November 2, 2009

ሦስት የጡመራ ዓመታት (Three Years of Blogging)


(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 1/2009)፦ እግዚአብሔር ይመስገን እነሆ “ደጀ-ሰላም” 3 ዓመት አስቆጠረች። ሦስት የጡመራ ዓመታት (3 years of blogging) አሳለፈች ማለት ነው። በዚህ መልካም አጋጣሚ እንግዲህ ለምን እንደተጀመረች ማውሳቱ ተገቢ ነው።
በ2006 (1999 ዓ.ም) ሀ ተብላ ከመጀመሯ በፊት የሐሳቡ ጀማሪ መጣጥፎች ለሌሎች ድረ ገጾች የመላኩ ልምድ ነበረው። አብዛኞቹ ድረ ገጾች በተለምዶ “የፖለቲካ፣ ዓለማዊ” የሚባሉ ዓይነት እንደመሆናቸው እነርሱን የሚስማማ ጽሑፍ ካልሆነ በስተቀር ለማውጣት ፈቃደኞች አይደሉም።

በ2006 በጅማና በአካባቢዋ የክርስቲያኖች ጭፍጨፋ ወቅት የደጀ ሰላም ሐሳብ አመንጪ የተለያዩ ጽሑፎችን በማዘጋጀት ለድረ ገጾች ለመላክ ሞከሮ ነበር። ነገር ግን ድረ ገጾቹ እነዚያን ጽሑፎች ለማስተናገድ ፈቃደኞች አልነበሩም። ምክንያታቸውን እነርሱ ያውቃሉ። የጽሑፎቹ ዋነኛ መልእክት ግን ስለ ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያናችን “ችግር” እና እየደረሰባት ስላለው መከራ “ከፖለቲካዊ ትርጉም” በወጣ መንገድ የራሱን ትንታኔ ለመስጠት የሞከረባቸው ነበሩ። ይሁን እንጂ ድረ ገጾቹ አልተደሰቱባቸውም። ስለዚህም በቁጭት “ለምን የራሳችን የጡመራ መድረክ አንጀምርም?” ሲል አሰበ። እናም በማይም እጁ ደጀ ሰላምን መጦመሩን ሀ አለ። እነሆ 3 ዓመት ሆነ። ይህንን ያደረገ አምላክ ክብር ምስጋና ይድረሰው።

“ደጀ ሰላም” በአንድ ሰው ትጀመር እንጂ በአሁኑ ወቅት ግን በሁሉም መስክ የሚረዷት ብዙ ደጀ-ሰላማውያን ወንድሞችና እህቶች ተገኝተዋል። እርስ በርሳቸው ሳይተዋወቁ ነገር ግን በብዕር ስማቸውና በኢ-ሜይላቸው ብቻ በመገናኘት ይህንን የጡመራ ሥራ በማካሄድ ላይ መሆናቸው የደጀ ሰላም አንዱ ጠንካራ ጎኗ ነው። ወደፊትም እያደገችና እየሰፋች እንደምትሄድ በእግዚአብሔር ተስፋ አላት። ለቤተ ክርስቲያናቸው የሚያስቡ ሁሉ ይረዷታል።

ለግንዛቤ እንዲሆን ከሁለት ምንጮች የምናገኘውን መጠነኛ ስታቲስቲክስ ማሳየት ያስፈልገናል። የ“http://blogpatrol.com” ዘገባ የደጀ-ሰላማውያንን ቁጥር ማስላት ከጀመርንበት ከ2007 ጀምሮ 123 521 አንባብያን እንደጎበኟት ያሳያል። ሌላው ከ27 March 2009 ጀምሮ ስታቲስቲክስ የምንሰበስብበት (http://webstats.motigo.com) ደግሞ የሚከተለውን ዘገባ ያስቀምጣል።

United States 215,529 64.8 %
2. Germany 21,169
3. Canada 19,123
4. United Kingdom 15,574
5. Norway 6,811
6. Ethiopia 6,432
7. Italy 5,426
8. Austria 3,980
9. Sweden 3,744
10. Netherlands, The 3,190
The rest 31,441
Total 332,419

ለሁሉም አምላካችንን እያመሰገንን የጽሑፍ አገልግሎታችንን እንቀጥላለን። ታማኝ ዜናዎችንና መረጃዎችን እናቀርባለን። ጥብቅናችንን ለማንም ሳይሆን ለቤተ ክርስቲያናችን ብቻ እንዳደረግን እንዘልቃለን። ምእመናን ስለ ቤተ ክርስቲያናቸው አውቀው እንዲያሳውቁ የበኩላችንን እንጥራለን። ለዚህም ሁላችሁም “ደጀ ሰላማውያን” ትተባበሩ ዘንድ በድጋሚ እንጋብዛለን። አስተያየቶቻችሁ፣ ጥቆማዎቻችሁና ጸሎታችሁ አይለየን።
ቸር ወሬ ያሰማን
አሜን
++++++++++

ደጀ ሰላም የማን ናት?
(ደጀ ሰላም፤ ጁላይ 28/2009)
ሁልጊዜም ቢሆን ማንነትን መጠየቅ፣ ማወቅና መለየት ይገባልና አንዱ ሌላውን “አንተ ማነህ?” ይለዋል። “ደጀ ሰላምም” ተራው ደርሷት “ማነሽ? የማነሽ? ከማን ወገን ነሽ? ከእኛ ወይስ ...?” ተብላለች። ጥያቄው የመጣው በተለያዩ መንገዶች ቢሆንም ዋነኞቹ ግን የሚከተሉት ናቸው።
1. አስተያየት ሰጪዎች በመሰላቸው መንገድ፣ በተለያዩ አጋጣሚዎች “የነእንትናና የነእንቶኔ” ብለዋታል፣
2. የዲሲው ባለ 10ሺህ ዶላሩ “የማፊያው ጋዜጠኛ” የማህበረ ቅዱሳን ናት ብሏታል፣
3. ማህበረ ቅዱሳን ራሱ ደግሞ “የእኔ አይደለችም፣ አላውቃትም” ብሏታል፣
4. የማፊያው ቡድን ምንጯን ለማወቅ ደፋ ቀና እንደሚል ተረድተናል፣
5. ቅዱስነታቸውና አቡነ ገብርኤል “ስማችንን አጥፍታለች” ብለው “የት ባገኘናት” ብለዋታል።
“ደጀ ሰላም” ስለ ራሷ እንዲህ ትላለች።

የተጀመረችው በ2006 ነው። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ላለፉት 3 ዓመታት ደስ ባላት፣ አትኩሮቷን በሳቡ ጉዳዮች ዙሪያ ስትጦምር (ብሎግ ስታደርግ) ቆይታለች። ብሎግ ናትና ከየት ሀገር ነሽ፣ ማነው የጣፈሽ፣ ማን አገባሽ? ማን ፈታሽ? የሚላት የለም። ስለ ጡመራ (መ ይጠብቃል) ወይም ብሎጊንግ የማያውቁ ሰዎች ደግሞ መከራዋን ሲያበሏት ይህንን ለመጻፍ ተነሳች።

አንድ ታሪክ ስለ ታዋቂ ጦማሪ (ብሎገር) በማንሳት እንጀምር።
ሰውየው ኢራቃዊው ሳላም ፓክስ (Baghdad Blogger Salam Pax) ይባላል። እውነተኛ ስሙ አይደለም። መጦመሪያ ስም ነው። ምንም ውስጥ አወቅ ዜና በማይሰማበት የኢራቅ ጦርነት ወቅት ከባግዳድ ተቀምጦ ስለ ከተማዋ ሁናቴ ለወዳጁ ይጽፈው የነበረውን ሐተታ “ብሎግ”ከፍቶ ይልክለት ነበር። በሁዋላ ያንን ብሎግ ("Where is Raed?" የሚል ብሎግ) ዜና ማሰራጫዎች አገኙትና የሰውየው ማንነት ሳይታወቅ ነገር ግን በሚያቀርባቸው ሐተታዎችና ተአማኒ ዜናዎች ከበሬታን አገኘ።
It began as an internet joke with a friend. But then the media - including the Guardian - picked it up, and suddenly he was the Baghdad blogger, the most famous web diarist in the world. Salam Pax describes what it was like to play cat-and-mouse with Saddam's censors.

ጦርነቱ አልቆ፣ አማሪካኖች ባግዳድን ተቆጣጥረው ነገር ከበረደ በሁዋላ ያንን ጦማሪ ቢፈልጉ ማግኘት አልቻሉም። በሁዋላ ላይ በብዙ ማግባባት ማንነቱን ዘ ጋርዲያን ደረሰበት፣ እርሱም ራሱን ገለጠ። ዘግየት ብሎ ለእነርሱው ተቀጥሮ እስከ መስራት ደረሰ። ለህይወቱ የሚያሰጋው ነገር ሲመጣ አገር ጥሎ ለተወሰኑ ዓመታት አሜሪካ እስከመኖር ደረሰ። ታሪኩንና ይጦምረው የነበረው ነገር ሁዋላ ላይ መጽሐፍ አድርጎ The Baghdad Blog (ISBN 1-84354-262-5) አሳትሞታል።ወዘተ ወዘተ። ዝርዝሩን ራሳችሁ አንብቡት!!!

ይህንን ለማለት የተፈለገበት ምክንያቱ አንድን ጦማሪ “የት ነህ? ከማን ወገን ነህ?” ብሎ ማፋጠጥ ያሳፍራል፣ ነውርም ነው ለማለት ነው። ንጉሴ ሆነ አቡነ ገብርኤል፣ ፓትርያርክ ጳውሎስ ሆኑ ገለልተኛ-ስደተኛ፣ ማህበረ ቅዱሳን ሆነ ማህበረ ሰንበቴ “ድንበር አትለፉ” እንላቸዋለን።

መልሳችን “የምንጽፈውን እንጽፋለን”፤ “ለቤተ ክርስቲያናችን የሚበጀውን እገሌ ይቆጣናል፣ እገሌ ያፈርሰናል፣ እገሌ ያግደናል፣ እገሌ ይቀየመናል ሳንል እንጽፋለን”። ከልባችን መሆኑን ሁሉም እንዲረዳው ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስም ሆኑ ከቧቸው ያለው የማፊያ ቡድንን ለምን እንደምንቃወማቸው እንዲያውቁ በሰፊው መዘገባችንን በእግዚአብሔር ቸርነት እንቀጥላለን። “አባቶቼን አዋረዱብኝ” የሚል ካለ ጠበቃነቱ ለቤተ ክርስቲያኑ ወይም ለማፊያው መሆኑን እየጠየቅን እንሞግተዋለን።
“እኛ የቤተ ክርስቲያን ነን”!!! የማንም አይደለንም!!!
ቸር ወሬ ያሰማን፤
አሜን
Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)