November 24, 2009

የእኛ ቤተ ክርስቲያን “በአማኞቿ ላይ ያላት ሥልጣን” እና “ተሰሚነት” ምን ድረስ ነው?

(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 23/2009)፦ ከሰሞኑ የአሜሪካንን ዜና ለተከታተለ ሰው የታዋቂው የጆን ኤፍ. ኬኔዲ ትንሽ ወንድም (በቅርቡ ያረፉት) ዝነኛው ሴናተር ቴድ ኬኔዲ ልጅ የሆኑት ፓትሪክ ኬኔዲ ከእምነት አባታቸው ካቶሊካዊው ጳጳስ Bishop Thomas Tobin ጋር የገቡትን እሰጥ አገባ ማግኘቱ አይቀርም። ነገሩ የተጀመረው ፓትሪክ ኬኔዲ ከካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ጋር በሚጋጭ መልኩ “ውርጃን በመደገፋቸው”፣ ይህም ሳያንሳቸው “መቁረብ መቀጠላቸው” ነው። ስለዚህ የአካባቢው ጳጳስ “መቁረብ እንዲያቆሙ” በምሥጢር ምክር አዘል ማሳሰቢያ ከሰጧቸው በኋላ ነው። አቶ ፓትሪክ ኬኔዲ ይህንን “የግል ውይይት” ለአደባባይ በማብቃታቸው ነገሩ የሚዲያ ሲሳይ ሆኗል። ለዛሬ የደጀ-ሰላም አጀንዳ የሆነበት ምክንያት “እገሌ ትክክል ነው፣ እገሌ ትክክል አይደለም” ለማለት ሳይሆን አንድ ጳጳስ በታላላቅ ፖለቲከኞች ላይ ሳይቀር ያለው የሞራልና የሥልጣን የበላይነት ስላስገረመኝ ነው። ጳጳሱ ካቶሊኩን ፓትሪክ ኬኔዲን “እንዲህ ማድረግ የለብህም” ያሏቸው ፓትሪክ “ካቶሊክ መሆናቸው” በሰጣቸው ሥልጣን ነው።
ነገሩን ወደ እኛ እንመልሰው።

እንደዛሬው “ቤተ ክርስቲያንና መንግሥት ተለያይተዋል” ሳይባሉ ይልቁንም “ክርስትና የሀገሪቱ ብሔራዊ ሃይማኖት” ከነበረበት ዘመን ጀምሮ ቤተ ክርስቲያን (አባቶች) በአማኞቻቸው ላይ በተለይም የመንግሥት ሥልጣን በያዙት ላይ ምን ያህል “መንፈሳዊ ሥልጣን” አላቸው/ነበራቸው? በተለይም “አብዮት ፈንድቶ”፣ አብዮት ልጆቿን “እየበላች” ልጆቿ ያልሆኑትንም “እየበላች”፣ ራሷም “ከተበላች” በኋላ እና አሁን ደግሞ “ሕዝብ የራሱን ዕድል በራሱ ይወስን” ከተባለ በኋላ በሀገሪቱ ውስጥ ብዙ ብዙ ነገር ቢደረግም/ እየተደረገ ቢሆንም “ቤተ ክርስቲያን የዳር ተመልካች” ናት እንጂ ከነገሩ ያስገባት/ የሚያስገባት የለም። አንዳንድ ምሳሌዎችን ላንሣ።
ባለፉት 40 ዓመታት በኢትዮጵያ ውስጥ በተደረጉ ነገሮች የትኛውም መንግሥት የቤተ ክርስቲያንን ይሁንታ አይጠብቅም። ደርግም ሆነ ኢሕአዴግ ቤተ ክርስቲያን ድርሻ ያላት መሆኗንም የሚያውቁ አይመስለኝም። የተለያዩ ሕጎች ሲወጡና ሲጸድቁ ቤተ ክርስቲያን ከራሷ እምነትና ሥርዓት ጋር አነጻጽራና አመሳክራ “ይህ ይሁን፣ ይህ ይደረግ” አትልም። የሚጠይቃትም የለም። ሌላው ቀርቶ ጋብቻን፣ ውርጃን፣ የክርስቲያኖችን የቀን ተቀን ሕይወት የሚመለከቱ ሕጎች ሲወጡ ቱባ ቱባ ባለሥልጣናቱ ኮታቸውን ኮትተው፣ ከረቫታቸውን ከርቭተው ሲያውካኩ ውለው ያድራሉ እንጂ ከዚያ መካከል የቤተ ክርስቲአን አቋም ይህ ነው ተብሎ ሲነገር ሰምተን አናውቅም። ችግሩ ሁለት ነው።
ችግር አንድ፦ የኢትዮጵያ ፖለቲካና ፖለቲከኞች ለቤተ ክርስቲያኒቱ ክብር የላቸውም። አመለካከታቸውም ጤናማ አይደለም።
ችግር ሁለት፦ ቤተ ክርስቲያኒቱና መሪዎቿ ቤተ ክርስቲያኒቱን የሚያስከብሩ አይደሉም። ቤተ ክህነቱ ራሱ ዘመኑ በሚመጥነው ዕውቀት የተጠናከሩ ሊቃውንቱን ከዓመት ዓመት እያጣ በመሔዱ አሁን ያለው አስተዳደር “ግብረ በላ” ካህናትን የሰበሰበ በመሆኑ እንዲሁም ዕውቀታቸውም እዚህ ግባ የሚባል ባለመሆኑ ሀገሪቱ ውስጥ እየተደረገ ስላለው ክርክር በቂ ዕውቀት የላቸውም። ቤተ ክርስቲያኒቱ ዕውቀት ያላቸው ሊቃውንት ስለሌሏት ሳይሆን ዕውቀት ያላቸውን በተገቢው ቦታ አስቀምጦ የሚሠራ አሠራር ስለሌለ ለሁሉም ጉዳይ ተጠያቂ የሆኑ ሊቃውንት ያለቦታቸው በመጣላቸው ቤተ ክርስቲያኒቱ ድምጽ አልባ ያውም የሚገባት ክብር የማይሰጣት ልትሆን በቅታለች።
ቤተ ክርስቲያን ያላትን ተሰሚነት ማግኘት አለባት። ካህናቷም ከእርጥባን ልመና ወጥተው፣ የማንንም ፊት ሳያዩ፣ ሳይፈሩና ሳያፍሩ እምነታቸው የሚያዛቸውን የሚናገሩ እንዲሆኑ ምኞታችን ነው። የእነርሱ መናገር ብቻ ሳይሆን የሚሰሙ (ሰ ጠብቆ ይነበብ) መሆን ሲችሉ በርግጥም ቤተ ክርስቲያኒቱ ተሰሚ ሆናለች ማለት ነው። አለበለዚያ ግን የእግዚአብሔር እንደራሴዎችና ዐዕይንተ-እግዚአብሔር (የእግዚአብሔር ዓይኖች) መባላቸው የቃላት ኳኳታ ብቻ ነው የሚሆነው። በቅርቡ በፈረንጁ ሀገር የሚገኙ አንድ ቄስ (ሰባኪም ናቸው) ዘበነ ለማ የተባሉ፣ “አንዲት እህት ቅዱስ ቁርባን እንዳትቀበል ለመከልከል በመሞከራቸው” ጠብ መነሣቱን በድረ ገጾች ላይ አንብበናል። ሴትዬዋም የቀሲሱን ቃል እንዳልተቀበሉም ተጠቅሷል። በጠቅላላው አንድ ካህን የሚናገረው ቃል፣ ትምህርቱም ሆነ ውግዘቱ የሚሰማው ሲያጣ “ወፈ ገዝት” (ወፍን እንዳትበርሪ ብሎ የሚገዝት) ይሆናል። የሚናገረው ምንም እርባና አይኖረውም። ያን ጊዜ ክህነትም ዋጋ ታጣለች፣ ካህኑም ሥልጣኑ የማይሠራ ይሆናል ማለት ነው። ከዚህ አንጻር ከመረመርነው ካህናቶቻችን (ጳጳስም ሆነ ፓትርያርክ፣ ሰባኪም ሆነ ቄስ) ያላቸው ብሔራዊ ተሰሚነት ምን ያህል ነው ብለን መጠየቅ አለብን። ከዚህ በፊት አንድ ፀሐፊ በዚህ ርእስ ዙሪያ ግሩም ጽሑፍ አቅርቦ እንደነበር እናስታውስ ይሆን?
በጠቅላላው ተሰሚነት ያለው ቤተ ክህነት፣ ተሰሚነት ያላቸው አባቶች እንፈልጋለን!!!
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን
Is the Orthodox Church losing ground?
By arefe (http://arefe.wordpress.com/2008/12/08/is-the-orthodox-church-losing-ground/#more-1448)
One thing which may be a cause for concern in the new census is its indication of decrease in the number of Orthodox Christians, traditionally the dominant church in Ethiopia. The orthodox now comprise 43.5 percent of the population, as against just over 50 percent in 1994.The erosion is mainly due to the rising influence of Pentecostal churches and the recent Muslim revival in the country, it was said.
What does this mean?Why is the Orthodox Church finding it hard to cope with its competitors, the evangelicals and the radical Islam?
What implications does it have for the future? What should be done to reverse the trend?
The rise of secularism and the erosion of faith, and a new mood of independence are often cited for why the Orthodox Church is losing its privileges status.
But historian Professor Medhane Tadesse in his 2003 essay, “Religion, Peace and the Future of Ethiopia” mentions other reasons. The Orthodox Church (EOC) is “weak economically and organizationally,” he says.
“Lack of vision and leadership is part of the problem. Orthodox Christians do their teaching more in their capacity as committed individual believers than as commissioned agents of an international church organization,” writes Prof. Medhane.
There is a marked contrast in the modus operandi between the EOC on the one hand and the charismatic movement and radical Islam on the other, according to the analyst.
“The latter have shown a capacity for mobilization, discipline, patience, flexibility and social engagement that has consistently outshone the EOC. In fact, the EOC has become an easy prey and a soft target for all other religious institutions as each of them seems to be in competition to secure as many members of the EOC as possible for their churches”, argues the scholar.
The EOC opposes what it calls the unnecessary project of evangelizing the Evangelized. This remained key in the conflict between missions and the EOC for many years. According to Prof.Tadesse Tamrat, the clear basis for the permission given by the Ethiopian Christian rulers to the missionaries to operate in their domains was always the understanding that they try to convert only non-Christian subjects of the periphery. Now both revivalism and freedom of movement and other structural, financial and organizational advances have enabled other churches to focus on the center and target followers of the EOC.
Prof. Medanhe notes the fact that the EOC is losing its dominant position could be bad for the country.
”One major basis for the long history of religious tolerance in Ethiopia , I believe, was the feeling on the part of EOC that its dominant position was not in any way challenged; hence it was willing to tolerate the other religions. Now that equilibrium is threatened. Indeed, Ethiopia is undergoing a fundamental revolution, perhaps the deepest in its history, in the area of religion. The religious fabric is in perpetual turmoil. Engulfed by other religions, both radical and moderate, the EOC seems to be worried about losing members to missionary churches and the Wahabis. The long-held belief that the missionaries came to Ethiopia to destroy the Ethiopian Orthodox church has a large following. Arguably, if it has to survive it must prevail. Sooner or later this will lead to violent confrontation and conflict. The chronic problem of denying burial grounds to the Pentecoste and the violent confrontation during religious holidays between the EOC and the Pentecoste in recent years should be taken a s early warnings of an imminent problem.” says the Prof. Medhane.
But Prof. Medhane points that the big threat also come from foreign involvement which he said is “at its highest level.”
“The Saudi-based Muslim World League has remained at the forefront of spreading Wahabism in Ethiopia since the 1980’s.more disturbing, Ethiopia has occupied center stage in the struggle between radical and moderate Islam at a global level. One of the principal points of difference between moderates and extremists is the position they take on Ethiopia, i.e. Christian Najashi versus Islam Al-Nejashi. The former considers Ethiopia as a country which saved Islam and it should be accepted and tolerated while the latter believes that Ethiopia has remained a major obstacle to the southward (Sub-Saharan African) expansion of Islam and it should be punished. This camp seeks not to ensure the rights of Muslims but rather total Islamic victory over the country. Saudi Arabia’s more fundamental wing is at the forefront of this militancy against Ethiopia,” he points out.Radical Islamic groups are flourishing in Ethiopia in various forms and organizations, different from each other and depending rather on thier association with external funding than ideology.Hence, poverty at home and financial and organizational support from abroad is dramatically influencing the nature of political Islam in Ethiopia.

Despite the setbacks, the scholar argues that Orthodox is still important to the Ethiopians.
“Whether it is against aging and frustrating or it is more utopian than practical, the EOC still commands a sizable and very influential section of the Ethiopian society.”
But, as the religious equilibrium is collapsing very quickly, the Ethiopian Orthodox Church should be encouraged to face the challenges. How?
The first advice is to look out for religious militancy that come from foreign radical Islam and evangelical church.Explaining his reason, Prof. Medhane says that indigenous Islam and the early actvities of the Ethiopian Evanglical church were not directed against the Ethiopian state.Indeed although excluded from national life, indigenous Muslims had infact proven themselves to be unwilling to collaborate with external aggresive forces and they were no less loyal or patriotic than Christians.There has been an ongoing process of religious revivial in Ethiopia over the centuries, but the contemporary religious militancy should be seen as a wholly new phenomenon and a threat to the peace, stability and independence of the country.It is externally energized and directed, and focus should be made on the Ethiopianization of its leadership, resources and religous content.We should be consistently reminded that the new trend does not automatically equates to Islam or Western Christianity in its broader, cultural sense, and Ethiopia must always make efforts to distinguish between the two.
According to Prof. Medhane, something should be done to effect a mechanism of shared resources among the different religious institutions, above all capacity building and internal reform In the EOC, so that it cope with the new challenges.

Prof. Medhane warns that Saudi Arabia is becoming the main influential factor in Ethiopia’s Islamic affairs.” This new trend, coupled with Saudi economic activities in Ethiopia, triggers mixed signals. Ethiopia needs to learn how to seek accommodation with the Saudi connection, carefully mange its dangers, and possibly turn its advantage as a momentum that enriches its economy, pluralism and international dynamism.
The scholar is of the opinion that that religious freedom should be regulated (e.g. through a code of conduct), but religious conflict should be handled wit great care by the government.” A critical feature here is properly interfacing uncontrolled religious freedom with controlled democracy in the country. The media and school should play a pivotal role in disseminating a culture of tolerance and serving as forum for interreligious dialogue. Civic education is very important in this regard. The most serous challenges to religion tolerance and diversity usually come from exclusivist truth claims. Religious institutions should take such issues into account when preparing religious books and materials.
But of great consideration, according to the scholar, is poverty.” At the heart of militancy, the fast change in religious equilibrium and the growing influence of religion lies in the wide spreading of poverty, the economic weakness the state and the bankruptcy of ideologies.” he states.
“Whether to dream of better world, or try to live less poorly in this one, many people in Ethiopia (as elsewhere when the state fails) have switched their allegiances from politics to religion. Surely, the Ethiopian state couldn’t prevail if its economic policies continue to be poorly financed, directed or implemented. With events unfolding, it will have little chance to prove its usefulness to the masses. Instead, substantial majorities of Ethiopians will continue to pin down hopes on religion, but are likely to become more ready to experiment and accept different versions of it” concludes Prof .Medhane.

12 comments:

Anonymous said...

"For if you forgive men when they sin against you, your heavenly Father will also forgive you.But if you do not forgive men their sins, your Father will not forgive your sins"
Mathew 6:14

This is the order of our Fathers, the Apostles: Let non keep in his heart rancor or revange or envy or hatered towards his neighbours, or towards anybody else.

Kidase
If this is the order from our Lord and from our Fathers,the Apostles, why not our current fathers obey before even going to Kidase?

ኢትዮጵያ የእኛ said...

የሚሰማ ጆሮ ያለው ሰው ሁሉ ሊያነበውና የእኔ ድርሻ ምንድነው ብሎ ሊያስብብት የሚገባ ይመስለኛል
ወስብሐት ለእግዚአብሔር

Orthodox unit said...

This is very critical issue for us and we should discuss to the target both the problem as well as the solution. I will come back with my proposal in detail.

Anonymous said...

The truth is:This generation,i.e
We, are being punished because
1.we killed patriarch Tewoflos
2.Emperor Hailessilassie
3.collaborated with indiginous,derg and eprdf,and foreign enemies of Ethiopia and tewahedo-two sides of a coin.
4.just like Abraham tried to intercede sodom and gomorah,but failed to find 5 righteous people,there are no 5 people that speak the truth.This does not include the late and the only one Aleka Ayalew Tamiru.
5.In the eye of GOD and His words and the church's canon,the true synod of the church is in Addis Ababa and the legalpatriach is in America.There is illegal patriach and here is illegal synod.As long as we do not bring a genuinesolution to this problem we continue to suffer.
6.As indicated in revelation the spirit of antiJesus who is given power over language and race is reigning Ethiopia and except few most of us are not opposing this evil spirit or force.
so, we continue to be punished until we come to our senses and repent for all our sins.
The comparison given above should be seen in the aforementioned perspective of ours,not just between two persons.

Anonymous said...

አንድ ቄስ (ሰባኪም ናቸው) ዘበነ ለማ የተባሉ፣ “አንዲት እህት ቅዱስ ቁርባን እንዳትቀበል ለመከልከል በመሞከራቸው” ጠብ መነሣቱን በድረ ገጾች ላይ አንብበናል። ሴትዬዋም የቀሲሱን ቃል እንዳልተቀበሉም ተጠቅሷል። why the sconde priest give becouse Zebene Lemma his no't a priest his hoddam if you give him money he will give you any thing try him he have two gas station in washington DC for the lady you say she is over sixtey she call Emmma thanks

Anonymous said...

Zebene Lema is not a priest becouse nobody ordeaned him and he called himself a priest.Second he has not power to stop someone from reciving Holy communion. Lady does not have any falt about her faith. please tell Zebene to stop what he is dong.

kale Hawaryat said...

ወንድሞቼ ይህ አዲስ ነገር ነው ወይ? መጽሐፍ ቅዱስ አታነቡም ወይ? የካቶሊኩ ጳጳስ አንዲ ታዋቂ ፓለቲሻን ያውም በምሥጢር እንዳይቆርብ ከለከለው ወይም እንዳይቆርብ አስጠነቀቀውና ታላቅና አስገራሚ ነው ወይ? በእርግጥ እንደ ቅዱስ ወንጌሉ ቃል። በመጅመሪያ ብቻውን አድርጎ መምከሩ ተገቢ ነው። ከዚያ ካለፈ ግን ሌሎች ሰዎች በመጨመር መምከር ካልሰማም በመጨራሻ ለቤተክርስቲያን መንገር ነው። ለቤተክርስቲያን ማለትም ለመላው አማንያን መንገር ነው። በአጠቃላይ መጽሐፍ ቅዱስም የሚያስተምረን የእግዚአብሔር መልእክተኞች ነቢያትም ሆኑ ሐዋርያት” ይሄይሰነ ናድሉ ለእግዚአብሔር እምነአድልዎ ለሰብእ’ ለሰው ከምናደላ ለእግዚአብሔር ማድላት ይሻለናል። በማለት ከዓለማውያን ጋር አንገት ላንገት እየተናነቁ አልፏል። የመጨረሻው ነቢይ፡ ካህን፡ ሐዋርያን የሆነው የዘካርያስ ልጅ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ያደረገውን አስተውሉ።”ኢይደልወከ ታውስብ ብእሲተ እኁከ ፊልጶስ” የወንድምህን የፊልጶስን ሚስት ልታገባ አይገባም ብሎ ሄሮድስን እንደተቃወመና በዚህም ምክንያቱ ሰማዕትነት እንደተቀበል እንገነዘባለ። ወደ አባቶቻችን ስንመለስም 13ኛው መቶ ፍለዘመን የነብሩ እነ ቅዱስ አኖሬዎች እነ ቅዱስ ፊሊጶስ፡ አስታውሱ። አፄ ዓምድ ጽዮን የአባታቸው ሚስት( እቅብት) ባገቡ ጊዜ ፊት ለፊት ንጉሡን እንደተቃወሙና በዚህም ምክንያት ያለ ምሕረት እንደተገረፉ ከሚኖሩበትም ገዳም ደብረ ሊባኖስ ወድ ትግራይና ኤርትራ ገዳማት እንደተስደዱ ታሪክ ያስተምረናል። አሁኑም ቢሆን አባቶቻችን የንስሐ ልጆቻቸው ሃይማኖታቸውንና ቀኖናውን ሲጥሱ የሚያደርጉትና እያደረጉት ያለ ተግባር ነው። ብቻ እኛ ሁሉ ጊዜ የሌላ ሰው ታሪክ አደናቂዎች ስለ ሆን እንጂ ወንድሞቼ አንድ የካቶሊክ ጳጳስ ይህ በማድረጉ ታላቅ ነግር አይደለም። ስለዚህ ማወቅ ያለባችሁ አባቶቻችን ጳጳሳትም ሆኑ ካህናት ይቅርና በምድራዊያን በለሥልጣናት በመላእክትም ሥልጣን እንዳላቸው አትርሱ። ይህ በምልበት ጊዜ ግን ከስንዴ እንክርዳድ እንደሚግኝ ለሆዳቸውና ለምድራዊ ረብ የሚቆሙ፡ ደንታ የለላቸው ተረፈ ይሁዳ እንዳሉ ሳልዘነጋ ነው። እንደ ቤተክርስቲያን ግን እባካችሁ በራሳችሁ አባቶች መንፈሳዊ ሥራ ተደነቁ ሥራቸውም ተከተሉ። እባካችሁ እነ አቡን ጴጥሮስን አቡን አብርሃም ወዘተ አስቡ።

ወስብሐት ይደሉ ለአብ ወወልድ ወመንፍስ ቅዱስ አሜን!!

kale Hawaryat said...

ወንድሞቼ ይህ አዲስ ነገር ነው ወይ? መጽሐፍ ቅዱስ አታነቡም ወይ? የካቶሊኩ ጳጳስ አንዲ ታዋቂ ፓለቲሻን ያውም በምሥጢር እንዳይቆርብ ከለከለው ወይም እንዳይቆርብ አስጠነቀቀውና ታላቅና አስገራሚ ነው ወይ? በእርግጥ እንደ ቅዱስ ወንጌሉ ቃል። በመጅመሪያ ብቻውን አድርጎ መምከሩ ተገቢ ነው። ከዚያ ካለፈ ግን ሌሎች ሰዎች በመጨመር መምከር ካልሰማም በመጨራሻ ለቤተክርስቲያን መንገር ነው። ለቤተክርስቲያን ማለትም ለመላው አማንያን መንገር ነው። በአጠቃላይ መጽሐፍ ቅዱስም የሚያስተምረን የእግዚአብሔር መልእክተኞች ነቢያትም ሆኑ ሐዋርያት” ይሄይሰነ ናድሉ ለእግዚአብሔር እምነአድልዎ ለሰብእ’ ለሰው ከምናደላ ለእግዚአብሔር ማድላት ይሻለናል። በማለት ከዓለማውያን ጋር አንገት ላንገት እየተናነቁ አልፏል። የመጨረሻው ነቢይ፡ ካህን፡ ሐዋርያን የሆነው የዘካርያስ ልጅ ቅዱስ ዮሐንስ መጥምቅ ያደረገውን አስተውሉ።”ኢይደልወከ ታውስብ ብእሲተ እኁከ ፊልጶስ” የወንድምህን የፊልጶስን ሚስት ልታገባ አይገባም ብሎ ሄሮድስን እንደተቃወመና በዚህም ምክንያቱ ሰማዕትነት እንደተቀበል እንገነዘባለ። ወደ አባቶቻችን ስንመለስም 13ኛው መቶ ፍለዘመን የነብሩ እነ ቅዱስ አኖሬዎች እነ ቅዱስ ፊሊጶስ፡ አስታውሱ። አፄ ዓምድ ጽዮን የአባታቸው ሚስት( እቅብት) ባገቡ ጊዜ ፊት ለፊት ንጉሡን እንደተቃወሙና በዚህም ምክንያት ያለ ምሕረት እንደተገረፉ ከሚኖሩበትም ገዳም ደብረ ሊባኖስ ወድ ትግራይና ኤርትራ ገዳማት እንደተስደዱ ታሪክ ያስተምረናል። አሁኑም ቢሆን አባቶቻችን የንስሐ ልጆቻቸው ሃይማኖታቸውንና ቀኖናውን ሲጥሱ የሚያደርጉትና እያደረጉት ያለ ተግባር ነው። ብቻ እኛ ሁሉ ጊዜ የሌላ ሰው ታሪክ አደናቂዎች ስለ ሆን እንጂ ወንድሞቼ አንድ የካቶሊክ ጳጳስ ይህ በማድረጉ ታላቅ ነግር አይደለም። ስለዚህ ማወቅ ያለባችሁ አባቶቻችን ጳጳሳትም ሆኑ ካህናት ይቅርና በምድራዊያን በለሥልጣናት በመላእክትም ሥልጣን እንዳላቸው አትርሱ። ይህ በምልበት ጊዜ ግን ከስንዴ እንክርዳድ እንደሚግኝ ለሆዳቸውና ለምድራዊ ረብ የሚቆሙ፡ ደንታ የለላቸው ተረፈ ይሁዳ እንዳሉ ሳልዘነጋ ነው። እንደ ቤተክርስቲያን ግን እባካችሁ በራሳችሁ አባቶች መንፈሳዊ ሥራ ተደነቁ ሥራቸውም ተከተሉ። እባካችሁ እነ አቡን ጴጥሮስን አቡን አብርሃም ወዘተ አስቡ።

ወስብሐት ይደሉ ለአብ ወወልድ ወመንፍስ ቅዱስ አሜን!!

Orthodox unit said...

Kale Hawariat, You are right. I agree with you as far as the priest is right.

Unknown said...

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን !!

ውድ ኦርቶዶክሳዊያን :
እኔ መምህር ዘበነን በቅርበት ባላውቀውም ትምህርቱንና የራዲዮ ፕሮተግራሙን እከታተላለሁ። በጣም ጥሩ ትምህርት የሚሰጥ መምህር ነው አሁንም እግዚአብሔር በእድሜ በጸጋ ይጠብቀው። ሆኖም አሁን አንዳንድ ሰዎች አውቀውም ሆነ ሳያውቁ ስሙን ሲያጠፉ አያለሁ። በመጀመሪያ መምሀር ዘበነ እንደማናችንም ሰው በመሆኑ ስህተት ሊፈጽም ይችላል። ሆኖም አሁን እየተከሰሰባቸው የሚገኙት ነግሮች ግን ትምህርቱን በሚቃዎሙ ሰዎች እየደረሱ ያሉ መሆኑን አትዘንጉ። በአንድ የራዲዮ ፕሮግራሙ ይህ ሁሉ ክስ ሳይደርስበት ገና ወደ ሰላሳ የሚሆኑ የፕሮቴስታንት ድርጅት መሪዎች ስሙን ለማጥፋትና ከአገልግሎቱ ለማደናቀፍ እንዳቀዱ መረጃ እንደደረሰው ተናግሮ ነበር።ያን በተናገረ በጥቂት ጊዚያት ውስጥ እርሱን የሚቃወሙ ጽሑፎች ማየቴ በጣም ገርሞኛል ::

እርሱን የሚቃዎሙ ሁሉ ፕሮቴስታንት አለያም ታድህሶዎች ብቻ አይደሉም ነገር ግን ሳያውቁት አንዳንድ ጥቃቅን ነገሮችን ይዘው የእነርሱን ዓላማ የሚደግፉ ኦርቶዶክሳዊያንም ይገኛሉ። እኔ ለምን ተተቸ የሚል እምነት የለኝም ነገር ግን እዚህ የሚቀርቡት ሁሉ አገልግሎቱን ለማደናቀፍ እንጂ በእውነት አለ የሚባለው ችግር እንኳን በጣም የወረደ ነው ::

መስቀልን በተመለከተ : መሰቀሉን ስጡኝ ብሎ አልተቀበለ : አንድ ሰው ስጦታ ሲሰጠው ይቀበላል ::
በእርግጠኝነት መስቀሉ እንዲመለስ የሚፈልጉ ለመስቀል ክብር የሌላቸው ጭምር ናቸው። በመጀመሪያ እንደ እርሱ ያሉ ህዝብን በማገልገል ላይ ያሉ መምህራን እንደማበረታቻ ያባቶቻቸውን መስቀል ቢሸለሙ የሚያስከፋው ነገር ምንድን ነው። ቅርስ ቅርስ የምንለው ቅርሳችንን እየዘረፍን እየሸጥነው አይደለምን። ያም ሆኖ ይመለስ ከተባለ እንኳን እርሱ እምቢ እንደማይል እርግጠኛ ነኝ። አንድ ሰባኪ ከራሱ ይልቅ ለቤተ ክርስቲያኑ እና ለህዝቡ የሚያስብ ነውና :: እናም ለምን ወሰደ ተብሎ ሊከሰስ አይገባም መሰጠት ካልነበረበት የሰጡትን አባቶች ክሰሱ እርሱን ግን አትናገሩ ዝም ብሎ ክስ ይሆንባችሗል።
ትምህርቱን በተመለከተ ::

ትምሀርቶቹ በተለይ መናፍቃንን በተመለከተ የሚያስተምራቸው በጣም የሚያሰገርሙና የሚያስደምሙ ናቸው ለዚህ ነው መናፍቃን ማንነታቸውና ውሸታቸውን ስለሚያገልጥባቸው የሚያሳድዱት። ይህ የራሳቸው አቋም ነው ማነኛውንም እነርሱን የሚቃዎምን አካል ማሳደድ የእነርሱ አቋም ነው :: ውሸታቸውን ስለገለጠ ትክክለኛውን ክርስቶስ በመጽሐፍ ቅዱስ መሰረት ስላሰተማረ ይሰድቡታል ያሳድዱታል :: ይኸውም ከእነርሱ የሚጠበቅ ነገር ስለሆነ የሚያስገርም ነገር የለውም ::

Unknown said...

እና እኛም ሳናውቀው የእነርሱ ተባባሪ በመሆን የእግዚአብሔርን አገልግሎት እንዳናደናቅፍ :: ይልቁንም ህብረት አንድነትን መፍጠር ይገባናል። በመካከላችን ያሉ መለያየቶችን ልናስወግድና ለአንዲት ቤተ ክርስቲያን እድገት ለትክክለኛው የእግዚአብሔር ቃል መስፋፋት ልንሰራ ይገባል። ማህበረ ቅዱሳን ፤የግል ሰባኪ ፤ የዚህኛው ሲኖዶስ፤ የዚያኛው ሲኖዶስ ፤ ገለልተኛው ቤተ ክርስቲያን በመባል ራሳችንን ሳንከፍል ለአንዲት ቤተ ክርስቲያንና እውነት እንቁም። እርግጥ ነው የፓለቲካው ነገር በመካከላችን ገብቶ እንደከፋፈለን ይታወቃል። ግን ይህ ዛሬ ይበቃል። በመካከላችንም አንዳንድ ልዩነቶች ይታያሉ ግን ልዩነቶቹ መሰረታዊ እምነታችን ላይ የሉም አስተዳደራችን ላይ እንጂ።፡እና ከሁሉም ይልቅ መቅደም የሚያስፈልገውን በማስቀደም ፍቅርን እናድርግ።
የሰላም አምላክ ኢየሱስ ክርስቶስ በፍቅር እንድንኖር ይርዳን አሜን !!

Anonymous said...

ግን አንድ የቤተ ክርስቲያን አባት እንዲህ አይነት ተቃውሞ ሲበዛበት በተለይም በስነምግባር ዙሪያ እራሱን ሊመረምር ይገባል። መናፍቃንን በመቃወም ቀሲስ ዘነበ መቼም የመጀመሪያው ሰው አይደለም። ስለዚህ ቀሲስ ዘነበ ከሚሰጠው በጎ አገልግሎት በተጨማሪ ቆሞ ሊያስብ ይገባል እላለሁ

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)