December 14, 2009

ትውልደ ኢትዮጵያዊው ፓኪስታን ውስጥ በሽብርተኝነት ጥርጣሬ ተያዘ

(ሪፖርተር):- የአሜሪካ ዜግነት ያላቸው ሁለት ትውልደ ኢትዮጵያዊ እና ኤርትራዊ ፓኪስታን ውስጥ በሽብርተኝነት ተጠርጥረው ተያዙ፡፡ ረቡዕ እለት ፓኪስታን ውስጥ የተያዙት የዋሽንግተን አካባቢ ነዋሪዎች ባለፈው ወር ከአሜሪካ መሰወራቸውን የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል፡፡ በሃያዎቹ የእድሜ ክልል የሚገኙት እነዚሁ አምስት አሜሪካውያን ወደ ፓኪስታን ያቀኑበት ምክንያት ገና በመጣራት ላይ በመሆኑ በወጣቶቹ ላይ እስካሁን ምንም ዓይነት ክስ አልተመሠረተባቸውም፡፡

የአሜሪካው የፌዴራል ምርመራ ቢሮ አባላትና በፓኪስታን የአሜሪካ ኤምባሲ ባለስልጣናት ዓርብ ዕለት እነዚሁኑ አምስት አሜሪካውያን በታሰሩበት እንዳነጋገራቸውም ተገል..ል፡፡

ከአምስቱ አንዱ ትውልደ ፓኪስታን አንደኛው ደግሞ የግብፅ ትውልድ እንዳለውም የዜና ምንጮቹ ጠቁመዋል፡፡ አምስተኛው ታሳሪ የየመን ትውልድ እንዳለውም ተገል..ል፡፡

ሁኔታው በአሜሪካ ቁጥሩ የበዛ አገር በቀል የሽብር እንቅስቃሴ ተስፋፍቶ እንዳይሆን ስጋት ፈጥሯል፡፡ እስካሁን በተገኘው መረጃ ኢትዮጵያዊ ትውልድ አለው የተባለው ተጠርጣሪ አማን ሃሰን ይመር በመባል እንደሚጠራ የአሜሪካና የፓኪስታን ደህንነት ክፍሎች መግለፃቸውን የዜና አውታሮች ዘግበዋል፡፡

እንደ ፓኪስታን ደህንነት አባላት አገላለፅ አሜካውያኑ ከአክራሪ ቡድኖች ጋር ግንኙነት ለመፍጠር የተለያዩ ድረ ገፆች ላይ ሙከራ ቢያደርጉም ጥረታቸው ባለመሳካቱ በቀጥታ ፓኪስታን ውስጥ በመግባት ምኞታቸውን ሊያሳኩ እንደሞከሩ ይጠረጠራል፡፡

ወደ አሜሪካ መልሰው ስለመላካቸው ወይንም ደግሞ እዚያው ፓኪስታን ውስጥ ለፍርድ ስለመቅረባቸው የሚወሰነው በመካሄድ ላይ ያለው ምርመራ ሲጠናቀቅ መሆኑንም የፓኪስታን የደህንነት አባላቱ አሳውቀዋል፡፡

27 comments:

Kalehawaryat AA said...

በጣም አሳዛኝ ነው። የሚያሳዝነውም የንጹሐን ሕይወትና የራሳቸውን ሕይወት እያጠፉ ባሉት ወገኖች ነው። በሰከነ መንፈስ ከተመለከትነው እነዚህ ወገኖች በተሳሳተ መንገድ ሰውን አጥፍቶ መጥፋት ዋነኛ የመንግሥተ ሰማያት መግቢያ መስሎ ስለታያቸው ነው። በመሆኑም በእጅጉ ሊታዘንባቸው ሳይሆን ሊታዘንላቸው ይገባል። ዛሬ በስልምና ስም የተሸፈኑ የጽንፈኞ አክራሪዎች አስተምህሮ ይህ ነውና። በዚህ ድርጊት የተሰማሩ የአክራሪ ሙስሊሞች ተከታዮች ወጣቶች አንድ ነገር ይጠብቃሉ ይህም “አንድ ወጣት በተሰጠው ግዳጅ አጥፍቶ ከጠፋ በገነት የወንድ የማያውቁ 70 ደናግል ይጠብቁታል። በዚያም ማሪ፡ ወተትና ዋይን እየጠጣ ይኖራል” የሚል አጉልና ሰይጣናዊ ተስፋ ነው። ለዚህም “ Where is Heaven? Who might be there? “ By Barbera Walttr: የሚል የተሰራጨው ፊልም መመልከት በቂ ነው። ስለዚህ እነዚህ ወገኖችን ከዚህ እኩይና ሰይጣናዊ ድርጊታቸው እንዲመለሱ ከሁሉም በፊት የሙስሊሙ ሕብረተ ሰብ ሊታጋና ሊታገለው ይገባል። እላለሁ። ይህ የምለውም ሁሉ ሙስሊሞች ይህን ሽብር እንደማይደግፉት ስለምረዳ ነው። እባካችሁ እንጸልይላቸው። በነገራችን ላይ አንድ ነገር ላሳስባችሁ። ሰውን ያለ በደሉና ያለ ኃጢአቱ በቦም ሐሰትና ሐሜት ማጥፋትም ነፍሰገዳይነት ነው። በተለይ ክርስቲያን የሆነ ሰው የበደለና ኃጢአት የሠራ ሰው ብናውቅም ከኃጢአቱና ከበደሉ እንዲመለስ ማስተማርና መምከር እንጂ ማሳደድና ማሳጣት አይፈቀድለትም።፡ ተመክሮ የማይመለስ ግን በሕገ ወንጌል ምክንያት በይፋ ከማህበረ አማንያን ይገለላል። ለሁሉም ልዑል እግዚአብሔር ዓይነ ልቡናችንን ይክፈትልን።፡ አሜን!!!!!!!!!

ቃለ ሐዋርያት ነኝ ከአዲስ አበባ

Estifanos usa said...

I thank you very much Kalehawaryat. I like the way you always post on this site. By the way, I have the documentary film presented by Barbara Waltters. I strongly recommended to you all to watch the documentary film. You can find it in Google. Search it saying “ Barbara Walters on heaven - Beliefnet.com

Once again thank you for your good advice

Berhanu said...

ገና ምኑ ታይቶ ምኑ ተሰምቶ፡ የአይስበርጉ ጫፍ ነው የሚታየን። እውነቱን አስተምሩ እናስተምር ጊዜው እንደ ዱሮው እንዳይመስለን፡ የእስልምና ተከታዮች አይን አውጣ ሆነዋል፡ ይህም ክኛ ስንፍናና ድካም የተነሳ ነው። እስከ መቼ ታግሰን እንዘልቀዋለን? የመቀስቀሻው ደውል ሃቁን ያለ ይሉኝታና ፍርሃት በመናገር ሊደወል ይገባል።

Anonymous said...

by Ethio-Muslim

እንደምን አላችሁ ወገኖች

አጥፍቶ መጥፋት ማለት ምን ማለት ነው?
ሙስሊሞች አይን አውጣ ሆነዋል ማለት ይሰግዳሉ ይጾማሉ ካልሆነ በስተቀር ምን ለማለት ተፈልጎ ነ?
በገነት 70 ሚስት ታገኛላችሁ ሰለተባልሉ ነው አጥፍተው የሚያጠፉት የሚለውን ከየት አመጣችሁት?
የማንኛውም ሰው ሃሳብ ወደራሱ ነው የሚመለሰው።
እስኪ በተቻላችሁ መጠን የሚመለከታችሁን ነገር ብቻ ለመስራት እና ለመናገር ሞክሩ።

ቃለ ህይወት፦
ስለ እስልምና ብታውቅ ኖሮ በዚህ መልኩ አትሳለቅበትም ነበር
በአሁኑ ጊዜ በአለም ላይ ከ 4 ሰው አንዱ ሙስሊም ነው።ይህም ዝም ብሎ በዘፈቀደ አይደለም።
ኢስላም እና ሙስሊሞች ይህን ያክል ጫና በ እስራኤል እና በአሜሪካ እየተደረገባቸው የ እስልምናን እድገ ልብ በልህ ተመልከት።አስፈካጊም ከሆነ አንብብ።
እናንተ ከ ትናንት እስከ ዛሬ ስንቴ እምነታችሁን ቀይራችሁ ይሆንናል።እስኪ ከጊዜያችሁ ወስዳችሁ ስለ ኢስላም ትንሽም ቢሆን አንብቡ።
ጭፍን ጥላቻ መጨረሻው ጸጸት ነው ያውም ጸጸት በማይጠቅምበት ጊዜ።
ሠላም ሁኑ
ኢትዮ ሙስሊም

Orthodox Unit said...

ወንድም ኢትዮ ሙስሊም፡
ቃለ ሐዋርያትን ተገንዝበኸውም ይሆናል ወይም አልገባህም ይሆናል። እርሱ እንዳለሁ ሁሉ እኛ እናንተ እንዲህ ስላደረጋችሁ ታሳዝኑናላችሁ እንጂ በገደልናቸው የሚል አቋምም ሆነ አላማ የለንም። ጠላትህን ግን ቢራብ አብላው ቢጠማም አጠጣው ትላለችና ወንጌል። ክርስቲያኖች በተለይም ኢትዮጵያውያን በሰላምና በፍቅር ለመኖር መቸም ቢሆን እጃቸው የተዘረጋ ነው። አሁንም የሚጠቅመው ህዝባችንን በፍቅርና በሰላም ማኖር ነው። በትክክል እናማማር ከተባለ ደግሞ ምንም ችግር የለውም ቁራንንና መሐመድን በትክክል አውቀናል ዘመኑ የመረጃ ዘመን ነው። በየትም ሄዳችሁ የሐሰት ትምህርት ይዛችሁ ልትዘልቁት አትችሉም። ያለው አማራጭ ሁለት ነው።
የቁራንን የተሳሳተ ትምህርት ትቶ ህይወትና መድሃኒት ወደ ሆነው ኢየሱስ ክርስቶስ መምጣት
ወይም በዚያው ሰይፍ እንደመዘዛችሁ ወደ ገሃነም መውረደ

እኛ ክርስቲያኖች ወንድሞቻችን ለድህነት ሳይበቁ እያየን እንዲሁ ማለፍ በጣም ያሳዝነናል ሆኖም እናንተ ደግሞ እንኳን እናስተምራቸሁ ተብላችሁ ሰይፋችሁ አይጣል ነው።
ወደ እርእሱ ስመጣ ይህ ልጅ በዚህ በልጅነት እድሜው ወደዚህ ወደ ሞት ህይወት የመራው መቸም ሃይማኖቱ እንደሆነ ግልጽ ነው።ስለዚህ ኢትዮጲያውያን እሳሞች ቢያንስ ወደዚህ የተሳሳተ የአክራሪነት ስራ እንዳይገቡ ልጆቻቸውን ሊመክሩ ያስፈልጋቸዋል። በጅሓድ አምላክ አይገለገልም፤ ሀገር አይበለጽግም፤ ሰላም አይገኝም። በተለይም ደግሞ ይህንን የሚያደርጉ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ከተበራከቱ ኢትዮጲያ ውስጥም አሸባሪ የማይሆኑበት ምክነያት አይኖርም ጊዜውና ሰዓቱ ከተሳካላቸው።
እና ሙስሊሞች እባካችሁ ከማነኛውም አካል የተሻለ አክራሪነትን መከላከል የምትችሉት እናንተ ስለሆናችሁ አስቡበት ተወያዩበት። በእየመስጊዶቻችሁ የክርስትናን ሃይማነት እንዲህ እንበል በማለት ጊዜችሁን ከማባከን የራሳችሁን ሰዎች ከአሸባሪነት ለማዳን ስሩ።

ሰላም ሁኑ

Kalehawaryat said...

by Ethio-Muslim
ብለህ ላቀረብከው ወገኔ በተፈጥሮ።
ለላም ላንተ ይሁን።
ቃለ ሐዋርያት ነኝ።

በደጀደሰላም ብሎግ ላይ በቀረበው ሐሳብ፡ በማያሻማ ሁኔታ ትክክለኛ መረጃ ባለው መልክ የዓለማችን የራስ ምታት የሆኑትንና አብዛኛውን የሙስሊሙ ሕብረተ ሰብ እየኮነናቸው የሚገኙትን የአጥፍቶ ጠፊ ዓላማና እነርሱን እያሳሳቱ ስለሚገኙ አክራሪ ሙስሊሞች በተመለከት ባቀረብኩት ሐሳብ ቅር እንደተሰኝህ ከጽሑፍህ ለመረዳት ችያለሁ። ይህ ብቻ ሳይሆንም ጥያቄም አቅርበሃል። ወንደሜ አንተ ራስህ የዚህ በሽታ ተጠቂ ካልሆንክ በስተቀር ባቀረብኩት ሐሳብ ትደሰት ነበርክ እንጂ ማዘን አይገባህም ነበር። እንዳንተ እምነት መላው ሙስሊም ሕብረተ ስብ የ እነዚህን ዓላም ይደግፋል ካልከኝ፡ በሚቀጥለው ልመልስልህ እችላለሁ። ይሁን እና ወዳነሳኸው ጥያቄ ለመልስ”አጥፍቶ መጥፋት ማለት ምን ማለት ነው?”ላልከው እንደ እኔ እምነት ይህ ተርጓሜ የሚያስፍልገው አይምስለኝም። አጥፍቶ መጥፋት ማለት ፡ ሌላውን ገድሎ ራሱን መግድል{ ማለት ነው፡ ስለ አገሩ ስለ ሕዝቡ የሚዋጋና ራሱን መስዋእት የሚያደርግ ማለት አይደለም። መቸም ሰው ስለ ሃይማኖቱ ሰውን ይገድላል እንደማትለኝ ተስፋ አደርጋለሁ። ከተስማማህ ግን ባርባራ ገነት ወይም መንግሥተ ሰማይ የት ናት በማለት Barbara Waltter Where is Heaven ዋልተር ቃል በቃል በኢየሩሳሌም ከፍልስጢኤማውያን አጥፍቶ ጠፊዎች ያደረግችውን ቃለ መጠይቅና ከሙስሊም ሙሑራን ያደርገችውን ውይይት ሰምትህ ትስማማልህ ማለት ነው። ሌላው በጽሑፌ ሙስሊሞች አይጾሙም አይሰግዱም የሚለውን አላነሳሁም። ርእሱም አይድለም። “በገነት 70 ሚስት ታገኛላችሁ ሰለተባልሉ ነው አጥፍተው የሚያጠፉት የሚለውን ከየት አመጣችሁት?” ላልክው ፡ ወንደሜ ኢትዮጵያዊ ከሆንክ ምናልባት ያቀረብከው ጥያቄ ከቅንነት ተነስተህ ይሆናል። ምክንያቱም የዓረብኛ ቋንቋ ያስቸግርህ ይሆናል ብየ አምናለሁ። ወይም ደግሞ እንዳልኩት ይህንን ጥፋት ከማይደግፍ የሙስሊም ሕብረተ ሰብ የተወለድክ ትሆናለህ። ነገር ግን በአነጋገርህ ደግሞ እንደሰማህና እንደምታምንበት ትመስላለህ። ያም ሆነ ይህ፡ ዋቢ ያደርጉልህን መረጃ እባክህ ተመለከት፡ ሰምትህ ካላመንክም እግዚኦ!! የሚያሰኝ መረጃ እስከማቀርብልህ ድረስ አስተማሪዎችንህ ጠይቃቸው። ይነግሩህ ይሆናል። ውድ ወገኔ በሌላ በኩል፦“ቃለ ህይወት፦ስለ እስልምና ብታውቅ ኖሮ በዚህ መልኩ አትሳለቅበትም ነበር” ላልከው እኔ በእስልምና ፈጽሜ አልተሳለቁም። ባሕሪዬም አይደልም። በጽሑዬም በሚገባ ለይቼ ነው ያስቀመጥኩት። ስለ እስልምና ግን በእርግጠኝነት ልንገርህ ከአንተ በበለጠ አውቃለሁ። ስለ እስልምና ብቻ ሳይሆንም በዓለም ላይ ሰላሉ ሃይማኖቶችም በሙሉ አውቃለሁ ብልህ ማጋነን እንዳይምስልህ። ፈቃድህ ከሆነ ሰለ ቁርዓንና እስላማዊ ትውፊቶች በሙሉ በየጊዜው ለጽፍልህ እችላለሁ። ብቻ ይሁን በለኝ። “በአሁኑ ጊዜ በአለም ላይ ከ 4 ሰው አንዱ ሙስሊም ነው።ይህም ዝም ብሎ በዘፈቀደ አይደለም “ በለሃል። አዝንልሃለሁ በዝተናልና ሃይማኖታችን ትክክል ነው ለማልት ከሆን ነገሩ ፡ እምንት በሰው ብዛት አይለካም። አላነብብከውም እንጂ ቁርዓን እርስ በራሱ ቢጣረስም ስለ እውነተኛ አዳኝ መስክሮልህ ነበር። እውነቱን ልንገርህ እንደ እኔ አድርገህ በየረድፉ አድርገህ ወንጌልን፡ ቁርዓን ብታንብ ኑሮ አንድ ቀን ባለህ እምነት አትውልም፡ አታድርም ነበር። ታዲያ ምን ይሁን ወንጌልን እንዳታነብ እንድትጽየፈው ተደረግህ። ስለዚ አሁን እምነግርህ በገንት 70 ወንድ ያላወቁ ደናግል ይጠብቁናል በማለት በአጉል ተስፋ የሚጃጃሉ እንዳሉ ላሰምርበት እፈልጋለሁ። ከመቃብር ተንስተህ በገነት ዓለማዊ ፍላጎትህን እየፍጸምክ ለመኖር ተስፋ እንዳለህም አንተ ራስህ ታውቃለህ። ከዚህም በመንሳት ላንተ ያለኝ ምክር “ነቢይ ኤሳ” ብለህ በምትጠራው፤ ቁርዓንህ “የአላህ ቃል፡ የአላህ ስትንፋስ፡ ቅዱስ፡ ወዘተ ብሎ በሚጠራው ፡በድንግል ማርያም ልጅ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም አምነህ በትጠመቅ፡ እንደ መላእክት በሰማይ ቅዱስ ቅዱስ እያልክ መኖር ትችላለህ። እናም ለመዳን ፍጠን። በአንተ አጠራር ነቢይ መሐመድ፡ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት በፍርድ ወንበር እንደሚቆም አትርሳ። ወንድሜ !!! እባክህ ቁርዓንን በሚገባ አንብብና ተረዳ። እንደ ቃልህ፡ ነቢይ መሐመድ መጽደቃቸውንና መኮነናቸውን እንዳማያቁ አላነበብክም ወይ? እርሳቸው እንኳን የእምንቱ ሐዋርያ ሆኖው ለመጽደቃቸው እርግጣኛ አልሆኑም። ነገሩን ለማሳጠር ከዚህ ላቁመው። አትርሳ በተፈጥሮ ወንድሜነህና አከብርሃለሁ።
ቃለ ሐዋርያት ነኝ

enochtaken said...

why are you posting non-orthodox related news here, Is it not this is an issue for the security department of Ethiopia?

As betekehnet said you meddle to much in poletics.

Meseriwoch said...

Ha ha ha
The so called Ethio Muslim, did u forget that we are on information age?
What u did anywhere on this earth is disseminated to each corner of the world with in a minute.

I would like to invite u what the human monestors are doing under the cover of muslim.

We know since time of Gragn Ahmed , u were slaughtering Christian Ethiopians till now.

And then, dont u think that we have had enough knowledge of you sensless guys who are always thirsty of Christain blood

Please dont open this link if u are under 18 and pregnant

http://somalisforjesus.blogspot.com/2009/01/mansur-mohamed-sfj-martyr-of-year-2009.html

Down with terrorists said...

FOR GOD SAKE OPEN THIS LINK AND WATCH HOW MONSTERS ARE THESE GUYS
http://somalisforjesus.
blogspot.com/2009/01/
mansur-mohamed-sfj-martyr-
of-year-2009.html

Here R ze Real demons said...

Ethio Muslim,
I hope u are happy like ur brothers there, when they drink human blood alive.

wE KNOW U VERY MUCH .EVEN ANIMALS ARE NOT AS CRUEL AS THIS. WATCH THE VIDEO UNDER. FOR U AND UR "BROTHERS" THIS IS BEING HERO.BUT U DONT ACTUALY KNOW THAT U ARE DOING DEMONIC, INHUMAN AND SENSLESS ACT.
WE NEED THE WORLD WITH OUT U AND UR TYPES.
GO TO HELL, U HUMAN DEMONS
http://somalisforjesus.
blogspot.com/2009/01/
mansur-mohamed-sfj-
martyr-of-year-2009.html

1234 said...

For the last thousands of years, u were beheading Ethiopian Christians and drinking their blood. Especially Christains around the border were ur victims.
The world never knows this. Gragn Ahmed , the Blood sucker, killed and slaughtered thousands of Ethiopians. U may forget , but we rember it always. Still u are planing to repeat ur demonic mission.
Human being created in the image of God. We humans do have dignity. But still even on the 21 th centuary, u are doing what animals are not doing. Killing and bombing innocents, beheading humans for being Christains and etc
It is amazing to see an Ethiopian going to Pakistan. Think of what is the plot for the Ethiopian Christains.
Watch the link

http://somalisforjesus.
blogspot.com/2009/01/
mansur-mohamed-sfj-
martyr-of-year-2009.html

Anonymous said...

these people are crazy, they are humanly evil. satan with two legs and two feet.

wey gud said...

Ethio Muslim,
Dont be stupid as Ahmed Gragn, ur hero was, was stupid enough.
Why are u guys always happy of human blood. Please try to have dignity for human beings. It is wild dog or beast who is happy of human blood.
History tells us what u guys were doing in the past. Especially against Ethiopian Christains and still ongoing.
Also we know that u are brutal for ur own followers too.
By cutting the head of human, do u guys feel that God will be happy? funny . and funny. U are monsters.
Terrorists. U are always happy by detonating boms and seeing the suffering of humans, beheading innocents and enjoying his blood,..
This is 21 st century. Be civilized. Stop terror. be human. terrorism doesnt pay. dont be blood thristy animals. Correct ur doctrinewhich orders u to bomb and kill innocents.

http://www.truthtube.tv/play.php?vid=522
Oh God,

murders said...

PLEASE DONT WATCH THIS CLIP IF U ARE UNDER 18 , and are pregnant
http://www.truthtube.tv/play.php?vid=522

down with terrorits said...

BRUTALITY UNDER THE COVER OF ISLAM ISLAM
SEE HOW THAY ARE TRAINING KIDS ON HOW TO SLAUGHTER HUMAN

http://www.truthtube.tv/play.php?vid=522

demons under cover said...

VIDEO RESPONSE

For Ethio MUslim

U DAMN IDIOT TERRORITS . WE KNOW WHAT U ARE DOING.THE FOX COVERED WITH SHEEP LEATHER. U WANT TO LOOK LIKE SAINT. BUT WE KNOW U .
LOVE PEACE, NOT BEHEADING. FEEL THAT THE WORLD IS UR FAMILY. NEVER BE THIRSTY OF CHRISTIANS AND HUMAN BLOOD. THIS IS ANIMAL BEHAVIOUR

http://www.truthtube.tv/play.php?vid=522

the real site said...

BE HUMANS


http://www.truthtube.tv/play.php?vid=2008

terror doesnt pay said...

GOD where are u?
See how humans are doing?
Terror, terror and terror
http://www.truthtube.tv/play.php?vid=2008

Stop terrorism said...

Video response for Ethio Muslim

http://www.truthtube.tv/play.php?vid=2008

Unknown said...

2 Corinthians 11 >>
King James Bible

13 For such are false apostles, deceitful workers, transforming themselves into the apostles of Christ. 14 And no marvel; for Satan himself is transformed into an angel of light. 15 Therefore it is no great thing if his ministers also be transformed as the ministers of righteousness; whose end shall be according to their works.

Anonymous said...

Islam is not a peaceful religion. Everybody knows it, even the muslim. The problem is most Muslims or some Christians are scared to say anything for fear of death/violence. Most Christians want to ignore it b/c it takes courage to defy islam. Most non muslim world leaders in Europe and America don't want to say anything against Islam due to "political correctness". "Oh! the Muslims might love us and vote for us if we keep quite or praise them. The (false) prophet Mohammed is a peaceful man. We should respect Islam. " What a load of crap !
So, anyone of you who knows the truth work to spread the truth and help the lost Muslims to know the only Savior of the world our LORD and God Jesus Christ and be saved from the fire of hell that expects them all. That is the only alternative, because the ones that pretend to sleep (like EthioMuslim) will never wake up. You either wake up and work for the Kingdom of God or go back to sleep.

Peace!
Ankiro from AA

Berhanu said...

«እኛ ግን ነፍሳቸውን ሊያድኑ ከሚያምኑቱ ነን እንጂ ወደ ጥፋት ከሚያፈገፍጉ አይደለንም፡፡» ዕብ.10፡39

Anonymous said...

Ethio-Muslim....

ሠላም ወገኖች
የሁላችሁንም ሃሳብ በጽሞና አንብቤዋለሁ
ብዙ ማለት ይቻል ነበር ነገር ግን ቦታው አይደለም።
እናም አንብቡ ብዙ ለማወቅ ጣሩ...

መሬታቸው በ እስራኤል በግፍ የተነጠቀባቸው በኢራቅ አንጡራ ሃብታቸው የሚጋዝባቸው በአፍጋኒስታን እንዲሁ በተመሳሳይ ለወረራ የተዳረጉ የነጻነት ተዋጊዎች ናቸው አጥፍተው ሲጠፉ ያየናቸው።ከዚያ ውጭ ማንም ከመሬት ተነስቶ እራሱን የሚያጠፋ እብድ የለም። ይህ ማልት ግን ስራቸውን እደግፋለሁ ማለትን አያስይዝም።
ስለ እስልምና ከኔ በላይ ብዙ እንደምታውቁ እንደውም ልታስተምሩኝ እንደምትችሉ በመገንዘቤ እነሆ አስተያየታችሁን ለመቀበል
http://dejeislam.blogspot.com/ እንገናኝ

ከምስጋና ጋር
ኢትዮ ሙስሊም

Anonymous said...

ሰላም ኢትዮ ሙስሊም፤

በቅድሚያ ስለምታሣየው ጨዋነት እያመሰገንኩህ፤ አንድ ነገር በእርግጠኝነት የምነግርህ አንድ ሠው እስልምና በደንብ ከገባው አጥፍቶ ጠፊ ይሆናል ቢባል ማጋነን አይደለም። እስልምና ኢትዮጵያዊ ቨርዥኑ ሰላማዊ ነው፤ ኢትዮጵያዊ ባህሉም ተጽእኖ አድርጎበት ሊሆን ይችላል፤ ወይም የሀዲስ ትርጓሜው በአብዝሃኛው የሚተነተነው በዚሁ ኢትዮጵያዊ ባህል ስለሆነ ሊሆን ይችላል/ መንዙማው ሳይቀር - በነገራችን ላይ መንዙማ መስማት እጅግ የምወደው ነገር ነበር/ ኢትዮጵያዊው እስልምና ሰላማዊ ነበር። ነገር ግን አሁን ወደ አገራችን እየገባ ያለውና በብዛት ወደ አረባዊነት የሚያደላው፤ እስልምና ግን ሰላማዊ ነው ብትለኝ፤ በእርግጠኝነት መልሴ አይደለም ነው።

ለምን? ብትለኝ ያደኩት በብዛት ኅብረተሰቡ ሙስሊም የሆነበት አካባቢ ነው። በስጋም ዘመዶች አሉኝ፤ እጅግ በርካታ መልካም ሰዎችን አውቃለሁ፤ ነገር ግን ፓኪስታን ለትምህርት ሄደው ከመጡ በኃላ ሁሉም ያጋጠሙኝ ማለት ይቻላል፤ በልዩነት የሌላውን መብት አክብሮ መኖር የሚባል ፈጽሞ የላቸውም ቢባል ማጋነን አይደለም። ሽብር የሚነዙትና አብሮ ለዘመናት የኖረን ህዝብ በጠላትነት እንዲተያይ እያደረጉ ያሉት እነዚሁ ናቸው፤ በአንድ ወቅትም በመስጊድ ውስጥ ሽብር ፈጥረውም ትልልቆቹን አባቶች ሲያንገላቱ ነበር፤ እንደነዚህ ያሉት ብዙዎቹ በመድረሳ ትምህርት ቤቶች ውስጥ አስተማሪ ናቸው፤ ለህፃናት ምን እንደሚያስተምሩዋቸው ደግም ሳስብ እጅግ አሳሳቢ ሆኖ ነው ያገኘሁት፤ ወደፊት ምን አይነት ትውልድ ይከሰት ይሆን? ያስብላል.... ያሳስባልም። እንደ ሰርግና ሃዘን በመሳሰሉት ማኅበራዊ ጉዳዮች ላይ አብሮ እንደድሮው መገናኘት ከቀረ ተዎው ዘመናት የለውም…. ይህን ካየሁ በኃላ አንድ ሰው አረባዊው እስልምና በደንብ ሲገባው፤ ጨካኝ ይሆናል ወደሚል ድምዳሜ ያደረሰኝ።

ስለዚህ በእኔ እምነት ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ኢትዮጵያዊውን እስልምና ተጠብቆ እንዲኖር የማስተማር ኅላፊነት አላባቸው ብዬ አምናለሁ። ዝም ብሎ በጭፍን በእስልምና ስም ስለሆነ ብቻ አረባዊውን እስልምና መደገፍ ዋጋ የለውም፤ ለማንም አይጠቅምም፤ ካሁኑ “ሳይቃጠል በቅጠል” ነው መሆን ያለበት። በትክክል ለወገኖቻችን የምናስብ ከሆነ ይህን የማድረግ ኃላፊነት አለብን ብዬ አስባለሁ። በዚህ ችግራችን ላይ የኃይማኖት ግጭት ቢከሰት በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ ነው የሚሆነው፤ መብረጃም የለውም፤ውጤቱም ለማንም የማይጠቅም ጥፋት ብቻ ነው የሚሆነው። በእውነት ቆም ብለን ማሰብና የበኩላችንን ማድረግ ይጠበቅብናል።

ለማንኛውም ሰላማዊ ሆነን በሰላም ከማንም ጋር ለመኖር እግዚአብሔር ይርዳን!

ክርስቲያን ወንድምህ

Anonymous said...

ሰላም ኢትዮ ሙስሊም! Do you think the Muslims who murdered the Christians in Jima and Bale and Harar, killed them because they are occupied by them? We are awaken by know to understand your intention to take our Christian country by force, just because we were nice for you for the last hundred years. But know time is up, we will defend the truth and our country. Don’t try to fool us. We see news when your Muslim brothers kill innocents all over the world.
May God wake up all of us Christians.
Thanks Dejeselam for your wise service to our country and the Church

Hatsani said...

I really would like to ask the Deje Selam bloggers to stop posting anti-islamic propaganda and to concentrate on the issues of our church.

And to this person who thinks that he is smart and writes the same thing over and over again, acting as he was 20 different people: Who do you think you can fool with that? Once is enough... and stop the name calling! We all know that the vast majority of Muslims in Ethiopia are peace loving people who live brotherly/sisterly with their Christian neighbors!

Haymanot yegil new,
Hager yegara new!

Anonymous said...

by Ethio-muslim

ስለ ቅን ሃስባችሁ አመሰግናለሁ ቅንነት በራሱ መታደል ነውና!
በተረፈ እኔ በራሴ ስም ነው እየተናገርኩ ያለሁት 20 ስም እየቀየርክ የሚለው አስተያየት ምንም አይመስለኝም።

ምክንያቱም " በአካልም ሆነ በአእምሮ ራሱን መሆን ሲችል ሌሎችን ለመምሰል እንደሚሞክር ሰው ይበልጥ ጭንቀት የሚበዛበት የለም"የሚለው አባባል አምንበታለሁ እና!
ከዚህ በላይ ማስረዘም አልፈልግም

ለሁላችሁም ግን በኢትዮጵያዊነቴ አንድ ምክር ልምከራችሁ

የአማኝ ስነምግባር what ever is his religion እምነት ከሌላቸው በባህሪ የተለየ መሆን አለበት።
አንዳንዴ በተለያዩ ዌብሳይቶች እንደማየው ግን አማኝ ነኝ የሚል ሰው ነው ለሌሎች ሰዎች ያለው አስተያየት እጅግ ደካማ ሆኖ የማገኘው።ግን ለምን?ግራህን ሲመታህ ቀኝህን ስጠው ነበር አባቶቻችሁ የሚሉ የ አንዳንዶቻችሁ አቲቲዩድ ግን በጣም የሚያሳዝን ነው።
በቤተክህነት ትምህርት ወደ መልካም ጸባይ እራሳችሁን መለወጥ ካልቻላችሁ ......

ጽድቅ እና ኩነኔ ቢኖርም ባይኖርም
ከክፋት ደግነት ሳይሻል አይቀርም....
በሚለው አባባል ራሳችሁን አርሙ
አመሰግናለሁ።
ኢትዮ-ሙስሊም

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)