December 12, 2009

ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል እንዳይሆንብን!

Selam Deje Selam,
How are you doing? I afraid this may be my last article for the blog if you keep allow anti-church bodies dominate the blog as it has been so far. Please, try to do whatever it costs to make our blog working for the benefit of the Church, not against it. May God be with you?
Birhanu
+++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ብዙዎቻችን ደጀ ሰላምን በተደጋጋሚ የምንጎበኝበት መሠረታዊ ምክንያት ስለኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያናችን ወቅታዊ መረጃ ለማግኘት እና ከተቻለም ለቤተክርስቲያናችን መጠናከር ይበጃል የምንለውን ሃሳብ ለመግለጽ ይመስለኛል። ከዚህ የተለየ ዓላማ ያላቸው ወገኖች መኖራቸው ባይካድም መኖራቸው በራሱ የሚያሳስበን ጉዳይ አይሆንም፤ የእነርሱ ዓላማ የዚህችን ቤተክርስቲያን ገጽታ ማጥፋት፣ ምእመናን ከበረት ቤተክርስቲያን በማስደነበር ማውጣትና ለተኩላው መዳረግ ነው። ስሙን መጥራት እንጂ ኃይሉን ንቀዋልና ስለቸሩ መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያናችንን ለቀቅ አድርጉዋት ማለትም የሚያስፈልግ አይመስለኝም'። ስለሆነም በዚህ ጽሑፍ ብሎጓን ለመቆጣጠር የደረሱትን መናፍቃን ወይም ስለቤተክርስቲያን በቂ እውቀት ሳይኖራቸው የተሰማቸውን የሚጽፉትን ለመተቸት አልሞክርም፤ ከላይ እንዳልኩት እነርሱም እኩይ ዓላማቸውን ለማስፈጸም ይትጉ እኛም ሃይማኖታችንን ይዘን በኃያሉ አምላክ ተመክተን የልጅነት ድርሻችንን እየተወጣን እንቀጥላለን።

ነገር ግን እኔን በእጅጉ እያሳሰበኝ የመጣው ጉዳይ ሌላ ነው። የኦርቶዶክሳዊያን ሞኝነትና (የዋህነት አይደለም) የምንሰራውን ያለማወቅ!! ጥሩ ምሳሌ የሚሆነን በደጀ ሰላም ላይ የምንወያይበት መንፈስ እና የብሎጓ ባለቤቶች አሠራር ነው። ይህንን ሰል የብሎጓ ባለቤቶች (የአንድ ሰው ሥራ አይደለም ብንል) ስለቤተክርስቲያን ቀና አመለካካት ያላቸው ናቸው ከሚል እሳቤ ነው።( ምናልባትም እኔም እንዲህ እንዳስብ ያደረገኝ ያው ‘ኦርቶዶክሳዊ ሞኝነቴ’ እንዳይሆን እንጂ!) ወደተነሳሁበት ቁም ነገር ልመለስና ይህችን ብሎግ ማንበብ ከጀመርኩበት ጊዜ ጀምሮ ያስተዋልኩት ነገር ቢኖር ኢትዮጵያዊያን በማንኛውም ጉዳይ ላይ ለመግባባት እይተችገርን መሆኑን ነው። ይልቁንም በአንዲት ሃይማኖት እናምናለን የምንል የተዋሕዶ ልጆች ስለቤተክርስቲያናችን ስንነጋገር እየተደማማመጥን ያለመሆኑና አንዳንዶች የምንጽፈውን ያለማወቃችን ያሳዝናል። እያንዳንዱ ሰው ስለሚናገረው ነገር በፍርድ ቀን መልስ እንደሚስጥ የምናውቅ መንፈሳውያን ስለምናውቀውና ስለምናምነው ነገር ከመመስከር እና የቤታችንን ችግር በመፈሳዊ ጥበብ ከመወያየት ይልቅ ቤተክርስቲያንንም ሆነ መንፈሳዊ ሕይወታችንን በማያንጽ አሉባልታ መጠመዳችን ያስገርማል።በተለይም አብዛኛዎቹ በዚህች ብሎግ ላይ የምንጽፍ ወጣቶች መሆናችን የነገዋን ቤተክርስቲያን ተስፋ በስጋት እንድመለከት አድርጎኛል። ስለ ቤተክርስቲያን ግድ ይለናል የምንል የቤተክርስቲያን ልጆችን እና የደጅ ሰላም አዘጋጆች እጅጉን ልናስስብበት የሚገባ ጉዳይ ያለ ይመስለኛል። በመጀመሪያ ለአዘጋጆቹ ከዚህ ቀደም “ደጀ ሰላማችን ሰላም እንድትሆን” በሚል ርእስ የተወሰኑ ሃሳቡችን ለመሰንዘር መሞከሬን ለማስታወስ እወዳለሁ። ብሎጓን የመናፍቃን መፈንጫ ያደረጋችሁት ‘ኦርቶዶክሳዊ ሞኝነታችሁ’ ይዞአችሁ ካልሆነ በቀር (ከምትጽፏቸው ጽሑፎች እንደምረዳው) ‘ዲምክራትስ’ ስለሆናችሁ አይመስለኝም። ለመሆኑ በየትኛው ሃይማኖት ድረ-ገጽ ነው የእምነቱን መሠረት የሚነቅፍ ጽሑፍ የሚስተናገደው- ከደጀ ሰላም በቀር። ከዚህም በላይ በቤተከርሰቲያን አባቶች እና ማኅበራት(በመረጃ የተደገፈ ጥፋት የተገኝባቸው አይጋለጡ ማለቴ አይደለም) ላይ የሚሰነዘሩ መሠረተ ቢስ አሉባልታዎችን (ማንኛውም ኦርቶዶክሳዊ የሚያውቀው እውነታተዛብቶ እየቀረበ) እያስተናገዳችሁ ‘እኛ ላልጻፍነው ጽሁፍ ኃላፊነት አንወስድም‘ በማለት ብቻ ከኃላፊነት ለመሸሽ መሞከራችሁ አግባብ እይመስለኝም። በእርግጠኝነት የምታውቁት መረጃ ተዛብቶ ሲቀርብ ጸሐፊውን የማረም ወይም ለአንባቢዎች ተጨማሪ መረጃ የመስጠት ወይም ጽሑፉን የማንሳት መንፈሳዊ ግዴታ አለባችሁ። በአሉባልታው የሚሰናከሉትን ማሰብ ከመንፈሳዊያን የሚጠበቅ ሥነምግባር ነውና። በብሎጓ ላይ የምንጽፍ ኦርቶዶክሳዊያንም የምንጽፈው በአንድ ክፍል የማስተማርያ ሰሌዳ ላይ ሳይሆን የቤተክርስቲያን ወዳጆችም ጠላቶችም እኩል በሚያነቡት ፤ ስለምንጽፈው ጉዳይ ትክክለኛ መረጃ አግኝተን ብንጸጽት እንኳ አንባቢዎችን አግኝተን መረጃውን ለማስተካካል በማንችልበት ገጽ ላይ መሆኑን እያሰብን ሊሆን ይገባል። ስለሆነም የግለሰቦችን ስብእና ከሚያጎድፉ አገላለጾች ተቆጥበን ለዘለቄታው የቤተክርስቲያን ጥቅም በመንፈሳዊ ጥበብ ብንወያይ የተሻለ ይሆናል። ያለበለዚያ ለውጥ በማናመጣበት ውይይት ለቤተክርስቲያን ጠላቶች ሌላ ሰፊ የመግቢያ በር እንዳንከፍት ያስፈራል። ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል የሚባለው እንዳይደርስብን። እስቲ በዚህ አስተያየት ላይ ውይይት እናድርግበት ፤ ይህች ብሎግ የመሰዳደቢያ መድረክ እንዳትሆን ምን ማድረግ ይቻላል?

Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)