December 10, 2009

ውይይታችን ስለ ማን እና ምን?

(ደጀ ሰላም፤ ዲሴምበር 10/2009)
ሰሞኑን ተጠፋፍተን ሰነበትን። ኑሮና እንጀራ በጠራን ሥፍራ ስንባክን ከኮምፒውተሩ ተለያይተን በመክረማችን ነው። ባለፉት 10 ቀናት፣ ሌላ ምንም ዓይነት ጽሑፍ ባልተጻፈባቸው ቀናት፤ ደጀ ሰላማውያን በምን በምን ጉዳይ ዙሪያ ተወያየን ብለን ብንመለከት “የአንበሳውን ድርሻ” ይዞ የሚገኘው አጀንዳ “ዳንኤል ክብረት” የሚል ስም ሆኖ አገኘነው። ደጀ ሰላም ብዙ የመወያያ አጀንዳዎች አቅርባለች፣ ቤተ ክርስቲያናችንም ብዙ ብዙ ወሳኝ ጉዳዮች ላይ መነጋገርን የሚሹ ነገሮች አሉባት። ነገር ግን ዞሮ ዞሮ ወሬያችንና ውይይታችን “የግለሰቦችን ስም ከማንሣት” አላለፈም። ቢበዛ ቢበዛ ከግለሰብ አለፍ ብንልም የምናነሣው “ስለ ማኀበረ ቅዱሳን” ብቻ ነው። እንዴ!? በቃ ይኸው ነው ሐሳባችንና አስተያየታችን?

በተለይ በመጨረሻ ላይ በተስተናገደው ዋናውና ሐሳቡ ስለ አክራሪ ሙስሊሞች በሆነው ጽሑፍ ላይ ከቀረቡት አስተያየቶች አብዛኞቹ ስለ ርዕሰ ጉዳዩ የተነገሩ ሳይሆን ከላይ ስለጠቀስነው ግለሰብ/ወንድም እና ማኀበር የተለዋወጥናቸው መሆናቸውን መመልከት ይገባል። የሐሳብ ንጥፈት፣ የአስተሳሰብ ድክመት ይሏል ይኽ ነው። ደጀ ሰላም ይህንን የሐሳብ ንጥፈት ለመሻገር፣ የውይይት አቅጣጫችንንና አስተያየታችንን “የታባቱ” ከምንላቸው ሰዎች ዘለፋና ስድብ በዘለለ ሰፋ አድርገን እንድናስብ ለማድረግ ትጥራለች። እናንተ ደጀ ሰላማውያንም ብዕራችሁን በማንሣት እንደተለመደው ሐሳባችሁን መግለጻችሁን እንድትቀጥሉ በትህትና ጥሪ እናደርጋለን።
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)