November 26, 2009

የአዲስ ነገር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅና ዘጋቢ የፓትርያርኩን ስም በማጥፋት ወንጀል ተከሰሱ


(በታምሩ ጽጌ)
በየሣምንቱ ቅዳሜ እየታተመ የሚወጣው አዲስ ነገር ጋዜጣ ዋና አዘጋጅና ዘጋቢ "የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስን ስም አጥፍታችኋል" በሚል የስም ማጥፋት ወንጀል ክስ ተመሰረተባቸው፡፡ ዋና አዘጋጁ ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ እና ዘጋቢው አብርሃም በጊዜው ለፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ለአራዳ ምድብ ችሎት በፌዴራል ዐቃቤ ሕግ መስከረም 25 ቀን 2002 ዓ.ም. በተፃፈ የክስ ቻርጅ የተከሰሱ ቢሆንም፤ ህዳር 11 ቀን 2002 ዓ.ም. መከሰሳቸውን መስማታቸውንና ህዳር 14 ቀን 2002 ዓ.ም. የክስ ቻርጁን ከነመጥሪያው መውሰዳቸውን ገልፀዋል፡፡

ተከሳሾቹ በ1996 ዓ.ም. የወጣውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ 32(1)(ሀ)፡ 613(3) እና በአዋጅ ቁጥር 590/2001 አንቀጽ 6(1) ስር የተመለከተውን በመተላለፍ፣ በመልካም ስም ላይ ከባድ ጉዳት ለማድረስ በማሰብ ግንቦት 15 ቀን 2001 ዓ.ም. የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ያካሄደው ስብሰባ (ጉባኤ) ያሳለፈውን ውሳኔ "አዲስ ነገር" በሚባለው ጋዜጣ ላይ የፓትርያርኩን ስም ማጥፋታቸውን የክስ ቻርጁ ይገልፃል፡፡

"አቡነ ጳውሎስ ከአስተዳደር ኃላፊነት በሚያገል በሲኖዶሱ ፀደቀ፤ በሲኖዶሱ መካከል የተፈጠረው ችግር በይቅርታ እንዲፈታ እንቅፋት የሆኑት ፓትርያርኩ ናቸው፤ በሲኖዶሱ የተቋቋመው የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የፓትርያርኩን አስተዳደራዊ የበላይነት በማስቀረት መንፈሳዊ አመራር ብቻ እንዲሰጡ ያደርጋል" በማለት የፓትርያርኩን ስም በማጥፋታቸው መከሰሳቸውን የክስ ቻርጁ ይገልፃል፡፡
WEDNESDAY, 25 NOVEMBER 2009

4 comments:

Anonymous said...

MK take a look at this and try to respond:
http://www.ethiopianorthodox.org/amharic/miscellenous/betekirstianbefetena.html

Ze Hayk Estifanos said...

Aba Woldetinsae is one of the monks who was linient when "churches" introduced rock and roll music instruments like Piano ,Guitar and etc.Even he was resisting those who request for the removal of these instruments from the church

I can mention so many places for this.
Do you think that he can be the same with Mahibere Kidusan.
He can go his own way, but i feel it is hard to accept him in the conventional Orthodox churches.
His fans are telling us that he was educated in Tana monasteries. But i want to know if there is any monk from tana monasteries who taught and follow the same foot step like him. Do Tana monasteries have Piano and Guitar???

Anonymous said...

enante aba [pawlos endihu endetasesachu ltnoru new? metatarek stchlu sattareke mastarek stchlu satastarku endehu tkeru? tnbetu mefesmum algebachum memenun awekachhut memen bmesetachu genzeb tefagachuyezih memen amlak kdus egziabher yfred sertew endaybelu dhoch gazetegnochen tkesalachu enqwan kfu eyaderegu smme metfat kerto getachn medhanetachn eyesus krsetosm nsuhu tamtaul erso keamlak ybeltalu menekuse newot yemote sew tenesto sewnn mekses ychlal? lehulum amlak yfredew amen

Anonymous said...

ሰላም ለ ኢትዮጵያ ኦርቶዶስ ተዋህዶ ሃይማኖት ተከታዮች በሙሉ እንዲሁም የማኅበረ ቅዱሳንናየደጀላም አዘጋጆች፡ነቢዩ ዳዊት እንደተናገረው ልጆቼ ኑ ስሙኝ እግዚአብሔርን አስተምራችሁኋለሁ።ሕይወትን የሚፈቅድ ሰው ማነው?በጎ ዘመንም ለማየት የምትወድ? አንደበትህን ከክፉ ከልክል ከንፈሮችህን ሽንገላን እንዳይናገሩ ይላል ታዲያ ከማን ወርሰውት ነው በአባቶቻችነ ላይይ መጥፎ ስም እየለጠፉ ቤተ ክርስቲያንንን የሚያፈርሱ ራሳቸውን ረፀ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንና ሊቃውንት ሁንው እያሉ ሌላውን ይኮንናሉ እነሱ የሚሳደቡት ስድብ ጸሎትና ምርቃት አደረጉት ቅዱሱ ፓትሪያርካችንም በአለም ተወደው ተደንቀው ሲሸለሙ ማኩረፉ ምን አመጣው እንግዲያስ በእናንተ ግፍ ምክንያት አምላክ ከፍ ከፍ አደረጋቸው እናንተ የምትሳደቡበት ኣንደበት የተሰጣችሁ እኮ ከኣባታችሁ ነውምክንያቱ የስድብ አንደበት የተሰጠው ያው እሱ ነው። ኣሁንም እባካችሁ ንስሐ ግቡ አምላክ መሐሪ ነው ይቅር ይላችኋል አሁንም እባካችሁ ቤተ ክርስቲያንዋን አታፍርሱዋት በናንተ ሰበብ ብዙ ሕዝብ ወደ መናፍቃን ቤት እየሄዱብን ነው። ስለሆነም እርስ በርራችን እንከባበር እንጸላለይ የቤታችንን ገበና እንደ ሴም እንሸፍን እንጂ እንደ ካም እራቁትዋን አናውጣት

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)