛ ምሳሌ መሆን ትችላለች?

(አቤል ቀዳማዊ)
አንድ አባት በምገለገልበት አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን በመድረክ ቆመው የህንድ ቤተ ክርስቲያንን እድገት ምሳሌ እየጠቀሱ ስለ እኛ ቤተ ክርስቲያን እድገት ሲያስተምሩ በጥሞና ተመስጬ እያደመጥኩ አእምሮዬ ወዲያው ጥያቄ አቃጨለብኝ “የእኛ ቤተ ክርስቲያንስ የት ናት”?። እኚሁ አባት ስለምግባባቸው ከመድረክ በኋላ ጥያቄም አቀርብኩላቸው። “ለመሆኑ ዛሬ የተማርነው ትምህርት ለእኛ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን ይመለከታታል ወይ?፤ እርሶ እንዲቴት የህንድ ቤተ ክርስቲያንን በምሳሌነት ሊጠቅሷት ቻሉ”? ብዬ በትህትና ጥያቄዬን ሰነዘርኩ። እሳቸውም “ልጄ ምን ማለትህ ነው?፤ የህንድ ቤተ ክርስቲያን እኮ ከቤተ ክርስቲያናችን ጋር እህት ናት፤ ስለዚህ የህንድ ቤተ ክርስቲያን እድገት ለእኛ ቤተ ክርስቲያን ትልቅ ምሳሌ መሆን ትችላለች” አሉ። ጥያቄን በፈለኩት መልኩ ስላልመለሱልኝ በድጋሚ ማብራራት ጀመርኩ። የህንድ ቤተ ክርስቲያን በዲያስጶራ አገልግሎቷ ከኛ ቤተ ክርስቲያን ጋር ሲነፃፀር በእድሜ ብታንስም አንድነቷን ጠብቃ በመጓዝ፤ ሐዋሪያዊ ተልኳዋን ዘመኑን በዋጀ መልኩ እየፈፀመች ነው።


እንደውም በሰሜን ምስራቅ አሜሪካ ሀገረ ስብከት ድህረ ገፃቸው ላይ “The American Diocese of the Malankara Orthodox Syrian Church is located in the United States. It is the sub-wing of the Malankara Orthodox Syrian Church in India” ይላል። ጥያቄዬ ‘እርሶም ሆነ እኔ ያለንበት አጥቢያ ገለልተኞች ነን፤ የእነርሱ ግን የሰሜን አሜሪካ ሀገረ ስብከታቸው ህንድ ካለው ቤተ ክርስቲያን ጋር በአንድ ሰንሰለት የተያያዘ ነው። አንድ በሆነ የአስተዳደር መዋቅር ሀያ ስድስት ሀገር ስብከት አላቸው። እናም አሁን እኛ ገለልተኞች ስለሆንን በየትኛው መዋቅር ተገናኝተን በአጠቃላይ ቤተ ክርስትያናችን የህንድ ቤተ ክርስቲያን የደረሰችበትን ለመድረስ መስራት እንችላለን’? ብዬ በድጋሚ ጥያቄን አቀረብኩላቸው። “ልጄ የህንድ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ጎበዞች ናቸው፤ ሁለት ሆነው አንድ ቤተ ክርስቲያን ይሰራሉ የእኛ ምዕመናን ግን ይኸው ከሺ በላይ ነው፤ እቺን ቤተ ክርስቲያን መስራት አቅቷችኋል ለዛም ነው፤የህንድ ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ያመጣሁት” ብለው መለሱልኝ። ጥያቄዬም ሳይመለስልኝ ተሰነባበትን።
ለመሆኑ ቤተ ክርስቲያናችን አሀት አብያተ ክርስቲያናት የደረሱበት ደረጃ የምትደርሰው መቼ ነው? ይህ የሁል ግዜ ጥያቄዬ ነው። በትንሹ እንኳ ስለ ኢ/ኦ/ተ/ቤ መረጃ ለማግኘት በእንግሊዘኛው “ehtiopian orthodox church” ብለን ጎግል ስናደርግ የምናገኘው በአንዳንድ ግለሰዎች የሚዘጋጁ ድህረ ገፆች እናገኛለን። ከእነዚህም ከምናገኛቸው ድህረ ገፆች አንዳንዶች ለቤተ ክርስቲያን እድገት ተቆርቃሪዎች እንዲሁም ወንጊልን ለዓለም ለማዳረስ አለም የደረሰችበትን ጥበብ በመጠቀም የሚተጉ ወገኖች ቢኖሩም፤ አንድንዶችሁ ደግሞ ከቤተ ክርስቲያኒቱ አስተምሮ ውጪ የቤተ ክርስቲያናችን ስም ይዘው የሚዘግቡም አሉ። የዚህ ጽሁፌ ዓላማ እነሱን መተቸት አይደለም ምክንያቱም እኔ ምንም አልሰራሁምና፤ የሚሰራ ሰው ደግሞ ስህተት አያጣም ከስሀተታቸው እንዲታረሙ ግን ከማሳሰብ ወደ ኋላ አልልም።
ቤተ ክርስቲያናችን እንደ ሌሎች እህት አብያተ ክርስቲያናት ዘመኑንን በዋጀ መልኩ ወንጌልን ለዓለም የምታሰራጭበት እንዲሁም ስለ ቤተ ክርስትያናችን ሙሉ መረጃ የሚያሳይ የመረጃ መረብ መቼ ይሆን የምትዘረጋው?። መቼ ነው ቤተ ክርስቲያናችን ወንጌል ያላመኑትን በማሳመን “የዛሬ አምስት ዓመት ወይም የዛሬ አስር ዓመት የምዕመናን ብዛት በዚህ ያህል ቁጥር ማደግ አለበት በማለት የምታቅደው? ወይስ በየ መድረኩ እንደ ቅዱስ ፓትርያርኩ ቤተ ክርስቲያን ከልማት ጎን መሰለፍ አለባት ብቻ እያለች ልትኖር ነው። መልሱን ለእናተ ትቼዋልሁ።


3 comments:

Kalahawaryat said...

Dear my friend in Christ

Is that priest or monk priest who taught you this, working by keeping the rules and regulations of the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church? If not how could He dare to say that? But if that priest serving the church by following the canon of the holy synod of the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church, you are in the right truck. What do we have to know is this; the church which is established in the United States of America is founded by the politicians. The monk priests and priests are hired by them. As long as they are hiring, they do not have any power or authority to lead the church according to the rule and regulation of the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church. What should we do now? We have to ask the priest and monk priest to make reconciliation with mother church.. Otherwise ,they have to stop acting as priest and monk priest inside the church. Believe it or not 90% percent of the monk and priest are not called to be . . . .. anyway the holy bible says do not judge, you will be judged

Thank you for good comment

This Kalehawaryat

መልአከ ሳሌም አባ ገብረኪዳን እጅጉ said...

ሰላም ለደጀ ሰላም ታዳሚዎች በሙሉ አቤል ቀዳማዊ እንደ ዘገበልን አንድ አባት የህንድ ቤተ ክርስቲያን ለኛ ምሳሌ መሆን ትችላለች ብለዉ በመናገራችዉ ምክኒያት በተነሳ ጥያቄ እኒሁ አባት ሲመልሱ “ልጄ የህንድ ቤተ ክርስቲያን ምዕመናን ጎበዞች ናቸው፤ ሁለት ሆነው አንድ ቤተ ክርስቲያን ይሰራሉ የእኛ ምዕመናን ግን ይኸው ከሺ በላይ ነው፤ እዲት ቤተ ክርስቲያን መስራት አቅቷችኋል ለዛም ነው፤የህንድ ቤተ ክርስቲያን ምሳሌ ያመጣሁት” ብለው መለሱልኝ። ጥያቄዬም ሳይመለስልኝ ተሰነባበትን።ብሎአል ላባታችን እኔም አንድ ሀሳብ ልጨምር በማንኛዉ ሕብረታችን ነዉ እነደ ህንዶች የምንሆነዉ በዋሽግተን ዲሲ እና አካባቢዉ እንኳን ከ11 ያላነሱ አብያተ ክርስቲያናት አሉ ነገር ግን እነደ ዘመነ መሳፍንት ሁሉም የራሱን ግዛት ነዉ የሚያስፋፋዉ እነጂ ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አንድነት ግን ሁላችንም እየሰራን አይደለም ቢሆንማ ኑሮ 11 አብያተ ክርስቲያናት ከማቋቋም ይልቅ አንድ ትልቅ እነደ ቦሌ መድኀኔዓለም ያለ ቤተ ክርስቲያን ሠርተን በቀሪዉ ገንዘብ ትምህርት ቤት፣ ሆስፒታል ገንብተን ሕዝባችንን እነደሌሎች ሀገር ሰዎች በረዳንበት ነበር መች አደለን እና አሁን አሁን እማ ሁሉም ሲያኮርፍ ቤተ ክርስቲያን ነዉ የሚከፍተዉ ላምልኮት ሳይሆን ለመነገጃ እግዚኦ እግዚኦ የሚአሰኝ ነዉ። የኢትዮጵያ ሕዝብማ እነኳን ገንዘቡን ሕይዎቱንም ይሰጣል በአባቶቹ በኩል እምነት እያጣ ነዉ እነጂ ያሁሉ ከ35000በላይ አብያተ ክርስቲያናት የታነፁት በዚያ ደግና ድሀ በሆነ ሕዝብ ነዉ የተሠራዉ ብለህ ንገርልኝ ወንድሜ አቤል ዘቀዳማዊ።
ችር ይግጠመን አሜን

Anonymous said...

Selam readers.
The main issue intended in the above article is to start discussion about unity of our church,I believe.So here is the reality in my perspective.
In essence our Tewahedo church is not divided.But some people and historical enemies of this church say that it is divided like the one church was divide in the early 4th century.This is not true.The truth is our church has faced a number of challenges emanated from the present political conditions in Ethiopia and thirst for power among our 'holy' fathers.And hence, division has been created among these fathers quarreling for power,not one Tewahedo is divided.Why is that,therefore,all these bad wishes for this Apostlic church? The evil aspiration comes from three sources.
1.Heresies 2.The ruling class
3.power thirsty 'fathers' and accomplices
The present choas in our church has paved the way for heresies a good opportunity to carry out their long awaited plan of reevangilization of Ethiopian christians in to their teachings destined for absolute denial of the Almigthy GOD.A case in point is the acceptance of gay pastors in their congregations,and the descending number of faithfuls in their churches.But these so called churches increase their congregation in Ethiopia taking advantage of the situation in our church; as confused and shepherdless laity is easy prey to its predators. The life of the Ethiopian people purposely being driven in to coagmire of misery by the political leadership has also contributed a lot to the fulfilment of undercover NGOs' whose very objective is a religious one. Therefore,exaggerating the disagreements in our church,these in and out historical enemies of Tewahedo are benefitting from the situation.
2.The old method of divide and rule is not old in Ethiopia.In order to prolong its survival in power the ruling group is exploiting the opportunity to its advantage.Thus, this loud cry about a divided church is a deliberate act by people in power to create confusion and buy time.They infiltrate their accomplices and divide the people wherever there is a strong unity and opposition to these ethnocetric minded poor creatures.
3.Those politically affilated 'fathers' also play the same game as the political gamblers do.They condemn this and that person and organization which is not accepting their irresponsible leadership of the church.
When we examine our churches in the daispora, except those who established a pseudo synod,the rest fall in the same category but one thing different.And it is this one thing that makes them under the mother church or outside of it/independent/. But,as far as I know,and I had a chance to visit most of the churches here in the US,they are all led by board of trustees or sebeka gubae in which both of them are basically the same.They both do not follow the church's 'kalawade'/by-law.Both believe that the holy synod of the church is in Ethiopia and reject the pseudo synod led by the former patriarch.The only difference is one thing-mentioning and not mentioning Aba Paulos's name during liturgy.From religious point of view both sides have convincing argument.However,this name calling or not calling should not be the criterion to say this church is under the synod and that is independent.My understanding of independent means: not siding with those in church leadership who are not protecting the church,who are quareling for power,who are not carrying out their duty of shepherding their sheep,who are not voicing for the voiceless when they are murderd and watch carelessly the disintegration of Ethiopia along ethnic lines,etc...Therefore,when we talk about unity and division we should know first where the confusion come from and look at it critically if it true or not.I believe,so far there is not religious division but confusion created to cover up unorthodox practices in our church.
TEWAHEDO REMAINS UNITED AS IT IS ESTABLISHED WITH THE BLOOD OF OUR SAVIOUR-JESUS CHRIST.

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)