November 6, 2009

የቤተ ክህነቱ መግለጫና ቃለ ጉባዔ ላይ ብፁዓን አባቶች አልፈረሙበትም፤ ታዲያ የማን ፊርማ ነው የተቀመጠው?

(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 5/2009)፦ በቅርቡ በዌብሳይት “ዜሮክስ” ተደርጎ የተለቀቀውና ማህበረ ቅዱሳን ላይ የተላለፈውን ውሳኔ ለማስተላለፍ በአባ ሰረቀ ብርሃን ወልደ ሳሙኤል የተሰራጨው ቃለ ጉባዔ የቅዱስ ፓትርያርኩን ጨምሮ ሌሎችም ፊርማዎች የተደረደሩበት ሲሆን ፊርማቸውን ሊያኖሩበት የሚገባቸው ብፁዓን አባቶች እንዳልፈረሙ መናገራቸው ታውቋል። ይህንኑ ጉዳ ይ “ደጀ ሰላም” መዘገቧ ይታወሳል። አሁን ግን እርግጠኛ በሆነ መልኩ ፊርማዎቹ አባቶቻችን የፈረሟቸው አለመሆናቸው ታውቋል።

ታዲያ የቅ/ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን አባቶችን ፊርማ እያስመሰለ የፈረመው ማን ነው? ይህ ወንጀል ልክ እንደ በር ሰበራውና ማስፈራራቱ ዝም ብሎ ሊታለፍ ነው? እነዚህ ከ18 ያላነሱ ፊርማዎች የማን መሆናቸው ነው?
ቸር ወሬ ያሰማን፣
አሜን

57 comments:

Anonymous said...

This is a very big crime. Mahibere Kidusan do have the right to sue . why did they keep quite upon this crime????

Can this case be forwarded to radio stations like VOA so that the fathers can give their testimony upon the forged signature?

Forensic evidence can help to know who forged the signatures.
This should not be seen as something simple. Please Deje Selam do something to expose this fact at least to major radio stations like Germany Amaharic service, VOA , and etc who do transmit their programes in Ethiopia

Anonymous said...

ጥሩ ጥያቄ ነዉ ያቀረባችሁት ደጀሰላማውያን “ታዲያ የቅ/ሲኖዶስ አባላት ብፁዓን አባቶችን ፊርማ እያስመሰለ የፈረመው ማን ነው?”
መልሱ “አባ” ‘ሰ’ረቀ ወልደ ሳሙኤል እና መሰሎቹ ናቸዉ።
በሕይዎቴ በጣም የምሳዝነኝ ነገር ቢኖር በዚሁ ሰው የተነሳ “ቆብን” መጥላቴና ሰዎቹንም ማመን አለመቻሌ ነው። እውነተኛ መነኩሴ ሆኖማ ቢሆን ኖሮ ለዓለም የሞተ ይሆን ነበር የአባው ግን የተለየ ነው።

ክብሮም

SendekAlama said...

+++
እስከዚህ ድረስ መዝቀጥ ለፈለገ 'መለኩሴ' እኮ ፊርማ ማስመሰል በጣም ቀላል። ማስመሰል ብቻ ሳይሆን በቀጥታ ራሱን ማግነኝትም ይቻላል። በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት እኒህ አባቶች ፊርማቸውን ያሳረፉበትን ደብዳቤ ማግኘት ብቻ በቂ ነው። ያንን ፊርማ ቆርጦ እነ አባ ሰረቀ ባዘጋጁት ደብዳቤ ላይ ለጥፎ ስካን ወይም ኮፒ ማድረግ ብቻ በቂ ነው።

ይብላኝ

Anonymous said...

‘አባ’ ሰረቀ ብርሀን ሲባል ትዝ የሚለኝ ‘አባ’ ጨጓሬ የሚባል ትል ነው ሁለቱም ማን እንዳመነኮሳቸው ባላውቅም ‘አባ’ ተብለው ተሰይመዋል ግን ስራቸው ይኮሰኩሳል።

tesfa said...

ጳጳሳቱ መፈረማቸው አለመፈረማቸው አያሳስበንም መገለጫው ትክክል ነው
በጠቅላላው ማህበረ ቅዱሳን በማደራጃው ስር ሆኖ መሥራት አለበት እነዚያ የርግማን መጽሄቶቹም በመምሪያው ሥር ማለፍ አለባቸው ፤እንደዚሁም ኦዲት መደረግ አለባቸው የሚል ሐሳብ የያዘ መግለጫ ነው።
ይህ ነገር እንደ ልብ ወንጀል ለመሥራት አያስችልም ነገር ግን ቤ/ክርስቲያንን ለማገልገል በቂና ጥሩ መመሪያ ነው ምነው መታዘዝ አቃትችሁ?
እኔ በዚህ ደብዳቤ የሚጎዳ የለም ባይ ነኝ።
1ኛ ወንጌል እንቅፋት አይኖርበትም
2ኛ ትውልዱ የስሕተት ትምሕርት አይማርም
3ኛ የዘራአ ያቆብ ፖለቲካ ቤ/ክርስቲአያኒቱን እየለቀቀ ይመጣል
4ኛ እግዚአብሔር እንደሚገባው ይከበራል።
5ኛ እውነተኛ የውንጌል ልጆች አይሰደዱም።
6ኛ ጠቅላላ ለውጥ በሀገሪቱ ይመጣል
ለዚህ ሁሉ እንቅፋት የነበረው የ15ኛ ክፍለ ዘመን ፖለቲካ በሃይማኖት ሽፋን ሊያካሂድ የሚፈልገው ማህበረ ቅዱሳን ወሰን ተደርጎለታል።

አሣ ጎርጓሪ ዘንዶ ያወጣል እንደሚባለው አቡነ ጳውሎስን ለመገልበጥ ያሴረው ማሕበረ ቅዱሳን በራሱ ላይ ዞሮ ይኸው ይጮሃል እንጂ ቤ/ክርስቲያንስ አትጎዳም
መጽሐፉ እንዲህ ይላል "ግበ ከረየ ወደሐየ ወይወድቅ ውስተ ግብ ዘገብረ"

ጉድጓድን የሚቆፍር ራሱ ይገባበታል ማለት ነው
ማበረ ቅዱሳን ለተሐድሶዎች የቆፈረው ጉድጓድ ራሱ ተቀበረበት

አሁንም የምትጮኹት ጩኸት ገመዳችሁን ያጠብቀው ካልሆነ በስተቀር ለውጥ አያመጣላችሁም

ቸር ወሬ ያሰማን

Belayneh from Addis Ababa said...

አዬ!! እናንት በየጊዜው የሐሰት ምስክርነት የምትሰጡ ምን ነው ቆም ብላችሁ ብታስቡ? አላዝንባችሁም ነገር ግን በጣም አዝንላች|ለሁ። እንዴት የአባቶችን ፌርማ አስመስሎው አባ ሰረቀብርሃን ይፈርማሉ ትላላችሁ? የራሳችሁን ተንኮል ነው፡ የምትነግሩን አይደልም? በመቁረጥና በማጣበቅ የሰውን ስም ለማጥፋት እንደምትጥሩ መሰላችሁ? ከሆነ በጣም ተሳሳታችሁ። ይህን ያህል ለካ ሞኞች ናችሁ? ል ዑል እግዚአብሔር አስተዋይ ልብ ይስጣችሁ። እውነቱን ልንገራችሁ። በተላይ በአባ ሰረቀብርሃን የሐሰትና የዓመጽ ቃል የምትሰንዝሩ።

አባ ሰረቀብርሃን እናንተ እንደምትገምቷቸው አይነት ሰው አይደሉም። አባ ከታወቀው ቅዱስ ገዳም ደብረ ዓባይ ያደጉ፡ የመንኮሱ በዚሁ በአባቶች ሊቃውንት ዘንድ የተማሩ የቅኔው ማዕበል፡ ስለ እውነት ሕይወታቸውን የሚሰጡ የዘመናችን ምርጥ አባት ናቸው። ዛሬ ቅዲስ ሲኖዶስን እያተራመሱ የሚገኙ በውጭ አገርና በአገር ውስጥ የነበሩ ባለ ልዩ ልዩ ፎቆችና የአክሲዮን ባለቤቶች ሲኖኑ፡ እውንተኛው ሊቅ አባ ሰረቀብርሃን ግን ገዳማትን፡ የአብንት ትምህርት ቤቶችን፡ አባት እናት የሌላቸው ሕጻናትንና አረጋውያንን በመርዳት ላይ ይገኛሉ። ለመሆኑ እስኪ የጎንደር ባእታ የአkkም ትምህርት ቤት፡ የደበረ ዓባይ የቅዳሴ ት/ቤት፡ ጥንታዊትና ታሪካዊት ከሆነችው አክሱም እየተሰራ ያለውና በማዕከሉ እየተረዱ ያሉትን መጠየቅና በዓይን ማየት ይቻላል። የተላለፈ ውሳኔና መመሪያ ሕጋዊ እንደሆነ አያጠራጥርም። ሌላው ለምንድነው አፈረምንም ያሉትን ጳጳሳት ስም ያልጠቀሳችሁ? ስማቸው እንዳይገልጥ ፈርተው ነው። ይህ አይሆንም እንጂ ከሆነ አባቶች አይደሉም ማለት ነው። እንደተባለውም በሕግ መጠየቅ ይችላሉ። እውነቱን ልንገራችሁ? መሰረታዊ ችገግር ያላቸው አባቶች ስለዚህ ጉዳይ ወደ ሲኖዶስ አቅርበውት እንደነበር ታወቀዋል። ግን ምንም ሊያደርጉ አልቻሉም። ምክንያቱም የተወሰነው ሕጋዊነት ያለው ነውና።

ስለዚህ እውነተኞች ከሆናችሁ እስኪ ፊት ለፊት ቅረቡና እንነጋገር። በዚህ አጋጣም ለአባታችን የምናሳስበው እውነተኞች የቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንት፡ ትኦሎጂያን ፡የየአህጉረ ስብከቱ ስራአስኪያጆች. ሰባክያነወንጌል ካህናት፡ ዲያቆናት የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፡ ምእመናንና ምእመናት ከጎንዎ እንድሆኑ የተረዱት ስለሆነ፡ ጠላቶች አንዴ ትግሬ፡ አንዴ ዘረኛ፡ አንዴ መንኩሴ አይደለም፡ አንዴ ተሐድሶ፡ አንዴ መናፍቅ፡ አንዴ የፓትርያሪኩና የኢሃዴግ አሻንጉሊት ወዘተ ቢሎት የተለመደ የዓዞ እንባ ስለሆን ቅር ይበሎት። ሁሉ ለስሙና ለክብሩ ሲጥር ሕይወትዎን ለዚህ እውንት ስለሰጡ በጣም እናከብረዎታለን፡ እንወደዎታለን።

Aschalew ze Gonder said...

There is no another way to go for Mahber Kidusan than accepting this decision. The Association must follow the rule and regulation of the Church. Enough is enough. MK we know very well please do not drive the innocent people unto the wrong way. You know what you have been doing in the name of our church, you have been earning a lot of money for your personal packet. But thanks to the Almighty God, your sin is revealed throughout Ethiopia. So, take my advice. Please repent from your sine otherwise the Hand Of God is upon you. There is no bush for you to hide yourself. The truth will reveal you and you will be stood in front of us. Believe it or not you get it soon.
You have been drinking the blood of the innocent people for a long time. The blood of the brothers will bring you unto the judgment.. Return unto the Lord and repent from you sin. May God open your ear to hear the true word of God.

Mekonnen Ethiopian said...

ወይ ጉድ!!!!!! ፌርማው የእኛ አይደለም አሉ ሊቃነ ጳጳሳት ተባለ? ለመሆኑ እነማን ይሆኑ? እነ አቡነ ይስሐቅ ይሆኑ? እሳቸውማ አላየሁትም አላውቀም ብለው ተቃወሙ ተባልን አይደል ባለፈው በዚሁ ድህረገጽ። ምሪቱን ልብ ብላችሁ ተመልከቱ ዋና ስራአስኪጅ ናቸው በእርሳስ መስል እስክርቢቶ ለምክትሉ የመሩት፡ በሌላ በኩል ግን አላውቀውም አሉ ተባለ። ለምን ይሆን እንዲህ ያሉ? እኛ ግን እናውቃለን። ከአንድ መቶ ዓመት በላይ ያገኙትና በቅርብ ያጡትን . . . . ለማግኘት ነውና ጥረታቸው። መቸም ያለ እግዚአብሔር ቅዱስ ፈቃድ አይገኝም። በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ቴዎፍሎስ ጀመሩ አልተሳካም፡ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለሃይማኖት ሞከሩ አልተሳካም።
በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ጣሩ አልተሳካም። አሁን ደግሞ ተስፋ ሳይቆርጡ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ እየጣሩ ነው። ነግር ግን ያል እግዚአብሔር ቅዱስ ፌቃድ ምንም አይደረግም። ለምን እንደማይማሩ ግን አይገባንም፡ ከአሁን በፊት ከደብረ ሊባኖስ ግዳም ያልመነኮስ ፕትርክና አይሰጠውም ተብሎ ነብረ። ነግር ግን የግርማዊ ቀዳማዊ ሃይል ስላሴ ነፍስ ይማረ አሳፈርዋቸው። አሁንም ይህ ፈቃደ እግዚአብሔር ያልተጨመረበት ፍላጎት የትም አያደርሳቸውም። የዚሁ ማህበር ዋና ደብቅ ዓላማም ይህ ነው። ሌላ የለውም።

ስለዚህ ወንዶችና እውነተኞች አማኞች ከሆናችሁ ያሉትን በዝርዝር አቅርቡና እንስማቸው፤ ልብ በሉ ስብሰባው የሲኖዶስ ሲብሰባ አልነበረም። ጳጳሳት፡ ሊቃውንት፡ የየመምሪያው ሓላፊዎች፡ የመንግስት ባለስልጣናት፡ የማህበሩ አባላተ ወዘተ የነብሩበት ነው፡፡በዚህ የተገኙ ሁሉ የመፈረምም ሆነ ያለ መፈርም መብት አላቸው። አልፈርምም ያለ ካለ መብቱነው። የፈረመም መብቱ ነው። ዋና ቁም ነገሩ በስብሰባ ያለተገኙ ካሉና ያላሉት ቃል ከተነገር ያስማማናል። አለበለዚያ ግን አብሮ ውሎ አድምጦ፤ ተረድቶ ምንም ተቃውሞ ሳያሰማ ወጥቶ አልሰማሁም፡ አልፈረምኩም የሚለው፡፡ሐሳብ ዋጋ ቢስና የፈሪ ድምጽ ነው።

ሰለዚህ ማጭበርበር ይቅርባችሁ። ምከሬ ነው።

Anonymous said...

Si es verdad lo que se dio que pena
porfavor es mejor que seamos responsables DIOS nos bendiga atodo el mundo.

Anonymous said...

Hi DS,

MK do your work, this year temptation is great chance to expand the services. Many people overall the globe have open their eye. Thanks God.

Anonymous said...

የአዲስ አበባው ጦማሪ
ስለአባው አትከራክር እሳቸው የሚፈልጉት እንደ ማ.ቅ ጠንካራ ማህበር ሳይሆን እንደ አዲስ አበባው አይነት ወጣት ለሰላም ፎረም ነው::የቤተመንግስት ዘመዶቻቸው የሚዘውሩት ዓይነት::እርሳቸውንም ጝደኞቻቸውንም ሰምቻቸዋለሁ እዚህ ቨርጂንያ ::አምና ያመጡትን ዲያቆን ሳምሶንንም ሰምቻዋለሁ:እኔ ተራ ምዕመን ነኝ ለእኔ መሰናከል እንኳ አይጠነቀቁም-ሲያወሩ::ከአንድ መንፈሳዊ አባት ነኝ ከሚል ሰው ጨካኝ ጥላቻ ከአፉ ይወጣል ዘንድ አይገባም::እንደ እኔ ዓይነት ተራ ምዕመን ደደብ እንኳ ቢሆን ሊታዘብ እንደ ሚችል መገመት ይገባል::ከክርስቲያን ሰው ነፍስ ውስጥ ጨካኝ ጥላቻ ሊንጸባርቅ አይገባም::የአዲስ አበባው ጦማሪ የእርሳቸውን ገድል እንደ ዘረዘርክ ማ.ቅ የሰራውን በጎ ሥራም ልትናገር ይገባሃል::በእንዲህ ዓይነት የተምታታ ምስክርነት እዚህ ሰ.አሜሪካ ከቤ/ክ እንዳይለዩ የምንነግራቸው ልጆቻችን ለሚያነሱት ጥያቄ መልስ መስጠት ተቸግርናል::እኛ ስንናግር ጨካኞች ነን::አውደ ምህረት ላይ ቆመን ነፍሳችንን ውስጥ ያጨቅነውን ጥላቻ ስንዘረግፍ ትንሽ ቅር አይለንም::ለእግዚአብሔር መንግስት እየሰብኩ ጥላቻን ምን አመጣው !!?

Anonymous said...

ወይ የኛ ዘመን!... ምን ማለት ይቻላል? ለነገሩ ሰይጣን የገባበት ሠው እና ጥላቻ ያለበት ሰው እንኳን ፊርማ ማስመሰልና የሠውን ነፍስ ለማጥፋት ወደ ኋላ አይልም፤ እነ ተስፋም ጥላቻቸው ስር የሰደደ ስለሆነና የእግዚአብሔር ቸርነት ካልታከለበት በስተቀር ከዚህ መላቀቅ ከባድ በመሆኑ፤ “ጳጳሳቱ መፈረማቸው አለመፈረማቸው አያሳስበንም…” እንዲሉ እና አጋርነታቸውን እንዲገልጹ አድረጓቸዋል። ለሠዎቹ መጨረሳቸው ስለማያምር ቢታዘንላቸውም፤ማኅበረ ቅዱሳኖች እናንተን ግን ደስ ሊላችሁ ይገባል። የመነኩሴው ነገር ያበቃው እኮ በአዲስ አድማስ ላይ እንደተገለጸው ስብሰባውን ማኅበረ ቅዱሳን ነው የጠራው ሲሉ ነው። ታዲያ ለዚህ አይነት ሠው ሊታዘንለት እንጂ ምን ማለት ይቻላል? እባካችሁ እናንተ ግን እውነት የሚገለጥበት የብርሃን ቀን እስኪመጣ በጽናት መቆም እና ሥራችሁን መስራት አለባችሁ። ለሁሉም ነገር አምላክ ከእናንተ ጋር ይሁን!

ችር ወሬ ያሰማን

Estifanos the Virginia said...

From Estifanos the Virginia

O!! My goodness!! Save us Lord from the tongue of the enemy: this is for the 11th commentator. I wish me new you. The holy bible says “the light has come into the world, and men loved darkness rather than light, because their deeds were evil. for everyone practicing evil hates the light and does not come to the light, lest his deeds should be exposed” Janh3:18-19 I thing you are trying to criticized to Mekonnen the who delivered to us the good information, You see !! I live in Virginia I have been known to Aba Serekebrhan for a long time. He is the man of wisdom and the lover of his enemy. I never heard any bad words from his mouth except the word of God. You said that “አምና ያመጡትን ዲያቆን ሳምሶንንም ሰምቻዋለሁ:እኔ ተራ ምዕመን ነኝ ለእኔ መሰናከል እንኳ አይጠነቀቁም-ሲያወሩ:: ከአንድ መንፈሳዊ አባት ነኝ ከሚል ሰው ጨካኝ ጥላቻ ከአፉ ይወጣል ዘንድ አይገባም:: እንደ እኔ ዓይነት ተራ ምዕመን” please read it again and again. What do mean about this? Are you saying that Diyakon Samson was brought Virginia? If you say yes, you are a liar and the seed of the liar and murder name devil. What did you hear from Deacon Samson? And what did you hear from Aba too. You are saying that” it doesn’t expect from the spiritual Father” what is that? But I agree with your saying. You know nothing about the truth, because you are the seed of the liar and murder.

Dear Mekonnen Please keep going posting the truth. As long as I and many my brothers and sisters live in Virginia, we can handle the false allegation of Aba Serekebrhan May the true God bless those who are fighting against the enemy of our true Fathers who are working hard day and night to expose the truth.

Anonymous said...

"አባ" ሰረቀ፡ተጠሪነታቸው፡ለአቶ፡አባይ፡ፀሐዬ፡
መሆኑን፡ከተረዳን፡የሸፍጡ፡ሥር፡መሠረት፡የት፡
እንደሆነ፡ማወቁ፡አያዳግትም።

እውነተኛ፡የቤተ፡ክርስቲያን፡ኣባቶች፡የቀያፋ
ን፡የክህደትና፡ውንጀላ፡ሰነድ፡እንደማይፈርሙ፡
እናውቃለን።በማህበረ፡ቅዱሳን፡ላይ፡የተቃጣው፡
በነርሱም፣በቤተ፡ክርስቲያናችንና፡በተዋሕዶ፡እ
ምነታችንም፡ላይ፡እንደተቃጣ፡እያንዳንዳቸው፡
በሚገባ፡ያውቁታል።

እኛም፡በደንብ፡እንውቃለን።

መድኃኔ፡ዓለም፡ተዋሕዶ፡ሃይማኖታችንንና፡እውነ
ተኛ፡አገልጋዮቿን፡ከመጣብን፡መዓት፡ይጠብቅልን።

አሜን፤አሜን፤አሜን።

ሳሙኤል፡ዘአሰቦት።

Anonymous said...

enemy. I never heard any bad words from his mouth except the word of ፡አባይ፡ፀሐዬ. You said that “አምና ያመጡትን ዲያቆን ሳምሶንንም ሰምቻዋለሁ:እኔ ተራ ምዕመን ነኝ ለእኔ መሰናከል እንኳ አይጠነቀቁም-ሲያወሩ:: ከአንድ መንፈሳዊ አባት ነኝ ከሚል ሰው ጨካኝ ጥላቻ ከአፉ ይወጣል ዘንድ አይገባም:: የምትጮኹት ጩኸት ገመዳችሁን ያጠብቀው ካልሆነ በስተቀር ...እንደ እኔ ዓይነት ተራ ምዕመን በጽናት መቆም እና ሥራችሁን መስራት አለባችሁ :: የ21ኛ ክፍለ ዘመን ፖለቲካ በሃይማኖት ሽፋን ሊያካሂድ የሚፈልገው አባ” ‘ሰ’ረቀ ወልደ ሳሙኤል - አአባይ፡ፀሐዬ ከጎንዎ እንድሆኑ የተረዱት ስለሆነ ጠቅላላ ለውጥ በሀገሪቱ ይመጣል::አዬ!! እናንት በየጊዜው የሐሰት ምስክርነት የምትሰጡ ምን ነው ቆም ብላችሁ ብታስቡ? please read it again and again. What do mean a tesfa said...bout this? Are you saying that
"tesfa ...=Aba Serekebrhan =Estifanos the Virginia =ሳምሶንንም="Estifanos the Virginia said... አባ ሰረቀብርሃን ‘አባ’ ጨጓሬ የሚባል ትል ነው ማለት አይገባም ነበር ::አዬ!!የአባቶችን ፌርማ አስመስሎው የቅኔው ማዕበል አባ ሰረቀብርሃን ቆፈረው::አባይ፡ፀሐዬን ማግኘት ብቻ በቂ ነው:ወንጌል እንቅፋት አይኖርበትም ::እውነተኞች የቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንት፡ ትኦሎጂያን ፡የየአህጉረ ስብከቱ ስራአስኪያጆች ሰባክያነወንጌል ካህናት፡ ዲያቆናት የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፡ ምእመናንና ምእመናት ከጎንዎ እንዳልሆኑ የተረዱት ስለሆነ፡ አባይ ፀሐዬን ማግኘት ብቻ በቂ ነው:: የዚሁ አባ ሰረቀብርሃን ዋና ደብቅ ዓላማም ይህ ነው-ጨካኝ ጥላቻ!!

Anonymous said...

=Estifanos the Virginia said... አባ ሰረቀብርሃን ‘አባ’ ጨጓሬ የሚባል ትል ነው ማለት አይገባም ነበር ::አዬ!!የአባቶችን ፌርማ አስመስሎው የቅኔው ማዕበል አባ ሰረቀብርሃን ቆፈረው::አባይ፡ፀሐዬን ማግኘት ብቻ በቂ ነው:ወንጌል እንቅፋት አይኖርበትም ::እውነተኞች የቤተክርስቲያኒቱ ሊቃውንት፡ ትኦሎጂያን ፡የየአህጉረ ስብከቱ ስራአስኪያጆች ሰባክያነወንጌል ካህናት፡ ዲያቆናት የሰንበት ት/ቤት ወጣቶች፡ ምእመናንና ምእመናት ከጎንዎ እንዳልሆኑ የተረዱት ስለሆነ፡ አባይ ፀሐዬን ማግኘት ብቻ በቂ ነው:: የዚሁ አባ ሰረቀብርሃን ዋና ደብቅ ዓላማም ይህ ነው-ጨካኝ ጥላ

Anonymous said...

የምትጮኹት ጩኸት ገመዳችሁን ያጠብቀው ካልሆነ በስተቀር ...::እንደ እኔ ዓይነት ተራ ምዕመን በጽናት መቆም እና ሥራችሁን መስራት አለባችሁ :: የ21ኛ ክፍለ ዘመን ፖለቲካ በሃይማኖት ሽፋን ሊያካሂድ የሚፈልገው አባ” ‘ሰ’ረቀ ወልደ ሳሙኤል - አባይ፡ፀሐዬ ከጎንዎ እንድሆኑ የተረዱት ስለሆነ ጠቅላላ ለውጥ በሀገሪቱ ይመጣል::አዬ!! እናንት በየጊዜው የሐሰት ምስክርነት የምትሰጡ ምን ነው ቆም ብላችሁ ብታስቡ? please read it again and again. What do
አባይ ፀሐዬን ማግኘት ብቻ በቂ ነው!!!!

Anonymous said...

I never heard any bad words from his mouth except the word of ፡አባይ፡ፀሐዬ.

Anonymous said...

Abba tsereqe is a merchent. The reason he doesn't like mk is he have an NGO engaged in collecting money in the name of supporting some monestries and we don't know how it works. no disclosure. on the other hand MK is doing the samething with desclosures. but Abba dragged Abbay Tsehaye to foulish and scared MK. when Abbay Tsehaye knew this for Abba " enen ayargegne"

gorgoreyos said...

kzinb" MAR"antibkm!!! kato ke seriq min titebkalchu?" EWNET"? dnkaim!!!

Anonymous said...

ወይ ጉድ!.... ምድረ መናፍቅ እኮ በቃ ..ሃይ የሚለው ጠፋ አይደል?!! ……ይሁን እሺ! አንድ ወንድሜ እንዳለው “…..ደሞ በኢንተርኔት ለመጠዛጠዝ ምን ችግር አለው!”… እውነትም፣ እድሜ ለደጀ ሰላም፣ ክፉዉንም ደጉንም እየሰማን መጠዛጠዝ ነው! ምን ችግር አለና!!
እኔ ግን በጣም የሚገርመኝ…. ከኋላ ሆኖ አለሁ አለሁ የሚለውስ፣ ድሮም የለየለት መናፍቅ ስለሆነ “እንደ ተስፋ አይነቱ ……አድክም!”…. መናፍቁስ እሺ! ጭራሽ የአባ ሰ’ረቀ ጠማማነት ግን የሚገርም ነው!! ድሮ በስደት ያለውን “እኔ አውቅልሃለሁ” ባይ ሆነው፣ ሲያታልሉት ኖሮ። አልበቃ ብሎአቸው ኢትዮጵያ ሄደው አባቶችን ማሳደድ፣ ድሮ በአደባባይ የተመሰከረላቸውን የራሳቸውን መናፍቅነት በሌላ ለመለጠፍ ሞከሩ…… ወይ ጉድ! ቤተክህነቱን እንዲያ ሲያምሱት እንደልብ ሲጨፍሩበት “ፈጣሪ አይቶ እንዳላየ ዝም ቢልም”…. እሳቸው በቃ “ካለኔ ሰው የለም” ብለው “ለጵጵስናም እበቃለሁ” ብለው ብዙ አባቶች እያሉ እሳቸው ‘በደፋርነት’ ጳጳስ ሊሆኑ ሲሉ….. አምላክ በረቂቅ ጥበቡ አለፋቸው….. ሰው እስቲ በገዛ እጁ ማፈሪያ ይሆናል!

አሁን ደሞ የሌባ አይናውጣ ሆነው የሰው መታወቂያ/ ፊርማ መስረቅ ጀመሩ!! እግዚአብሔር እንደው ሁሌም ይፈርዳል……… ምን አለ በሉ.. እኚህ “እውነትም እንደ አባ ጨጓሬ ‘አባ’ ብቻ” …ቀኑን ሙሉ በፈጣሪ ፍርድ ይቀጣሉ!! ያውም አይናቸው እያየ። በነገራችን ላይ ማኅበረ ቅዱሳንን ብቻ አይምሰላችሁ የሚከሱት… በሰ/ት/ቤት ያለውን ወጣትም አይወዱም! ወጣት ሲደራጅ ወጣት ሲበረታ ክፉ ወባ ያለባቸው ይመስል ያንገፈግፋቸዋል። ……ዛሬ ማኅበሩን “ኦዲት ተደረጉ/ እኔ በናንተ ስራ ልወደስ” በለው እንደጀመሩ ……(ለማኅበሩም ሆነ ለሰ/ት/ቤቶች ምንም በጀት እንዳልመደቡ ልብ ይሏል!! …ደሞ ልክ በጀት እንደሰጠ ሰው ‘ኦዲት ተደረጉ’ ሲሉ አያፍሩም) ነገም ሰ/ት/ቤቶችን፣ ሌሎች ማኅበራትን ኑ ኦዲት ላርጋችሁ ማለታቸው አይቀርም። እንደውም አንዴ “ኢትዮጵያ ያሉ ዘማሪያን ገቢያቸው ከፍ እያለ ስለሆነ እነሱም ይመረመራሉ”…. በማለት እዚህ አሜሪካ በቅርቡ የመጡ ጊዜ ሲናገሩ ተሰምተዋል። …….ወይ ጉድ! ደሞ ብለው ብለው ዘማሪያንንም ኦዲት ላርጋችሁ ማለታቸው ይቀራል ትላላችሁ? አስቡት እስቲ እነዚያ ምስኪኖች ጅማ እና በሻሻ ድረስ በራሳቸው ወጪ ሄደው ሕዝቡን ያጽናኑ! በየገጠሩ የሰርክ ጸሎት ጉባዔ እንዲጠናከር የበኩላቸውን የተወጡ!! የተዋሕዶ ምዕመናን እኮ እነሱን ባያገኝ ኖሮ በነ’ተስፋ’ የጴንጤ ጭፈራና ዘፈን እስካሁን አልቆለት ነበር እኮ። እግዚአብሔር መቼም በየጊዜው እንደአስፈላጊነቱ ሁሉን እያስነሳ ተዋሕዶን ይጠብቃታል። …………እናንተ ዝማርያን በርቱልን በጣም በርቱልን፣ ገና ያልተዘመረ ስንት መዝሙር አለ…… ማኅበረ ቅዱሳንን የመሰለ ማኅበራትንም እግዚአብሔር አሁን ብዙ አድርጎ ያብዛልን ይመስርትልን!! እነ ‘አባ’ ሰ’ረቀ ተስፋ ቆርጠው ብቻ ሳይሆን ተስፋም አጥተው ትተውን ወደመጡበት እንዲሄዱ ያርግልን!! ብጹአን አባቶቻችንንም በእድሜ ያቆይልን!

ተዋሕዶ ትስፋፋ……… እመብርሃን ለትውልዱ ሁሉ እናት ናትና

John Ze Baptist said...

Very Shame for protestants: They are to bring homesexuality to ethiopia after a while:

Mekane Yesus members fellowship rejects to roster homesexua for Church Ministry

http://www.eecmy.org/?page=!news&article=18

Haymanot said...

Lone the Baptist, What are you talking about? Your comment is out of the discussion, and your own word is contradict it self. Are you out of your mind? or you want change the subject? If you do you are pathetic.

Belayneh said...

From Belayneh Addis Ababa

እባካችሁ አትቀባጥሩ፡ የምትናገሩትን አስተውሉ፡ አባ ሰረቀ ብርሃንን አንዴ አባ ጨጓሬ፡ አንዴ የአቶ ዓባይ ተጠሪ፡ አንዴ ዘረኛ፡ እንዴ ተሐድሶ ወዘተ. ብትሉ እውንት አሸናፊ ነው። ነገ ታያላችሁ። አሁን ደግሞ የማህበረ ቅዱሳን ሃብትና ንብረት ኦዲት ይደረግ አሉ፡ የሰንበት ት/ቤቶችም ) በጀት ሳይበጅቱ እንዴት ይጠይቃሉ። አሁንም ዘማርያን ወዘተ ሊጠይቁ ይችላሉ። ትላላችሁ። ምንዓይነት ሞች ናችሁ። ለነገሩ ይህን የምትሉና ነገሩን የምታምታቱ ያው ራሳችሁ ናችሁ እናውቃቻ|ለን።

በጅት ላይበጅትላቸው እንዴ ኦዲት ይደረጋሉ?አልማወቃችሁ ነው እንጂ የቤት ክርስቲያኒቱ አብዛኛው በጅት የምእመናንና የምእመናት ገንዘብና ብሎም ቅርሶችዋ ናቸው። ታዲያ ማህበሩ እይሰበሰበው ያለ ገንዘብ የማንና ከማን ነው? በስሟ ከልዩልዩ በጎአድራጊዎች፡ ዓውደ ርእይ በማዘጋጀት በቅርሶችዋን የሚያገኘው፡ ቅዱሳት መጻሕፍቷ እያስተረጎመ በመቸብቸብ፡ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ሊገባ የነብረውን አስራት ለራሱ በማስቀረት ወዘተ. የሚሰብስበው ሃብት እንጂ ከራሱ በራሱ ያመጣው መሰላችሁ። ምነው ይህን ያህል ሞኞች ሆናችሁ። ለነግሩማ የተቃውሞ ሐሳብ እየሰጣችሁ ያላችሁ፡ እናንተው ተጠቃሚዎች ናችሁ።

ሌላው መታወቅ ያለበት ጉዳይ ማንም ማህበርም ሆነ ሌላ አካል የቤተክርስቲያኒቱን ሃብትና ንብረት ያለ አግባብ የሚዘርፍ ከሆነ ኦዲት መደረግስ ይቅርና ሊዘጋም ይችላል። ይህ ደግሞ አንድ መነኩሴ ተግባር ብቻ ሳይሆን የሁሉም አማኞች ተግባር ነው። በዚህ ላይ ቅር የሚላችሁ እናንተው በጓዳ መክበር የለመዳችሁ ናችሁ።

አስተዋል ልብ ይስጣችሁ

tesfa said...

ምን ነው ፈርኦኖች (ደጀ ህውከት) ለራሳችሁ ታወካችሁ ሰላማዊ ህዝብ ለማወክ ቆርጣችሁ የተነሳችሁ? ቃለ ጉባኤው ከዲያቆኑ ድህረ ገጽ (www.thwtruthfighter.net) አልሰረቅነውም ከታማኝ ምንጮቻችን ያገኘነው ነው በማለት ይፋ ሆነ በማለት ይስነበባችሁን እናንተ ነገሩ እየዋለ ስያድር ያደረጋችሁትን ትክክል አለመሆኑ ሲገባችሁ ደግሞ ዘወር ብላችሁ አባ ሰረቀ አስመስለው የፈረሙት ፌርማ እንጂ አባቶች የፈረሙት አይደለም ማለትስ ምን ማለት ነው? በግልጽ እግዚአብሔርንም አላውቅም እውነትንም አልዘግብም ማለት እኮ ያለ ነው።

selamawi said...

ምን ነው ፈርኦኖች (ደጀ ህውከት) ለራሳችሁ ታወካችሁ ሰላማዊ ህዝብ ለማወክ ቆርጣችሁ የተነሳችሁ? ቃለ ጉባኤው ከዲያቆኑ ድህረ ገጽ (www.thwtruthfighter.net) አልሰረቅነውም ከታማኝ ምንጮቻችን ያገኘነው ነው በማለት ይፋ ሆነ በማለት ይስነበባችሁን እናንተ ነገሩ እየዋለ ስያድር ያደረጋችሁትን ትክክል አለመሆኑ ሲገባችሁ ደግሞ ዘወር ብላችሁ አባ ሰረቀ አስመስለው የፈረሙት ፌርማ እንጂ አባቶች የፈረሙት አይደለም ማለትስ ምን ማለት ነው? በግልጽ እግዚአብሔርንም አላውቅም እውነትንም አልዘግብም ማለት እኮ ያለ ነው።

Anonymous said...

ምን ነው ፈርኦኖች (ደጀ ህውከት) ለራሳችሁ ታወካችሁ ሰላማዊ ህዝብ ለማወክ ቆርጣችሁ የተነሳችሁ? ቃለ ጉባኤው ከዲያቆኑ ድህረ ገጽ (www.thwtruthfighter.net) አልሰረቅነውም ከታማኝ ምንጮቻችን ያገኘነው ነው በማለት ይፋ ሆነ በማለት ይስነበባችሁን እናንተ ነገሩ እየዋለ ስያድር ያደረጋችሁትን ትክክል አለመሆኑ ሲገባችሁ ደግሞ ዘወር ብላችሁ አባ ሰረቀ አስመስለው የፈረሙት ፌርማ እንጂ አባቶች የፈረሙት አይደለም ማለትስ ምን ማለት ነው? በግልጽ እግዚአብሔርንም አላውቅም እውነትንም አልዘግብም ማለት እኮ ያለ ነው።

Anonymous said...

አጥብቆ ጥያቄ የእናቱን ሞት ተረዳ "Please Deje Selam do something to expose this fact at least to major radio stations like Germany Amaharic service, VOA , and etc who do transmit their programes in Ethiopia" ds(Anonymous)ይህን ያደረጋችሁ ዕለት ለእውነት መቆማችሁን ያስረዳል። ደግሞም እኔ እብሳለሁ ተጃጅሎ ከሚያጃጅል ጅል መድረቄ እናንተ የተያያዛችሁት ፖለቲካ እኛ የምናወራው እውነት አልተገናኘንም።

kebkab said...

ምን ነው ፈርኦኖች (ደጀ ህውከት) ለራሳችሁ ታወካችሁ ሰላማዊ ህዝብ ለማወክ ቆርጣችሁ የተነሳችሁ? ቃለ ጉባኤው ከዲያቆኑ ድህረ ገጽ (www.thwtruthfighter.net) አልሰረቅነውም ከታማኝ ምንጮቻችን ያገኘነው ነው በማለት ይፋ ሆነ በማለት ይስነበባችሁን እናንተ ነገሩ እየዋለ ስያድር ያደረጋችሁትን ትክክል አለመሆኑ ሲገባችሁ ደግሞ ዘወር ብላችሁ አባ ሰረቀ አስመስለው የፈረሙት ፌርማ እንጂ አባቶች የፈረሙት አይደለም ማለትስ ምን ማለት ነው? በግልጽ እግዚአብሔርንም አላውቅም እውነትንም አልዘግብም ማለት እኮ ያለ ነው።

tesfa this is my frist time to agree with your issue you are right!

shambel said...

የተከበራችሁ የድንግል ማርያም የአስራት ልጆች የቅድስት ቤ/ያን ጠበቆች ደጀ ሰላማውያን እንደምን አላችሁ? እኔ በዚህ ድህረ ገጻችሁ ተጠቃሚ ከሆኑ ወገኖች አንዱ ነኝ ምንም እንካን ጸሐፊ ባልሆንም እንደው አነሰ ቢባል በሳምንት 3ት አራት ጊዜ ሳልጎበኛችሁ አላልፍም ዛሬ ያስጻፈኝ ጉዳይ ቢኖር ግን ቀደም ብሎ ከቅድስት ስላሴ መንፈሳዊ መናፍቅ ተብሎ በተባረረ ዲያቆን የሚመራ ድህረ ገጽ ላይ ማኅበረ ቅዱሳንን አስመልክቶ ከሚጽፋቸው ሳምንታዊ ጽህፎቹ በዚህ ሳምንት በፒዲኤፍ የተዘጋጀ ዶክመንት ይዞ እንደቀረበና እናንተም ከጠቅላይ ቤተ ክህነት በኩል የተባለውን ይፋ እንደሆነና ድህረ ገጻችሁም የክሱና የውንጀላው ሰላባ እንደሆነች አስነበባችሁ ለማወቅ የፈለግኩት እናንተ ከወደ ቤተክህነት ይፋ ሆነ ስትሉ ዛሬ ደግሞ ውሽት ነው ያስባላችሁ ምን ተገኝቶ ነው? እናንተስ ዶክመንቱን ያገኛችሁን ከማን ነው? ደግሞስ ሳታጣሩ ነው እንዴ ተከሰስን ያላችሁን? አላዚያ ተስፋ እውነተኛ ሊሆን።

Ashenafi said...

what will be your Answer for the question ሀገር እስከ መቼ ልጆችዋን ትቀብራለች? for more join www.thetruthfighter.net

Anonymous said...

" Ashenafi said...

ሀገር እስከ መቼ ልጆችዋን ትቀብራለች?
November 07, 200 "

መልስ፦

አገርማ፡ያሳደገቻቸው፡ልጆች፡ተዋሕዶ፡ሃይማኖታ
ቸውን፡ከድተው፡የሉተር፡ሎሌዎች፡በመሆን፡ሕዝ
በ-ተዋሕዶን፡በመውጋትና፡በማስወጋት፡ላይ፡ናቸ
ው።የጥፋት፡ርኩሰት፡የተገለጠበት፡አንዱ፡ባህሪ፡
እንደናንተ፡ያሉ፡መሣሪያዎችን፡የተዋሕዶ-ኢት
ዮጵያ፡ጠላቶች፡በአገራችን፡በመግዛታቸው፡ነው።

አገርስ፡በንዲህ፡ያሉ፡ከሃድያን፡እየተፈጸመባት፡ያ
ለውን፡የኑፋቄ፡ጦርነት፡እየተዋጋች፡ነው።

ኢትዮጵያ፡አገራችን፡ልጆቿ፡በተዋሕዶ-ፈሪሃ፡እግ
ዚአብሔር፡ታንጸው፡እንዲያድጉላትና፡አለሁሽ፡እ
ንዲሏት፡ዘወትር፡እየተጣራች፡ነው።

የተሐድሶ-መናፍቃን፡ግን፡በኢትዮጵያ፡ማሟረታ
ችሁን፡ብትተዉትና፡"የቀበራችሁ"ታለ፡እዛው፡ሉ
ተር፡አገር፡ገሃነም፡ደጆች፡ሂዳችሁ፡አሟርቱ።ማልቀ
ሱም፡እዛ፡ያዋጣችኋል!

ድንግል፡ማርያም፡ምድሯን፡ኢትዮጵያን፡ከተሐ
ድሶ-መናፍቃን፡ጦርነትና፡ሟርት፡ትጠብቅልን።

በመስቀሉ፡የተከላትን፡ተዋሕዶ፡ሃይማኖትያችን
ን፡መድኃኔ፡ዓለም፡ክርስቶስ፡ከጥፋት፡ርኩሰት፡ይ
ጠብቅልን።
አሜን።

ሰይፈ፡ገብርኤል።

Ydnekachew said...

Dear Tesfa,

Most of the time I really agree with you. Those people who are fighting against the truth are always thinking about themselves. As you said, they have the heart of Feron and their heart is as hard as the back-stone. They already missed the right way. In other words, they do not have any personal relation-ship with our Lord and Savior Jesus Christ, the only way of our Salvation. That’s why they are blaming others instead of blaming themselves. Therefore, we have to stop corresponding with them, because they do not have the internal ear to hear the word of the Living God, before I sum up my opinion, I would like to assure that the foundation and corner-stone of our Ethiopian Orthodox Tewahdo Church is the Son of the Living God named Jesus Christ the Savior of the entire world. Our Church is strongly believe that no one can inter the kingdom of God without Him (Jesus Christ) and He is the only way for our Salvation, believe it or not, the way of Heaven is one way. There is no two ways. And the only way is our Lord Jesus Christ the Lamb of the Living God. So, please follow the right Church of Christ the Lord of lords,

I thank you for your comment

Ydnekachew Asgedom
From California

Unknown said...

new blog, let us discuss other issues as well. We don't want to hear about MK or Tehadiso. Let us also hear about the Christian Life itself which is wongel. Jesus and His wongel will be glorified on the new blog. Every thing about the truth church of Christ according to bible and Holy Tradition will be stated. Please Visit us and participate in sending your documents. For the time being we accept any type of Christian literature.
http://wongelforall.wordpress.com

God Bless our work

Anonymous said...

Tesfa and Yidnekachew,

EOTC is the oldest church in the world. It is established on the belief that there is one way to Heaven that is through Jesus Christ. No other way, period. But that doesn't mean that Jesus Christ is mediator (amalage) today. He did it once on the Cross. He is the Living God, Creator and Saviour of the world. His Holy Mother, Saint Marry and His Saints who He chooses from the world serve the role a mediator today. This doesn’t mean that there is another way. The way is still one, and it is through Jesus Christ.
Don’t try to confuse things. First understand then try to teach others.

May Jesus Christ lead you to the Truth!!

velavelo said...

ምን ነው ፈርኦኖች (ደጀ ህውከት) ለራሳችሁ ታወካችሁ ሰላማዊ ህዝብ ለማወክ ቆርጣችሁ የተነሳችሁ? ቃለ ጉባኤው ከዲያቆኑ ድህረ ገጽ (www.thwtruthfighter.net) አልሰረቅነውም ከታማኝ ምንጮቻችን ያገኘነው ነው በማለት ይፋ ሆነ በማለት ይስነበባችሁን እናንተ ነገሩ እየዋለ ስያድር ያደረጋችሁትን ትክክል አለመሆኑ ሲገባችሁ ደግሞ ዘወር ብላችሁ አባ ሰረቀ አስመስለው የፈረሙት ፌርማ እንጂ አባቶች የፈረሙት አይደለም ማለትስ ምን ማለት ነው? በግልጽ እግዚአብሔርንም አላውቅም እውነትንም አልዘግብም ማለት እኮ ያለ ነው።

Anonymous said...

tesfa you are the winner of this game!

Ydnekachew said...

Anonymous said..) Tesfa and Yidnekachew

Please listen carefully, and when you want to write something please write it with understanding. I am sorry about you. You said: “EOTC is the oldest church in the world” who says the Ethiopian Orthodox Tewahdo is not the oldest Church in the World. Did I say that? No. But the good news is you agreed with me by saying that.” It is established on the belief that there is one way to Heaven that is through Jesus Christ. No other way, period.” You are right. I agree with this point. Did I say Jesus Christ mediator ( Amalag) today or yesterday ? you read did you read this from my statement? How silly are you? What do I learn from is: You know nothing the belief of the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church and the teaching of our church about Christ the Lord of lards.

“His Holy Mother, Saint Marry and His Saints who He chooses from the world serve the role a mediator today. This doesn’t mean that there is another way.” My goodness!! What are you talking about? Did I say the mother of God Saint Marry and others are not chosen By God? And they are not mediators? O! my God give mercy upon him/her. Even you are Amalag( Mediator) if you are the true follower of the Lord Jesus Christ. We are given this authority from Him. Praise to this Name. the problem is you are so confused because of your lack of knowledge. May the Almighty God richly bless you and give you the wisdom of understanding.

Ydnekachew said...

this is for the one who said
Anonymous said..) Tesfa and
Please listen carefully, and when you want to write something please write it with understanding. I am sorry about you. You said: “EOTC is the oldest church in the world” who says the Ethiopian Orthodox Tewahdo is not the oldest Church in the World. Did I say that? No. But the good news is you agreed with me by saying that.” It is established on the belief that there is one way to Heaven that is through Jesus Christ. No other way, period.” You are right. I agree with this point. Did I say Jesus Christ mediator ( Amalag) today or yesterday ? you read did you read this from my statement? How silly are you? What do I learn from is: You know nothing the belief of the Ethiopian Orthodox Tewahdo Church and the teaching of our church about Christ the Lord of lards.

“His Holy Mother, Saint Marry and His Saints who He chooses from the world serve the role a mediator today. This doesn’t mean that there is another way.” My goodness!! What are you talking about? Did I say the mother of God Saint Marry and others are not chosen By God? And they are not mediators? O! my God give mercy upon him/her. Even you are Amalag( Mediator) if you are the true follower of the Lord Jesus Christ. We are given this authority from Him. Praise to this Name. the problem is you are so confused because of your lack of knowledge. May the Almighty God richly bless you and give you the wisdom of understanding.

Anonymous said...

የፓትሪያርኩን ሹመት (የዓለም አብያተ ክርስቲያናት ፕረዘዳንት) መሆን የስተዳደራቸውንትርፋማነት ለማሳየት እንደማስረጃ መቆጠሩን ሳይ አንድ ጊዚ ዋርካ በሚባል ድህረ ገጽ ያነበብኩትን እንድታነቡት ለመጋበዝ ቅጂዉን ከዚህ በታች እለጥፈዋለሁ

ተግጥሙ አረእስት "ኢትዮጵያና 'የዓለም ቢተክርስቲያናት' ህብረት" የሚል ነው

ስንዱ እንቁዋን ንቃ
የሰው መዳብ ያምራል ብላ
በ 41ዓመተ ምህረት ከሰዳቢዎቿ ተደባልቃ
ማለቂያ ከሌላቸው ሁከተኞች ተራ
ከቁባቶች ተደምራ
በ 67 ቢደግሱላት
የጋለሞቶች ቁንጮ ሊያደርጓት
በቀኑ
የመበለትነት ማቅ ለበሰችበት
ስንዱ አልቀረላት
ቁባቶች እንደገና ሸነገሏት
በአዲሱ ዘመን አቅራቢያ ወንበራችን እነሆ አሏት
ስንዱ ስሟ በወንበሩ ተጠራ
እቁባቶችም አሉ :-
ስንዱ ገባች ከኛ ተራ
ከጋለሞቶች መንደር
ባሏ ከማይደርስበት ሠፈር

ስንዱ
አንቺ ሙሽራ
የተቆለፍሽ አዝመራ
መዓዛሽ ከሊባኖስ የተመረጠ
ከሽቱ ሁሉ የበለጠ
ቡቃያሽ ገነት የሮማን ፍልቃቂ
አንቺ የህይወት ወንዝ
ከታተመ ምንጭ የምትፈልቂ

ከጋለሞታ ሰፈር በገባሽ ማግስት
ውድሽ ከቤትሽ እንዳልመጣ
ዝማሬሽ ተቀባይ እንዳጣ
እጣንሽ ወደላይ እንዳልወጣ
መርዶው የእንግልትሽ የኃዘኑ
እነሆ ይድረስሽ በስልሳ ዘመኑ

ስንዱ ተነሽ
እረኛሽን ፈልጊው ከበረሃው
ተናገሪው
የሰሜን ነፋስ ሆይ ተነስ
የደቡብም ነፋስ ና በይው

ውድሽ ቀናተኛ ነውና
መዓዛሽን ይወዳልና
የጋለሞታውን መንደር ተይው

ስንዱ
ማር ከከንፈሮችሽ እንዲንጠባጠብ እንደገና
እጣኑ ከኮረብታሽ ወደሰማይ እንዲያቀና
ተራራሽ ካጋለሞቶች ሜዳ እንዲልቅ
ከጉድጓድሽ የህይወት ውኃ እንዲፈልቅ
ወድሽ ወደ ገነትሽ እንዲመጣ
እግርሽ ከጋለሞቶች ማህበር ይውጣ

Anonymous said...

To Ydnekachew,

You said "Even you are Amalage (Mediator) if you are the true follower of the Lord Jesus Christ. We are given this authority from Him."

Please leave me alone. I am not a mediator. I am a sinner. You can claim that. You know yourself. You can even say I am an Angle. Some protestant sects even claim that they are small gods. May be you are one of them. But remember, it is God, and only God that chooses them. (Matthew 10: 1- )

EOT Church doesn't teach such arrogance. It teaches you to be humble in front of God, and confess your sins every day until death.

Anonymous said...

“ይሄይሰነ ናድሉ ለእግዚአብሔር እምነ አድልዎ ለሰብእ” ቃለ ሐዋርያት
በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያና በማህበረ ቅዱሳን ላይ የተላለፈው መመሪያ በየአህጉረ ስብከቱ መተግበር መጀመሩ ታወቀ። ከማህበሩ የአመራር አባላት የተሳሳተ ግንዛቤ ይዘው ከነበሩት አባቶች መካከል የማደራጃ መምሪያው ዓላማ ጥቅመኞች እንደሚያ ወሩት ማህበሩን ለመበተን ሳይሆን ስርዓት እንዲይዝና ብሎም በቤተክርስቲያኒቱ ስም የሚሰበስበው ማንኛውም ሃብትና ንብረት መታወቅ እንዳለበትና በአጠቃላይ ማነኛውም ማህበር ዘለቄታ ሊኖረው ላይኖረው ስለሚችል፡ የማህበሩ ማንኛው ንብረት ወራሽ ቤተክርስቲያን መሆንዋን በሕግ መደንገግ እንዳለበት አስረድተዋል። ከ1994 በፊት በተሻሻለው መተዳደሪያ ደንብ እንደነበረ ያስታወሱ አባቶች በ1994 ዓ/ ም በተሰጠው መተዳደሪያ ድንብ እንደቀረ አለማወቃቸው አክለው መግለጻቸው ታውቀዋል።
በተለይ በየአህጉረ ስብከቱና በየወረዳው ራሱን ማደራጃ መምሪያ አስመስሎ ካህናትንና ሊቃውንትን ስያቃልልና የፈለገውን ስያደረግ የነበረው ማህበር ዛሬ በየአቅጣጫው ተቃውሞ እየገጠመ መምታጡ ተረጋጧል። በሚቀጥለው፡ መመሪያውን ተቀብለው በመተግበር ላይ ያሉትን ሁሉ እንደምናቀርብ ከወዲሁ ቃል እንገባለን።

Anonymous said...

Home Sections ኢትዮጵያ የዐጀሚ ሥነ ጽሑፍ ሀገር
ኢትዮጵያ የዐጀሚ ሥነ ጽሑፍ ሀገር
Sunday, 08 November 2009 ETHIOPIAN REPORTER
በሔኖክ ያሬድ

ኢትዮጵያ፣ ሥነ ጽሑፋዊ ቅርሶቻቸውን በዐረብኛ ፊደላት እየጻፉ ያስተላለፉ 11 ቋንቋዎች ያሏትና በዚህም፣ በአፍሪካ በተጠቃሚ ቋንቋዎች ብዛት የመጀመሪያውን ደረጃ መያዟ አንድ ጥናት አመለከተ፡፡


ጥቅምት 26 ቀን 2002 ዓ.ም. በተጠናቀቀው 17ኛው የኢትዮጵያ ጥናት ዓለም አቀፍ ጉባኤ በሦስተኛው ቀን ውሎው፣ “ኢትዮጵያ አንጋፋዋ የአፍሪካ የዐጀሚ ሥነ ጽሑፍ ሀገር” በሚል ርእስ ጥናት ያቀረቡት፣ አቶ ሙሐመድ ሰዒድ አብደላ እንዳመለከቱት፣ ሀገር በቀል በሆኑት የኢስላም ሃይማኖት ተቋማት የተማሩና ከፍተኛ የዕውቀት ደረጃ ላይ የደረሱ ኢትዮጵያውያን፣ አንዳንዶቹ በዐረብኛ ቋንቋ፣ ከፊሎቹ ደግሞ በአማርኛና በሌሎች የሀገሪቱ ቋንቋዎች የዐረብኛ ፊደሎችን በመጠቀም ድርሳኖችን እየጻፉ፣ ሥነ ጽሑፋዊ ቅርሳቸውን ከትውልድ ወደ ትውልድ ሲያስተላልፉ ኑረዋል፡፡

ዐረብኛ ያልሆኑና በዐረብኛ ፊደላት ሲጻፉ የቆዩ ቋንቋዎች፣ ያፈሯቸው የጽሑፍ ቅርሶች፣ ዐጀሚ ተብለው እንደሚጠሩ የጠቀሱት አቶ ሙሐመድ፣ የአጻጻፍ ስልቱ የአፍሪካና የእስያ ሕዝቦች፣ ቋንቋቸውን በዐረብኛ ፊደል በመጠቀም የታሪካቸው፣ የባህላቸውና የሥነ ጽሑፋቸው መግለጫ መሣሪያ በመሆን አገልግሏል፡፡ በኢትዮጵያ የዐጀሚ ጽሑፍ ታሪካዊ መነሻን የሚገልጽ መረጃ ለጊዜው ባይገኝም፣ በእጅ የሚገኙት መዛግብት ከ18ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ የተጻፉ መሆናቸው አጥኚው አመልክተዋል፡፡

በሀገሪቱ፣ በዐጀሚ የጽሑፍ ቅርስ በብዛት የተገኙት፣ በሴሜቲክና በኩሽቲክ ቋንቋዎች የተጻፉና ይዘታቸውም በአብዛኛው በሃይማኖታዊና መንፈሳዊ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡ በአቶ ሙሐመድ ማብራሪያ፣ እስከ አሁን ድረስ በኅብረተሰቡ ውስጥ በብዛት የሚታወቀውና በተለያዩ ቋንቋዎች ለሕዝብ የሚደርሰው መንዙማ፣ ሥነ ጽሑፋዊ ይዘቱ በዐረብኛ ፊደል የተጻፈና በከፊልም ቢሆን በአማርኛና በሌሎች ሀገርኛ ቋንቋዎች የተደረሰ ነው፡፡ ብዙዎቹ የመንዙማ ጽሑፎች በኢትዮጵያውያን የእስልምና ሃይማኖት ሊቃውንት የተደረሱት ከምእት ዓመታት በፊት ነበር፡፡

አጥኚው ባቀረቧቸው የሰነድ መረጃዎች፣ በዐጀሚ ከተጻፉት የሴሜቲክ ቋንቋዎች አማርኛና ትግርኛ፣ ሐደርኛና አርጎብኛ፣ ስልጥኛና ወለንኛ፣ ከኩሽቲክ ቋንቋዎች ደግሞ አፋን ኦሮሞ፣ አፋርኛና አላባ፣ ቀቤንኛና ሶማልኛ ይገኙባቸዋል፡፡ የዐጀሚ ጽሑፍ የተጻፈባቸው አስራ አንድ ሀገር በቀል ቋንቋዎች መገኘታቸው ያመለከቱት አቶ ሙሐመድ፣ የሥነ ጽሑፉ ቅርስ ከሃይማኖታዊና መንፈሳዊ ጉዳዮች ጎን የተለያዩ ማኅበራዊ ጉዳዮችን፣ የንግድ ግንኙነትን፣ የጋብቻ ሥርዓትን፣ የሕዝብ አስተዳደርን፣ የንብረት ዝውውርንና የመሬት ይዞታን ወዘተ. በብዛት እንደሚዳስስ አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ የዐጀሚ ሥነ ጽሑፍ ቅርስ፣ ለረዥም ዘመናት አትኩሮት ሳያገኝ በመቅረቱ፣ ትውልዱም ስለሁኔታው ያለው ዕውቀት ውስን ቢሆንም፣ ያላት ቅርስ ከአፍሪካ ሀገሮች ቀደምት ቦታ የሚያሰጣት መሆኑን ከአፍሪካ ሀገሮች ቅርስ ጋር በማነፃፀርም አብራርተውታል፡፡

በሰሜን አፍሪካ የሚኖሩ ዐረብኛ ተናገሪ ሀገሮች፣ እስካሁን ድረስ የቅድመ ዐረብኛ የጽሑፍ ቅርስ በብዛት ስለመኖሩ የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ በምዕራብ አፍሪካ ያለውን ሁኔታም ወደ አስር የሚሆኑ ቋንቋዎች በቡርኪናፋሶ፣ በጋምቢያና በጊኒ፣ በሴኔጋልና በማሊ፣ በኒጀርና ናይጄሪያ የሚነገሩ በዐጀሚ የተጻፉ መኖራቸው መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ እስልምና ከነቢዩ ዘመን ጀምሮ በኢትዮጵያ የሚገኝ መሆኑ፣ ሃይማኖቱን የተቀበሉ ኢትዮጵያውያን ከሰሜን አፍሪካ ሕዝቦች በተለየ ሁኔታ ከቅድመ እስልምና ዘመን ጀምሮ ይዘዋቸው የቆዩትን ቋንቋዎች እስከ አሁን እንደያዙ ቀጥለዋል፡፡ ሃይማኖቱን ለመማርና ለማስተማር በስፋት የተገለገሉት ሀገር በቀል በሆኑት ቋንቋዎች ሲሆን፣ ለመጻፍም በዐረብኛ ፊደል ሲጠቀሙ ኖረዋል፡፡

ከቋንቋ ስርጭት አኳያም፣ ኢትዮጵያ ከስዋሂሊኛ በስተቀር በአፍሪካ ቀንድ የሚነገሩት ቋንቋዎች የሚነገሩባት በመሆኗ፣ አሁን ባለው መረጃም በሀገር በቀል ቋንቋዎች በዐጀሚ ተጽፈው መገኘታቸው ከአፍሪካ ጎልታ እንድትታይ አድርጓታል፡፡ በአቶ ሙሐመድ አገላለጽ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዐረብኛ ተናጋሪ ከሆኑት የግብፅ የሃይማኖቱ ተከታዮችና ተቋሞቻቸው ጋር በነበራት ታሪካዊ ግንኙነት ጥንታዊ የክርስትና ሃይማኖት የጽሑፍ ቅርሶች ከዐረብኛ ወደ ግእዝ፣ አማርኛና ትግርኛ እየተተረጎሙ፣ ለሕዝብ አገልግሎት የመድረሳቸው ድምር ውጤት፣ ዛሬ በኩራት የምንጠቅሰውን ሰፊና ጥንታዊ የኢትዮጵያ ዐጀሚ ሥነ ጽሑፍ ቅርስ ለማፍራት አብቅቷል፡፡

ኢትዮጵያ፣ ከአፍሪካ አንጋፋዋ ዘርፈ ብዙ የዐጀሚ ሥነ ጽሑፍ ቅርስ ባለቤት በመሆኗ፣ ከመቶዎች ዓመታት በፊት የነበረውን የሕዝቦቿን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ ጉዳዮችን ለማጥናት ጽሑፉ እንደ መጀመሪያ ምንጭ ሊሆን ስለሚችል፣ የሀገሪቱ ትምህርትና የምርምር ተቋማት የሚገባውን ግምትና አትኩሮት እንዲሰጡበት አጥኚው ማሳሰቢያ ሰጥተዋል፡፡ “የኢትዮጵያ የዐጀሚ የጽሑፍ ቅርስን በምርምር እና በጥናት ታሪካዊ ዋጋው ግምት አግኝቶ ለማኅበረሰቡ ጥቅም የሚውልበት ሁኔታ ለማመልከት በኅብረተሰቡ ተጠብቆ የቆየውን ሀገር በቀል የሃይማኖትና የሥነ ምግባር የባህልና የሥነ ጽሑፍ ቅርስ በሚገባ ለማወቅ ይረዳል፡፡”

የዐጀሚ ሥነ ጽሑፍ ቅርስ በተለይ የኅብረተሰቡን ባህላዊ ታሪክ ለሚያጠኑ ተመራማሪዎች ጥሩ መረጃ ሊሆን እንደሚችልም ተጠቁሟል፡፡

Anonymous said...

በአቶ ሙሐመድ አገላለጽ፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ዐረብኛ ተናጋሪ ከሆኑት የግብፅ የሃይማኖቱ ተከታዮችና ተቋሞቻቸው ጋር በነበራት ታሪካዊ ግንኙነት ጥንታዊ የክርስትና ሃይማኖት የጽሑፍ ቅርሶች ከዐረብኛ ወደ ግእዝ፣ አማርኛና ትግርኛ እየተተረጎሙ፣ ለሕዝብ አገልግሎት የመድረሳቸው ድምር ውጤት፣ ዛሬ በኩራት የምንጠቅሰውን ሰፊና ጥንታዊ የኢትዮጵያ ዐጀሚ ሥነ ጽሑፍ ቅርስ ለማፍራት አብቅቷል፡፡

Anonymous said...

+++
To the last anon.
Which hagere sibiket oppose MK spritual work?
What are basic /segnificant/ problem on thier spritual work?
Try to tell the truth things, b/se tomorrow history can explain the truth. You member of tser-EOTC, please leave for truth.
ለእውነት እንጂ በእውነት ላይ ምንም ለማድረግ አንችልምና። 2co13:8
ስለዚህ ስለ ክርስቶስ በድካም በመንገላታትም በችግርም በስደትም በጭንቀትም ደስ ይለኛል፤ ስደክም ያን ጊዜ ኃይለኛ ነኝና። 2co12:10
ራሳቸውን ከሚያመሰግኑ ከአንዳንዶች ጋር ራሳችንን ልንቆጥር ወይም ራሳችንን ልናስተያይ አንደፍርምና፤ ነገር ግን እነርሱ ራሳቸውን ከራሳቸው ጋር ሲያመዛዝኑ፥ ራሳቸውንም ከራሳቸው ጋር ሲያስተያዩ፥ አያስተውሉም።

እኛ ግን እግዚአብሔር እንደ ወሰነልን እስከ እናንተ እንኳ እንደሚደርስ እንደ ክፍላችን ልክ እንጂ ያለ ልክ አንመካም።

ወደ እናንተ እንደማንደርስ አድርገን ከመጠን አናልፍምና፥ የክርስቶስን ወንጌል በመስበክ እስከ እናንተ እንኳ ደርሰናልና፤

በሌሎች ድካም ያለ ልክ አንመካም፥ ነገር ግን እምነታችሁ ሲያድግ ከእናንተ ወዲያ ባለው አገር እስክንሰብክ ሥራችንን እየጨመርን፥ በክፍላችን በእናንተ ዘንድ እንድንከብር ተስፋ እናደርጋለን፤ በሌላው ክፍል ስለ ተዘጋጀው ነገር አንመካም።

የሚመካ ግን በጌታ ይመካ፤ እግዚአብሔር የሚያመሰግነው እንጂ ራሱን የሚያመሰግን እርሱ ተፈትኖ የሚወጣ አይደለምና። 2co10:12-18

Ze Zeway

Ydnekachew the California said...

Even now you missed the point; even now you are so confused. Please do not judge at anybody, otherwise according to the holy bible you will be judged. According to your word, you are sure as I am a protestant. You are totally wrong. I think you have a problem of understanding of English Language. I was not saying even you are Amalag (Mediator) only. What I was saying was, If” you are the true follower of the Lord Jesus Christ. We are given this authority from Him” You have to know the meaning of if. As you said, if you are not the true follower of our Lord Jesus Christ, yes. I agree with you. You are a sinner. Remember this, except the mother of God the Saint Merry, no one was or is perfect in human history but the different is; when the true Christian made a mistake, right away; they repent from their sin according to the word of God. All our Saints were the true followers of the Lord Jesus Christ. That’s why our church accepts them as Mediators (Amalagoch) so, we are called to be like them, but to be like them or not to be like them is ours. What I would like to recommend is if you really know as you are a sinner, please repent from it. You do not have to keep it please!! The time of salvation is today not tomorrow or yesterday. My brother or my sister, let tell you one word, a man is higher than an Angel, but I am not saying I am an Angel do not worry, being humbleness in front of God means becoming a true follower of the true GOD. I think one word is enough for the wise man. Do not judge, you will be judged.

yetsyon said...

The person who wrote the one below...May God bless you!

"To Ydnekachew,

You said "Even you are Amalage (Mediator) if you are the true follower of the Lord Jesus Christ. We are given this authority from Him."

Please leave me alone. I am not a mediator. I am a sinner. You can claim that. You know yourself. You can even say I am an Angle. Some protestant sects even claim that they are small gods. May be you are one of them. But remember, it is God, and only God that chooses them. (Matthew 10: 1- )

EOT Church doesn't teach such arrogance. It teaches you to be humble in front of God, and confess your sins every day until death."

Anonymous said...

I really like the idea above from the annonymous person. It is very helpful and please please let's all keep real news for our people

Anonymous said...

ሳይፈርሙ ፈርመዋል የተባሉ አባቶች ስንት ናቸው? እነዚህን አባቶች በስም መጥቀስ ያላስፈለገበት ምክንያት ለምንድን ነው? ሊደርስባቸው የሚችል አደጋ አለ ማለት ነው ?

በእውነቱ የአባቶችህን ፊርማ አስመስለው የፈረሙ ሰዎችህ ካሉ ዝም ተብለው ሊታለፉ አይገባቸውም። በቤተ ክርስቲያን ላይ እና በብጹ አን አባቶችህ ላይ የተፈጸመ ታላቅ በደል ስለሆነ ይህን ያደረጉ ሰዎችህ ለፍርድ መቅረብ አለባቸው።

Anonymous said...

Dear Deje Selam Editor:
Since you are on track to expose the hypocrisy and noxious people in the EOTC (specially the shameful so called leaders), I have some questions.

1st. Can you dig in more and list down which Papasat were in this meeting and which ones refused to sign the minute (Wusane) and why ?

2nd. If you can interview some of the ones(Papasat) that refused and put the audio online. I know they might get scared of giving an interview, since the "ninjas" could come after them, too.

3rd. If you can arrange with some insiders (Kahnat who were in the meeting) to give their testimony about this forgery by "Abba" sereqe.

And one last thing:- What happened to the petition we all signed ?

Thanks,
Keep up the good work.

May God protect His Church and the true followers,

YeAwarew

Anonymous said...

To the angel[a] of the church in Sardis (EOTC) write:
These are the words of him who holds the seven spirits[b]of God and the seven stars. I know your deeds; you have a reputation of being alive, but you are dead. Wake up! Strengthen what remains and is about to die, for I have not found your deeds complete in the sight of my God. Remember, therefore, what you have received and heard; obey it, and repent. But if you do not wake up, I will come like a thief, and you will not know at what time I will come to you. Yet you have a few people in Sardis who have not soiled their clothes. They will walk with me, dressed in white, for they are worthy. He who overcomes will, like them, be dressed in white. I will never blot out his name from the book of life, but will acknowledge his name before my Father and his angels. He who has an ear, let him hear what the Spirit says to the churches
Revelation 3

Anonymous said...

Hi DS

Please read the news on addis admass newspaper. It is a disturbing story about our children.

Please write some thing to encourage our church leaders, the government, Christians and all Ethiopians to punish those evil people who spoil this small kids. Our government has to do some thing to put those people in jail, or to punish them onece and for all. I surprise how the government doesn't have enough resources to protect these kids, why the government secret service doesn't work on this matter. Why our church leaders and we Christians wast our energy on unnecessary issues but our kids are dying in their own country.


http://www.addisadmass.com/Yesemonun/news_item.asp?NewsID=284


Your brother in Christ.

November 11, 2009

nafkoteyegetalij@gmail.com said...

አዎ ማሞ ሌላ ፎቶው ሌላ ይላሉ ይሄ ነው

ትላንትና አባቶቻችንን አነዴ ጎንደሬ አንዴ ትግሬ እያላችሁ ስትሰድቡ ዋላችሁ ግራ ሲገባችሁ ቶሎ አወጣችሁት የካም ዘሮች ጥፉ

በአባቶቻችን ወይንም በወንድማማቾች መካከል የዘረኝነትን ፍላጻ ስታነሱ እውነተኛ የተዋህዶ ልጆች ተነሱባችሁ የሰራችሁት ክፏኛ ስለተጠላና እናንተም ሰላፈራችሁበት ጽሁፉን አወጣችሁት ድሮም ከበቅሎ ልጅ አንጠብቅም ማህበረ ሰይጣን ትላንትናም ዛሬም ነገም የተዋህዶና የኢትዮጵያ ውስጣዊ ጣለት ነው ለመሆኡ የናንተን አመሰራረት ለሚያውቅ ሰው እኮ ልክ የጠንቁዩ ታምራት ገለታ ቢጠዎች ናችሁ በጥንቆላውና የንጹሃን ሴቶችን ክብረ ንጽህና ስት ገፉ ኖራችሁ ሰው አስገድላችሁ አልበቃ ሲላችሁ የዛር መንፈስ ያለባትን ሴት ከዚያ ባለጌ መስራች ዲያቆን ተብዬአችሁ ጋር አስማምታችሁ ከመንግስት ጋር ተዋዳችሁ ቅዱሰ ቴዎፍሊዎስን አስገደላችሁ ጠላትነታችሁን የማይረሰ ጌታ ግን አይምራችሁም አልፋችሁ ደርሳችሁ ደሞ ቅዱስ ተክለሃይማኖትን በመርዝ ገደላችሁ አልፋችሁ መታችሁ ቅዱስ መርቆሬዎስን ለመግድ አልተፈቀደላችሁም ለምን ተሰደደ ይመትሉትም እንደለመዳችሁት ለምን አልበላነውም ብላችሁ ነው ግን አለ አምላክ ፈቃድ ምንም አይሆንም እና ተዋረዳችሁ በሰሜን አሜሪካ ተሰዶ ቢወጣም ህዝቡን ከእንደ እናንተ አይነት መናፍቅ ተኩላ የክረስቶስን ደም ሊያስከብር ህዝቡን ይዟል አሁንም ቅዱስ ጳውሎስን ለማጥፋት ጣራችሁ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ነገር የውም እምነት የለሽ የጠንቃዮች ማህበር /ማህበረ ሰይጠን አያጠፋውም

እውንት ተሸፍና ብትኖርም
መጋለጧ አይቀርም

ማህበረ ሰይጣን ከመሆን እስላም መሆን ይሻላል
ማለትም ሁሉ በሙሉ ሳያምኑ መኖር ይሻላል
ያመኑ እየመሰሉ ያመኑትን ከሚያጠፉ እርኩሶች

ገና ገና ገና ጉዳችሁን በቪዲዮ የሚያወጣው ሰው ይመጣል እናንተን አያርገኝ እንደ ጴጥሮስ ማሀበሩን አላውቀውም የምትሉበት ቀን እሩቅ አይደለም!!!!!!

Anonymous said...

" Anonymous said...
" ከራሱ ቡድን ውጪ ያለ ቄስንም ጳጳስንም ከመጤፍ ሳይቆጥር ራሱን ብቻ እያኩራራና እያጋነነ፣ ሌላውን እየናቀና እየገፋ፣ የዘረኝነትን አዝመራ እያስፋፋና እያጎለመሰ ሄዶ ድንገት በትግሬዎቹ መሳፍንት ልጆች ኃይልና ብልጠት ተበልጦ ሁሉን ለማጣት ተገደደ፡፡ ፓትርያርኩ ከሥልጣናቸው ወረዱ፡፡ ሌሎቹም ጎንደሬዎች ይዘውት የነበረው ወንበር ከሥሩ ተፈነቀለ፡፡ ‹‹የጎንደር ወጪት ይውጣ … የትግሬ ወጪት ይግባ›› ተባለ፡፡ ሥልጣን ከጎንደር ወደ ትግሬ ገባች፡፡ መርቆርዮስ ወረዱ … ጳውሎስ ወጡ፡፡ በዘመነ መሳፍንትኛ ብትመለከቱት የቋራው ካሳ ወረደ የትግሬው ካሳ ተሾመ እንደማለት ነው፡፡ ዘረኝነትን እያስፋፉ በሌላው ሲቀልዱ ኖረው በራሳቸው ብልሃት የመጣ ሌላ ዘረኛ ወንበራቸውን ቀማቸው፡፡ ተደላድሎም ተቀመጠ፡፡ ዛሬ እርሱን በዘረኝነት ቢያሙት ማንም የሚሰማቸው የለም፡፡ ‹ስልቻ ቀንቀሎ … ቀንቀሎ ስልቻ››፡፡ "


Anonymous said...
" መቸም ዛሬ እውነትን መፈለግ ሞኝነት ስለሆነ ‹‹አንዱ ባንዳ ሰደበኝ›› ወይም ምናልባት ‹‹አንዱ ወያኔ ስሜን አጠፋው›› ሊሉ ይችሉ ይሆናል፡፡ በእነርሱ የዘር ጨዋታ ውስጥ የለሁበትም፡፡ የማንም ፍርፋሪ ፈላጊም አይደለሁም፡፡ ሁለቱም ቡድን ቤተ ክርስቲያናችንን እያጠፋና እያመሰ መሆኑን ነው የማውቀው፡፡ ስለዚህ የዘረኝነትን በሽታቸውን በሃይማኖት ስም ከሚያስታምሙት ‹‹በሽታቸውን አውቀው መድኃኒት ቢፈልጉለት›› ይሻላል፡፡ ዘረኝነቱን እነርሱ ሲያስፋፉት ትክክል የሚሆንበትና እነ አባ ጳውሎስ ሲያደርጉት ግን ስሕተት የሚሆንበት ምክንያቱ አይታየኝም፡፡ ሁለቱም ቡድኖች የመሳፍንት ዘመን ተፍካካሪዎች እንጂ የሃይማኖት ሰዎች አይመስሉም፡፡ ግባቸውም ቤተ ክርስቲያኒቱን መጠበቅ፤ ማሳደግና ማስፋፋት አይደለም፡፡ ጭንቀታቸው የወንበር ጉዳይ ነው፡፡ የሚያሳዝነው ግን ይህንን ሁሉ ምዕመን እንዲህ ያለጠባቂና እረኛ ማስቀረታቸውና አባት አልባ ማድረጋቸው ነው፡፡ ስለዚህ በእውነት ለቤተ ክርስቲያን የሚያስቡ ሁሉ የነገሮችን ምንጭና መነሻ ማጤን አለባቸው፡፡ በሃይማኖትና በአገር ስም የግላቸውን ፈቃድ ለመፈጸም ደፋ ቀና የሚሉ ሰዎችን ስሜትና ፍላጎት ስናስፈጽም መኖር የለብንም፡፡ በተለይም ምዕመናን ከነዚህ ዘረኛ መነኮሳት ቅጥ ያጣ ውድድር ራሳቸውን ገሸሽ ማድረግ አለባቸው፡፡ እኛ በምንሰጣቸው ድጋፍ ነው እንዲህ ቤተ ክርስቲያኒቱን መጫወቻ ያደረጓት፡፡ "

mike said...

http://www.ethiopianreview.com/content/11189
Lelaw ambagenen zebene lemma

Bekele Alemu Addis ababa said...

አዲስ ዜና ስለቤተክርስቲያናችን አንድነትና ሰላም ለምትናፍቁ ሁሉ።

እንደሚታወቀው በሰንበት ት/ቤቶች ማደራጃ መምሪያ ስር የሚመራው ማህበረ ቅዱሳን ቋሚ ንብሩቱንና ገንዘቡን፡ ኦዲት እንዲያስደርግና እንዲያስመዘግብ፡
ማነኛውም ስራው ሁሉ በማደራጃ መምሪያው እውቅና ብቻ እንዲንቀሳቅስ፡ የሚያሰራጨው ማነኛውም ጽሑፍም ሆነ በኢንተርኔት የሚተላለፍ ሁሉ በማደራጃ መምሪያና በሊቃውንት እንዲታሪሙ ወዘተ የሚል መመሪያ መስከረም12 ቀን2002 ዓ/ም መተላለፉ አይዘነጋም። ይሁን እንጂ ማህበሩ ነገሩን ለማድበስበስና በለመደው የማጭበርበር ዘዴም ይደግፉኛል ለሚላቸው አንዳንድ ሊቃነ ጳጳሳት ደብዳቤ በመጻፍ በሲኖዶስ አጀንዳ እንዲያዝለትና ውሳኔውን ለመቀልበስ ያልገባበት ጉድጓድና ያልፈነቀለው ድንጋይ አልነበረም። ይባስ ብሎም አዲስ የተሾሙት ሊቀ ጳጳስ በአዲስ መልክ እንደሚያዩትና መፍትሔም እንደሚሰጡ ገና ስራ ከመጀመራቸውና ከማ/መምሪያ ሳይተዋወቁት በግል ስብሰባ በማድረግ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደ ቆዩ ለማወቅ ተችለዋል። ይሁን እንጂ ሕዳር 7 ቀን የማህበሩ አጠቃላይ የአመራር አባላት፡ የማደራጃ መምሪያ ዋና ሃላፊ፤ የማ/መምሪያ ምክትል ሃልፊና ሌሎችም ሰራቶኞች፡ እንዲሁም በርከት ያሉት ሊቃነጳጳሳት፡ ቅዱስ ፓትርያርኩና ብፁዕ አቡን ይስሐቅ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ስራ አስኪያጅ በተገኙበት፤ መስከረም 12 ቀን 2002 የተላለፈ መመሪያ ፈጽሞ የማይቀየርና በመፍጸም ያለበት ስለሆነ ማህበሩ እንዲተገብረው የመጨረሻ ጊዜ መታዘዙን ታወቋል። የማህበሩ ሊቀ መንበር ዶ/ር ሙሉጌታ የተላለፈው መመሪያ ለመፈጸም ዝግጁ ነን ነገር ግን ቅዱስነትዎ ከስተላለፉት ባለ5 ነጥብ መመሪያ ሌላ ተጨምሮበታልና በዚሁ እንድንወያይበት የመጨረሻ ዕድል ይሰጠን በለው እንደ ነበር ምጮች አስታውቀዋል። ይሁን እንጂ የማደራጃ መምሪያው ሃላፊ ተጨመረ የምትሉት የገንዘብና የንብረት ማሰባሰቢያ ደረሰኞች ሕጋውያን በሆኑት የቤተ ክርስቲያኒቱ ሞደላሞዴሎች እንድተሰበስቡ የሚል ከሆነ ስድስተኞ ቁጥር ተሰጥቶት ከመቀመጡ ውጭ ፈጽሞ የተጨመረ አይደለም በማለት በማስረዳታቸው። አንድ የመጨረሻ ዕድል ይሰጠን የሚለው ቃል። ተቀባይነት እንዳላገኘ ተነግረዋል።
ሌላው በመካከል የተገኙ ሊቃነ ጳጳሳትም ማህበሩ መመሪያውን ተቀብሎ ከመስራት ውጭ ምንም ዓይነት አማራጭ እንደሌለው አስረግጠው እንደተናገሩ በስብሰባው ከተገኙት መካከል አስረድቷል። በተላይ ማህበሩ ለማ/መምሪያ ሊቀጳጳስ በመመረጡ መመሪያው ይቀለበስ ይሆናል የሚለው አስተሳሰቡ የተሳሳተ እንደሆነና የተመደቡት ሊቀ ጳጳስም ይህን ከመፈጸምና ከማስፈጽም ሌላ ሐሳብ እንደማይኖራቸው ማወቅ እንዳለበትና ብሎም ከማደራጃ መምሪያ ሃልፊዎች ውጭ ተነጥለው ሊሰሩት የሚቸሉ አንዳች ነገር እንደማይኖር በጉባኤው ተውስቷል። የማህበረ ቅዱሳን የአመራር አካላት ችግራችን የማደራጃ መምሪያው ሃላፊ አባ ሰረቀብርሃን ናቸው ይሉት የነበረ አባባለ ፍጽሞ የማያስቸድና ሃላፊው በተሰጣቸው ሕገ ደንብ ለመፈጸመና ለማስፈጸ ተንቀሳቀሱ እንጂ ይህ የቤተ ክርስቲያኒቱ ጉዳይ ነው በማለት እንክቹ እንደተነገራቸው ታወቋል። በመሆኑም ከእንግዲህ ወዲህ ማህበሩ ሁሉት ነገሮች ይጠበቀበታል። አንደኛው መመሪያውን ተቀብሎ መስራት፤ ሁለተኞው አያደርገውም እንጂ ራሱን ችሎ ከቤተ ከርስቲያኒቱ መለየት ነው። ከዚህ ያለፈ ምንም ዓይነት አማራጫ ይለውም። እንግዲህ ልብ ይስጣችሁ። እወቁ የቤተክርስቲያኒቱ አምላክ አያንቀላፋም። የንጹሐን ሊቃውንት ዕንባ በከንቱ አይደርቅም።
ቸር ዜና ያሰማን!!
\

Anonymous said...

እስቲ አባት ጠቁሙኝ
እናዳትታዘቡኝ፣
ችግሬን ተረዱኝ፣
አባት አምሮኛል ፍፁም መንፈሳዊ፣
የሃይማኖቴ መሪ ፍፁም ኦርቶዶክሳዊ፣
እስቲ አባት ጠቁሙኝ የቆሙ ለእዉነት፣
የደፉትን ቆብ ፍፁም ያከበሩት፣
“አባት ድሮ ቀረ” ብዬ እንዳልሟገት፣
አባ እገሌ በሉኝ፣
መስቀል ያሳልሙኝ።
ያልተንበረከኩ ለድሎት ለዝና፣
ከቶ ያልያዛቸዉ የወንበር ካቴና፣
ያላሸነፋቸዉ የስጋ ዝምድና፣
ለዚህች ቤተክርስቲያን የቆሙ ጥብቅና፣
የክርስቶስ ተከታይ የቤተክርስቲያን መሪ፣
የምዕመናን አለኝታ የህይወት አስተማሪ፣
እዉነተኛ አባት የእምነት ተቆርቋሪ፣
እስቲ አባት ጠቁሙኝ የእምነት አርበኛ፣
እምባዬን ያብሱኝ ይሁኑኝ መጽናኛ።
ኸረ አባቶች እኮ አሉ ብላችሁ ካላችሁ ስንት ነዉ ቁጥራቸዉ፣
የቤተክርስቲያን እምባ ስንቶቹ ታያቸዉ፣
በቅጥር ወንበዴ የተደበደቡት፣
በአድርባዮች ዛቻ መናገር ያልቻሉት፣
ቁጥራቸዉ ስንት ነዉ ለዚህች ቤተከርስቲያን በአንድነት የቆሙት።
እንክርዳድ ከስንዴ ተቀላቅሎ ቢያስቸግር፣
ይለዩ ይሆናል እንደተደፈነ አይቀር፣
ጽዋዉ የሞላ ዕለት ሲያበጥር እግዚአብሔር።

ከኃ.ገ

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)