November 4, 2009

የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንትና ሌሎች ባለሥልጣኖች ተጠመቁ


(ደጀ ሰላም፤ ኖቬምበር 4/2009)
በጋምቤላ ሕዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድርን ጨምሮ 103 የአኙዋክና የኑዌር ብሔረሰብ ተወላጆች በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ እምነት መሠረት ሥርዐተ ጥምቀት እንደ ተፈፀመላቸው ታወቀ፡፡

የክልሉ ርዕስ መስተዳድር አቶ ዑመድ ዑቦንግ ዑሎም (Foto)፣ የርዕሰ መስተዳድሩ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሁሙሉና የክልሉ የፀጥታ ቢሮ ኃላፊን ጨምሮ 103 የአኙዋክና የኑዌር ብሔረሰብ ተወላጆች ሥርዓተ ጥምቀት የተፈፀመው በክልሉ በምትገኘው ቅድስት ኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ መሆኑ ታውቋል።

በጋምቤላ ክልል የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ለረዥም ዘመናት ሐዋርያዊ አገልግሎት ስትፈጽም የቆየች ሲሆን የዚህ ሐዋርያዊ አገልግሎት ውጤት የሆነው የእሑዱ ሥርዓተ ጥምቀት ደግሞ አንድ ትልቅ እመርታ ይሆናል። የአኙዋክ ሕዝብ ቁጥሩ ግማሽ ሚሊዮን የሚሆን ሲሆን ከሱዳን ጋር ባለው ድንበርተኝነት ቤተ ክርስቲያናችንን ወደ ደቡብ ሱዳን ለማስፋፋት ትልቅ በር ይከፍታል። ኑዌሮችም በዚያው በጋምቤላ አካባቢ ያሉ፣ በቁጥራቸው ከአኙዋኮች የሚበልጡ የሱዳን ድንበርተኞች ናቸው።

Post a Comment

Blog Archive

የአቡነ ጳውሎስ "ሐውልተ ስምዕ"

ነጻ ፓትርያርክ ምርጫ ቢሆን ኖሮ ማንን ይመርጡ ነበር? እንበልና ሁሉም ነገር ሥርዓቱን ጠብቆ የተከናወነ የእጩዎች ምርጫ ቢሆን ኖሮ፣ አሁን የምናነሣቸው ጉድለቶች ባይኖሩ ኖሮ፣ 6ኛው ፓትርያርክ እንዲሆን የምትመርጡት ማንን ነበር? (ማሳሰቢያ፦ አሁን ያለው ክፍፍል እና የመንግሥት ተጽዕኖ ባይኖር ኖሮ ተብሎ የሚመለስ ጥያቄ ነው። የምን “ባይኖር ኖሮ ነው” የሚል አስተያየት ካለዎትም እናከብራለን።)